Sunday, February 18, 2024

   ‹‹የቆላ አጋዘን የገደለ መቶ ከብት ወይም ተመጣጣኝ ካሣ እንዲከፍል አባ ገዳዎች ወሰኑ፡፡››    
ኢት-ኢኮኖሚ            /ET- ECONOMY

  ‹‹የወባ ትንኝ ለመግደል መድፍ አይተኳስም!!!›› Do not use a cannon to kill a mosquito.

ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

‹‹ወጡ ሳይወጠወጥ

ወስከንባው ላይ ቁጢጥ!!!››

‹‹ በዚያም ወራት በግንቦት አስር ቀነ በ1901 ዓመተ ምህረት ዳግማዊ ምኒልክ ሰፊ በሆነችው አደባባይ በጃንሜዳ ጉባዔ አደረገ፡፡ አዛውንቱን፣ መኳንንቱን፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ሁሉ ሰበሰበ፡፡ እንዲህም አላቸው፡- በአፄ ቴዎድሮስ ሞት ጊዜ የተደረገውን ልንገራችሁ ስሙኝ፡፡ አንዱ ሁለተኛውን እየገፋው፣ ሁለተኛው ሦስተኛውን እየገፋው ሠራዊቱ ሁሉ አለቁ፡፡ ከእነርሱም አንድ አልቀረ፡፡ በአፄ ዮሐንስ ሞት ጊዜም በየሀገሩ የሆነውን  አይታችኃል፤ ይልቁንም በትግሬ ምድር፡፡ በሀገራቸው ህመም /በሽታ/ ሳይገባ፣ጠላትም ሳይመጣባቸው ሁሉም እርስ በእርሳቸው አለቁ፡፡ ይህ ሁሉ እንዳይሆንባቸው ሁላችሁም በፍፁም ልባችሁ ተዋደዱ፡፡ ፍቅር ሁሉንም በደሎች ይደመስሳልና፡፡ አነዱ የሌላውን ሹመት አይመኝም፡፡ ለእርሱ በተሰጠው ይፀናል እንጂ፡፡ እርስ በእርሳችሁም አትቀናኑ፣ ቅንዓት የብዙዎችን ልብ በቁጣ ትበላዋለችና፡፡ በቅናትም የእግዚአብሔር ፀጋ አይገኝም፡፡ ልጄን አደራ ሰጥቻችኃለሁ፣ ፈቃዳችሁን ቢያደርግ ከእርሱ ጋር ኑሩ፡፡ ፈቃዳችሁን ባያደርግ፣ ምክራችሁን ባይሰማ ግን ወደ ውጭ አውጡት፤ እኔ ንቄዋለሁ፣ እንደ ጉድፍ ጥራጊም ጥየዋለሁና፡፡››…………………………….……………….(1)

‹‹የቆላ አጋዘን የገደለ መቶ ከብት ወይም ተመጣጣኝ ካሣ እንዲከፍል አባ ገዳዎች ወሰኑ፡፡›› አዲስ አበባ ግንቦት 16 ቀን 2013 ኤፍ ቢሲ (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን) አማራ በማንነቱ የተነሳ፣ በእምነቱ የተነሳ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” እና ‹መጤ/ ሠፋሪ› በሚል የጥላቻ ትርክት ተገድለዋል፣ ታርደዋል፣ ተቃጥለዋል፡፡ ይህ ግፍ ዛሬም አልቆመም፡፡ የኦሮሞ አባገዳዎች አማራ እንዳይገደል በይፋ ያሉት ነገር የለም፡፡ የኦሮሞ አባገዳ አጋዘን እንዳይገደል ሲሞገት፣ ለምን በኦሮሞ ምድር አማራ እንዳይገደል አልተማፀነም? ለምን  የኦሮሞ ድርጅቶች ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች አላወገዙም? ለምን  የክልል መንግሥቶች ይህን ገደላ አላወገዙም?   ዛሬም የአማራ ልጆች መገንዘብ የሚገባቸው በዚህ የአማራ የህልውና ትግል  አማራ ከእንሰሳ ያነሰ ዋጋ እንደተሰጠው በመረዳት ትግላችንን ምንም ሳንከፋፈል በህብረት በወንድማማችነት ከመቀጠል ሌላ ለክፍፍል ቦታ መስጠት አይገባን እንላለን፡፡  የአማራን ህዝብ ከኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የሰው አልባ ድሮውን ጥቃት ሳናስጥለው፣ በመራዊ በግፍ ተረሽነው በየመንገዱ ለተጣሉት የአማራዎች ደም ሳይደርቅ፣ የአማራ ገድለው በጅምላ መቃብር በግሬደር ለተቀበሩት ረስተን፣ የተቃጠሉትን የታረዱትን አማራዎችቤቱ ይቁጠራቸው ብለን፣ የሴቶችን መደፈር ሳናስቆም፣ የአማራ ፋኖ ለበትረ ሥልጣን ሳይደርስ ለሥልጣን ተጣላ ቢባል አባቶች ምንኛ ያዝናሉ! ‹‹ወጡ ሳይወጠወጥ፣ ወስከንባው ላይ ቁጢጥ ›› ከማለት በስተቀር፣ ለቅሶችን ከመቼው ተረሳ! ሐዘናችን ከመቼው ተረሳና! እግዚአብሔር ልብ ይስጠን!!!

 

የኮነሬል አብይ አህመድ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት መር ሽብርተኛነት በአማራ ህዝብ ላይ

‹‹በሀገራችን ውስጥ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ግምባር ቀደም ተጠቂ ይሁኑ እንጂ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” በሚል የጥላቻ ትርክት የተቀመረው ሕገ-መንግሥት ሌሎች ብሄረሰቦችንም ለጥቃት አጋልጧቸዋል። ጉራጌዎች፣ ስልጤዎች ጋሞዎች…ወዘተ ተጠቂዎች ሆነዋል። በሃይማኖትም ክርስቲያን ኦሮሞዎች የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ይገኛሉ። የፌዴሬሽኑን ሕገ-መንግሥትና የክልል ሕገ-መንግሥቶችም፣ ተቀርፀው የተዋቀሩት አንዱን ‹ኖሪ/ባለቤት› የአንደኛ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ‹መጤ/ ሠፋሪ›  በሚል የሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ማዕከልነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።  በቡራዩ፣ በአርሲ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሻሸመኜ፣ በዝዋይና በባሌ እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ የተካሄደው ጥቃት፣ ባመዛኙ የአማራና ሌሎችንም “መጤ” ተብለው የተሰየሙ ብሄረሰብ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞችንና የዕምነት ቤቶችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ነው። በኢትዮጵያ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) የዘር ማፅዳትና ኃይማኖት ፍጅት ከ1982 እስከ 2016ዓ/ም ለትውስታ ያህል እንሆ፡-

- በ1982 ዓ/ምመግቢያ ላይ፣ ህወሓት ሥልጣን ከመያዙ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ፣ በአሶሳ ከተማ ኦነግና ሻዕቢያ የተሳተፉበት ክርስቲያኖችንና አማራዎች የሚሏቸውን ለይተው ቤት ዘግተው በእሳት ማቃጠላቸው የሕዝቡ መፃዒ ዕድል ምን ሊሆን እንደሚችል አመላካች አሰቃቂ ተግባር ነበር። በሻብያ፣ ህወሓትና በኦነግ የተፈፀመ የዘር ጭፍጨፋ ነበር፡፡ ሻብያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ መለስ ዜናዊና ሌንጮ ለታ በጆኖሳይዱ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡

- በ1984/85 ዓ/ም በአርሲ ሃገረ-ስብከት አርባጉጉ አውራጃ በ680 ካህናትና ኦርቶዶክሳዊያን በአሰቃቂ አረመኔዊ ተግባር ታርደዋል፣ ተቃጥለዋል ከገደል ላይ ተወርውረዋል፡፡ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፣ ቅርሶች ተዘርፈዋል፣ አርባ ሦስት ሽህ ምዕመናን ተሰደዋል፡፡ አብዛኛዎቹ በማንነታቸው አማራዎች በመሆናቸው ነበር፡፡

- በምዕራብ ሐረርጌ ሃገረስብከት አሰቦት ገዳምና አቡነ ሣሙኤል ገዳም መነኮሳትና ምዕመናን በግፍ ታርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፡፡ አብዛኛዎቹ በማንነታቸው አማራዎች በመሆናቸው ነበር፡፡

- 1998 ዓ/ም በህዳር 8 እና 9 ቀን፣ በአርሲ ሃገረስብከት ኮፈሌ ቆሬ ከተማ አይሻ ሰበካ ስድስት ምዕመናን ተገለዋል፡፡ ከመቶ በላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ተከታዬች ቤታቸው ተቃጥሎ ተሰደዋል፡፡ የማርያም ቤተከርስቲያን ተቃጥላለች፡፡ አብዛኛዎቹ በማንነታቸው አማራዎች በመሆናቸው ነበር፡፡

- 1999 ዓ/ም ከመስከረም እስከ ጥቅምት አምስት፣  በሻሻ ዴዴሳና በሞናቶ  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ተቃጥሎል፡፡ካህናትና ምዕመናን ታርደዋል፣ የምዕመናን መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ አብዛኛዎቹ በማንነታቸው አማራዎች በመሆናቸው ነበር፡፡

- በ2011 ዓ/ም የጁዋር መሃመድ የተከብቢለሁ የ86 ሰዎች ሞት፣ ንብረት ውድመትና የሰብዓዊመብት ጥሰቶች ወንጀሎች ተፈፅመዋል፡፡ አብዛኛዎቹ በማንነታቸው አማራዎች በመሆናቸው ነበር፡፡

- በ2012 ዓ/ም ሃጫሉ ሁንዴሳ 187 ሰዎች ተገድለዋል የኦነግቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ቄሮ ድርጅታዊ የዘር ፍጅት ተዋናዬች በነፃና ገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ!!!  በዚህ የህቡዕ መፈንቅለ መንግሥት  የፖለቲካ ሴራ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት የተደገሠው የዘር ፍጅት ሁለት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሰዎች ሞት፣ ሁለት መቶ ሰዎች መቁሰል፣ ሁለት መቶ ሃምሳ መኪኖች መሰባበርና ሃያ መኪኖች መቃጠል፣ የአርባ  አምስት ፎቆች መቃጠል፣ ብዙ ሽህ ቤቶች መቃጠል፣ መሠረቱ በዘርና በኃይሞኖት የማንነት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የመንግሥት ሥራ ሲሆን በአመዛኙም የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ሠራዊቱና የፀጥታና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እንዲሁም የክልል ሹማምንቶች የኦዴፓ/ብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ሃላፊነትና ተጠያቂነት  መኖር አለበት እንላለን፡፡ ዓለም አቀፍ ትብብር በኢትዮጵያ መብት ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችንና ዲያስፖራውን አስተባብረው ለዓለም አቀፍ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት (International Criminal Court)  በገለልተኛ ተቆማት ፍርድ እንዲሰጥ ማድረግ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነበር፡፡ አብዛኛዎቹ በማንነታቸው አማራዎች በመሆናቸው ነበር፡፡

- በ2013 ዓ/ም በጥቅምት 9 ቀን እና ጥቅምት 13ቀን እንዲሁም  ጥቅምት 23 ቀን በኦሮሚያክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት እስካሁን የ54 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ይታወሳል። የክልሉ ቃል አቀባይ ጥቃቱ የተፈጸመው በስብሰባ ስም በአንድ ቦታ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ነው ብሏል። አብዛኛዎቹ በማንነታቸው አማራዎች በመሆናቸው ነበር፡፡

- ‹‹በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጉር ወረዳ ዳቢስ በሚባል ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 22 ሰዎች መገደላቸውን የዞኑ አስተዳዳሪና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለፁ።  "በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ብሔር አባላት ላይ መሆኑን" የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ደቻሳ ይህንኑ አረጋግጠዋል።…"ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው" ብለዋል፡፡ አብዛኛዎቹ በማንነታቸው አማራዎች በመሆናቸው ነበር፡፡

- ከየካቲት27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ በሆሮጉድሩ ወረዳ ውስጥ አማራዎች ላይ ማንነትን መሰረት ባደረጉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ምክንያት ከ60 በላይ ወገኖቻችን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ታርደውና ተጨፍጭፈው ተገድለዋል፤ በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለው ለችግር ተጋልጠው ይገኛሉ፡፡ ንጹሃን  ዜጎች በኦህዴድ/ብልጽግና ይሁንታ እና በኦነግ ሸኔ አድራጊነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ሆነዋል፡፡ አብዛኛዎቹ በማንነታቸው አማራዎች በመሆናቸው ነበር፡፡

የኮነሬል አብይ መንግሥት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያካሄደው የድሮውን ጥቃት ብዙ ዜጎች ተጨፍጭፈዋል በትግራይ ክልል (መቀሌ ከ23 እስከ 30 የአየር ጥቃት፣ተጎጋ ገበያ፣ አዲያቦ ከተማ፣ ደደቢት)በኦሮሚያ ክልል ወለጋ (ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ)፤ በአማራ ክልል ደሴ ጭፍራ ቤት፣ቆቦ፣ ባቲ፣ ወልዲያ፣ ስሪንቃ፣ ደላንታ ውርጌሳ፣ በረህት፣ መራቤቴ፣ ፍኖተሠላም፣ ደብረማርቆስ፣ ውኃ በር፣ ወይን ውኃ፣ ሞጣ ደጋዳሞት፣ ዓይና ቡጉና፣ ዘመሮ ወዘተ በገበያ ሥፍራ፣ በተፈናቃዬች ካንፕ ላይ፣ ወዘተ የቦንብ ጭፍጨፋ ተደርጎል፡፡ በአንድ ላይ ተነስቶ ሥርዓቱን ማስወገድ ጊዜው አሁን ነው፡፡

በ2016ዓ/ም በመራዊ  ከመቶ ኃምሳ እስከ ሁለት መቶ አማራዎች ከየቤታቸው ተወስደው በአደባባይ መንገድ ላይ በግፍ ተረሽነዋል፡፡ ዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ድርጊቱን አውግዞል፡፡ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የካናዳ፣ የሲውድን መንግስቶች ድርጊቱን በማውገዝና ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ተቆቁሞ እንዲያጣራ አሳስበዋል፡፡

የአማራ ፋኖ የድል ጎዳና የጎንደር፣ የጎጃም፣ ወሎና የሸዋ አርበኞች ገድል፤ብአዴን ከአማራ ክልል ተነቅሎል! የአማራ ፋኖ ያፈረሰውን መንግሥታዊ መዋቅር ዳግም የማዋቀር፣ ህግና ሥርዓት ማስከበር፣ ግብርና ታክስ ሰብስበው ተማሪዎችን በትምህርት ቤቶች ማስተማር፣ የጤና ተቆማት ሥራ ማስቀጠል፣ የንግድና ገበያ ስርዓቱን ማስቀጠል፣ ወዘተ የፍትህና የዳኝነት ሥርዓት መገንባት፣ ዴሞክራሲያዊ ህዘባዊ አስተዳደር እንዲገነባ መጣር  የመሳሰሉት አድካሚ ሥራዎች ከፊቱ ይጠብቀዋል፡፡

አማራ ብአዴን፡- የብልፅግና ፓርቲ የተመሠረተው በቀሪዎቹ ዋነኞቹ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ እና ደኢህዴን ፓርቲዎች  ሲሆኑ በአሁኑ ጊዜ በፋኖ የአማራ ህዝባዊ ትግል ከአማራ ክልላዊ መንግሥት መዋቅሮች ውስጥ 95 (ዘጠና አምስት) በመቶ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)  አባሎች ከክልሉ መንግሥት መዋቅር በህዝባዊው አመፅና እንቢተኛነት ተባረዋል፡፡ በዚህም መሠረት ብአዴን ተወካዬች ከፌዴሬሽን ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባልነት የህዝብ ውክልና የላቸውም፡፡ ብአዴን ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥታዊ መዋቅር ሳይወድ በግዱ ከሥልጣን መንበሩ ከአማራ ክልላዊ መንግሥት መዋቅራዊ አስተዳደሩ ተንኮታኩቶ ወድቆል፡፡

ለህዝብ ተወካዩች የፌዴራል ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫ ወንበሮች  የአማራ ክልል 138 ወንበር በብአዴን የተያዘ ነበር ፋኖ የአማራ ህዝብ በትግሉ የብአዴን ተላላኪ ምስለኔዎች ነቅሎ ጥሎል፡፡ ለክልል ምክር ቤት ካሉት 1900 መቀመጫ ወንበሮች የአማራ ክልል 294 ወንበሮች በብአዴን የተያዙ ነበሩ ፋኖ የአማራ ህዝብ በትግሉ የብአዴንን ተላላኪ ምስለኔዎች ከክልሉ መንግሥታዊ መዋቅር አባሮ፣ የአማራ ፋኖ በድል ጎዳና በጎንደር፣ በጎጃም፣ ወሎና ሸዋ አርበኞች ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት እየመሠረተ ህዝቡን በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡   የአማራ  ሠላሳ ሚሊዮን ህዝብ በላይ በፌዴራልና ከህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ውስጥ ህዝብ ያልወከላቸው አሻንጉሊት ተወካዬች ይገኛሉ፡፡ የአማራ ህዝብ የብአዴንን አንባገነን የጦር አበጋዞች መንግሥትን አስወግዶ በፋኖ አማራ ህዝባዊ ትግል ጋር ተቀናጅቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀጣይ ህልውና የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት የአማራ ፋኖ ታላቅ ኃላፊነት ከፊቱ ይጠብቀዋል እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከአማራ ፋኖ ትግልን በመደገፍ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥትን የግፍ ዘረኛ አስተዳደር ነቅሎ በመጣል የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት በተስፋ ይጠብቃል፡፡

የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ትግል አፈፃፀም ፋኖ ባንኮች አይዘርፍም፣ የህዝብ ንብረት አይወስድም፣ ሴቶች አይደፍርም፣ ስብዓዊ መብቶች አይጥስም፣ የማንነት መብትን አይጥስም፣ የእስረኞች መብትን በዓለም አቀፍ ህግ መሠረት በማክበር ያሳየው ሥነ-ሥርዓት በዓለም ተመስክሮለታል፡፡ የአማራ ብሔርተኛነት በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎና ሸዋ በህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ ተጋድሎ እያደገ ሄዶ ወደ አንድ የአማራ ፋኖ እዝ  ወታደራዊ ኃይልና አመራር  ያመራሉ ብሎ የአማራ ህዝብ ይጠብቃል፡፡ የአማራ ፋኖ ወደ አንድ እዝ ያልተካተቱ ፋኖዋች በፍቃዳቸው ወደ ውህደቱ እስኪገቡ ድረስ በትግሥት በመጠበቅ ከአንድ የአማራ ዕዝ ጋር ተናበው እንዲሠሩ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ በተመሳሳይ የአማራ ብሔርተኛነት አንድ ወጥ የፖለቲካ አመራር  የሚሠጥ የአማራ ብሔርተኛነት የፖለቲካ ፓርቲ መመሥረት ይገባል፡፡ በመቀጠልም ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ የሽግግር መንግስት መመስረትና በጋራ ሃገር አቀፍ ፍኖተ-ካርታ መቅረፅ፤ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ጉዳይ ያካተተ ማኒፌስቶ ማውጣት  ይጠበቅባቸዋል፡፡ የፋኖ አማራ ብአዴንን ከስልጣን አውርዶ ጥሎል፣ የኦሮሞ ህዝብ ኦህዴድን አሽቀንጥሮ ይጣል፣ የትግራይ ህዝብ ህወሓትን አሽቀንጠሮ ከሥልጣኑ ይጣል እንላለን፡፡ ህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ ተጋድሎ ይቀጣጠል!!! የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብረህ የኮነሬል አብይ አህመድን መንግሥት ገርስሰህ ጣል እንላለን፡፡

በአማራ ከልል የተጣለው ዳግማዊ ‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ!!!›

‹‹በመሣሪያ የመጣ፣ በመሣያ ይወጣ!!!›› ‹‹ በኃይል የመጣ፣ በኃይል ይወጣ!!!››‹‹ከአጋዘን በፊት ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለውና!!!›› የኮነሬል አብይ አህመድ ኦህዴድ ብልፅግና  መንግሥት፣ ህወሓት ኢህአዴግ፣ ‹ብልፅግና ሸኔ› ኦነግ ሸኔና ኦነግ በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (International Criminal Court) መቅረባቸው አይቀርም!!! እንደ ህወሓት የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ደኢህዴን ወንጀለኞች ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡

የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአሜሪካ፣ የእንግዚዝ፣ የካናዳ፣ በአጠቃላይ የአለም ህብረተሰብ በተደጋጋሚ በኦሮሚያ ክልል፣ በወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ክልል፣ መተከል ዞን፣ በቅርቡም በጎጃም መራዊ በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ተከታታይ የዘር ማፅዳት ወንጀል የኦነግ፣ ኦነግ ሽኔ እና ሌሎች ታጣቂ ጏይሎች ወንጀል በማስረጃ አቅርቦ ማስቀጣት የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው፡፡ የዘርና የኃይማኖት ፍጅቱንና ጥቃቱን ባለማስቆም የክልሎቹ መንግስታት እና የፌደራል መንግስቱም እኩል ተጠያቂዎች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡ የአገር ውስጥና የዲያስፖራው ትግል በዘላቂነት ከቀጠለ የኮነሬል አብይ አህመድ እድሜ እንደሚያጥር ምንም ጥርጥር የለም፡፡

የአለም ህብረተሰብ ዓይን ኢትዮጵያ ዜጎች ላይ ነው ለአንዴና ለሁሌ በነፃነት በህይወት የመኖር መብታችንን ለማስከበር ጊዜው አሁን ነው!!!! አራጆቻችንን ለዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መስጠት ታሪካዊ ሃላፊነት አለብን፡፡  ፌዴራል መንግሥት ብልፅግና ፓርቲና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መር ሽብርተኛነትን አጋልጦ መስጠት ጊዜው አሁን ነው!!! የኦነግ ሠራዊት ኦነግ ሸኔ በህዝብ ላይ ጥቃት ሲፈፅም የአማራ ፋኖ በሠላም አሰከባሪ ኃይል ሆኖ  በክልሎች የሚፈፀም ግድያን በጋራ መቅረፍ ይጠበቅበታል አጋርነቱንም በተግባር ማሳወቅ ይጠበቅበታል፡፡ የኦነግ ተረኞቹ አራጆች የሚወገዱት ጊዜው አሁን ነው!!! በተመሳሳይ ሁኔታም ትግራይ ውስጥ በንጹሐን ዜጎች ላይ ለደረሰው እና እየደረሰ ላለው አሰቃቂ ጉዳት፤ በሰሜን ዕዝ እና በማይካድራ የደረሱትን እጅግ አሰቃቂ ጥቃቶች ጨምሮ ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው፤በአንደኛ ደረጃ ህውሃት እና አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሉ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱን ከመለኮስ ጀምሮ ለደረሰው ጠቅላላ ጉዳት፣በሁለተኛ ደረጃ፣ ገዥው ፖርቲ ብልጽግና እና አመራሮቹ፤ በዋነኝነት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው፤ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደኢህዴድ ካቢኔቸው ጦርነቱ ተጠናቋል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው ሰቆቃ፣በሦስተኛ ደረጃ የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፎወርቂ፤ በወታደሮቻቸው ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤ በእነዚህ አካላት በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ለተፈጸሙት የዘር ማፅዳት ወንጀል፣ የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋዎች እና ግጭቶች፤ ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ይሁን፤ ማድረግ የሚገባቸውን ባለማድረግ ተጠያቂ የሆኑትን ሁሉ በገለልተኛ አካል በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲጣራ ማድረግ ለኢትዮጵያ ህዘብ  ጊዜው አሁን ነው!!! ይሄን ፍርድ በተግባር ማስፈፀም የሚችለው የአማራ ፋኖና አጋሮቹ ብሄር ብሔረሰቦች ከጎኑ በማድረግ ነው እንላለን፡፡ የታሪክ አደራ ነውና!!!

ምንጭ

(1) የልፁል ራስ መኮንን ዜና መዋዕል በግራ ጌታ ኃይለ ጊርጊስ ዘ-ሐረር የተሰናዳ (ከግዕዝ 1938ዓ/ም ተፃፈ ወደ አማርኛ ሰኔ 2015 ዓ/ም የተተረጎመ ) ገፅ 124 የዳግማዊ ምኒልክ የአዋጅ ቃል ለአማራ ፋኖ
https://amharic.zehabesha.com/archives/188862

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...