Friday, December 22, 2023

ጎሽ ፋኖ! የአምስቱ ዘመን ፋኖች እነ በላይ ዘለቀም ጥምጣም ቆልለው የመጡ ተላላኪ ባንዶችን ወንፊት የፋሽሽት አሽከር እያሉ ልክ ያስገቧቸው በዚህ መንገድ ነበር!
ፋኖነት

✅ጀግንነት

✅ንቃት

✅ግብረገብነት

✅ሰብአዊነት pic.twitter.com/asTWWQyLAa

— Mizanu M. ⚖️ (@tabor97) December 22, 2023

“ማተብም እምነትም የሌላቸው ናቸው!” ሲል ሸልሏል ሚሊዮን ጊዜ መባዛት ያለበት ሞላ ሰጥ አርጌ!  Mola Setarge - emenitm yelachwu - ሞላ ሰጥአርጌ |እምነትም የላቸው- New Ethiopian Music 2023 (Official Video (youtube.com)

እምነትና ማተብ ተሌለው ጭራቅ ጋር እንዴት ሰው ለሽምግልና ይቀመጣል?

ውሻ እንኳን ማተብ የሌለውን ውሸታም ያውቃል፡፡ ተውሻም ያነሰ ሰው ታልሆነ በቀር ማተብና እምነትን ለሌለው የእርጉዝ ሆድ ለሚቀድን፣ ሕፃናት ለሚያርድ፣ ሕዝብን በመደዳ በድሮን ለሚያርድ ሳጥናኤልና ይሁዳ ተላላኪ ሆኖ ከሮማው ፋሽስት ለከፉ ጭራቆች ተላላኪ ሆኖ ተፋኖ ፊት ይቀርባልን? እነዚህን ታሪክ ሲገርፋቸው የሚኖሩ የታሪክ አተላ ሽማግሌ ተብዮዎች በሚገባ አስተናግደኻቸዋል! ጎሽ ፋኖ! የቅድመ አያቶችህን የአምስቱ ዘመን ፋኖዎች ገድል ዳግም ሰርተኻል፡፡

ይገርማል! ከእነዚህ ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታቸው ተማታውቃቸው አይናቸውን በሚጥሚጣ ከታጠቡ ከሀዲ፣ ውሽታም፣ አጪበርባሪና ቁማርተኛ ጭራቅ ገዥዎች ጋር ዛሬም እንደ ትናንቱ   “ሽምግልና” የሚሉ ከንቱ ሆድ አደሮች ማየት ያለመታከት “እግዚኦ! እግዚኦ! እግዚኦ!” የሚያሰኝ ነው፡፡

የውሸት ሽምግልና አቀንቃኝ ሆይ! ከሀዲዎችን አንጠርጥረው ተሚለዩትና ዳግም ማመን ቀርቶ ይቅርም ተማይሉት አንዳንድ የውሻ ዝርያዎች እያነስክ ነው፡፡ አንድ 260 ውሾችን ያካተተ ምርምር እንደሚያስረዳው አንዳንድ የውሻ ዝርያዎች ያታለሏቸውን ሰዎች በደንብ እንደሚያውቁ፣ ዳግም ለማመን ብቻ ሳይሆን ይቅር ለማለትም እንደሚቸገሩ አረጋግጧል፡፡ ከጽሑፉ ግርጌ ያሉት ዋቢዎችን ይመልከቱ፡፡ 

የትግሬ ነፃ አውጪ፣ ይህ አድግ፣ ብአዴን፣ ኦፒድኦ፣ አዴፓ፣ ኦዴፓ፣ ወነግ፣ ብልጥግና  ወዘተረፍ እያሉ በሶስትም በአስርም ስም የሚመጡ በእርኩስ መንፈስ የተለከፉ ከሀዲዎችና ከሰይጣን የከፉ ሞላጫዎች የኤፍሬም ይስሃቅ አይነቱን ይሁዳዊ ሽምግልናን የወንበር ማስጠበቂያና የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ አድርገው ሲጠቀሙበት እንደኖሩና አሁንም በዚሁ የማጭበርበር ቁማር እንደቀጠሉ አገር ያወቀውና ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ ዛሬም ስለሽምግልና በማውራት ላይ ያለነው የከዳውንና ያጭበረበረውን ሞላጫ ማመን ቀርቶ ይቀር ተማይለው ውሻ አንሰን ነው?

በታሪካዊትና መንፈሳዊት ኢትዮጵያ ሽምግልና ከእውነተኛ ችሎት እጅግ የበለጠ ርትኡ ፍርድ የመስጥትና ዘላዊ ሰላምን የማስፈን መለኮታዊ ሀይል ነበረው፡፡ የኢትዮጵያን መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶች እየጠራረገ የሰይጣንን የቅጥፈት፣ የሌብነት፣ የአውሬነትና የጭራቅነት መንፈስ ሲሰራና ሲተክል የኖረው ይሁዳው ይህ አድግ ከመጣ ጀምሮ ሽምግልና ተበዳይን ከበዳይ እግር የሚያስደፋና የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ እንደሆነ እንኳን ነፍስ ያወቀ ህጻንም የሚረዳው ነው፡፡ የወሮብሎች ሽምግልና ከርሳም ካህናትንና ሼህችንም በሆዳቸው እየገዛ የመልኮትን ማምለኪያ ስፍራዎች እንደተዳፈረ የታወቀ ነው፡፡

ይህ አድግ የተባለው የትግሬ ነፃ አውጪ እርጉም የእጅ ሥራ እነ ኤፍሬም ይስሀቅን የይሁዳዊ ሽምግልና መሪ ተዋናይ አድርጎ ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ እደተጠቀመበት ሁሉ  በአምስት ዓመታት ውስጥ ወደ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ የጨፈጨፈና ያስጨፈጨፈው ከአስራ አምስት ሚሊዮን ሕህዝብ በላይ ስደተኛ ያደረገው ከሁሉም የከፋው የጭራቅ ቡድን  ስለሽምግልና ምንም የማያውቁትን ሆደ አደር ምሁር ተብዮዎች፣ ከርሳም የቤተክርትያንና የመስጊድ ሰዎችን የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ አድርጎ መጠቀሙን እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአለፈው መማር ያቃተው ልብ የለሽም በማያባራ ይሁዳዊ ሽምግልና እየተጠለፈ ታግሎ ማስወገድ ያለበትን መከራ እያራዘመው ነው፡፡

እምነት ቀርቶ የአውሬ ያህል እንኳ የደመነፍስ ባህሪ ካልፈጠረባቸው እነዚህ አረመኔዎች በሽምግልና በኩል፣ እርቅን፣ ፍትህንና ሰላምን መጠበቅ ከሳጥናኤል በረከትን ተጭራቅ ርህራሄን እየጠበቁ ሲንዘላዘሉ እንደመኖር ነው፡፡

አማራ ሆይ! ቅዱሱን የሽምግልና ባህልህን እንደ ድክመት ቆጥረው ለስት ጊዜ ያጭበርብሩህ? ለስንት አስርተ ዓመታት በሽምግልና እያታላለሉ ዘርህን ያጥፉት? እርስትህን ይውረሱት?

ተውሻ ያነሰ ሆዳም ለፍርፋሪ የውሽት ጥምጣሙን ቦጅሮና ቆቡን ደፍቶ እንደ ቡችላ ጭራውን እያወራጨ ማተብም እምነትም ለሌላቸው ከሞሶሎኒ እጅግ ለከፉ  ጭራቆች ይላላካል፡፡ ፋኖ ለህዝቡ፣ ለአገሩ፣ ለእምነቱና ለማተቡ ይዋደቃል፡፡ ጎሽ! ፋኖ የቅድመ አያቶቹን አደራ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ጎሽ ፋኖ! የቅድመ አያቶቹን የአምስቱ ዘመን ፋኖዎች ገድል ዳግም በመፈጠም ላይ ይገኛል፡፡

ዋቢ፡- (All last accessed in December, 2023)

- Big Think, Dogs Know When People Are Lying  Dogs know when people are lying - Big Think

- Life Science, Dogs Know When Humans Are Lying to Them Dogs know when humans are lying to them | Live Science

- Psychology Today,Can Dogs Know When We Are Lying to Them? Can Dogs Tell When We're Lying to Them? | Psychology Today

 

ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/187781

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...