Saturday, March 16, 2024
ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)
(ለሻለቃ መሣፍንት ልጅ መታሰቢያ ትሁን)
የኃላው ከሌለ የፊቱ የለም!!! ታሪክ አልባዋ ከተማ A City Without Its Past
‹‹ወይ አዲስአበባ፣ ወይ አራዳ ሆይ፣
አገርም እንደሰው፣ ይናፍቃል ወይ!!!
አዲስ አበባ ከተማ ያለ ጥንታዊ ታሪክ!!! A City Without Its Past ………. Demography Change የእስክንድር ቃል ጠብ አላለችም!!! ‹‹ከሰው በፊት የአዲስ አበባ ህዝብን አታፈናቅሉ፣ ቅርሳችንን አታውድሙ፣ አረንጎዴ፣ቢጫ ቀይ ባንዲራችንን አትንኩ፣ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት እየተደረገ ነው›› እያለ በአገር ውስጥ በአደባባይ የሞገተ፣ ዘጠኜ የታሠረ፣ በዓለም አቀፍ አደባባይ በተባበሩት መንግሥታት ፊት ከፕሮፊሰር ጌታቸው ኃይሌ ጋር የአማራን ጀኖሳይድ ያስመዘገበ ባለ ራአዩ የጥንት የጠዋቱ ቆራጥ ታጋይ ታላቁ እስክንድር ያሉት ፕሮፊሰር መስፍን ወለወደማርያም ናቸው፡፡ የእስክንድር ስምና ብዕር ለመለስ ዜናዊ ለወያኔ ኢህአዴግ ፋሽስታዊ አገዛዝ መቅሰፍት ነበረች፣ የእስክንድር ስምና ብዕር ለኮነሬል አብይ አህመድ የኦህዴድ ብልፅግናም ዘረኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ የማትዋጥ የማትተፋ መርዝ ናት፡፡ የታላቁ እስክንድር ትንቢተ ቃል ተፈፅሞል…..በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት (ጀኖሳይድ) ተፈፅሞል!!!
እስክንድር የሞቀ ትዳሩንና ቤቱን ከሃገረ አሜሪካ ጥሎ አገር ቤት በርሃ ወርዶ፣ ህዝብቀስቅሶ፣ ፋኖን አደራጅቶ ባይመክት የአማራ ህዝብ ዛሬ ለኦሮሙማ ሥርዓት! ለኦህዴድ ብልፅግና እንቁላል ይገብር ነበር፡፡ የእስክንድር ብዕር ኮነሬል አብይን አሥር ክፍለጦር ድባቅ ይመታል፣ እስክንድር የህዝብ መከታና የደሃ አሌንታ፣ ሰው ሰው የሸተተ ስብእና የተላበሰ የህዝብ ልጅ በወያኔ፣ ኦህዴድና ብአዴን ማንም ምናምቴ ስሙ አይጠራም፡፡ እስክንድር በብዕሩ ሲወድቅ ሲነሳ፣ ሲታሰር ሲፈታ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለእኩልነትና ለነፃነት እድሜ ልኩን የታገለ የኢትዮጵያ ፋኖ አርበኛ ነው፡፡ አንድ ለእናቱ! እስክንድር ዱር ቤቴ ብሎ እናንተን አምኖ፣ ለእናንተ ለመሞት፣ የዘር ፍጅትን ለማስቆም፣ የሃገር ጥፋትን ለማስቆም፣ ሁላችንም ፈርተን በራድን ጊዜ፣ ለኮነሬል አብይ አገዛዝን እንቢ አሻፈረኝ ያለ ለመሠረታዊ ለውጥ የታገለ ጀግና የጥንት የጠዋቱ እሱ ብቻ ነው፡፡ ቤታችንን ሲያፈርሱ ከእኛ ጋር ነበር!!!.......... ሲርበን ሲጠማን ከእኛ ጋር ነበር!!! ባንዲራችንን ሲያወርዱ የሰቀለ እሱ ነበር፡፡ የእስክንድር ግፍ ብዙ አለብን!!! ከሰው በፊት የተገለጠለት እሱ ነበር!!!……….የእስክንድር ራዕይ ህዝብን ለማዳን እንጂ ለሥልጣን አልነበረም፡፡ ኮነሬል አብይ እስክንድርን ለማስገደል ዶልቶ፣ ከጎጃም ምድር ፣ አንዴ አሳፍኖ ሊወስደው ሲል ህዝብ አስለቀቀው እስክንድር የህዝብ ልጅ ነውና!!! ኮነሬል አብይ ሴጣን ካልገደለ አይተኛምና እስክንድርን ከደብረ ኤልያስ ገዳም በደም ነጋዴዎች ጠቆሚነት አሳዶ ሊገለው ሲል በጎዶቹ ብርታት አመለጠ፡፡ እስክንድር
‹‹በርከክ በርከክ አሉ፣ አውሬ መስያቸው
ከሰው መፈጠሬን ማን በነገራቸው
ወንደድሙን ሲገለው፣ ወንድሙን ካልከፋው፡፡
ሱሪውን አምጡለት፣ ደሙ እንዲከረፋው›› ተባለለት፡፡
እስክንድር የሃገሪቱ ታሪካዊ ቅርሶች በኮነሬል አብይ አህመድ ኦህዴድ ብልፅግና ካድሬዎች እየፈረሰ ነው ህዝብ ተነስ ተቃውሞህን አሰማ ብሎ ከፊት እመራ ሲታገል ሁሉም ፈርቶ፣ተከታይ አጣ፡፡ ዛሬ ሜክሲኮ ሠንጋተራ አካባቢ ሸበሌ ሆቴል ጎን የፈረሰው የዘጠና አመት ያስቆጠረው ቅርስ ሎምባርዲያ ሬስቶራንት ህንፃ በዓይናችን አይተናል፡፡ ዛሬ ለገሃር አካባቢ የፈረሰው ቅርብ ጊዜ የተሠራው የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅትና፣ የቬርኔሮ ህንፃ መኪና ተራ ጎን የነበረ ህንፃ ወደ አመድነት ተቀይረው፣ በዓይናችን አይተናል፡፡ ለአረብ ኢምሬትስ ኤግልስ ሄልስ ፕሮጀክት (Eagle Hills project – La Gare in Ethiopia) በስድስት አመት ተሰርቶ የሚያልቅ ህንፃዎች ሰዕልለላንቲካ የሚሆን ፎቶግራፍ አሳይተውን ወፍም የለ!!! አብይ ሦስት ሽህ ስድስት መቶ ሜትር ካሬ ቦታ ለአረብ ወዳጆቹ ሸጠ፡፡ ዛሬ አራት ኪሎ የተፈጥሮ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ ህንፃ አፈረሰው፡፡
የሥነ-ሕዝብ ለውጥ (Demography Change) የኮነሬል አብይ መንግሥት የአዲስ አበባ ህዝብ የሥነ-ህዝብ ለውጥ ማድረግ የፈለገው የአዲስ አበባ ብሔር ብሔረስብ ስብጥር በ2007 እኤአ Ethnic groups of Addis Ababa (2007) አማራ Amhara (47.05%)፣ ኦሮሞ Oromo (19.51%)፣ ጉራጌ Gurage (16.34%)፣ ትግራይ Tigrayan (6.18%)፣ ስልጤ Silt'e (2.94%)፣ ጋሞ Gamo (1.68%)፣ ልዩ ልዩ Other (6.3%) በመሆኑ የአማራ፣ የጉራጌ ህዝብ ቁጥር በቤት ማፍረስ ለመቀነስ፣ ከአዲስ አበባ ለማስወጣት ብሎም የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ለመጨመር በአዲስ አበባ ማስፈር ጀመሩ፡፡ ኮነሬል አብይ መንግሥትን የኦሮሞ ህዝብ አንቅሮ ስለተፋው እቅዳቸው ከሽፎል፣ በፍቅርና በአንድነት የኖረውን የኢትዮጵያን ህብረ-ብሔር ህዝብ መለያየት የኦህዴድ ብልፅግና ካድሬ አይችልም፡፡ የወያኔ ኢህአዴግ ካድሬም ወድቆልና!!!
2019 እኤአ ጀምሮ የኮነሬል አብይ የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ ዘመን ከፍተኛ የቤት ማፍረስ ዘመቻ በ‹‹ህገወጥ ንብረት ስም››በአዲስ አበባ ከተማና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ፣ለገዳዲ፣ሱሉልታ፣ኢልሞጆና፣ ገላን ከተሞች ንዎሪዎች የነበሩ አስራሁለት ሽህ አባወራዎች ቤት ፈረሰ፡፡ እስክንድርና ባልደራስ ድርጅት ብቻ ነበሩ በግንባር ቀደምትነት የቤት ፈረሳውን የተቃወሙት፡፡ Since early 2019, the Ethiopian government under Abiy Ahmed administration begun large-scale house demolition that deemed "illegal property" in Addis Ababa and the Oromia Region in the area of Sebeta, Buraryu, Legetafo, Legedadi, Sululta, Ermojo, and Galan towns, with 12,000 houses destroyed by the government, which led to further unrest in the country…………………..(1)
በፌብሪዎሪ 19 ቀን 2019እኤአ ማለዳ ጠዋት የለገጣፎ ከተማን ቡልዶዘሮች ወረሮት የሦስት ሽህ አባወራዎችን ቤቶች ዶጋ አመድ አደረጉት፡፡ ሦስት ሽህ ቤት አልባ ዜጎች፣ ከነመተዳደሪያ ንግድ ቤታቸው ተዘጉ፡፡ የለገዳዲና ለገጣፎ ከተሞች ከንቲባ ሐቢባ ሲራጂ የቤቶቹ መፍረስ በ2017 እኤአ ማስተር ፕላን መሰረት የከተማ ስትራቴጂ መሆኑን በመደገፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠጭ፡፡ On 19 February 2019, bulldozers were raid into Legetafo area and demolished 3,000 homes, leading to thousands homelessness and ruin business activities. Mayor of Legetafo Legedadi Habiba Sirajs supported the demolition as a necessary steps corresponding to the 2017 master plan, which was part of urban strategies.
ኮነሬል አብይ አህመድ ሃገር ለመሸጥ፣ የሰው ጎጆ ለማፍረስ፣ እናቶችን ለማስለቀስ የመጣ ሴጣን ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ደሓዎቹን ጠራርጎ በማፈናቀል ለዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ኤግል ሒልስ ኩባንያ (Eagle Hills) 360000 (ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ) ካሬ መሬት ቦታ የሸጠ ነውረኛ ሰው ነው፡፡ ለኤግልስ ሒልስ ፕሮጀክት ሲባል የፈረሱ ህንፃዎች ከላይ ከፎቶግራፍ ላይ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ማየት ይቻላል፡፡ ኢምሬትስ ኤግል ሒልስ በፈረሰው ቦታ ላይ ከአንድ ፎቅ ሌላ የሠራው የለም፡፡ ቦታው ድረስ ሄዶ በማየት ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት አብይ፣ አዳነች አቤቤ፣ ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ የአዲስ አበባን ከተማ ንዋሪዎች በማፈናቀል ላይ እንዳሉ መገንዘብ ያሻል፡፡
{1} በዳግማዊ ዐፄ ምኒሊክ ዘመን በ1917እኤአ የተገነባው የመቶ አመታት ታሪካዊው ፍራንኮ ኢትዮጵያ ምድር ባቡር ይፈርሳል፣ ኮነሬል አብይ የምኒልክን ታሪካዊ ውርስና ቅርስ በማጥፋት ቤተመንግስታቸውን በአንድነት ፓርክ ብሎ ሰይሞታል፣ ከመቶ አመታት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ መንግሥት ምድር ባቡር ቅርስ አጥፍተዋል፣
{2} የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ብዙ መቶ ሚሊዩን ብር የወጣበት አዲስ ህንጻ ፈርሷል፣
{3} የቡፌ ደ ላጋር ታሪካዊ ባህላዊና ዘመናዊ የመዝናኛ ሥፍራ ፈርሷል፣
{4} የቬርኔሮ ህንፃ ባለ ስድስት ፎቅ ህንፃ ፈርሷል፣
{5} የሞዓ አንበሳ ሃውልት ከጣልያን ሃገር የተመለሰው ሐውልት፣ በሮም የጀግናው ዘርዓይ ድረስ የተሠዋበት ታሪካዊ ሃውልት በደንብ አልተያዘም፣ ወዘተ
ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ (United Arab Emirates)፡- የአቡ ዳቢ ኩባንያ፣ ኤግል ሒልስ (Eagle Hills launches project – La Gare in Ethiopia) በአዲስ አበባ ከተማ ለገሃር ሠፈር ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት 360,000 sq metres (ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ) ካሬ ሜትር ባለ ይዛታ ሲሆን የቦታው የስፋቱ ትልቅነት ሃምሳ የአዲስ አበባ ስታዲየምን ያክላል፡፡ ኤግልስ ሒልስ ኩባንያ በተሰጠው ቦታ ላይ ባለ አራትና አምስት ኮኮብ ሆቴሎች ለመገንባት፣ የመዝናኛ ሥፍራዎች ለመስራት፣ አራት ሽህ ቤቶች ለመስራት እቅድ ነድፎ ነበር፡፡ ኤግልስ ሒልስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ወጪ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት 27% (ሃያ ሰባት) በመቶ ድርሻ አለው ተብሎል ነበር፡፡ ኤግልስ ሒልስ ኩባንያ ስልሳ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ በጀት በመመደብ ለአንድ ሽህ ስድስት መቶ አባወራዎች የመኖሪያ ቤቶች እንደሚሰራና ምንም ዓይነት መፈናቀል እንደማይኖር ለንዋሪዎቹ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ ኤግልስ ሒልስ ኩባንያ የለገሃር ፕሮጀክት ለሃያ አምስት ሽህ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርና በሰባት አመት ፕሮጀክቱ ተሠርቶ እንደሚያልቅ ተገልጾ ነበር፡፡ ወፍም የለ!!! ወሬ ነው ኮነሬል አብይ አገር የሸጠ ባንዳ መውደቂያው ደርሶል፡፡ “Abu Dhabi firm, Eagle Hills has launched a massive integrated community development project, La Gare in Ethiopia. La Gare will cover 360,000 sq metres of the Ethiopian capital, Addis Ababa and would include multi-star hotels, leisure outlets, commercial units, and 4000 homes. The estimated value of La Gare is $2 billion and the Ethiopian government is reported to hold a 27% share in the project. According to the Ethiopian Prime Minister, Abiy Ahmed, Eagle Hills has set aside an additional budget of $68 million for 1600 households that would be uprooted during the development process……..Reportedly, apart from creating a new city center, La Gare would also lead to an increase of approximately 25,000 jobs. The project is said to finish its first phase of development, mainly the construction of malls, in three years. The overall estimated time for project completion is reported to be seven years.”………………………………….(2)
ኤግልስ ሒልስ (Eagle Hills)፡- የጡት አባታቸው ኮነሬል አብይ አህመድ በተገኘበት አቡዳቢ መሠረቱን ያደረገ የግል ሪል ስቴት ኢንቬስተር ወደ ኢትዮጵያ ምድርና ንግዱ ህብረተሰብ ሠተት ብሎ ገባ፡፡ በአዲስ አበባ ለገሐር ባቡር ጣቢያ እንዲከትም ኮነሬል አብይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ተመቻቸለት፡፡ በለገሐር ባቡር ጣቢያ ሦስት ሽህ ስድስት መቶ ካሬ ሜትር ኩታ ገጠም ቦታ በኮነሬሉ ያለ አንዳች ጨረታ ገጸ-በረከት ተበረከተለት፡፡ የለገሃር አራት ሽህ ንዋሪዎችን ያፈናቀለ ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት ለንዋሪዎች መኖሪያ ቤት ይሠራል ተብሎ በውሸት ተሰበከ፡፡
ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት በስድስት አመታት የግንባታ ጉዞው አንድ የመኖሪያ ኮንዶሚኒየም በመስራት ገና ተጠናቆ ሳያልቅ በሙሉ መሸጡ ታውቆል፡፡ ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት የገነባውን እየሸጠ በሚያገኘው ገንዘብ ሌላ በመገንባት ላይ የሚገኝ ደሃ ደላላ ድርጅት ነው፡፡ ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት ሌላ ቦታ አንድ አምስት የመሠረት ግንባታ የሠራባቸው ሥፍራዎች በተለያዩ ሳይቶች ይስተዋላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ጋዜጠኞች፣ የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የከተማችን የፓርላማ አባሎች ካሉ ይሄን ሥፍራ ጎብኝተው፣ የሚሠራውን የወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ላለፉት ስድስት አመታት የተሠራ የኤግል ሒልስ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት በመመልከት ኃላፊነታቸውን እንዳልተወጡ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ኤግል ሒልስ ሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ድርጅት ሥፍራውን ተነጥቆ ለኢትዮጵያዊያን አገር በቀል ሪል ስቴት ኢንቨስተሮች በጨረታ ቦታውን እንዲያለሙ እድል ቢያገኙ ተዓምር መሥራት ይችልሉ፡፡ አገር በቀል ሪል ስቴት ኢንቨስተሮች፣ ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ ሊዝ ገዝተው እንዲያለሙና በግፍ ለተፈናቀሉ ደሃ የህብረተሰብ ቤት ጨምሮ በመገንባት፣ ኤግል ሒልስ ከአገር እንዲወጣ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው እንላለን፡፡ የኮነሬል አብይ አህመድና የሼክ መሃመድ ቢን ዛአይድ አል ናህያን ሚስጢራዊ ግንኙነት አገራችንን ወደ ማያባራ ጦርነት በማሸጋገር ላይ ይገኛል፣ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ደግሞ ሰው አልባ ድሮውን በመስጠት ንፁሃን ዜጎች እንዲጨፈጨፉ አድርገዋል፡፡ ዲያስፖራው በየአረብ ኢምሬትስ ኢንባሲዎች ሠላማዊ ሠልፍ በማድረግ ሼክ መሃመድ ቢን ዛአይድ የኮነሬል አብይ አህመድን መንግስት መቃወም ይገባቸዋል፡፡ ኢምሬትስ ሰው ዓልባ አውሮፕላኖች በመስጠትና በመሸጥ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ጦርነት በማቀጣጠል እንድትወገዝ ማድረግ ያሻል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቃውሞውን ማሰማት ይጠበቅበታል እንላለን፡፡
እስክንድር ነጋ ዳግማዊው ጥቁር ሰው በአማራ ለመሠረታዊ ለውጥ፣ ጠቅላይ ጦር ሠፈሩን አውድም (Bombard the Headquarter) የወያኔን የኦህዴድና ብአዴን ካድሬዎች ለፍርድ እናቅርብ!!! የሻለቃ መሣፍንት ልጅ መሆንን በሰማን ጊዜ ልባችን ክፉኛ አዘነ፣ እኛ ተቀምጠን የአስራሰባት አመት ልጅ ስለእኛ መሞቱ በምን እዳው አስባለን፤ መልካም አገር አላወረስናችሁም እና አዘንን፣ በጀግንነትህ በኮነሬል አብይ መቃብር ላይ ከአዲስ አበባ የአንተን ኃውልት የፋኖ አርበኛ እሸቴ ሞገስና የልጅ የታገሱ እሸቴ ኃውልት እናቆማለን፡፡ በኮነሬል አብይ ፋሽታዊ አገዛዝ በማያባራ ጦርነት ልጃቻቸውን የተነጠቁ የትግራ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ ወዘተ እናቶች የልጆቻችሁን ኃውልት በኮነሬል አብይ መቃብር ላይ እናቆማለን፡፡ የልጆቻችሁ ታሪክ በወርቅ ቀለም ይፃፋል፡፡ ትላንት የፋሽስቱ ኮነሬል መንግሥቱ የቀይ ሽብር ሠማእታት የጋራ ኃውልት ቆሞልና፡፡ ቃል ለምድር ለሠማይ!!! ይህ ጊዜም ያልፋልና!!!
የእስክንድር ትንቢተ-ራዕይ ከሩቅ ይሰማል!!! የአማራን ጀኖሳይድ እናስቁም፣ የቤት ፈረሳን እናስቁም!!! ህዝባዊ መንግስት እንመሠርታለን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ እናብስ!!! ለሥልጣን አንጣላ፣ ሥልጣን በህዝብ ምርጫ የሚመጣ ታላቅ ኃላፊነት ነው፡፡ የደም ነጋዴዎች ሴራን እንበጣጥስ!!! ስልጣን ከእውቀት ጋር ለአዲሱ የዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመን ወጣት ፖለቲከኞች የሃገራችንን ችግሮች በጠረጴዛ ዙሪያ ብቻ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ብቃት ያላችሁ አዲስ ትውልድ ስልጣኑን መጨበጥ ታሪክ የጣለባችሁ አደራ ነው፡፡ አንባገነኑ የኮነሬል አብይ መንግሥት በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች ከ111(መቶ አስራአንደ) ሽህ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አስታውቆል፡፡ ግማሽ ሚሊዮኝ ህዝብ ተፈናቅሎል፡፡ ገና የኮነሬል አብይ ቤተመንግሥትና የሽመልስ አብዲሳ ቤተመንግሥት ሲገነባ የሚሊዮኖች ቤት ፈርሶ ተፈናቃዬች ቁጥር የትየለሌ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከፋኖ አርበኛ ጋር ዛሬውኑ ቆርጠ ለትግል በመነሳት የኮነሬል አብይ መንግሥት ግፍ ማስቆም ታሪካዊ አደራ አለብን፡፡ የፖለቲካ እስረኞችን ጋዜጠኞችን፣ ምሁራኖች የእስር ቤቶቸ በር ሠብረን ማስፈታት ታሪካዊ ስራ አለብን!!! የእስክንድር ግፍ ብዙ አለብን ….ብዙ አለብን…. እስክንድርን ከነ ድክመቱ እንውደደው፣ እናርመው፣ እንደግፈው፣ የኃላው ከሌለ፣ የፊቱም የለምና!!! እንበል አሥራሁለት!!!
የኮነሬል አብይ ኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት ከአማራ ክልል ይውጣ!!! ከትግራይ ክልል እንደወጣ ሁሉ!!!
ምንጭ
House demolition in Ethiopia (2019–present)
(2)Abu Dhabi Based Eagle Hills Invests in Ethiopia/By D&B Bureau/ November 21, 2018
https://amharic.zehabesha.com/archives/189355
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment