በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮንሺፕ የወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ። የሀገሩ ልጅ ሞስነት ገረመው የብር ፣ ቤልጂየምን የወከለው ባሺር አብዲ ደግሞ የነሃስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪገን ኢዩጂን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮንሺፕ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ በታምራት ቶላ አማካኝነት አግኝታለች ።
አመሻሹን በተደረገው የወንዶች ማራቶን ውድድር ባለ ድል የሆነው ታምራት ከበርሊኑ ቻምፒዮንሺፕ ወዲህ በኬንያዊው አቤል ኪሩይ ለ13 ዓመታት ያህል ተይዞ የቆየውን የርቀቱን የቻምፒዮንሺፕ ክብረወሰን አሻሽሏል።
ውድድሩ ሊጠናቀቅ 10 ኪሎሜትሮች ገደማ ሲቀረው ጀምሮ ከተፎካካሪዎች ተነጥሎ ወደፊት የገሰገሰው ታምራት ቶላ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ 5 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በድል አጠናቋል።ይህ ሰዓት አቤል ኪሩይ ከገባበት ሰዓት ከ ደቂቃ በላይ የፈጠነ ነው።አቤል በቲዊተር ገጹ በኩል " ከ13 ዓመታት በኃላ ክብረወሰኔ በዛሬው ዕለት ተሰብሯል !" በማለት ለታምራት የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክቱን አስተላልፏል ።ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሞስነት ገረመው በአንድ ደቂቃ ከስምንት ሰከንድ ዘግይቶ በመግባት የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል። ቤልጂየምን የወከለው ትውልደ-ሶማሊያዊው በሺር አብዲ በበኩሉ 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በሆነ ሰዓት 42 ኪሎ ሜትር ማካለል የሚጠይቀውን ውድድር በማጠናቀቅ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኗኑን አረጋግጧል።
ከዛሬው የወንዶች ማራቶን ድል በፊት ፣ በትናንትናው ዕለት በተደረገው የሴቶች 10ሺ ሜትሮች ውድድር በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች እልህ አስጨራሽ ፉክክር ያደረገችው ለተሰንበት ግደይ የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስመዝግባለች ።
https://amharic-zehabesha.com/archives/175224
Monday, July 18, 2022
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
The west is rigidly stuck in its heydays of colonialism and slavery. And it has a very good reason for being so stuck, albeit sentimental. ...
-
By Ameyu Etana BBC Afaan Oromoo, Nairobi/BBC In the latest sign of the deep crisis that has engulfed Ethiopia, conflict in the vast Oromia...
-
ዛሬ አንድ የፌስ ቡክ ጓደኛየ የአቶ በቀለ ገርባን ሽሽት ከተመለከተ በኋላ የሚከተለውን መልእክት ጻፈ። " አገሩን አርማጌድዮን አደገህ ብልሆች ወደ ሰሩት አገር በነጻነት ለመኖር ሄድክ? " አባባሉ እኔንም...
No comments:
Post a Comment