Saturday, December 30, 2023

አዲሳባ ገንፍል!
addis ababa zehabesha

እስከ መቼ ጥደው ያንፈቀፍቁሃል፣

ስንት ዘመን ቀቅለው ንፍርቅ ያረጉሃል፣

አዲሳባ ገንፍል እሳት በዝቶብሃል!

ተቤትህ አውጥተው መንገድ ጥለውሃል፣

የግዛትን ቀንበር በጫንቃህ ጭነዋል፣

ሲፈልጉ እንደ በግ ጎትተው ያስሩሃል፣

ሰውነትን ገፈው ግዑዝ አርገውሃል!

በራራ አዲሳባ ምንድን ይሰማሃል?

እንደ በሬ አፍነው አፍህን ዘግተዋል፣

ደንቆሮም ሊያደርጉህ ጆሮህን ደፍነዋል፣

አውረው ሊሸጡህ ዓይንህን ጋርደዋል፣

መብትህን ተገፈህ ስንት ዘመን ያልፋል?

ወገንህን ሕዝብህን በድሮን ፈጅተዋል፣

ለድሮኑ መግዣም ብር ያስገብሩሃል፣

እግርህን በእጆችህ ቁረጠው ይሉሃል፣

እንዲያው አዲሳባ ምንድን ይሻልሃል?

በቋንቋ ወረንጦ ሲነቅሱህ ኖረዋል፣

ጠርገው ሊያስወጡህም ቁማር ቆምረዋል፣

ፈተና የሚባል መጥረጊያ ሰርተዋል፣

አወይ አዲሳባ ምንድን ይበጅሃል?

ፈረስ ሲለጉሙት በኮቴው ያደማል፣

ዶሮ ለእርድ ሲጎተት በጥፍሩ ይጭራል፣

በሬ ለእርድ ሲጠለፍ በቀንዱ ይዋጋል፣

ያንተ ዝምታ ግን እግዚኦ! እግዚኦ! ያሰኛል!

ግለት ሲያሰቃየው ፈንድሻ ይንጣጣል፣

በከሰል ሲፈላ ቡና ቡልቅ ይላል፣

እሳት ሲበዛበት ሽሮ ተክ ተክ ይላል፣

አንተ ተቃጥለህም ድምጥን ዋጥ አርገሃል፡፡

በእሳት ሲፍለቀለቅ ውሀም ይፎክራል፣

ወደ ታች ነጥሮም እሳቱን ያጠፋል፣

ይበቃል! ይበቃል! አንድ በአንድ መቃጠል፣

ይበቃል! ይበቃል! በጅሎች መቀቀል፣

እሳቱን ለማጥፋት አዲሳባ ገንፍል!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

ጉድ ‼️ በሻሻው እና ጅሉ ተፈሳፈሱ ‼️🤣🤣🤣 pic.twitter.com/M7Lqon53Fb— Tordit -ቶ 🦅 (@Fano_Eagle) December 29, 2023
https://amharic-zehabesha.com/archives/187942

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...