Saturday, December 2, 2023
Abiy Ahmed's War of Terrorism to Eradicate Amhara from earth
ብዙ የጦርነት ታሪክ ካላቸው የዓለማችን ሀገሮች አንዷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ናት። ከቅድመ ልደተ ክርስቶስ ጀምሮ ከተለያዩ ተፃራሪዎቿ ጋር በርካታ ጦርነቶችን ያደረገችና በሕዝቦ ኃያልነትና ጀግንነት የምትደነቅ የመጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ የግሪክ ፈላስፎችን ምስክርነት ያገኘች ሀገር መሆኗ የታወቀ ነው። የዜጎቿ ሀገርወዳድነትና አይበገሬነት የምይጠረጠር ሀቅ ስለመሆኑ በአድዋና በማይጨው የታየው ድል ምስክር ነው። ይሁን እንጂ ይህች ለወራሪና ለድንበር ሰባሪ የውጪ ጠላት ያልንተበረከከች ሀገር በእርስ በእርስ ጦርነት ስትሰቃይ የኖረችና በመሰቃየት ላይ ያለች ሀገር መሆኗ የሚካድ አይደለም። የተፈጥሮ አደጋዎች አሉታዊ ሚና እንዳለ ሆኖ የሀገሪቱ የአስከፊ ድህነት፣ የሰላም እጦትና የስደት የሌሎችም ሀገራዊ መከራዎች ዋና መንሥኤዎች ለሥልጣንና ለጥቅም ወይም ለተንሻፈፈ ፖለቲካዊ አጀንዳ መሳካት ሲሉ በክፉ አሳብ የተመረዙ ፖለቲከኞችና ባለሥልጣኖች የሚያመጡት የእርስ በርስ ጦርነት ነው። በተለይም ደግሞ ከአምስት ዓመታት ወዲህ መሉውን ሀገር ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ሀገሪቱን ወደ ከፋ ጦርነት ውስጥ ያስገባትና በመከራ ላይ መከራ እየጨመረባት ያለው ኢፍትሐዊ የሆነው በሕዝብ ላይ ያነጣጠረው ጦርነትና ፍጅት ነው።
የዚህ ጦርነትና እልቂት ጠንሳሽም ሆነ እየደረሰ ላለው እልቂት ተጠያቂ ሊሆን የሚችለው የዜጎችን ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶና ሠርቶ መኖርን የሕልም እንጀራ ያደረገ ጦርነት በ ለየን የሚቆጠሩ ንጹሐን ዜጎችን ለከፋ ድርቅና ረሀብ ያጋለጠ ፣ መቶ ሺህዎችን ቤት አልባ ያደረገ፣ ሰዎችን በዘራቸው፣ በሚናገሩት ቋንቋና በሚከተሉት ሃይማኖት ምክንያት አስከፊ ጥቃት እንዲደርስባቸው የሚያደርግና በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙትን ከሰማኒያ በላይ ብሔሮች ደፍጥጦ ከአንድ ብሔር ለተውጣጡ ኤሊቶች ክብርና ጥቅም ብቻ የቆመው ጨካኝ ፖሊሲ የሚከተለው የመንግሥትን ሥልጣን የያዘው ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የብልጽግና ፓርቲ ነው።
ይህን ፓርቲ የሚዘውሩት ፖለቲከኞች ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ነው ሀገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ በፊታ ያሳለፈቻቸውን የመከራ ጊዜዎች የሚያስረሱ አረመኔያዊ ተግባሮች የተፈጸሙት፤ አሁንም በመፈጸም ላይ ያሉት። ሰው ያለፍርድ በአደባባይ ተዘቅዝቆ ሲሰቀል በእሳት ሲቃጠል ወደ ገደል ሲወረወርና እንደ ከብት በስለት ሲታረድ ያየንበት ከአስከፊ ጊዜዎች ሁሉ የከፋ የሆነ ጊዜ የገጠመን አሁን ነው። ይህን ሁሉ በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸም ዘግናኝ በመንግሥት የታገዘ ጥቃትና የዘር ፍጅት የታወጀበት ዜጋ ቢያንስ ተፈጥሯዊ በሕይወት የመኖሩን መብት እንኳ ለማስከበር በማንነቱ ብቻ በአራጆችና በጨፍጫፊዎች የሚያስፈጀውን የመንግሥት ሥልጣን የያዘ ፀረ ሕዝብ አካል በማንኛውም ዓይነት አማራጭ ከሥልጣን ለማስወገድ ከመጋደል በቀር ሌላ አማራጭ የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም። መንግሥት ባለበት ሀገር፣ ሕገ መንግሥትን በኃይል ለመናድ መሞከር ኢዲሞክራሲያዊ አካሄድ ነው እያሉ ሕዝብን የሚያዘናጉ ፖለቲከኞችና ለዛቢስ መካሪዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንግሥት ተብዬው ከሚፈጽመው ሕዝብን የመፍጀትና ሀገርን ሕዝብ አልባ የማድረግ አረመኔያዊ ተግባር ተባባሪዎች ከመሆንና አብሮ ከመጠየቅ ሊያመልጡ እንደማይችሉ ሊያስተውሉ ይገባል። እውነት ሀገር ወዳዶች ነን ካሉና የዲሞክራሲ ፅንሰ አሳብ ገብቷቸው ከሆነ ያለአንዳች ምክንያት ሰፊውን ሕዝብ ለዚያውም የመንግሥት ሥልጣን ተቀናቃኝ ያልሆነውና ኑሮውን ለማሸነፍ አርሶ ቆፍሮ የሚኖረውን ገበሬ በድሮን እያደነ ሲፈጅ ዜጎችን በቦንብና በፈንጅ መፍጀት አትችልም፣ ሕዝብን ማጥፋት ሀገርን ማጥፋት ነው ብለው ለመምከርም ይሁን ለመሞገት ሲጥሩ መታየት በተገባቸው ነበር።
ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሀገሩ ጥንታዊ ሥልጣኔዋና በስነ ጽሑፍ ሀብቶቿ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ድንቅ ቅርሶቿ በዓለም መድረክ በመኩራት ፈንታ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለማለት የሚሳቀቅና የሚሸማቀቅበት የውርደት ጊዜ ያጋጠመው አሁን ነው። ወገን እስከ መቼ ድረስ ነው በውሸታም ዲስኩር ተታለህ መቼም በሰላምና በነፃነት እንድትኖር እድል የማይሰጥህን ሀገር አፍራሽና ፀረ ሕዝብ የሆነ መንግሥት አምነህ በማይጨበጥ ተስፋ የምትኖረው? ቤትህን ዘግተህ ብትቀመጥም ቤትህ ድረስ እያንኳኳ መጥቶ የሚገድልህ ገዳይ ፀረ ሕዝብ ጦር ወይም ልጅህን አግቶ በገንዘብ የሚደራደር አፋኝ ልኮ በሞትና በሕይወት መካከል የሚቀረቅርህ የህልውናህ ፀር እንጂ መንግሥት ያለህ መስሎህ የምትዘናጋበት ጊዜ ላይ አይደለህም። ቤተ ክርስቲያንህን ወይም መስኪድህን በተጠና ስልት አቃጥሎ ሲያበቃ እነ እገሌ አቃጠሉት ብሎ አስቀድሞ በመጮህ በአማኞች መካከል ፀብና አምባጓሮ የሚያስነሣና የሚያጋድል መንግሥት ለመሆኑ በየትኛው ሀገር በየትኛው ዘመን ነው ያየኸው? ወገን ስማ ልንገርህ ከብልጽግና በቀር ይህን አረመኔያዊ የፖለቲካ ቆሻሻ ጨዋታ በሕዝብና በሀገር ላይ የሚጫወት ክፉ የሕዝብ ጠላት የለም።
የድሆችንና የተጎጂዎችን የእህል ርዳታ የሚዘርፍና ሕዝብን በረሀብ የሚቀጣ ጨካኝ ከብልጽግና በቀር ሌላ ይኖር ይሆን? በሕፃናት ላይ ቦንብ የሚያዘንብ የርኅራኄ እንጥፍጣፊ የሌለው የጨካኞች ስብስብ ማለት ብልጽግና መሆኑን በየቀኑ የሚፈጽመው አረመኔያዊ ተግባሩ ማስረጃ ነው። ይህን ሁሉ ሕዝብ ከጨረሰና ካስጨረሰ በኋላ እንኳን ኧረ ይሄ ነገር ወዴት
እየወሰደን ነው? እስኪ ቆም ብለን እናስብ፣ የሚል የሌለበት እኛ በሥልጣናችን ላይ ከሌለን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይጥፉ የሚሉ የፀረ ኢትዮጵያ ስብሰብ ነው። ሀገርህን የምትወድ ሁሉ ይህን ሀገር አልባ ሊያደርግህ የተነሣውን የጥፋት መልእክተኛ ለማስወገድ ከተነሡና መሥዋዕተነት እየከፈሉልህ ካሉ የሕዝብ ልጆች ጋር ሆነህ ጠላትህን ልትዋጋውና ልታስወግደው ይገባሀል። ወደድንም ጠላንም ህልውናችንን ልናስቀጥል የምንችለው ዛሬ በምንከፍለው መሥዋዕትነት ነው። ሀገራችን እኛ ጋር የደረሰችው አባቶቻችን በከፈሉላት የደም መሥዋዕትነት ነው፤ ከእኛ አልፋ ዘመን ልትሻገርና ለትውልድ ልትተርፍ የምትችለውም መክፈል የሚገባንን መሥዋዕትነት ስንከፍል ነው። ስለሆነም ለነፃነታችንና ለተገፋው ምስኪን ሕዝብ ደኅነንት የሚጋደሉትን የሕዝብ ልጆች በሚያስፈልገውና በምንችለው ሁሉ ድጋፍ ልናደርግ ይገባል።
In an impassioned speech, his Holiness Abune Lukas☦️ denounces the Abiy regime's war crimes in Ethiopia's Amhara Region:💬"How can you destroy your own country with drones purchased from the country's resources & wealth? May God give you a heart". #WarOnAmhara pic.twitter.com/oDmcqFJIft
— Dej-Azmach | ደጅ-አዝማች 🦁🦅 (@TheDejazmach) December 2, 2023
https://amharic-zehabesha.com/archives/187526
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment