Sunday, July 2, 2023

ምዥለጋ መሰወር ና ቶርቸር ፤ የአበልፃጊው መንግሥት መገለጫ ሆኗል
ፀሐፊው ፣ ሰው ዘ ሰው ነኝ

 በራስህ ቁስል እንጨት ሰድዶ “ ኡ! ኡ ! …”  አመመኝ በማለት የሚጮኽ ተከስቷል ። ዛሬ ።

ዛሬ ኑግ ነጭ ነው ። ወተት ጥቁር ነው ። ወሃ ወፍራም ነው ። ራሐባችንን የወስፋታችን ጩኸት እያሳበቀ “ ጠግባችኋል ! “ የሚሉን መሳፍንት ና መኳንንቷች ተፈጥረዋል ። ያውም በብልጭልጭ ነገር ፤ በአርቴፊሻል ነገር የሚደሰቱና ህዝብ ያንን እያየ እንዲደሰት የሚመክሩ ። ( ዛሬ ኳስ መጫወት ጀምረዋል ። እናም እንጠይቃቸዋለን ፤ ሎው ኦፍ ፉትቦል አሥራ ሦሥተኛው አንቀፅ ምን ይላል ? )

 “ እየራበኝ የማከው ሆዴ ቆስሏል ። ተመልከቱ !! … “ ሲባሉ የሚበሳጩ ። ከሀብታምና መካከለኛ ገቢ ካለው ሰብስበው ደሃን መመገባቸው እየታወቀ ከደሞዛቸው ቀንሰው ፣ ቀብራራነታቸውን ጥለው ፣ እየተቸገሩ ደሃውን ህዝብን እንደመገቡ ሁላ በየመድረኩ የሚመፃደቁ ። ህሊና ቢሶች …

" ብቻውን የሚቆጣ እብድ ተብሎ ተቆንጥጦ ይሞታል ። " እንዳለው ፣ ፀሐፊ ተውኔት በለቅኔ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ዛሬ ይኽንን እውነት በአደባባይ በመናገራቸው ከላይ በጠቀስኩት አግባብ የሚመራው መንግሥታችን በእስርቤት የህዝብ ልጆችን በማሰቃየት ላይ ይገኛል ።

የደርግን ና የወያኔንን አገዛዝ ባስከነደ ጭካኔና ወራዳነት በየዋሁ ሚሊቴሪና ፓሊስ ታግዞ እስከመቼ በአምባገነንነት እንደሚገዛ አላውቅም ። ነገር ግን በሥልጣኑ ላይ የሚቆይበት አንዳችም የህዝብ ድጋፍን የሚያስገኝ እውነት እንደሌለው የታወቃል ።

ጦርነትን ለሥልጣን መቆያ ለመጠቀም ይፈልጋል ። ይሁን እንጂ ይኽም አይሳካለትም ። ያለጦርነት በሰላምና በፍቅር ከኤርትራ ህዝብ ጋር በጋራ ልንኖር እንችላለን ። ለዚኽም ኤርትራዊያን ዝግጁ ናቸው ። የአሜሪካንንና የሩሲያን ጦርነት እኛ ኢትዮጵያዊያን በራሳችን ቀጠና ለመዋጋት ለምን እንገደዳለን ?

ደሞስ ለአምባገነኖች ሺ ዓመት መንገሥ ሲባል ፣ ለምን ውሃ ቀጠና እየተባለ ሃቀን እና ሰቅዓዊነትን ተንተርው መንግስትን የሚሞግቱ እንደ ነፍሰ ገዳይ እየታደኑ በየእስር ቤት ይወረወራሉ ?

እርግጥ ነው ፤ በዓለም ላይ ፣ በሰላማዊ ትግል ና ተቃውሞ  ፤ ብዙሃኑ ከሚያውቃቸው ፣ በታሪክ ድርሳናት ከተፃፉ ግለሰቦች ባሻገር   ፣ ለሰው ነፃነት ለፍትህ ፣ ለእኩልነት ፣ለሰብዓዊ መብት ፣ ለእኩል ተጠቃሚነት  ፣ ለፆታ እኩልነት ... ብቻቸውን በብዕርና በአንደበት ብቻ  ጨቋኝና አምባገነን ሥርዓቶችን በየአገሩ የታገሉ ዜጎች ፣ በገዢዎች ተመዥልገው መሞታቸውን  ታሪክ መዝግቦታል ።

ሥንትና ሥንት ምሁራን ፣ ጋዜጠኞች ፣ የኪነጥበብ ሰዎች ፣ ፓለቲከኞች እስከዛሬ ለህዝቦች ነፃነት ፣ እኩልነት ፣ ፍትህ ፣ ዴሞክራሲ ...ሲጮኹ በሥውርና በግልፅ በአምባገነን መንግሥታት ተገድለዋል ? ቁጥሩን ለታሪክ እንተወው ። ( አምባገነኖቹም በባዮሎጂ እና በጥይት መሞታቸውን አትዘንጉ ። ይኽም ይቀጥላል ። ሺ ዓመት አይኖርም ። )

በእኛም አገር ከንጉሥ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን አንስቶ “ የተጋነነ ምዥለጋ ና መሰወር  “ በጥቂቱና በብዛት እየተከናወነ ለዘመነ “ ብልፅግና “ ደርሷል ።

ባለፉት ዘመናት ሁሉ እና አሁንም   በነፃነት የመናገር እና የመፃፍ መብት በግልፅና በሥውር ክልከላ ተጥሎበት ዜጎች አፋቸውን እንዲቆልፉ በነጭ ለባሾች ፣ ዛሬ ደግሞ በካድሬዎች ና በጠመንጃ አፋኝ ነፃ አውጪዎች ተገደዋል ። በጉማ የሽልማት ሥነ- ሥርዓት ጀግናችን ያሳየችን ሃቅ ይህንኑ ነው ። “ ዝም ካለላልክ  ባግባርህ ፣ በግምባርሽ ጥይት ይቀረቀራል ። “ ነው ። መልዕክቱ ። ኢትዮጵያ ዛሬ በጥቂት ስግብግቦች ( ትላንት ወያኔ ስግብግብ ነበር ብለው ይሳደቡ ነበር ። ዛሬ ከወያኔ የባሰ ስግብግብ ሆነው ተገኝተዋል ። ) አፏ ተፍኗል ።

ሳንሱርድ ወይም አፈና ዛሬም አለ ። ያውም በፖሊስና በአቃቢ ህግ የሚመራ ። በተፈጥሯዊ መብትህ በመጠቀምህ ሌላ ታርጋ ለጥፎ ያስርሃል ። ይከስሃል ።

ይኽንን እውነት ደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ ሥለ ሣንሱር በፃፈው ፅሑፍ ፣ እንዲህ ሲል ያብራራል ። ለዛሬም ይሰራል ።

" በደርግ ዘመን የጠጡት ና ያሰከራቸው የፍርሃት  አልኮሆል _ሀንግኦቨር ( የዞረ ድምር ) እስካሁን ሳይለቃቸው ቀርቶ ነው እንበል ? እባብን ያየ በልጥ በረየ እንዲሉ ።ወይስ የማናውቀው ስውር የመንግሥት መዳፍ ባለማተሚያ ቤቶችን በጥፊ እያጮላቸው ? - አናውቅም  ! እነሱ ግን አናውቅም አይሉንም ፤ ' እናውቃለን ፤  ብንናገር እናልቃለን ባዮች ናቸው ። ( የሥፖርት ጋዜጣ ብቻ ሥንት ነበር ? ሌሎችን ሁሉን አቀፍ መፅሔቶችን ሳንቆጥር ኪነት ነክ መፅሔቶች ሥንት ነበሪ ? በዘመነ ወያኔ / ኢህአዴግ ። ዛሬ እንዲህ የሚነበብ ጋዜጣም ሆነ መፅሔት ለአይን ብርቅ ሆኖ ሲታይ ያስገርማል ።)

' ሟቷል ' ከተባልኩ በኋላ ፣ መሞቴን ላልሰሙ እንዲያሰማ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ጡርንባ ነፊ ሆኖ አዋጁን እንዲናገር በመንግስት ከታዘዘ በኋላ  ፤ አዋጅ ለፋፊዎችን  ውሸታም '  አስብዬ አላውቅም ?

ገጣሚው

“ ...መቃብር ፈንቅሎ - እንደ ክርስቶስ

ትንሳኤ    ጀመረ - የሳንሱር መቀስ ..."

ብሎ የገጠመው ለምን ይመስላችኋል ? ሞቼ ስነሳ ስላየኝ ነው ፤ የእባብን ባህሪ ተውሼ ፤ ከተቀጠቀጥኩ በኋላ አፈር ልሼ ነፍስ ስዘራ ስላየኝ ነው ። አውቃለሁ አምባገነኖች  ያለ እኔ አይሆንላቸውም ። ፤ ያለ እኔ አይናቸው ተገልጦ አያይም ። ሕይወት ምቹ ፍራሽ በመሆን ፈንታ የምታረገርግ አልጋ እንደምትሆንባቸው ያውቃሉ -እኔ ሳንሱር ነኝ የሕይወታቸው ዘብ - የበትረ መንግስታቸው - ጠባቂ - ርዕዮተ ዓለማቸውን አስፈጻሚ  ! ... "

እንዳለጌታ ከበደ  " ማዕቀብ "   ገፅ 90 እና 91 ።

በዚህ መፅሐፍ ክፍል አንድ ላይ " ድርሳነ ሳንሱር " በሚል ርዕስ የኢ- ልቦለዱ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ፣ በሳንሱር የተነሳ ፣ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ ፣ በመንግሥት ደህንነት ና ሹማምት የተሰቃዩ ፣  የተጋዙ ፣ በሴራ ህይወታቸው እንዲያልፍ የተደረገ የብዕርና የኪነት ሰዎች እንዳሉ ይተርካል ። የሰው ምሥክርም ያቀርባል ።

እኛም ለታሪክ የጎለተን ፣ በዘመነ ህውሃት / ኢህአዴግ የሥልጣን ጅማሮ እስከ 1997 ዓ/ም የነበረው ነፃ ፕሬስ እጅግ የሚደነቅ እንደነበር እናውቃለን ።በዚህ ረገድ ፣ በወቅቱ  የአገሪቱ ጠ/ሚ የነበሩት አቶ መለሥ ዜናዊ ከሚገባው በላይ ታጋሽነትን ያሳዩ እንደነበር መካድ አይቻልም ። ለዚህም  የጦቢያ መፅሔት ምሥክር ናት ። በ13 ዓመቷ ምርጫ 97 ን ታዝባ ከመሞቷ በፊት ፣ በመፅሔቷ የሽፋን ስእል ሣይቀር የአቶ መለሥን አሥተዳደር ክፉኛ ትተች ነበር ። አቶ መለሥ ዛሬ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ ፣ ከመፅሔቷ አምደኞች አያሌ ቁም ነገር እንደገበዩ ይመሰክሩ ነበር ።

ዛሬ ድረስ ያለችው የሪፓርተር ጋዜጣ ባለቤት ጋዜጠኛ አማረ አረጋዊም በፕሬስ ነፃነት ተማምኖ በጋዜጣው ባወጣው ፅሑፍ ሰበብ የክልል ባለሥልጣናት ሳይቀሩ እንዳገላቱት ታሪክ መዝግቦታል ።

ዛሬስ ? ዛሬ እንኳን ህሊናችንን ለመመገብ ይቅርና ሰውነታችን ቆሞ እንዲሄድ የሚረዳው ምግብ መግዣ ቸግሮናል ። ጋዜጦች ፣ መፅሔቶች እና መፅሐፍቶች የህሊና ምግቦች መሆናቸው ቀርቶ   የቅንጦት እቃዎች ሆነውብናል ። ከዚህ ነባራዊ እውነት የተነሳ ድንቁርና በዚች አገር እየተስፋፋ እንደሆነ ግን ሊሰመርበት ይገባል  ።

ወዳጄ ፤ ወስፋቱ እየጮኸ ሬዲዮ ና ቴሌቪዥን  የሚከታተል ፤ የሚያዳምጥና የሚመለከት ሰው ከቶም አታገኝም ።

"እኔ መንግስት ስለሆንኩ ያዳምጠኛል ። " ብለህ የምታስብ ከሆነ ፍፁም ተሳስተሃል ። እዬዬም የሚያምረው  የጠገበ ላይ ብቻ ነው ። በችጋር የተጠበሰ አንጀት ለመጮኽ  የሚችል አንጀት ከቶም የለውምና ።

ዛሬ በመንግሥት እየተያዙ ወደ እስርቤት የገቡት ግለሰቦች ፣  የህዝብን በጠኔ ውስጥ እና በተዛባ የሀብት ክፍፍል ውስጥ መኖርን  የተገነዘቡና ያስቆጫቸው ናቸው ። የህዝቡን  አሁናዊ ችግሩን በመገንዘብ  መንግሥት “የለውጥ  አራማጅ ነኝ ። አሻጋሪያችሁ እኔው ነኝ ። “ በማለቱ መንግሥት  የሥርዓት ለውጥ እንዲያመጣ በብርቱ ይመክሩ የነበሩ ናቸው ። አንዳንዶቹ ጋዜጠኛ በመሆናቸው ከንባብ ክምችታቸው ውስጥ ከአንጎላቸው እያወጡ ህዝብን ያሳወቁ ናቸው ። ከታሪክ አንፃር በግለሰቦች የሚጠነጠኑትን የወገኑ አፈታሪኮች የኮነኑ ናቸው ።  ህገ መንግሥቱ በቋንቋ መደራጀትን በመፈቀዱ በአማራነት ያለመደራጀታችን አሥጠቅቶናል ። ብለው እንደ ኦሮሞ ና ትግሬ የአማራን ህዝብ ለማደራጀት በግልፅ በአደባባይ የተናገሩትን ነው መንግስት አሸባሪ በማለት ፈርጆ ወደእስር ቤት የወረወራቸው ።

ይኽ መንግሥት  የሚያራምደው የውርስ ፓለቲካ ለአጠቃላይ ህዝቡ   እንደማይጠቅም  ካለማየቱ የተነሳ ወይም ከእውነት ጋር መፋጠጥና እውነት አርነት እንድታወጣው ካለመሻቱ የተነሳ ፣  ጠብመንጃ ሳይዙ በሃሳብ እየታገሉ  ያሉ ዜጎችን ፣ ( ጋዜጠኞችን ፣ ምሁራንን ፣ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ...) እስር ቤት አጉሯል ። ( የፍትህ ጥያቄ የህግ የበላይነት ጉዳይ ነው ቢባል እንኳ በመንግሥት ላይ ሸፍተው ጫካ ያልገቡትን እና ጫካ የደበቁት ጦር የሌላቸውን ምሥኪን ዜጎች በየጊዜው ቀጠሮ እየሰጡ የዋሥ መብታቸውን መከልከል ፤ ከሃሳባቸው ጋር የወገነን ዜጋ ብቻ ሣይሆን ፈጣሪንም የሚያስከፋ ነው ። )

ደሞም ይኽ የመንግስት ድርጊት በራሱ የመንግሥትን  በራስ ያለመተማመን ወይም ፍርሃት የሚያሳብቅ ነው ። “ አምባገነኖች  ፈሪዎች ናቸው ። “ ያለው ማነው ? እውነት ነው ። ቦካሳም ሆነ ኢዲያሚን ፣  ጋዳፊም ቢሆን ፖልፖት ፤ ወዘተ ። በፍርሃት ብዙ ንፁሐንን ገድለዋል ።  በሃሳብ ልዩነት ብቻ በማሰር ና በመግደል  ብሎም በመመዥለግና  በማሰቃየት ሠላምን አገኛለሁ ማለት ግን ዘበት ነው ።

ሠላም የሚገኘው ፤ ከእውነት ጋር ታርቆ ፣ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ በመወያየት  ብቻ ነው ። “ ይቅር ለእግዛብሔር ... “ በመባባል ። ይኽንንም  እውነት ከትግራይ ክልል ጋር በተደረገው ጦርነት እና ባልተጠበቀው “ የፕሪቶሪያ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት  ፍፃሚው “ መንግሥት የተማረ መስሎኝ ነበር ።

የትግራይ ጦርነት ፍፃሜ በጠረጴዛ ዙሪያ ድርድር የተገኘ ነው ። ከዚህ ድርድርና ሠላም መውረድ የኢትዮጵያ ህዝብ ትምህርት አግኝቷል ። የኢትዮጵያ መንግሥት ከዛ አውዳሚ ፣ በጣም ዘግናኝና  አሥፈሪ እንዲሁም በእጅጉ አሳፋሪ የእርስ በእርስ ጦርነት ካልተማረ ግን “ መንግስት በተባለው ግዙፍ  መዋቅር ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ከሣይንሳዊ ፓለቲካ ይልቅ በሴራ ፓለቲካ በእጅጉ ያምናሉ  ። “ ብሎ መደምደም ይቻላል ።

ጭራቅ እና የልጆች ማስፈራሪያ መሆን አለባቸው ከተባሉ " የወያኔ " ቁንጮ መሪዎች  ጋር መንግሥት ቁጭ ብሎ በመነጋገር ጠመንጃቸውን እንዲያስቀምጡ ማድረጉን እና ጭራቅነታቸውን መሰረዙን ( ጭራቅ የማድረግና የመሠረዝ የሰው መብት ባይሆንም ) የሰማነው በጠረጴዛ ዙሪያ ነው ።

ዛሬ ወያኔ / ኢህአዴግ የፓርቲውን ስያሜ እንኳን አልቀይርም ብሎ ( ዳሩ ደሃውን የበለጠ ደሃ ከማድረግ አልፎ ሀብታሙንም ደሃ እያደረገ ያለ ፓርቲ መሆኑ ይታወቃል ። ) ዛሬም መሐት አካለ ግዶሎ ሰው ለማምረት የጦርነት ነጋሪት ውስጥ ውስጡን ይመታል ።

በእውነቱ ፣ የጠረጴዛ ዙሪያ ድርድሩን ለሌላ ጦርነት መንደርደሪያ ለማድረግ የትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደርም ካሰብ   ዛሬም ለህዝብ ሞት ፤ ለአካሉ  ጉዳት ፤  መፈናቀል ፣ መራብ ና መጠማቱ ፤ ወዘተ ። ደንታ እንደሌለው ነው ፣ የሚያሳብቀው ።

በነገራችን ላይ ፣ ሰው ጭራቅ ከሆነ ሁላችንም ጭራቆች ነን ። ብዬ ለመደምደም እገደዳለሁ ። ወያኔ የሰው ስብስብ እንደመሆኑ ዓባላቱን በሙሉ በጭራቅነት መፈረጅ ድንቁርና ነው ። ሰው በአንድ ፋብሪካ የተመረተ ጠርሙስ ወይም ቆርቆሮ አይደለም ። ከአንድ መሐፀን በአንድ ጊዜ የተወለዱ መንትዮች እንኳን ፍፁም የሆነ ተመሳሳይነት አይኖራቸውም ። በድምፃቸው ወይም በአንዱ የአካል ክፍላቸው ሊለያዩ ይችላሉና !

ያም ሆነ ይህ ፣ ያን ሰሞን ሁላችንም በስሜት እንነዳ ነበር ። በነገር አሳማሪነቱ ለታወቀ ሁሉ እናጨበጭብ ነበር ። ከተረታው ህዝብ እስከ ከፍተኛ የመንግሥት  ባለሥልጣን  አጨብጫቢነት ነግሶ ነበር ።

ዛሬስ ? ሰከን ብለናል ወይ ? በበኩሌ አይመስለኝም ። " በለው ! ፍለጠው ! ቁረጠው !  "ብቻ ሳይሆን በየከተማው ረብጣ ብር እየመነዘርን  ሰማይን በእርግጫ እየመታን  ፤ በየመድረኩ ፣ ስለልማት ፣ ስለድህነት ቅነሳ ፣ ስለዳቦ መወደድ ፣ ህዝቡ ላይ ሥለተጫነው የኑሮ ውድነት ፣ ... መደስኮር በእውነቱ ፊዝ ነው ።

እውን ህዝቡ ሥለ ራሱ የወስፋት ጩኸት አያውቅምና ነው ፤ በመንግሥት ካድሬ በድግግሞሽ  የሚነገረው ? የመንግሥት ዋና ተግባርስ በመንግሥታዊ ግዛቱ ውስጥ ሠላምና ፀጥታ እንዲሰፍን ያላሰለሰ ስራ የሚሰራ ጠንካራ ማዋቅር መዘርጋት አይደለምን ?  መሰረተ ልማቶችን በመዘርጋት ወይም  ህዝብ ፣ ውሃ ፣ መብራት ና መንገድ  እንዲኖረው ዜጎችን አስተባብሮ በተግባር መንቀሳቀስ አይደለምን ? የሥራ ዕድል መፍጠርስ በከፊል የመንግሥት ድርሻ አይደለም እንዴ ?  የውጭ ግንኙነትን ለአገር ጠቃሚ ማድረግስ  ? የማን ሥራ ነው ? ህዝብ ዳቦ ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲንም እንዲመገብ በዚች አገር ሰፊ ምህዳር መክፈት የለበትምን ?

ሰፊ የፓለቲካ ምህዳር ባለመፈጠሩ እኮ ነው ፤ ዛሬም ግለሰቦች በሃሳባቸው ልዩነት ብቻ እስር ቤት እየታጎሩ ያሉት ። እነዚህ የፓለቲካም ሆነ የነፃ ሃሳብ እሥረኞች  እኮ ፤  መንግሥትና በግራና በቀኝ የተሰለፈው  የኢትዮጵያ ህዝብ በሥሜት ተነሳስቶ  ከሰራው ጥፋት የበለጠ ጥፋት አላጠፉም ። መሳደብ ፣ ማንጓጠጥ ፣ ማጥላላት ፣ መዛት ና መፎከርን ሁላችንም በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ፈፅመናል ። ጥቂት የማይባሉ ዜጎችም ከግራና ከቀኙ ተሰውቷል ። አካሉን አጥቷል ። ...

በዛን ጊዜ  በስመ ወያኔ ፍፁም የማያኗኑር " ሰው ጠልነትን "   በሰላማዊ ሰልፍ ሳይቀር አንፀባርቀናል ። በሰሜኑ ያለው ወንድምና እህታችን በመሪዎቹ ተነጂ እንደነበረ  ሁሉ በተቃራኒነት የተሰለፍንም ተነጂ ነበርን ።

ከተነጂነታችን አንፃር የፈፀምናቸውን ጥፋቶች ዛሬ ስናስተውል ፍፁም እናፍራለን ።... ከተተብተብንበት አዚም የተነሳ ...ሰውን በሰውነቱ ማየት እኮ አቁመን ነበር ። ዛሬም ከዛ አዚም የተላቀቅን አይመስልም ።

አንዳንድ የመንግስት ባለሥልጣናትም ከአዚሙ የተላቀቁ ያለመሆናቸው ድርጊታቸው ያሳብቃል ። ከአዚሙ  ቢወጡ  ኖሮ ፤ በተጨባጭ የሚታየውን የሥግብግብነት ተግባር እና ህገመንግስታዊ ችግር   እና መፍትሄ   በኃይለ ቃል  ወይም በአንክሮ  የሚነግራቸውን ሰው ይወዱትና ያከብሩት ነበር  ። እብድ በማለት በመመዥለግ ለመግደል ወደ እስር ቤት አይወረውሩትም ነበር  !

 

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/184257
ወልቃይት፤ በቦታው ነበርኩ - አንዱ ዓለም ተፈራ
#image_title

ቅዳሜ፣ ሰኔ ፳ ፬ ቀን ፳ ፻ ፲ ፭ ዓ. ም.  (07/01/23)

ወልቃይት ወደ ትግራይ እንድትገባ የተደረገው፤

አንድም ለመሬቷ ልምላሜ፣ ሌላም ለሱዳን ወሰንነቷ ሲሆን፤

ያ ሲደረግ፤ ሕገ−መንግሥቱም ሆነ ፓርላማው አልነበሩም፣ አልተሳተፉበትም።

 

የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር፤ ወልቃይትን ወሮ ከያዘበት ከዛሬ አርባ ሶስት ዓመታት (፲ ፱ ፻ ፸ ፪ ዓ. ም. – ) ጀምሮ፤ ወልቃይትን፣ ራያንና ጠለምትን ከሰማይ በታች የሚችለውን ሁሉ በማድረግ፤ የትግራይ አካል አስመስሎ ሲያስቀምጣቸው፤ በነዋሪዎች ላይ የኅብረተሰብ ምሕንድስና ሠርቷል። እንግዲህ ይሄን የፈጠራ ትርክቱን ይዞ፤ ውስጥ ለውስጥ የትግራይ አካል አለመሆናቸውን እያወቀ፤ ባደባባይ ግን የትግራይ አካል ናቸው በማለት፤ ባገር ቤት ውስጥ በሕገ−መንግሥቱና በየቦታው ባስቀመጣቸው ተቀጣሪ ሆድ አደር ባለሙያዎቹ፤ በውጪ አገራት ደግሞ በዲፕሎማሲዊ ሥራው፤ “ዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ!” ጨዋታ ይዞ ቆይቷል። ለመሆኑ የዚህ ትርክቱ መሠረት ምንድን ነው? ሕጋዊነትስ አለው ወይ? ታሪካዊ መረጃና አግቦትስ ይገኛል ወይ? ስለሕጋዊነቱና ስለ ታሪካዊ መረጃው ብዙ የተባለ ስለሆነ፤ እኒያን አዋቂዎች መመልከቱ የበለጠ ይረዳል። እኔ እዚህ ላይ ላቀርብ የፈለግሁት፤ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር መጀመሪያ ወልቃይት ሲገባ፤ የነበረውን እውነታ ነው።

የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ወልቃይት ሲገባ፤ በቦታው ነበርኩ። ይህ የሆነው የዛሬ አርባ ሶስት ዓመት ነበር። በወቅቱ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የታጠቀ ክፍል፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት (ኢሕአሠ)፤ አባል ሆኜ፤ በወልቃይት እንቀሳቀስ ነበር። በወልቃይት ከተመደበው የሠራዊቱ ክፍል፤ አብዛኛው በበለሳ ሠራዊቱ ሊያደርገው  ካቀደው የማጥቃት ዘመቻ ጋር በተያያዘ፤ ለእርዳታ ወደዚያ ተልኮ ነበር። ይሄንን የሠራዊቱ አብዛኛው ክፍል ወደ በለሳ መሄድ በሰላዮቹ የተረዳው የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር፤ ቁጥሩ እጅግ የበዛ የታጠቀ ክፍሉን ወደ ወልቃይት ላከ። በወቅቱ ቦታውን ክፍት ላለማድረግ ወልቃይት የቀረነው በጣም ትንሽ ቁጥር ያለን የኢሕአሠ ታጣቂዎች (ከሃያ አምስት የማንበልጥ)፤ ከሁለት ተከፍለን ነበር። በዚያ ወቅት ጠገዴ በኛ ቁጥጥር ሳይሆን፤ በደርግ እጅ ነበር። አውራ በኛ እጅ ነበር። በጠገዴ በኩል ያለውን ለመከታተል አንዲት ትንሽ ቡድን (አስራ አንድ ጓዶችን የያዘች) በጠለሎ እንድትዘዋወር ተደረገች። ሌላዋ እኔ ያለሁባት ክፍል (አስራ አራት ጓዶች)፤ በሶስቱ ብላምባዎች አድርገን ወደ ቀብትያ ተንቀሳቀስን። የቡድኗ የፖለቲካ ኃላፊ ነበርኩ። ከቀብታያ ዋና ከተማ፤ ከአዲ ሕርጻን ወደ ሑመራ በሚወሰደው መንገድ ወጣ ብለን በምንንቀሳቀስበት ወቅት፤ አንድ የአካባቢው አርሶ አደር ወደኔ ጠጋ ብሎ፤ “አያ ጓዱ፤ እንዲህ ወደ አዲ ረመጥ የመጣው ነፋስ እንዲያው ደስ አይልም!” አለኝ። ከጓዶች ነጠል አድርጌ ወስጄ፤ “ምን ወሬ ተገኘ?” ስል ጠየቅሁት። “ኧረ! ይቺ የከብት ሌባ አዲ ረመጥ ገባች!” አለኝ። ይሄን አባባሉን ልብ በሉልኝ!

ይሄን ስሰማ፤ በጠለሎ ያለችው ቡድን አደጋ እንደተጋረጠባት ገባኝ። ዋናው ግን፤ ወደ ቆላው መዘጋ ሄጄ፤ ጠለምት ካለው ዋናው የሠራዊቱ ክፍል ጋር ግንኙነት መፍጠር መሆኑን አሰብኩ። በኛና በቆላው መዘጋ መካከል፤ ትሕነግ ከትግራይ ወደ ወልቃይት የምትመጣበት ዋናው መንገድ አለ። ከሁሉ በላይ አስጊው ደግሞ፤ ከቆላው መዘጋ ወደ ደጋው ወልቃይት ለመውጣት የምትጠቀምበት ቀጥ ያለው የብላምባ ዳገት በር፤ የኛም ወደ መዘጋ መውረጃ የዳገት በራችን መሆኑ ነው። ይሄ የማያፈናፍን ግጥጥሞሽ ሊያመጣ እንደሚችል አውቃለሁ። በፍጥነት አዲ ሕርጻን ከተማዋን ወደ ግራ ትተን፤ ከከተማዋ አጠገብ ያለውን ቁጢጥ ብሎ የቆመ ትንሽ ተራራ ታከን ለማለፍ ገሰገስን። ሁለት ትግርኛ ተናጋሪዎች አብሪ አድርገን፤ ሌሎቻችን የማታ  ልብሳችን የሆነችውን ቁራጭ ነጠላ (ኩሽክ) ጠመንጃችንን በሚደብቅ መልኩ ለብሰን፤ በጣም በተራራቀ ሁኔታ አንዳንድ ሆነን እየተንጠባጠብን ገፋን። ተራራዎ አጠገብ ስንደርስ፤ “ጠጠው በል! ማኒሃ!” (ቁም ማነህ!) የሚል ትዕዛዝ ከተራራው አናት ላይ ከቆሙት የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ታጣቂዎች፤ ለሁለቱ አብሪዎቻችን ተወረወረ። እነሱም በትግርኛ፤ “ንዕና ኢና!” (እኛ ነን!) ብለው ወደኋላ በማፈግፈግ ወደኛ ተቀላቀሉ። ጠባቂዎቹ፤ አርሶ አደሮች ናቸው ብለው አላስተባቋቸውም። አካባቢውን በደንብ ስለምናውቀውና፤ ጠባቂዎቹ ሁለቱን ጓዶቻችንን እንጂ ሌሎቻችንን ስላላዩን፤ በሰርጓዳው በኩል አድርገን መንገዱን ቶሎ በማቋረጥ፤ በቀብትያና በአዲ ረመጥ መካከል የሚኖሩትን ፊታውራሪ የሺወንድምን ለማግኘት፤ ባፋጣኝ ቀብትያን ለቀን ወደ ሾኔ የሳቸው መኖሪያ ቤት አመራን። እዚያ ስንደርስ ፊታውራሪ የሺወንድም በጣም ደስ አላቸው።

እሳቸው በልጅነታቸው ካባታቸው ጋር እዚሁ ሾኔ በገደሉ መሽገው ጣልያንን እንዳላስገቡት ነግረውኝ፤ “አሁን በዚህ በቆላው በዱሩ ምሽግ መያዝ አለብን! ሸመዶቼን አሰባስቤ፤ ይቺን የከብት ሌባ ድርሽ አናስደርጋትም!” በማለት፤ የራሳቸው የመከላከል ዕቅድ አውጥተው፤ እኔንና ጓዶቼን ሊያግባቡ ሞከሩ። እኔ ደግሞ ያለብኝን ኃላፊነት፣ የሠራዊቱ እኔን መረጃ እንድሠጣቸው መጠበቅና፣ በጠለሎ የሚንቀሳቀሱ ጓዶችን ጉዳይ አንስቼ፤ ላግባባቸው ሞከርኩ። አልተዋጠላቸውምና፤ አድሮ ሃሳቡን ይለውጣል በማለት፤ ከሳቸው ቤት አሳደሩን። በመጨረሻ ከኔ ዕቅድ እንደማልወጣ ሲረዱ፤ “በሉ እኔን አስቡኝ!” ብለው ሸኚ ሠጥተው ቆላውን ወርደን፤ ብላምባ ላይ እንድንወጣ፣ ከዚያ የማገኛቸውን ሰው በጥንቃቄ እንድቀርብ፤ ነገሩኝና ተሰነባበትን። ብላምባ የማገኛቸውን ሰው ስጠጋቸው፤ በድንጋጤ፤ “ለምን መጣህብኝ! የሷኮ ሠራዊት ቁጥር ስፍሩ አይታወቅም! በየቀኑ ሲጎርፉ ነው የሚውለው! በል ቶሎ ምግባችሁን ያዙና ከዚህ ጥፉልኝ!” በማለት ፍርሃታቸውን ገለጡልኝ። ወዲያው ሴቶቹ፤ “እኒህስ የኛዎቹ ናቸው!” ብለው በጥድፊያ ምግባችንን አዘጋጁልን። ከመካከላቸው አንዷን ትልቅ ሴትዮ ስለሁኔታው ጠየቅኋቸው። እሳቸውም፤ “አዬ ጓዱ፤ ምኑን ብለኸው ነው! ትናንት አዲ ረመጥ ገበያ እንድንገኝ ትዕዛዝ ሠጥተውን፤ እዚህ ገበያው ላይ ሰው በተሰበሰበበት፤ አዋጅ ነገሩ።” አሉኝ። በዚህ ወቅት ሌሎችን ቶሎ ቶሎ ምግባችን እንዲያዘጋጁልን አዘዋቸዋል።

“ምን ነበር አዋጁ?” ብዬ ጠየቅኋቸው። “አዬ አያ ጓዱ፤ ‘ከዛሬ ጀምራችሁ ትግሬዎች ናችሁ! ለቅሷችሁን በትግርኛ ማድረግ አለባችሁ! ዘፈናችሁን በትግርኛ ማድረግ አለባችሁ! አቤቱታ ለኛ ነው በትግርኛ ጽፋችሁ የምታቀርቡት!’ አሉን። ደሞ ማነው ትግሬ ናችሁ ብሎ የሚያዘን! ማነው በማናውቀው የትግርኛ ዘፈንና የትግርኛ ለቅሶ እንድናደርግ የሚያዘን! መንግሥት ይሁኑና ከከተማቸው ይቀመጡ! ግብር እንከፍላለን! እኛ ዳቧቸውን አልቀማናቸው! ሻሂያቸውን አልወሰድንባቸው! አልደረስንባቸው!” በማለት ንዴታቸውን ዘረገፉት። ማመን አቅቶኛል። በአዋጅ ትግሬ መሆን ምን ማለት እንደሆነ፤ ማሰቡ ቸገረኝ። ግን ይሄን ነው ወልቃይት ሲገቡ ያወጁት። የሕዝቡን ማንነት በአንድ አዋጅ መቀየር! የኅብረተሰብ ምሕንድስና ያልኩት ይሄን ነው። ተመልከቱ፤ ያኔ ገና ተከዜን መሻገራቸው ነው። ፓርላማ የለም። ሕገ−መንግሥት የለም። ወልቃይት የተወሰደው፤ አዲስ አበባ ከመግባታቸው ከአስራ ሁለት ዓመታት በፊት ነው።

ወዲያው ምግባችን ስለደረሰና ቶሎ ቦታውን ለቀን እንድንሄድ መፈለጋቸውን ስለተረዳሁ፤ ብዙ ዝርዝር ሳልጠይቃቸው ተሰናብቼ ወደ ቁልቁለቱ ገሰገስን። አጋጣሚ ሆኖ፤ እኛ በደረሰንበት ጊዜ የትሕነግ ሠራዊት በቦታው አልነበረም። ወርደን መዘጋ ገባን። መዘጋ ሰሊጥ እየበላን ወደ ጠገዴ አቅጣጫ በፍጥነት ተጓዝን። መሸት ብሎ ወደ ሸረላ ስንጠጋ፤ የተኩስ ልውውጥ ሰማን። የኛ ጓዶች ከትሕነግ ጋር መገናኘታቸው መሆኑን ማወቁ አላስቸገረንም። አስራ አንድ ጓዶች ከሁለት ሺህ በላይ የተገመተን የትሕነግ ታጣቂ ገጥመዋል። ስንገሰግስ፤ ከበለሳ የኛ ጓዶች ተመልሰው እነሱም ወደ ተኩሱ ሲሮጡ ተገጣጠምን። ሁኔታውን ከኛ በኩል አስረዳናቸው። መረጃው ደርሷቸው ቶሎ ገስግሰው እንደመጡ ነገሩን። እነሱ አንድ መቶ ይሆናሉ። በደስታ በሩጫ ተራራውን ወጥተን ጫፉ ላይ ስንወጣ፤ ካስራ አንዶቹ ጓዶቻችን ጋር ተገናኘን።

ፊታቸው ፈግቷል። የደስታ ሲቃ ይዟቸዋል። እነሱም፤ “ከአዲ ረመጥ እየተግተለተለ የሚመጣ ሰልፍ ዓየን። ግራ ገብቶን፤ ለሁሉም ቦታ እንያዝ አልንና፤ መሸግን። ሰልፉ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ሲሆን፤ እንደጎርፍ ቅደምና ተከተል ይዞ የተደራረበ ነበር። እየቀረቡ ሲሄዱ፤ የታጠቁ እንደሆኑ ገባን። ከተ.ሀ.ሕ.ት. (የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር − ትሕነግ) ሌላ ማንም ሊሆን እንደማይችል አውቀናል። ማፈግፈግ ፈለግንና፤ የለም! የኛን ቁጥር ስለማያውቁ፤ ለምን አንተኩስባቸውም! አልን። የመግደያ ሜዳው ላይ ሲገቡ፤ ተኩስ ከፈትንባቸው። እንዳልጠበቁት ግልጥ ነበር። ሲደናበሩ፤ የምንችለውን ያህል ረፍርፈን ወደ ሸረላ አቀናን። ከኛ በኩል ምንም ጉዳት አልደረሰም። የትስ ብለው ይተኩሳሉና!” አሉን። ሸረላ ተኩስ ከተከፈተበት ወደ ምሥራቅ የሚገኝ ተራራማ ገጽ አለው። “እነሱ ባሉበት ሆነው ምሽጋቸውን ማጠናከር ያዙ። እኛ ተራራማውን ቦታ ተቆጣጥረን እነሱን መከታተል ያዝን።” በማለት ያለፉበትን ሁኔታ አስረዱን።

በበነጋታው ሸረላ ላይ ከባድ ጦርነት ተድርጎ፤ ከኛ በኩል አስራ ሰባት ቁስለኞች (እኔን ጨምሮ) ከነሱ ደግሞ፤ ከአራት ቀን በኋላ፤ “ቅበሩ!” ተብለው የታዘዙ አርሶ አደሮች እንደነገሩን፤ ሰማንያ አስከሬኖችን ቀብረዋል። መብዛታቸው አይገርምም። ምክንያቱም፤ የግጥሚያ ስልታቸው ውጤት ነው። እኔ ባደፈጥኩበት ጉብታ፤ ትንንሽ ልጆች በገፍ ሲግተለተሉ መጡ። እስኪቀርቡ ድረስ፤ ከላይ እየተመከትን ዝም አልናቸው። ከኋላ ያለ አንድ አዛዣቸው፤ “ንቅድሚት! ወዲዛ ሸራሙጥ!” ሲል ሰማሁት። በጣም የሚያሳዝን ነበር። እሱ የትግራይ ወጣቶችን ለመማገድ ግድ የለውም። ከኋላ ሆኖ “ወደፊት! የሸርሙጣ ልጅ ሁላ!” ይላል። ወዲያው እሱን ስመታው አልወደቀም ግን እጆቹን በፊቱ ላይ ከልሎ፤ ወደኋላው ሩጫ ያዘ። እንደመታሁት እርግጠኛ ነበርኩ። ወጣቶቹ ረገፉ። ተከታትለን ሶስት ሆነን በመገስገስ፤ ከምሽጋችን በጣም ራቅን። ያን ጊዜ እኔ ቆሰልኩ። ሁለቱ ጓዶቼና እኔ ወደኋላ ተመለስን። በዚህ ዓይነት ሁለቱም ወገን ባለበት ቆመ። ቁስለኞች ወደ ኋላ ተላክን። ይሄንን ጦርነት

ይህ ነበር የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር የወልቃይት አገባብ። አንባቢ እንዲያውቅ የፈለግሁት፤ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር፤ በፖለቲካ ግቡ ተመርቶ፤ አንድም የሱዳንን በር ለማግኘት፤ ሌላም ለም መሬት ለመውሰድ ሲል፤ ያደረገው ወረራ መሆኑን ነው። ከሕዝቡ ማንነትና ፍላጎት፣ ከመሬቱ የመልክዓ መድር አቀማመጥ ወይንም የታሪክ መሠረት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። በወቅቱ የወልቃይት ሕዝብ ራሱን አማራ እንጂ፤ ትግሬ ብሎ አልቆጠረም። አንድ ምሳሌ ላቅርብ። እኔ በነበርኩበት ወቅት፤ አንድ ሰው ሞቷል ብሎ ከጉብታ ላይ ነጋሪ ከወዲያ ሲያሰማ፤ “ሰው ነው ትግሬ!” የሚል ከወዲህ ተቀባይ ይጠይቃል። ይህ ማለት፤ ሰው የሚሉት ወልቃይቴውን ነው። ትግሬ የሚሉት መጤ የሆነውን ትግሬ ነው። ትግሬዎች ሥራ ፍለጋ ለተወሰነ ጊዜ መጥተው፤ በወልቃይት ተቀጥረው ይሠራሉ። ገንዘባቸውን ሰብስበው፤ ሥራው ሲያልቅ ወደ ትግራይ ይመለሳሉ። አንዳንዶቹ ይጥማቸውና፤ ወይ ተጋብተው አለያም ቤተሰባቸውን ይዘው መጥተው ወልቃይት ይሠፍራሉ። ማንም ከልካይ አልነበረባቸውም። ይህን ነው፤ አማራውን ወልቀቴ ሰው በአዋጅ ገድለው፣ ትግሬነትን በአዋጅ አስፍረው፣ ወልቀቴን ትግሬ አድርገው ፈጥረው፤ ወልቃይትን የትግራይ መሬት ያደረጉት። ይህ የኅብረተሰብ ምሕንድስና ነው። ፈጣሪ መሆን!

በመጨረሻ፤ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር፤ በትውልድ ማንነት የአገራችን ኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደት መሾፈሩን ከጀመረበት ሰዓት አንስቶ፤ መፈራራትና መጠላላት፣ በየጎጆው መደበቅና “እኛ” እና “እነሱ” የሚል ክፍፍልን ዘርቶ ወደማያልቅ መተላለቅ ደንጉሮናል። ከዚህ በቀላሉ የማንወጣበት አዘቅት ውስጥ ሆነን፤ አንዱን ወይንም ሌላውን፣ በዚህ ወይንም በዚያ መንገድ እያልን ስንዳክር፤ በመካከላችን ያለው የተካፋፈልንበት ምክንያት እየበዛ፤ ርቀቱ እየከፋ፤ “ደህና ሁኚ እትዮጵያ!” ልንል አንድ ሐሙስ ቀርቶናል። ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሥልጣኑን የተረከበው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፤ ከተረከበበት መንገድ በከፋና ጋጠ ወጥ በሆነ መንገድ አባብሶ፤ እየገዛ ነው። አሁን አማራውን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር አጠፋለሁ ብሎ ዘምቶበታል። ለሆዳቸው ያደሩ የ"አማራ ብልፅግና!” ነን ባዮች፤ መንገድ መሪና ጠራጊ ሆነው እያገለገሏቸው ነው። የአማራዎች ጠላት፤ አንድም ኦነግ ብልፅግና፤ ሌላም የ“አማራ ብልፅግና” ናቸው። ኦነግ ብልፅግና ጠላት ነው። የ“አማራ ብልፅግና” አሾክሻኪ ነው። እናማ! “ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው! አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው!” የተባለው ለቀልድ አይደለም።

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/184252
Ethiopia has made an official request to join the BRICS bloc of emerging economies
By TESFA-ALEM TEKLE

Ethiopia has made an official request to join the BRICS bloc of emerging economies, the Ministry of Foreign Affairs said.

The BRICS is a five-member bloc comprising Brazil, Russia, India, China and South Africa.

"We have applied for membership and we expect BRICS to give us a positive response to the request we have made," Foreign ministry's spokesperson Meles Alem said on Thursday.

He added that Ethiopia would continue to work with international institutions that can protect its interests.

"As a country that has been a founding member of global institutions like the AU and the UN, and as we seek to guarantee our national interests, it is important to join blocs like BRICS," he said.

Ethiopia, with the second highest population in Africa, is one of the continent's fastest-growing economies, according to the International Monetary Fund,

In its latest World Economic Outlook, the IMF revised its earlier forecast of Ethiopia’s GDP in 2023 from $126 billion to $156.1 billion. But, its economy is less than half of South Africa - the smallest of the BRICS partner states.

Other countries that have sought to join the bloc include Egypt, Algeria and Bangladesh.

Argentina, Iran, Indonesia, Saudi Arabia and Turkey have also expressed interest in joining the alliance.

Last month, South African officials said over 19 countries had expressed interest in BRICS membership.

The bloc, initially named BRIC as an acronym of the member states, was formed in 2009. A year later, in 2010, the letter S was included when South Africa joined.

Pretoria is set to host the annual BRICS summit in August.

https://zehabesha.com/a-new-global-reserve-currency-will-undermine-us-dollar/
https://zehabesha.com/ethiopia-has-made-an-official-request-to-join-the-brics-bloc-of-emerging-economies/
The Ethiopian Airlines: An Epitome of Oromummaa's Predatory Greed and Gangsterism
Yonas Biru, PhD

First, let us make one thing clear. Though Oromummaa means “Oromoness”, the term has been hijacked by criminal thugs and intellectual savages who have made robbing Ethiopia and institutionalizing mass murder, forced displacement and industrial level demolition of Churches and Mosques as an Oromo ideology and political theology. Professor Asafa Jalata defines Oromummaa as a political project. Anyone who has read the good professor's articles and listened to Shimelis Abdissa’s public speeches about Oromummaa cannot deny this.

The Oromummaa overlords have their eyes on the Ethiopian Airlines. Last month, I published two short blogs about the Ethiopian Airlines under the title “The Reason Behind Ato Girma Wake’s Termination.” In summary this was what I wrote.

“Two months ago, I predicted one potential source of foreign exchange to finance the PM’s Palace is taking loans from China collateralizing the Ethiopian Airlines. Two days ago, I speculated the reason behind Ato Girma’s termination is to transfer foreign exchange from the Ethiopian Airlines to the palace. Today, I learned the PM is in discussion with China to let them take over the Cargo business of the Ethiopian Airlines until Ethiopia pays its debt.”

Recently, I was with a friend at the Starbucks when he got a call from Addis Ababa. With his permission my friend put the call on speaker so I can talk to the person. The person took the opportunity to correct my blog about Ethiopian Airlines. Here is how he put it.

The Airlines’ Cargo business is run separately. What the Prime Minister has done is instructing the Airlines to use the profit from the Cargo business to pay Chinese contractors building the new palace along with its opulent surroundings. This is not far from what I wrote about how China does its business in Africa. They take collateral be it an airport (Zambia), a seaport (Kenya) or a minefield (Angola). Ethiopia does not have minefields other than goldmines that produce about $1 billion per year in a good year

Let us do the math. The palace is estimated to cost $15.3 billion. In most cases, construction projects cost far more than the original estimates. Let us say it will cost 25% to 50% more than the estimate. This is a modest projection. It can be more. This amounts to $19 billion to $23 billion.

If China is building the Palace and say China’s contract accounts for 75% of the total cost, this comes to or $14.3 billion to $17.3 billion. Let us say the profit the Cargo business produces is $2 billion per year. Let us also assume it takes China five years to build the palace. China will effectively hold the Cargo business from 7 to 9 years as a collateral until it is paid fully. If the Airlines business produces only $1 billion profit per year, that means 14 to 18 years. The longer it takes to pay, the more the interest rate component of the cost skyrockets. That means it can go beyond 14 to 18 years.

There is another story. The airline is interested in building a separate terminal for its business. How is it decided where this terminal should be? In a federalist system, this is done through competition. Each tribal homeland will be asked to submit a bid. Say Somali may say I will give the land for free and build infrastructures such as roads and electricity. The Amhara tribal land may say Debre Berhan is central to all regions and besides it will give free land and build infrastructure. The benefits for these homelands include job creation and tax revenues.

But this is not how it is done. The opportunity is exclusively given to the Oromo tribal land and Shimelis Abdissa is demanding billions in payment for the land. This is Oromummaa’s Predatory Greed and Gangsterism.

Can the Airline deny, the Cargo revenue is not and will not be used for the construction of the palace? Can it deny it is being asked to pay billions to build a terminal for the cargo business? Why should the airline pay billions for Oromo when other regions can potentially offer it free land with additional incentives?
https://zehabesha.com/the-ethiopian-airlines-an-epitome-of-oromummaas-predatory-greed-and-gangsterism-yonas-biru/

Saturday, July 1, 2023

https://youtu.be/NPE_evszlxo

አፌን ከፍተው ሽንታቸውን ሸኑብኝ'' ፥ የአሜሪካን ውሳኔ ፖለቲካዊ? ኢትዮጵያና BRICS
https://amharic-zehabesha.com/archives/184247
https://youtu.be/NPE_evszlxo

አፌን ከፍተው ሽንታቸውን ሸኑብኝ'' ፥ የአሜሪካን ውሳኔ ፖለቲካዊ? ኢትዮጵያና BRICS
https://amharic-zehabesha.com/archives/184247
Ethiopia’s Request to Join BRICS is a Sign of Desperation, Not of Strategy
Yonas Biru, PhD

Ethiopian intellectuals are half tribalized and half hermitized. They are driven by the emotional diktats of centuries past and Gadda this, Axum that, and Lalibela ኡኡ cacophony. They are, therefore, unfit to comprehend the nation’s geo-political challenges and opportunities. Ethiopia’s application to join BRICS is partially attributable to this phenomenon.

Let me spell out two key points from the outset. First, it is highly unlikely BRICS will admit Ethiopia. Second, even if it admits Ethiopia, there is no tangible benefit Ethiopia can get from joining the good-for-nothing Club.

BRICS stands for the regional economies of Brazil, Russia, India, China, and South Africa. It is a scheme China started to establish Chinese hegemony by countering the Bretton Woods institutions (the IMF and World Bank) and the United Nations that are dominated by the West.

The first question champions of BRICS need to answer is: What has BRICS achieved since it was established in 2001, nearly a quarter of a century ago? The answer is: “Nothing to write home about.” Here are the reasons why it has not succeeded to date, and it is unlikely to succeed in the near future - in the next 25 years or even 50 years.

Next to China, the most important country in the BRICS architecture is India in terms of economic significance. India is China’s strategic rival. First, there is an intractable border conflict between the two. Second, as the West is shifting its supply chain out of China, India is aggressively presenting itself as a hub for the West’s supply chains. The Wall Street Journal rightly headlined this phenomenon in two recent articles. “India, Wary of China, Expands Trade Ties With the West“ and “The U.S. Pursues India as a Supply-Chain Alternative to China.”

Let us look at the key Economic factors. According to the 2022 World Bank GDP data, China's GDP is more than double that of the other four BRICS nations combined. China’s GDP was $17.96 trillion compared to India ($3.39 trillion), Russia ($2.24. trillion), Brazil ($1.92 trillion) and South Africa (405.9 billion). In total, BRICS accounts for 25% of the World economy.

What explains BRICS’ failure to expand its membership and, therefore, its economic power vis-à-vis the West? There are two reasons. First, BRICS is envisioned as an exclusive club for emerging economies, not for what Trump called “shithole countries.” Trump says it out loud. BRICS policy is quietly excluding what Trump calls “shithole countries.”

If BRICS expands its membership to poor countries such as Ethiopia, it will have serious economic implications. Such nations need grants and concessional loans at or near zero interest rate. China is the only country with resources, but it does not provide grants and low interest rate loans. The other four countries are not in any position to provide grants and loans. Over the last decade, South Africa's and Brazil's economies have been on a downward trajectory. Simply put, BRICS cannot rival the West in supporting the development needs of poor countries. Then what good is it for nations like Ethiopia? Expanding its membership will expose this structural deficit.

Second, why is BRICS reluctant to expand membership for emerging countries? India, the second largest economy within the club, understands BRICS’ success lends itself to creating a Chinese hegemony. India joined BRICS not so much to support China’s initiative but to put a leash on it. India has been against adding new members especially those who are seen as pro-China or under China’s influence.

Nations such as Iran, Saudi Arabia, and Mexico have shown interest to join, but BRICS has been dragging its feet. First Iran and Saudi are rivals and Mexico’s economy is too dependent on the US. If BRICS wants to rival the West in earnest, it needs to establish a common agenda and its primary members need to be free of the West’s influence.

The reality is that BIRCS is a hotch-potch of nations with different, if not, irreconcilable geo-political and geo-economic interests. That is why it has not achieved any milestone in its over two-decade existence.

Let us return to Ethiopia's application to be a member. Prime Minister Abiy is a random walking soul. Not long ago, he was a Pan Africanist in the mold of Sankara. Not long after that he declared his allegiance to the US telling an American journalist that he will die for America. As evidence he emitted signals that he will send troops to remove the President of Eritrea from office if supported by the West. Soon after the President of Eritrea traveled to China and Russia. China and Russia sent an unprecedented signal to stand with Eritrea.

Today, the random walking Prime Minister wants to join BRICS to emit yet another signal to the West. The question is not whether BRICS will accept Ethiopia. The real question is: Will BRICS take the application as seriously as the tribalized and hermitized Ethiopian intellectuals have.

 

 
https://zehabesha.com/ethiopias-request-to-join-brics-is-a-sign-of-desperation-not-of-strategy/

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...