ጠኔውም ቢገልህ ስጋም አንቆህ ብትሞት
መዝግቦት ተጓዘ ታሪክ ያንተን ሐሞት
ስትሳለቅ ነበር ትናንት በእስክንድር
በአቋራጭ ቀዳድሞህ ቆሞልሃል ብድር።
ስማኝ የሸገር ልጅ ኳስ ዳንኪራ ብርቁ
ጊምቢ ቶሌ አይደለም እልቂቱ ፍጅቱ ያንተኑ ነገ ነው ያሳዩህ በሩቁ
ንብረትህን ዘርፈው ቤትህን ሲያነዱ
እትና እናትህን ልጅና ሚስትህን እንዴት እንደሚያርዱ
ምን እንደሚመስል ያንተኑ ነገ ነው ያሳዩህ በሽንቁር
ወለጋ ሩቅ መስሎህ የዋሁ ሸገሬ እንዳትደነቁር
ከነግብራበሩ ነገ ብልጽግና
ባንተ ደም ይዋኛል ግንፍሌ፣ ቡልቡላ፣ ቀጨኔ፣ ቀበና
ጅቡ ርቆ ሄዷል ዛሬ ካዲሳባ
ማን (man) ነው የሚበላው ነገ ያንተን ሬሳ ያካልህን ገራባ?
ያ እንጂ ጥያቄው ያልመለሱት ገና
በወለጋ ተውኔት የሸገርን እጣ ሲያሳይ ብልጽግና
ሁሉን ጨርሶታል ነግ ያንተ ነው ተራው
ገዳይህ ለታሪክ ተነግሮት አደራው
ቃል እየጠበቀ ቆሟል በየሥፍራው
ስምክም ተጽፎበት ተቀምጧል ገጀራው።
https://amharic-zehabesha.com/archives/173700
Tuesday, June 28, 2022
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment