Tuesday, June 28, 2022
ለደቂቃ እናሰባት! የኔ ልጅ ብለን ወይም እህቴ ብለን፤----- ብቻ በተረፈረፈ ሬሳ መሃል በሞትና በሽረት ውስጥ ያለን "ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም!" የሚለውን የተማጽኖ ድምጽ እንስማው። ዘር-ሃረጓን ወይም ሃይማኖቷን እንርሳው፤ አማራ ነሽ ወይም ነሽ ተብላለች። እሷግን ህጻን ልጅ ናት። ህጻን ልጅ። ሰው። በኢትዮጵያ ምድር እንደማንኛውም ሰው ሳትመርጥ የመጣች። አራጆቿ ግን መርጠዋታል። ቢለዋ ስለው፣ ሳንጃ ደግነው፣ መትረጊስ አቅቀባብለውባታል። እናም የመታረድን ትዕይንት በተረፈረፈ ሬሳ መሃል ሆነው፣ ገዳዮቹ እንደገደሏቸው የቆጠሯቸው፤ ግን በታምር የልተረሸኑት እናት እንደሚነግሩን ፤
"ራሴን በረፈረፈው ሬሳ ውስጥ አገኘሁት። ካንገቴ ቀና ስል አንዲት ህፃን በግምት 6 ዓመት ታጣቂዎች ተከባለች። እኔ እዛው አጠገባቸው ብሆንም ከተረፈረፈው ሬሳ አንዱ ስለቆጠሩኝ አላስተዋሉኝም።
ህፃኗን በአማርኛ ያናግሯቴል ፤ከዛ ሁሉም ባንዴ ድምጻቸው የገደል ማሚቱ እስኪያስተጋባ ይስቃሉ ።
በመጨረሻም ህፃኗ ጮክ ብላ ይህን ስትል ሰማኋት፤
"ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም"
ቀጥሎ የሰማሁት ድምጽ የጥይት ሩምታ ነበር። ለማየት በሚያሣሣ ገላዋ ላይ እሽቅድምድም በሚመስል መልኩ ሁሉም የጥይት አረር አዘነቡባት። ሞታ የሚረኩ አይመስልም ነበር።"'
የዚች ልጅ ድምጽና ታሪክ ወደድንም ጠላንም በኔ፣ በአንተ፣ በአንችና በመሰሎቻችን በህይወት እስከ አልን ድረስ አብሮን ይኖራል። ከትውልድ ወደ ትውልድም ይተላለፋል። '' የ’ኔ እጣ በሌሎች ህጻናት ላይ፣ በሰው ልጅ ዘር ላይ እንዳይደገም!'' እያለች የምትማጸን ይመስለኛል።
ታዲያ ይህን ዘግናኝ ግፍ ለማውገዝም ሆነ ሁለተኛ በኢትዮጵያ ምድር እንዳይፈጸም ለመታገልና ገዥዎቻችንን ለፈጸሙት የዘረ ማጽዳት ተጠያቂ ለማድረግ ሰው መሆን በቂ ነበር።
ዛሬ በዚች ህጻን የደረሰው ነገ-ከነገ ወዲያ ሌላው ''የዘረውን የማይሰበስብበት'' ምክንያት የለም። አሁንም እንዲህ ሌት- ተቀን የምንቃትተውና ለሁላችንም መዳኛው ''አንድነት ፤ ብሎም ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊንት ነው !'' የምነለው ሌላ እልቂትና ሌላ የዘር ማጽዳት በማንኛውም ሰው ላይ እንዳይፈጸምና ከ’ነ ውስጥ ቁስላችንና ዘላለማዊ ህመማችንም ፤ የዚች ህጻን ዋይታና አሟሟት የመጨረሻ እንዲሆን ነው። ለዚህም ነው “ ዓይን ላጠፋ ዓይን ይጥፋ ካልን ሁላችንም ዓይን ስውር እንሆናለን ።” የሚባለው።
ባደሙት ቁጥር - አዎ ደም ይደማል
ባፈሰሱት መጠን - አዎ ደም ይፈሳል
ደምም- ደም ነውና ፤ ድም-ድምን ይወልዳል።
ይህች ህጻን በታረደችበት ቀን በሺዎች ታርደዋል። ሬሳቸውንና የጅምላ መቃብራቸውን አይተናል። ከ20 ቀን ህጻን እስከ መቶ ዓመት አዛውንት በማንነታቸው ብቻ አዕምሮ ሊደርስበት፣ ብዕር ሊከትበው፣ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ተሰምቶና ታይቶ በማይታወቅ አረመኒያውነት በገዛ አገራቸው፣ በገንዛ ወገኖቻቸው፣ መንግሥት አለ በሚባልበት ምድር፣ ተመርጠው ስጋቸው ተዘልዝሏል፣ ቆዳቸው ተገፏል። ነፍሰ ጡሮች ጽንሳቸው በጪቤ ተተልትሏል። በ’ርግጥ እውነቱን እንናገር ካልን ለአለፉት ሰላሳ ዓመታትም ሆነ ላለፋት አራት ዓመታት የአማራ ህዝብ በማንነቱ የዘር ፍጅት ሊፈጸምበት የበቃው መንግሥት አለ ብሎ ማመኑና ራሱን ለመከላከል ምንም ዓይነት ሙከራ አለማድረጉ ነው። ሙከራ ተደርጓል ከተባለም አራጆቹን ማባበልና መለመን ነበር። መመበሩን የተፈናጠጡት የጎሳ ገዥዎች ታግለው ለሥልጣን የበቁት ''አማራን'' ከቻሉ ማጥፋት፤ ካልቻሉ ማንኛውንም መንገድ ተጠቅመው ማዳከም መሆኑ ተዘንግቷል።
አንጋፋው ጋዜጠኛ ዐለምነህ ዋሴ እንዳለው፤
"በአማራ ላይ ከናዚ የከፋ ዘር ፍጅት ደርሶበታል!የተፈጠረውን ጥቃት ለማቃለል የሚሞክሩ ለጥቃቱ ስልታዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚፈልጉ ናቸው። 55 አመቴ ነው። ረጅም አመት በጋዜጠኝነት ሰርቻለሁ። ባለፉት 30 አመታት ከናዚ በተቀዳ አስተምህሮ የሚያልቀው አማራ ብቻ መሆኑን አረጋግጫለሁ። ዝምታው ደግሞ በዝቷል፣ ያለቀው አማራ እኮ ናዚ ከጨፈጨፋቸው ንፁሐን ቢበልጥ እንጂ አያንስም። የሚገርመው የገዳዩ ስም ይቀያየራል፣ ሟቹ ግን ያው አማራ ነው።''
ታዲያ ኢትዮጵያን በማለቱ በማንነቱ ብቻ የዘር ፍጅት ከሚፈጸምበትን ህዝብ ጎን መቆምና በዚህ እኩይ ተግባር የተሰማሩትን ገዥዎቻችንም ሆኑ ፈጻሚዎቹን ማውገዝ ብቻ ሳይሆን፤ የሁላችን አገር ጸንትና ተከባብርን በአንድነታችን እንድንኖር መታገል የያንዳንዱ ዜጋ ኃልፊነትና ድርሻ ነው።
ለዚህ ደግሞ ሁላችንም ዛሬ መነሳትና አራጆቹንም ሆነ አሳራጆቹን በቃችሁ ልንላቸውና ልናስቆማቸው ይገባል። በወደቅን ቁጥር መነሳት እንደምንችል ታሪክ ያስተምረናል። እናም ፤
‘ባካችሁ ......... ’ባካችሁ..........
እናንት በምድረ- ኢትዮጵያ ያላችሁ፤
"አትሂዱ …..በ'ግራችሁ..."
ከቻላችሁ ..... "ብረሩ ክንፍ አው’ታችሁ።”
ግን…….. አደራ……….. ..........
አንዳትረገጡት ……. መሬቱን
እንዳታዩት……… አፈሩን፤
ብታርሱት...... አትዘሩበት
ብዘሩበት ........ አይበቅልበት፤........
ደም ነውና - የትላንና- የዛሬ - የአሁን፣ ትኩስ…. የፈሰሰበት
አጥንት ነውና ያልደረቀ ፣ "አጸደ-ህይወት" የወደቀበት
እናንተም ከእንግዲህ ፣ ''ዐጽም - 'ርስቴ'' የማትሉት፤………..
ያውም ......................................
የባቶቻችሁ፣…….. የናቶቻችሁ
ያውም....................................
የወንድሞቻችሁ፣…….. የህቶቻችሁ
ያውም..........................................
የእቦቀቅላወቹ፣…… የታዳጊወቹ፣........የልጆቻችሁ፤
ዓይናችሁ እያየ፣……. እየሰማ ጆሮ'ችሁ
የተመቱ! ... የቆሰሉ!..... የተወጉ! .... የተፈነከቱ!.....
የተቀጠቀጡ!.... የተዘለዘሉ!......! ……የተረሸኑ!
….. በገዛ ወገኖቻችሁ………..
ያውም ……......''ወገን እኮ ነን “ እያላችሁ።
በደመዋ ልባችሁ……………………………….
“ኤሉሄ .....ላማ ሰበቅተኒ!”....... ብላችሁ
ወሰን - ድንበር ለሌለው ሰቆቃችሁ
ብትነግሩትም “ለሰማይ አባታችሁ”፤
ግን..... ለምንም - ለማንም አይመችም
ሀዘናችሁ መልክ የለውም..........
ያልተነገረ እንጅ፣ ያልተፈጸመባችሁ ግፍ የለም።
ብትጎጉጡ፣ ደም አልቅሳችሁ፣.....
እየየ …ብላችሁ -
ቢያዳርስም ዓለም ….. ሲቃ - ዋይታችሁ ...
መቼም- መቼም ቢሆን፣ ምንጩ አይደርቅም የ'ምባችሁ::…..
እናማ...............................................
ሰላም፣ ፍትህ፣ እኩልነት - ሳታሰፍኑ - በመሀከላችሁ
አንድነትን ሳታነግሱ - በምድራችሁ
ይቅር ሳትባባሉ፣ ‘ርስ - በርሳችሁ
ሳይመለስ ክብራችሁ፣ ጠፈር - ድንበራችሁ
የድል ችቦው - ከፍ ሳይል ፣ ክብር ሰንደቅ ዓላማችሁ፤......
የወገናችሁን ደምና- አጥንት እንዳትረግጡት
“ይወጋችሁልና እሾኽ ሆኖ፣ የኢትዮጵያ ዐፈር - መሬት!”።
https://amharic-zehabesha.com/archives/173702
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment