Monday, February 26, 2024

በዝቋላ ገዳም አራት መነኮሳት መገደላቸውንየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርቲያን አስታወቀች
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ውስጥ የሚኖሩ አራት የገዳሙ መነኮሳት በታጣቂዎች መግደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርቲያን አስታውቃለች።

ቤተክርስቲያኒቱ የህዝብ ግንጙነት መምሪያ ባወጣው መረጃ መሰረት ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ/ም ታጣቂዎቹ አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ወስደዋል። የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት እያደረገ በነበረበት ወቅትም የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ/ም የገዳሙን መጋቢ አባተክለማርያም አስራትን፣ ጨምሮ አራት መነኮሳት መገደላቸውን እና አብረው ከነበሩት ውስጥ አንድ አባት ብቻ በህይወት መትረፋቸው ተገልጿል፡፡

የቤተ ክርስቲያኗ የህዝብ ግንጙነት መምሪያ ባወጣው መረጃ መነኮሳቱ የተገደሉት መንግስት «ኦነግ ሸኔ» እያለ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን ነው። በአሁኑ ወቅትም መነኮሳቱ እና የገዳሙ ቅርሶች አደጋ ላይ በመሆናቸው የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ አካላት ጥበቃ እንዲያደርጉ ቤተክርስቲያኒቱ ጥሪ አቅርባለች። በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ የሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በርካታ መነኮሳት እንዲሁም ቅርሶች የሚገኙበት ጥንታዊያን እና ታሪካዊ ገዳም ሲሆን፤ በተለያዩ ጊዜያት ዘረፋ፣ ቃጠሎ እና ከባድ ጉዳቶችን እንደደረሰበትም ቤተ ክርስቲያኗ ያወጣችው መግለጫ ያመለክታል።

DW
https://amharic.zehabesha.com/archives/188955

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...