Friday, July 29, 2022

ዕዉቀት አልባ  ወረቀት - የድንቁርና ጎርፍ !
በአገራችን በወረቀት ብዛት  አልቦ ዕዉቀት የመማር ማስተማር ስርዓት ወደ ክህደት እና ደህነት ቁልቁለት ሲነዳን ዘመናት ተቆጥረዋል ፡፡

ከጭልማዉ የዉድቀት ዕለት  ግንቦት ፳ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ቀለሟን እና ቁመናዋን ለማሳጣት የወረቀት አብይቶ ወረራ ተካሂዶባታል፡፡

ቱባ አገር በቀል የጥበብ እና ዕዉቀት በሮች ተከርችመዉ የባህር ማዶ ማንነት ከነእንክርዳዱ ሲዘራ በዓባይ ላይ ዕሞቦጭ በኢትዮጵያ ላይ የመደነቋቆር እና የመናቆር ዘር በወረቀት ተስፋፍቶ አሁን ከምንገኝበት ቁመና እንገኛለን ፡፡

ወረቀት እና ባርነት (አገልጋይነት) ካሉ ለአገር እና ለህዝብ አሚኬላ ይሁን ሌላ ቢተከል ጉዳይ የማይል ምን ቸገረኝ ትዉልድ በየብሱ ፤ዕምቦጭ በዉኃ ላይ  ተባዝተዉ መዉጫ ፤መተንፈሻ ማሳጣት በጊዜ ቅብብል እዚህ ላይ ተደርሷል፡፡

አበዉ   “እጂ ነጣ  ነጣ እግር ነጣ ነጣ……እንዲህ አይደለም ወይ ቁምጥና ሲመጣ ” እንዲሉ መጀመሪያ ለመደነቋቆር ተስማማን በኋላም የተጫነብንን ድንቁርና ሁሉ አሜን እያልን በቀን ጨለማ ዉስጥ እንባዝናለን ፡፡

ድንቁርና ፣ጭቆና…..ዕምቢ ማለት ትተተን ይሁን ባይ ሆነን ራሳችን ሀነን ተገኘን፡፡  ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት ከነበረንበት ስብዕና እና ብልፅግና  ተሸቀንጥረን ወርደን ዛሬ የምንችለዉ ስያሜ መቀየር ብቻ ሆኗል፡፡

ስምን እና ማንነት አጥቶ የሚቀየር ስም ለባሹን የማያሞቅ ነጠላ ሆኖብን አንድ ጊዜ ወደፊት  ሶስት ጊዜ ወደ ኋላ የዛሬ  ድንቁርና እና ኦና ማንነት ከወረቀት ብዛት የተቀዳ አልቦ ማስተዋል ፍሬ አልባ እንክርዳድ ነዉ፡፡

ከሰሞኑ እጂግ የምናከብራቸዉ እና የምንሳሳላቸዉ  ኢትዮጵያዊ ደራሲ እና ጠቢብ ከሰሞኑ የከፍተኛ ት/ት ምረቃ  ስነ ስርዓት በክብር ዕንግድነት በተገኙበት  ለተመራቂዎች እና ለመላዉ ታዳሚ የኢትዮጵያ መከራ ቀንበር ተጭኖ የሚገኘዉ በተማረዉ አካል መሆኑን ጠቅሰዉ ተመራቂዎች ግንዛቤ እንዲወስዱ አሳስበዋል ፡፡

ኢትዮጵያ  ባልተማሩት ተገንብታ እና ፀንታ ኖራ ዛሬ ተማርን በሚሉ እየቆሰለች እና እያነባች መሆኗን ገልፀዋል ፡፡ በመሰረታዊ ሃሳቡ አስማማለሁ ነገር ግን  የእኛ ኢትዮጵያዉያን ችግር በዕዉቀት እና በወረቀት መካከል ስላለዉ ልዩነት ትኩረት አለማድረጋችን የጥበብ እና የዕዉቀት ባለሀብቶችን ያልተማሩ የጥበብ እና ማስተዋል ድርቅ የመታቸዉን የወረቀት ነብሮች እንደ ተማሩ መቁጠር በራሱ ለዉድቀታችን እና ለአሳፋሪ ድንቁርና ወለድ ድህነታችን ምክነያት ሆኖ የሚጠቀስ  ነዉ ፡፡

ጥበብ እና ዕዉቀት በተግባር የሚገለጥ ካልሆነ የጋን መብራት ወይም የዱር ፍሬ ነዉ ፡፡ ለእኔ እንደ ክብር እንግዳዉ ( ንግግር አድራጊዉ ) ሶስት መቶ ሰዎች በኢትዮጵያችን ቢኖሩ ኢትዮጵችን ከገባች ሁለንተናዊ ጥልመት ለመዉጣት ዓማታት ሳይሆን ዓመት አይፈጂባትም ነበር ፡፡

ኢትዮጵያ ፣ ህዝቧ እና ምድሯ  በጥበብ እና በዕዉቀት የሚያስተባብራቸዉ ቢያገኙ ታምር መፍጠር የሚቻል መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል ፡፡

ወደ መማር አለመማር ስመለስ ኢትዮጵያን  ከመመስረት አስከ አስከ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት እና አንድነት ለነበረዉ ተተኪ ትዉልድ ሲያስረክቡ ልበ ብርኃን በጥበብ እና ዕዉቀት  በነበራቸዉ ቱባ ማንነት ነበር ፤ ነዉ ፡፡

የአክስሙን ሁዉልት ፣ የላሊበላን አብያተ ክርስቲያን (ኪነ ህንፃ)፣ ገዳማትን ፣ አገር አቃራጭ  መንገዶችን …..በመገንባት ለእኛ ያስረከቡን ጥበበኞች እና የተማሩ (በፀጋ የታደሉ) ነበሩ ፡፡

ኢትዮጵያዉያን ከዕፅዋት ሁሉ ጤፍን ለይተዉ ለእንጀራ ፤ አረቂን እና ጠላን  ጠምቀዉ  በዓለም ላይ አቻ የለሽ   የፈጠራ ባለቤት ሆነዉ ለእኛ የሰጡንን  ከመማር በላይ የሚገልጥ ቃል ቢኖር መግለጥ በተቻለ ነበር ፡፡

ዛሬ የተማረ የሚባል የወረቀት ነብር የያዘዉን የማይለይ  ፣ መልክ ያለዉ ድንጊያ መለየት የሚሳነዉ ፣ ጥበበኞች የሰሯትን አገር ለማፍረስ ግማሽ ክ/ዘመን የፈጀበትን ይህ ትዉልድ  የተማረ ከምንል  “ወረቀት አምላኪ ማለት ይቀላል ”፡፡

ምክነያቱም ወረቀት ይዞ ዕዉቀት እና ማስተዋል ድርቅ የተመታ በመሆኑ በምድር ቀርቶ በሰማይ የሚማር ሊሆን አይችልም ፡፡

ምክነያትም የጥበብ መጀመሪያዉ እ/ርን መፍራት ፣ ትምህርትም ሠባዊነትን ማሳደግ እና መቻቻል እንደመሆኑ የዚህ ሰለባ ትዉልድ የተማረ ከማለት ይቅር የሚባል እና ንስሃ ገብቶ የሚማር መሆን አለበት ፡፡

 

NEILOSS

 

Amber
https://amharic-zehabesha.com/archives/176340

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...