
በእኔ ነግስ እኔ ነግስ ውጊያ በመቀስቀስ
አንበሳና አንበሳ ተፋልመው እርስ በርስ፣
አንደኛው ድል ሆኖ የሞት ጽዋ ሲቀምስ
ሌላኛው ሲያጣጥር ግቢ ነፍስ ውጭ ነፍስ፣
የሞተን ተራምዶ የቆሰለን ገድሎ ጅቦ ሆነ ንጉስ፡፡
አማራና ትግሬ በጥቅል ሐበሻ
ወያኔ ባመጣው አንድነት ማፍረሻ
ርስበርስ ተዋግተህ በጦርና ጋሻ
ስትዳከምለት በስተመጨረሻ፣
ሥጋህን በጫጭቆ የበሻሻው ውሻ
ለሃች ይቀብርሃል እሶፍ ኡመር ዋሻ፡፡
ያገርህ፣ የምነትህ፣ ያንተነትህ ዳራ
ባንድኛችሁ እንኳ እንዲኖር ሲጠራ
ሳትጋደል በፊት ከወንድምህ ጋራ
የጋራ ጠላትህ መሞቱን አጣራ፡፡
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com
https://amharic-zehabesha.com/archives/188127
No comments:
Post a Comment