Tuesday, March 19, 2024
ግርማ ካሳ
ይህ ድርጅት፣ በወረቀት እንጂ በተግባር ያለ አይመስለኝም ብዬ ጽፌ ነበር፡፡ "ተሳስተሃል፣ መረጃው ስለሌለህ እንጂ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው" ተብያለሁ፡፡ እርማቱን ተቀብያለሁ፡፡ በመሆኑም "አላውቅም" ከማለት ውጭ "ያለ አይመስለኝም ወይም የለም" ብሎ መነገር አልችልም፡፡ ስለዚህ ብዙ መረጃ ስለሌለኝ እንዲህ ነው እንዲያ ነው ብዬ ለመናገር ይከብደኛል፡፡
ሆኖም ግን መረጃ ስላገኘሁበት ጉዳይ ግን መናገር እችላለሁ፡፡ በነ ሻለቃ መከታው ማሞና መምህር ምንተስኖት የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ፣ ከዚህ "የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት" ከሚባለው ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ ወንድም እስክንደር ነጋ ፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ አመራር ውስጥ አንዱም፣ ጋር የለበትም፡፡ ከጎጃም ወደ ሸዋ ሲመጣ፣ የህዝብ ልጅ፣ የአገዛዙ ታርጌት በመሆኑ ጥበቃ ለርሱ መድበው የርሱን ደህንነት ከመጠበቅ፣ አልፎ አልፎ አንዳንድ ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ፣ እንደ ታዋቂ በህዝብ ተወዳጅ ሰው፣ የሸዋ ፋኖዎችን ወክሎ ሳይሆን ራሱን ወክሎ ንግግሮች እንዲያደርግ ከማመቻቸት ውጭ፡፡
ከዚይ ባለፈ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ መሪዎች፣ ሌሎች እንደሚያደርጉት፣ በየቱቡና ሜዲያ ወጥተው የህዝብ ልጆች፣ ታጋዮች ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ተፈልጎ ከሆነ አያደርጉትም፡፡ ልዩነቶች፣ ክፍተቶችም ካለ የውስጥ ጉዳይ ነው በሚል ችግሮችን በውስጥ፣ በውይይት ለመፍታት ይሞክራሉ እንጂ፣ በየሜዲያው ለአገዛዙ ግባት የፖለቲካና የፕሮፖጋንዳ ትርፍ የሚስጥ ስራን አይሰሩም፡፡ የነርሱ ትኩረት አገዛዙ ላይ እንጂ ሌሎች ፋኖዎች፣ ሌሎች ለህዝብ የሚታገሉ ወገኖች ላይ አይደለም፡፡
ከዚህም የተነሳ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝን፣ ከአማራ ህዝባዊ ሰራዊት ከተባለው ጋር በማገናኘት፣ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት የተባለው ስብስብ አመራሮች ለሰሯቸው ወይንም ለሚሰሯቸው ስህተቶች፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ጋር ማገናኘት ተገቢ አይደለም፡፡
በተቃራኒው ደግሞ አንድ ዋሺንገትን ዲሲ ያለ ወንድም አለ፡፡ አገሩን የሚወድ ታጋይ ነው፡፡ ቢያንስ በውጭ፡፡ ግን የፖለቲካ ብስለት የሌለው፣ ምን አልባት የጤና ችግር ያለበት፣ ስራ ፈት ሰው ነው የሚመስለው፡፡ ሺመልስ ለገሰ ይባላል፡፡ ይህ ሰው የ እስክንድር ነጋ የቅርብ ሰው ነኝ ባይ ነው፡፡ ሆኖም የእስክንድር ነጋ የቅርብ ሰው ነው ማለት፣ እስክንድር ነጋ ነው ማለት እንዳልሆነ በትልቁ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ብዙ ፣ ካድሬ ይመስል፣ "እስክንድር፣ እስክንድር" የሚሉ አሉ፡፡ ይህም ሰው እንደዚያ ነው፡፡ ይህም ሰውም ሆነ በዳያስፖራ ያሉ ቢጤዎቹ፣ ሌላ የራሳቸው አጀንዳ ይኖራቸዋል፡፡ እነርሱ በሚያደርጉት ነገር ግን እስክንድር ነጋ ላይ ማላከክ ተገቢ አይመስለኝም፡፡
እነዚህ ሰዎች "የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ" በዳያስፖራ የድጋፍ ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ፣ ለእስክንድር ነጋ ጥበቃ ሲያደርግ የነበረና ምን አልባትም ወደሌሎች ጠቅላይ ግዛቶች እስክንድር ካልሄደ፣ ለእስክንድር አሁንም ጥበቃ እያደረገ ያለ መሆኑን ሳያውቁ ቀርተው አይደለም፡፡
ታዲያ፣ " የእስክንድር ነጋ ደጋፊዎች ነን"፣ እያሉ፣ እስክንድር ነጋን እየጠበቀ ያለ ኃይልን አለመደገፍ ፣ እዙ እያደረገ ያለውን የድጋፍ ማሰባሰቢያ ለማጨናገፍ መሞከር ምን ሊባል ይችላል ?? ጸረ እስክንድርነት፣ በእስክንድር ስም የሚደረግ የአብይ አህመድና ዘረኛው አገዛዝ ጥቅም የሚያስጠብቅ ፣ ብልጽግናዊ፣ ኦህድዳዊ አሳፋሪ ስራ ካልተባለ በቀር !!!!
ወገኖች እኔ ይሄንን በምጽፍበት፣ እናንተም በምታነቡበት ጊዜ ፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ውስጥ ያሉ ፍከለ ጦሮች ከአገዛዙ ጋር አንገት ለአንገት እየተናነቁ ነው፡፡ ህይወታቸውን አወራረደው፣ ለአገር፣ ለህዝብ ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ነው፡፡ እነርሱን አለመደገፍ፣ ከነርሱ ጎን አለመቆም አይቻልም፡፡
ከዚህ በታች ያለውን ማስታወቂያ እናንንብ፡፡ ባር ኮዱን በስልካችን ስካን በማድረግ እንዴት መደገፍ እንደሚገባ ወደ ሚያሳይ ገጽ ይሄዳሉ፡፡
https://amharic.zehabesha.com/archives/189394
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment