Tuesday, December 12, 2023
ኅዳር 29/2016 ዓ.ም በአቶ አረጋ ከበደ የሚመራ ቡድን ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ ለብልጽግና የታመኑ ናቸው ተብለው የተመለመሉ ሰዎችና የድርጅቱ አባላት በተገኙበት ስብሰባ አድርጎ ነበር። አቶ አረጋም ሆነ ሌሎች ወታደራዊ ባለስልጣናት በመድረኩ ላይ መንግስት የህዝብ ጥያቄ እንደሚሰማ፣ ለድርድር ፍላጎት እንዳለው ነገር ግን የትጥቅ ትግል የጀመረው ሃይል ለድርድር ፍላጎት እንደሌለው አስረድተው ከቤቱ አስተያየት ጠይቀው ነበር። የተሰበሰቡት የብልጽግና የውስጥ ሰዎች እንደወትሮው “አቶ አረጋ ሆይ ትክክል ብለዋል፣ ከመንግስታችን ጋር አብረን ቆመን ልማታችንን እናስቀጥላለን፣ አይዞን.....” የሚል ዲስኩር አልነበረም። ይልቁን እነ አቶ አርጋን ያስደነገጠ ጥያቄና አስተያየት መዥጎድጎድ ነበር የጀመረው። ደፋር ሴቶች እየተነሱ መንግስት ማዳመጥ አይችልም፣ መምራት አልቻለም፣ አብይ አህመድ አልቻለበትም፣ ሀገራችንን አስፈሪ ሁኔታ ላይ ወድቃለች፣ ብልጽግና ቅቡልነት የሌለው ፓርቲ ነው......... ወዘተ . የሚሉ ጥያቄዎች ሲጎርፉ የነ አረጋ ከበደ ፊት ተለዋውጦ ፍርሃት ነግሶ ነው የዋለው። አቶ አረጋን ያስደነገጠው ይህ አመለካከት በአካባቢው ባሉ እጅግ ታማኝ በተባሉ የብልጽግና ሰዎች ህሊና ውስጥ ነግሶ መገኘቱ ነበር። በስብሰባው ላይ የወታደሩ አዛዦች የነበሩ ሲሆን በስብሰባው ድባብ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቀው ታይተዋል።
አንድ አስተያየት ሰጪ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጃችኋል ነገር ግን አታሸነፉትም ብለው በድፍረት ተናግረዋል። አንዲት ብርቱ ሴት ደግሞ ለመሆኑ የአማራ ህዝብ ጥቁር ክላሽ ታጥቋል እያላችሁ የምታወሩት ለመሆኑ ይሄ ለአማራ ያንሰዋል ወይ? አማራ ይህንን መታጠቅ አያንሰውም...... ስትል የአማራን ትግል በነ አረጋ ፊት ፍርጥ አድርጋ ተናግራለች ። ተሳታፊዎች ሁሉ መንግስት በተለይም አብይ አህመድ ከፍተኛ የእውቀት ችግር እንዳለበትና መምራት እንዳልቻለ ያረጋገጡ ሲሆን ባለስልጣናቱን በአንድም በሌላም መንገድ አስፈራርተው አሰናብተዋቸዋል። አረጋ ከበደ እና አብረውት የነበሩት ባለ ስልጣናት ሁሉ እንዴት የራሳችን የምንለው የብልጽግና አባል እንዲህ ይከዳናል በማለት ከፍተኛ ብስጭት ገብቷቸው ነው የዋሉት። የስብሰባውን ውሎ የተከታተሉ ወገኖች ይህ ስብሰባ የሚያሳየው የብልጽግና መዋቅር በሰሜን ሸዋ ዞን ሙሉ በሙሉ መፍረሱን ነው ብለው ደምድመዋል።
ክብር ለኢትዮጵያ!
በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት አንዱ ያቀበሉን መረጃ
https://amharic-zehabesha.com/archives/187602
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment