Tuesday, December 5, 2023
ውዷ አገራችን ኢትዮጵያ አሁን የምትገኘው በታሪኳ አይታው በማታውቀው መከራ ውስጥ ነው፡፤ ከጣልያንና ከግራኝ አሀመድ ወረራ ወቅትም የባሰ መከራ፡፡ ብዙ ሚሊዮን ህዝብ እየተራበ ነው፡፤ ሌላ ብዙ ሚሊዮን ህዝብ በስዴት ላይ ነው፡፤ ሌላ በጣም ብዙ ሚሊዮን ህዝብ በገዥው መደብ ሆን ተብሎ በተደገሰ ጦርነት አልቋል፡፡ አሁንም እያለቀ ነው፡፡ በየቀኑ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ከፈጣሪ አምላኩ ቀጥሎ መንግስትን “በችግሬ ጊዜ ይደርስልኛል” ብሎ ከልቡ የሚያምን ህዝብ ነው፡፡ ብዙ ሽህ አመታትም በዚህ እምነቱ ጸንቶ ኖሯል፡፡ ትክክልም ነበር፡፡ ለብዙ ሽህ አመታትም ይህ እምነቱ ትክክል ነበር፡፤ በጣም ብዙ መሪወቹ ለአገራቸውና ለህዝባቸው ሲሉ ህይወታቸውን ሰጥተዋል፡፤ ምሳሌ፦ አጼ ቴወድሮስና አጼ ዮሐንስ፡፡ ይህ አይነት እምነትና ክብር የነበረው ህዝብ በአሁኑ በተረኞቹ የኦሮሙማ መንጋወች ወቅት መንግስት ነኝ የሚለው ይህ አገዛዝ ራሱ ህዝብ አሳድጅ፣ ህዝብ አፈናቃይና ህዝብን ገዳይ ሆኗል፡፡ በዚህም ምክንያት ህዝቡ እጅግ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቋል፡፡ በቅድሚያ ኦሮሙማ ስንል የኦሮሞ የበላይነትነትን፣ ሁሉ ኬኛነትን “ሁሉም የእኛ” ነትን የሚያራምድ እሳቤን (አይዶሎጅን) እንጅ ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብን እንደልሆነ ግንዛቤ ይወሰድ፡፡
ኢትዮጵያ አሁን ያጋጠማት ችግር ተባብሶ በመቀጠሉ ለመፈራረስ አንድ ሳምንት የቀራት ትመስላለች፡፡ የአገሪቱ መከራ የጀመረው ከወያኔ ጊዜ አንስቶ ቢሆንም በወያኔ 27 አመታት ክፉ ዘመን ውስጥ የአሁኑ አይነት መከራ አልተከሰትም፡፤ በመሪነት ቦታ ላይ የተቀመጡትንም የያኔዉንና የአሁኑን ሁለቱን ግለሰቦች ማለትም መለስ ዜናዊንና አብይ አህመድን ብናነጻጽር ሁለቱ ፈጽሞ ሊወዳደሩሩ የማይችሉ ግለሰቦች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ መለስ ዜናዊ መርዛም፣ ክፉና ተንኮለኛ ቢሆንም አገሪቱን አሁን ላለችበት አይነት መከራ አላደረሳትም ነበር፡፡ የአብይ አህመድ ስብእናውም ሆነ ስራው በትንሽ ቃላት ይገለጽ ቢባል “ብቃት የለሽ፣ እውቀት የለሽ፣ የሰው ጥጃ” ነው ብሎ ማለፉ በቂ ነው፡፡ ዋሽቶ ሲቀደድ ‘’ሙቱ ፓርላማና መንጋው ኦሮሙማ’’ ሲያጨበጭቡለት ህዝቡ የወደደውና ያደነቀው የሚመስለው ጭንጋፍ ነው፡፤ መንገድ ላይ 100 ሰወች ስለአብይ አህመድ አስተያየት ቢጠየቁ 97ቱ የሚሰጡት አስተያየት ስለአብይ አህመድ ጨምላቃነትና አታላይነት በጥራቃነት፣ ገዳይነትና እርባናቢስነት ነው፡፤ ቀሪወቹ 3 ከመቶወቹ ስለአብይ አህመድ እውነቱን የማይመሰከሩት የመንጋው አባል ወይንም ንክኪ ወይንም ሆዳም አማራ በመሆናቸው ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ይህ ነው ሀቁ፡፡ ይህም ማለት በጥቅሉ መለስ ዜናዊ ከእንሰሳው ከአብይ አህመድ እጅግ በጣም ይሻላል ማለት ነው፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በህዝብ እልቂት አያሾፍም ነበር፡፤ እንደ አብይ ደነዝም አልነበረም፡፡
ትግራይ በታሪኳ እንደ አሁኑ የወያኔ ባንዳወች መፈልፈያ ከመሆኗ በፊት ጀግናውን ጀኔራል አሉላ አባነጋንና መተማ ላይ ለእናት አገራቸው አንገታቸውን የሰጡትን ታላቁን የኢትዮጵያ ንጉስ አጼ ዮሀንስን ያፈራች ነበረች፡፡
በእናቱ ኤርትራዊ የሆነው መለስ ዜናዊ ለምን መርዛም ሊሆን ቻለ ለሚለው ጥያቄ አንዳንዶች ሲመልሱ አባቱ አቶ ዜናዊ አስረስ የጣልያን ሹምባሽ ስለነበሩ መለስ ልጅ ሆኖ በሰፈር ልጆች ”የባንዳ ልጅ” ተብሎ መጠቋቆሚያ በመደረጉ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ድረስ ያለውን የዘር ፌደራሊዝምን መርዝ ተክሎ የሄደው መለስ ዜናዊ በአገሪቱ ላይ ብዙ ጉዳቶችን ያስከተለ መሆኑ አይካድም፡፡ መለስ ስራወቹ በጥንቃቄ የሚታቀዱና የአብይን ያህል ጸረ ህዝብ አልነበሩም ብሎ ደፍሮ መናገር ግን ይቻላል;፡ ለዚያም ይመስላል 27 አመት ሙሉ አገሪቱ በአንጻራዊነት ከነችግሯ ጸንታ የቆየችው፡፡ በወያኔ ጊዜኮ ማንም ኢትዮጵያዊ በአገሪቱ ውስጥ የትም ቦታ መሄድና መስራትም መኖርም በሰላም ውሎ መግባትም ችግር ሆኖ አያውቅም፡፡ አሁንስ?? ስለአሁኑ ሁኔታ ህዝቡ ብቻ ሳይሆን መላው አለም እውነታውን ስለሚያውቀው እዚህ ማብራራት አያስፈልግም፡፡ ኣሁን አገሪቱ በአጭሩ ለህዝቦቹዋ “ገሀነም” ሆናለች ብሎ መልስ መስጠቱ እውነታውን ይገልጸዋል፡፡
ምንጊዜም የትም ቦታ እውነትን መመስከርና መናገር አስፈላጊ ነው፡፡ መለስ ዜናዊ መሀይሙን፣ በጥራቃውንና እውቀትም ብስለትም የሌለውን እንጭጩን አብይ አህመድ አይነቱን “”የሰው ከብት”” አንድ ሽህ ጊዜ ጠፍጥፎ የመስራት ችሎታ ያለው ሰው ነበር፡፡ በትምህርቱም ቢሆን በመላዋ ኢትዮጵያ ውስጥ በዉጤታቸው እየተመዘኑ ጎበዞች ተማሪወች ይገቡበት የነበረው የያኔው የወንጌት ተማሪና ቀጥሎም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ፣ የአጼ ሀይለስላሴም ሽልማት ተሸላሚ ተማሪም ነበር፡፡ አብይ አህመድስ?? እንጭጩ አብይ አህመድ ዶክተር ነኝ እያለ የሚያወናብደው 7ኛ ጨን ሳይጨርስ ነው፡፡
ከብቱ አብይ የተሳካለት ነገር ቢኖር በጥራቃነቱና በምላሱ ብቻ እያታለለ ሆዳም አማራወችን ይበልጥ ሆዳም እያደረገ በህዝቡ ላይ የኦሮሙማን መንጋ አሰማርቶ የህዝቡን የየእለት ኑሮ ሰቀቀን ውስጥ መክተቱ ነው፡፡ የተሳካለት ሌላው ነገር “ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” አይነት ትራጀዲን ማጧጧፉ ነው፡፤ የተሳካለት ጦርነት መጥመቁ ነው፡፤ የተሳካለት ከ22 ቢሊዮን ዶላር በላይ የአገሪቱን የእርዳታና የብድር ንዘብ ወደ ውጭ አገራት እንዲሸሽ ማድረጉ ነው፡፡ የተሳካለት በዘር የተከፋፈለውን ህዝብ ይበልጥ አናክሶና እርሱ ከላይ ሆኖ “መጣልህ በለው” ማለት መቻሉ ነው፡፤…. ወዘተ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: ከማንነትና ከክልል አስተዳደር ጋር የሚነሱ ጥያቄዎችና በኃይል ለመፍታት መሞከር የተጀመረውን የለውጥ ሒደት ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱንም ጭምር አደጋ ላይ እንደሚጥል ተገለጸ
በዚህ ሁሉ ውስጥ አንድ በእርግጥ እየሆነ ያለ ሁነት አለ፡፡ እውነትነቱም የማያጠራጥርበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ይህም የስርአት ለውጥ ካልተደረገ በስተቀር አሁን ያለው አገዛዝ ሊቀጥል አለመቻሉ ነው፡፡ ይህ ሀቅ ነው፡፤ ሀቁ የሚያንቀውን ያንቃል፡፡
በኦሮሙማ የተሰሩት ግፎች፣ በተለይም በአማራ ላይ የተፈጸሙት አረመኔያዊ ድርጊቶች በድምሩ ተጠቃለው ሲታዩ ግፎቹ ከወያኔ ፣ከሂትለርና ከሙሶሎኒ ጋርም ሊወዳደሩ አይችሉም፡፤ እጅግ መራር፣ እጅግ ጭካኔ የተመላባቸው፣ እጅግ ሰቅጣጭና በሰው ልጅ ህሊና ሊታሰቡ የማይችሉ ግፎች ናቸው፡፡ አማራን በአማራነቱ እየለዩ በመጨፍጨፍ ሂደት ውስጥ ለማሳያ የሚሆኑ ትንሾቹን ብቻ እንጥቀስ፦ የተገደለን ሰው በኤሌክትሪክ ግንድ ላይ ማንጠልጠል፣ የአማራ ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪወችን ዱካ ማጥፋት፣ እየለዩ የአማራ ቤቶችን አፍርሶ ህጻናትን በጅብ ማስበላት፣ የገበሬ የእህል ክምሮችን ማቃጠል (ከተሞችን ወርሮ ማጥፋት (አውራ ጎዳና ከተማና አጣዬ) ከአስክሬን ጋር ሰልፊ ፎቶ መነሳት፣ አስክሬን እንዳይቀበር ከልክሎ በጅብ ማስበላት፣ እርጉዝ ሴትን አንገቷን በካራ አርዶ ሽሉን ከሆዷአውጥቶ በሟች ክንድ ላይ ማስታቀፍ፣ “”ከዛሬ በኋላ ወላሂ አማራ አልሆንም”” ትራጄዲ፣ ወዘተ ወዘተ ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡
ይህ ሁሉ በመሆኑም አማራው በቃኝ ብሎ ለህልውና ተጋድሎው በተነሳ ማግስት ኦሮሙማወች ከመሪው ጀምሮ እስከ ኤታ ማጆር ሹሙና ወደታች በሙሉ በአማራ ህዝብ ላይ ዛቱ፡፡ ደነፉ፡፡ ፋኖን በ3 ቀን፣ በ10 ቀን፣ እስክዚህ ወር መጨረሻ፣ ደምስሰን መሳሪያውን ብቻ ሳይሆን ቀበቶውንም ሱሪውንም አስወልቀን እናንበረክከዋለን እያሉ ደጋግመው ፎክረው ነበር፡፡ መቀሌን በሻሻ አድርገናታል አይነቱ መበጥረቅ መሆኑ ነው፡፡ በመላው አገሪቱ ያሉትን ክፍለጦሮችን የስለላ ሀይሎችን ፌደራል ፖሊስን ወደ አማራ ክልል አዝምተው ህዝቡን ቀጠቀጡት፡፤ ይህንን ሁሉ አድርገውም የአማራ ህዝብ ሙሉ ድጋፍ ያለውን ፋኖ ማንበርከክ ባለመቻላቸው ታንክ፣ መድፍና ድሮን አዘነቡበት፡፡ በንጹሁ የአማራ ህዝብ ላይ፣ በከተሞች ላይ፣ በሀይማኖት ቦታወች ላይ፣ በአለምአቀፍ ደረጃ በዩኒሴፍ የተመዘገቡ የአማራ ህዝብ ዉጤት የሆኑ እጅግ ድንቅና ብርቅ የታሪክ አሻራወቹ ላይ የቻሉትን የማውደም ስራ ሁሉ ሰሩ፡፡ ነገር ግን ለህልውናው ቆርጦ የሚታገለውን የአማራ ህዝብና ለህዝቡ የህልውና ተጋድሎ የጀርባ አጥንት የሆነውን ፋኖን ሱሪውን እና ቀበቶውን ብሎም ትጥቁን ማሰወለቅ ቀርቶ በየአውደ ዉጊያው ሊቋቋሙት አልቻሉም፡፡ተረፈረፉ፡፡ አሁንም ፋኖ እያንበረከካቸው ነው፡፤ እነርሱም ህዝቡን በከባድ መሳሪያ በስፋት እየፈጁት ነው፡፤ ይህ ድርጊታቸው ነው እንደገና መልሶ ህዝቡን ይበለጥ ወደአልገዛም ባይነት የህልውና ትግሉ ውስጥ እየገፋው ያለው፡፤ ይህ ነው እየሆነ ያለው ሀቅ፡፡ ይህ ነው ከህዝብ ጋር እልክ የተጋባ መንግስት አዙሪት ዉስጥ የመግባቱ ዉጤት፡፡ እንኳን ባለ ደማቅ ታሪኩን አማራን በአለም ላይ አልገዛም ያለን ህዝብ አሸንፎ የገዛ ሀይል የለም፡፤ የቬትናምንና የአፍጋኒስታንን ህዝብ ተጋድሎ ያስታውሷል፡፡
አሁን ላይ ፋኖ የአማራን ክልል 80 ከመቶ ተቆጣጥሯል፡፡ 70 ከመቶ ፋኖ ትጥቁን የታጠቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒፎርምን ለብሶና በአገር መከላከያ ሰራዊት ስም ክልሉን ከወረረው የኦሮሞ መንጋ ሰራዊትን በመማረክ ነው፡፡ የኦሮሙማ መንጋወች የራሳቸው የሆነ የታሪክና የስልጣኔ አሻራ የሌላቸው በመሆኑ በዚህም በቅናት እርር ድብን ከማለታቸው የተነሳ የስልጣኔና የታሪክ ምቀኞች ለመሆናቸው ማረጋገጫው የፋሲሊድስና የላሊበላን በአለም የተመዘገቡ የስልጣኔና የታሪክ አሻራወች ላይ በከባድ መሳሪያ ያደረሱት ውድመት ቁልጭ ያለ በቂ ማሳያ ነው፡፡
በራሱ አሁን ባለውየወያኔ ህገ መንግስት ማንም ኢትዮጵያዊ የትም መኖርእንደሚችል ህጉ ይደነግጋል፡፡፡ኦሮሚያ ብሎ ወያኔ በከለለው ክልል ውስጥ 34 ሚሊዮን ህዝብ ይኖራል፡፤ ከዚህ ውስጥ 10 ሚሊዮኑ አማራ ነው፡፡ ሌሎች ኦሮሞ ያልሆኑም ብሄር ብሄረሰቦችም ክልሉ ውስጥ አሉ፡፡ ክልሉ የኦሮሞ ህዝብ መሬትና መኖሪያ ብቻ ተደርጎ በሌሎች ላይ የሚሰራው ግፍ ወደት እየወሰደን እንደሆነ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው፡፡ አንድ እውነታን እናስታውሳችሁ፡ አብይ አህመድ ራሱ የስብሰባው መሪ፣ ራሱ ብቻውን አስመራጭ እንደገናም ራሱ ተመራጭ ሆኖ የተከናወነበትን የምርጫ ድራማ ሁሉንም ፈገግ ያስደረገና የአውሬው አብይ አህመድ ሪከርድ የበጠሰ የታላቅ የውርደት ድራማ ስለሆነ ማንም አይረሳውም፡፡ በሪከርድም ተይዟል፡፡ ይህ ነው ኦርሙማ ማለት፡፡
የኦሮሙማ የዘረኝነት አደረጃጀት በየሲቪል የየሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የመንግስት ኮሚሽን መስሪያ ቤቶች፣ የመንግስት ባንኮች፣ አየር መንገድና….ወዘተ ብቻም ሳይሆን በአገሪቱ የመከላከያ፣ የጸጥታና የፌደራል ፖሊስ አድረጃጀትም ውስጥ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መልኩ በኦሮሞወች የታጨቀ ነው፡፡ ህዝቡ ሁሉንም ዝርዝር አሳምሮ ያውቀዋል፡፡
አይነኬ የሚመስለው አብይ አህመድ የሚነካው ስላጣ እንጅ እውነተኛ ማንነቱ በተቃራኒው ነው፡፡የመጨረሻ ገለባ ሰው ነው፡፣ ፈሪ ከመሆኑም የተነሳ ጨካኝ ሰው ነው፡፡ አብይ ውስጡ ባዶ፣ ወኔው የሸና፣ እውቀቱና ችሎታው የኮረጀውን ከማስመሰል የማያልፍ፣ ብዙ በዋሸና ብዙ በተበጠረቀ ቁጥር በህዝቡ ዘንድ “ አብይ አዋቂ ነው” ተብሎ የሚወደስ የሚመስለው ከንቱና ጨካኝ ሰው ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ህወሓትን እና ክስ ተቋርጦ የተፈቱ ፖለቲከኞችን አስጠነቀቁ
አብይ ስልጣኑን ከሚያጣ ይልቅ መቶ ሽህ ሳይሆን ሚሊዮኖች ሀያም ሰላሳም ሚሊዮን ህዝብ ቢሞት ጉዳዩ አይደለም፡፡ ይህንን ያህል ደነዝ ሰው ነው፡፡ አብይ ይህንን ያህል ጨካኝ ሰው ነው፡፡ የታረዱ ሰወች አስክሬኖችን በቴሌቪዥን ቀርቦ በዘር የቆጠረልን አብይ አህመድ በኦነግ ሸኔም ይሁን በኦህዴድ ሸኔ (አብይ ከላይ ሆኖ ሁለቱንም በማስታጠቅና በማደራጀት የሚጫወተው ግልጽና ስውር ቁማር እንዳለ ሆኖ) የታረዱት አማራ በመሆናቸው ብቻ አማራወቹን ለይቶ ካሳረዳቸው በኋላ ስለታራጆቹ ንጹሀን አማራወች “”ለመቃብራቸው ጥላ ይሆን ዘንድ ዛፍ መትከል”” እያለ በይፋ ያፌዘ ሰው ነው፡፡
ጭካኔ የፈሪ እንጅ የጀግና ባህሪ አይደለም፡፤ ለምን ይመስላችኋል ታላቁን ንጉስ አጼ ምኒሊክን ህዝቡ “ እምዬ ምኒሊክ” ይላቸው የነበረው?? በብዙ ሳይንሳዊ መለኪያወችና ተቸባጭ ማሳያወች የዘመናዊት ኢትዮጵያን የመሰረቱት ታላቁ ንጉስ አጼ ምኒሊክ ጀግናም ሩህሩህም ስለነበሩ ነው፡፤ በአድዋ ጦርነት ወቅት በውሀ ጥም ተይዘው ለነበሩትና ለተማረኩት የጣሊያን ወታደሮች ሩህሩሁ ንጉሱና ንግስቲቱ እቴጌ ጣይቱ ምን እንዳደረጉላቸው ለማወቅ ታሪክን መርምሮ መረዳት ያሻል፡፡ኦሮሙማ የታላቋን የአድዋ ጦርነት የሴት አርበኛና እንደዚሁም የአዲስ አበባ ከተማን የቆረቆሩትን የእቴጌ ጣይቱን መታሰቢያ ሀውልት እንዳይቆምላቸው መከልከሉ አይዘነጋም፡፤ በተቃራኒው ግን አገሩን ኢትዮጵያን ከወራሪዋ ሶማሊያ ጎን ሆኖ የወጋውንና መጨረሻም ላይም በታላቁ አርበኛ በጀኔራል ጃጋማ ኬሎ የተማረከውን ታደሰ ብሩን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሀውልት እንዲቆምለት አድርጓል፡፡ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ኦሮሙማ ከስልጣኑ በተገረሰሰ ማግስት የከተማዋ ብቸኛ ባለቤት የሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ የባንዳውን የታደሰ ብሩን ሀውልት ነቃቅሎ በመጣል የንግስቲቷንና የከተማዋን መስራች የእቴጌ ጣይቱን ሀውልት እንደሚያቆም ጥርጣሬ ሊኖረን አይገባም፡፡ ይህ ድርጊት በኦሮሙማ ውድቀት ማግስት መደረግ አለበት፡፤
ከህዝብ ግዲያና ጭፍጨፋ እንደዚህም ኢትዮጵያን አፈራርሶ የኦሮሚያ ኢምፓየርን ክመገንባት ሂደት ጎን ለጎን አብይ አህመድ እያደረጋቸው ያሉ ሌሎች የህዝቡን ትክረት ያላገኙ የሚመስሉ ጉዳዮችን እንጠቃቅሳቸው፡፡
አብይ አህመድ እስካሁን በ5 አመታት ውስጥ ያደረጋቸው የውጭ አገር ጉዞወች መለስ ዜናዊ በ 27 አመታት ውስጥ ያደረጋቸውን የውጭ አገር ጉዞወችን በብዙ እጥፍ ይበልጣሉ፡፡ እንሰሳውና በጥራቃው አብይ ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ አራት አገሮች ውስጥ ሚስቱን አስከትሎ በዚህ ድሀ ህዝብ ገንዘብ ተንሸርሽሮበታል፡፡ይታያችሁ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ አራት አገራት ከተጓዘ በአመት ለውጭ አገር ጉዞ ምን ያህል የአገሪቱ ገንዘብ እንደሚወጣ፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፤ በጦርነት የሚያልቀውስ ህዝብ ብዛት፡፤ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ አብይ ማለት ህዝብ እየተራበ፣ ህዝብ እያለቀ፣ ህዝብ በችግር አለንጋ እየተገረፈ በብዙ ቢሊዮኖች ዶላሮች የራሱ ቤተመንግስት ሊገነባ የተነሳ ከንቱና ግብዝ ሰው ነው፡፡ ነገሩ ፋኖ እየቀደመው ነው እንጅ እርሱማ እናቱ በነገሩት መሰረት በሚገነባው ቤተመንግስት ውስጥ ንጉስ ሆኖ ሊኖር አስቦ ነበር፡፡
አሁን ላይ በፋኖ አይበገሬነት ተስፋ የቆረጠውና በውጭ ምንዛሬ እጥረት ለጦርነቱ መሳሪያ መግዣ እየዋተተ ያለው አብይ አህመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤትን፣ ለም የሆኑ የጎንደር መሬቶችን፣ የስኳር ፋብሪካወችን ….ወዘተ ለውጭ አገራት ለመሸጥና መሳሪያ ለመግዛት እንደጉድ እየተሯሯጠ ነው፡፡ ማን ያውቃል ስውየው ዝም ከተባለ ባቡሩን ድርጅትንም የህዳሴ ግድቡንም ሊሸጥ ያስብ ይሆናል፡፡
እነዚህን የመሳሰሉ የአገርና የህዝብ ንብረቶችን አውሬው አብይ አህመድ ያሻው ቀን ተነስቶ የመሸጥም የግል የማድረግም ምንም ስልጣን የለውም፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በሙቱ ፓርላማ ማጸደቁና ለህዝቡ ይፋ ማድረግ አለበት፡፡ ሙቱ ፓርላማም ቢሆን አይችልም፡፡ ለምን ቢባል አንደኛ ፓርላማው ሙት ነው፡፡ሞቷል፡፡ ሁለተኛ ጉዳዩ ወደ ህዝቡና ሌሎች ወደ ሚመለከታቸው ክፍሎች ለምሳሌ ወደ ፖለቲካ ፓርቲወችና የመሰል አደረጃጀቶች ወርዶ በዚያ የአመዛኙን ይሁንታ በይፋ ማገኘቱ መረጋገጥ መቻል አለበት፡፡
ይህ አካሄድ አብይ አህመድ አሁን በወድብ ላይም በቀይ ባህር ላይ እንደሚያቀርበው የልጆች ተረት ተረት አይደለም፡፡ አካሄዱ እንደገና አሁንም አብይ አህመድ አገራዊ ምክክር፣ ድርድር ስምምነት እያለ እንደሚያላዝነው አይነት ድራማም አይደለም፡፡ ይህ የአብይ አህመድ የአገራዊ ምክክር አካሄድ አብይ አህመድ የደረተው ድሪቶ ነው፡፡ ቀልድ ነው፡፤ ጊዜ መግዣ ነው፡፡ ማታለያ ነው፡፡ ምክንያቱም አጀንዳው ራሱ ከሁሉ አስቀድሞ የእርሱን ከስልጣን መውረድ ግድ ይላልና ነው፡፡ ቀጥሎም ከሁሉም የአገሪቱ ህዝብ የተውጣጣና የሁሉንም የሚመለከታቸውን የአገሪቱ ሀይሎች በሙሉ ይሁንታ ያገኘ መሆን ስላለበት ነው፡፡ የኮሚሽን ህግ፣ የአሰራር፣ የአደረጃጀትንና የኮሚስን አባላትን ምርጫ የሚመለከተው ትክክለኛው የህዝብ ሀይል በሙሉ ተስማምቶ ማጽደቅ ስላለበት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ድካም ነው፡፡ ለነገሩ መፍትሄው የስርአት ለውጥ እንደሆነ ከአብይ አህመድና መንጋው ኦሮሙማ በስተቀር ሁሉም ስለሚስማማ ወደዚሁ መፍትሄ የግድ መኬድ አለበት፡፡
በሌላ በኩል ድግሞ አብይ ጦርነቱ ሆን ተብሎ የተራዘመ ጦርነት እንዲሆን ማድረግ፣ የአማራን ህዝብ ማስራብ፣ በተለያዩ መንገዶች ህክምና፣ ትምህርት፣ ንግድ፣ እርሻ፣ ትራንስፖርት፣ ግንኙነቶች፣ የምርትና ሸቀጥ ስርጭት እንዳይከናወን ማድረግ፣ ገበሬውን መጨፍጨፍ፣ አንድ የሆነውን የአማራን ህዝብ በአካባቢ ማለትም የወሎ፣ የጎጃም የጎንደርና የሸዋ ህዝብ ብሎ ለመከፋፈል መሞከር፣ በሀይማኖት ለመከፋፈል መጣር፣ የሀይማኖት መሪወችንና ሽማግሌወችን በገንዘብና በመናኛ ስልጣን እየማለሉ ለስለላ ማሰማራት፣ ፋኖ መሳይ ሀይልን በማደራጀትና በማህበረሰቡ ላይ ዝርፊያ በማስፈጸም ህዝቡ ፋኖ ዘረፈኝ እንዲል ማድረግ፣ ካድሬ ሰብስቦ የህዝብ ስብሰባ ነው ለማሰኘት መሞከር የመሳሰሉትን ዘደወቹን ሁሉ በመጠቀም ያዋጡኛል ያላቸው እንቅስቃሴወች እያደረገ ነው፡፡ በዚህ ጥርቱም ፋኖን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማንበርከከ እየተዘጋጀ ነው፡፤ ጀግናው የአማራ ልጅ ፋኖ ሁሉንም ሙከራወቹን አስቀድሞ በማወቅ እያመከነበት ነው፡፡ ለሁሉም እቅዶቹ እንደየአግባቡ ከህዝቡ ጋር ሆኖ አመርቂ ዝግጅቶችን እያደረገ ለኦሮሙማ መንጋ ተገቢውን መልስ እየሰጠው ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: መንግስት በዐማራ ፋኖ ላይ የሚያደረገውን ዘመቻና ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን!
እነዚህ በሙሉ በተጠቀሰው መልኩ እየሆኑ ያሉ ሁነቶች ናቸው፡፡ ስለሆነም በሰፊው ኦሮሙማ መንጋጋና ጥርስ ውስጥ የገባው የአዲስ አበባ ህዝብ መላው የኢትዮጵያ ህዝብና በተለይም በኦሮሙማ ለመስልቀጥ ዳርዳር የሚባልባቸውና ጥርስ ተነክሶባቸው እየተሰቃዩና እየተጎነተሉ ያሉ እንደ ጋምቤላ፣ ሶማሊያ፣ አፋር፣ ጉራጌና፣ ሌሎች ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የኦሮሚያ ክልል አጎራባች የሆኑ ብሄር ብሄረሰቦች የነገ “ተሰልቃጭ”ተረኞች እነርሱ ስለሆኑ ከፋኖ ጎን እንዲቆሙ ሁኔታው ግድ ይላቸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ የሆነው የኦሮሙማ እብሪት ሊፈነዳ ጫፍ ደርሷል፡፡ የሚቀረው ክብሪት መጫር ብቻ ነው፡፡ ክብሪቱን መቼና እንዴት ይጫር የሚለው ላይ ነው በጥንቃቄ እየተሰራ ያለው፡፡ ከዚያስ ቀጥሎ እንዴት በሚለው ላይ ነው ትኩረቱ፡፡ የኦሮሙማው ጭንጋፍ መሪ አብይ አህመድ ዶላር አሽሽቶና ጓዙን ሸክፎ የመጨረሻው የጥፋት ሙከራ ላይ ነው አሁን ሚገኘው፡፡ያ ሚተማመንበት የኦሮሙማ መንጋና ልዩ ሀይሉ፣ ባለ ቀይ ኮከብ ለባሹና ሪፐብሊካን ጋርዱ ሁሉማ ተመናምኖበታል፡፡ በፋኖ ታጭዶ ታጭዶ ተማናምኗል፡፡ የውጭ ፖለቲካውም ተበለሻሽቷል፡፡አሁን አብይን የሚያምን የውጭ አገር የለም፡፡ የተባበሩት አረብ ኢሚሬት መንግስትጋር ብቻ ነው የሚመላለሰው፡፡ውስጡን ባናውቅም መሪወቹ “ግለሰብ ለግለሰብ” ስለተወዳጁ ይመስላል;፡፡ አረብ ኢሚሬትስ እየትንፏቀቀች በዶላሩም በድሮኑም አብይን እየደገፈችው ነው፡፡ በመሰረቱ ይህችው አገር በብዙ አገሮችና ህዝቦች ላይ ጣልቃ በመግባቷ ምክንያት ብዙ የፈርሱ አገሮች አሉ፡፤ ሊብያና የመን ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይህንኑየኢትዮጵያ ህዝብ ቀድሞ ስላወቀው ብዙ አይገርምም፡፡ የአብይ የአገር ውስጥ ፖለቲካውም ምን ደረጃ ላይ እንዳለና ሁኔታውም እንደት ተስፋ አስቆራጭ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ህዝቡ በሚገባ ያወቃል፡፡ ስለሆነም አብይ አህመድን ጠንክረው ቢገፉት ተገፍትሮ የሚወድቅበት ጫፍ ላይ ተንተልጥሎ ያለ ነው የሚመስለው፡፡
በመሰረቱ በዘር በተከፋፈለ አገር ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነቱ የሚያስከትለው ውድመትና እልቂት ከባድ እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡ ነገር ግን ይህ ተፈርቶ ኦሮሙማ ሁላችንንም በየተራ እስከሚጨርስን ድረስ መጠበቁ ሞኝነት ስለሆነ አማራ “ያበጠው ይፈንዳ” ብሎ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡ ፋኖ የቅርብ ጊዜ ስሌቱ የክልሉን ድል አድራጊነት ማረጋገጥ ነው፡፡ የሩቅ ጊዜ ስሌቱና ዝግጅቱም ለአገሩ ለኢትዮጵያ ድል አድራጊነትነው፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው ወንድም ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በጋራ ለመጓዝ ስሌቱን ጨርሶ ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
እዚህ ላይ ሁሉም ልብ ሊለው የሚገባ አንድ መሰረታዊ ሀቅ አለ፡፡ ይህም ሀቅ ለሁሉም ግልጽ መሆን አለበት፡፡ የውጮቹ የብደኤን የዲያስፖራ ፋኖወቻና እንደዚሁም በስሌት እስር ቤት ውስጥ ያሉት የብአደን ፋኖወች በተጨማሪም በብአዴን የተደራጁትና ፋኖን መስለው ህዝቡን በመዝረፍ ትክክለኛውን የፋኖ ተጋድሎ ሊበርዙና ሊያኮላሹ የሚሞክሩ ሁሉ ተነቅቶባቸዋል፡፡ ስለዚህ እረፉ ነው አዲሱ ትኩሱ የፋኖ ጥሪ፡፡ ይህ ጥሪ መሬት ነክሶ በየአውደ ወጊያው እየተዋደቀ ያለው ፋኖ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ ይህንን ማስጠንቀቂያ ያለፈን ሽማግሌ፣ የሃይማኖት አባት፣ የብአዴን ካድሬና ሚሊሽያ፣ የኦሮሙማ መንጋ፣ ፋኖ መሳይ የብአዴን እስረኛና ፋኖ መሳይ የብአዴን ዲያስፖራ በጥቅሉ የአማራን ህዝብ የነጻነት ተጋድሎ ሊያደናቅፉ የሚሹትንና የተሰለፉትን ሁሉ ይመለከታል፡፤ ከዚህ በኋላ ፋኖ እንደ እስክሁኑ ይዞና ተንከባክቦ ማቆየትና ማርኮ በምህረት አስተምሮ የሚለቅበት ጊዜ ላይ አይደለም አሁን ያለው፡፤ አሁን የእርምጃ መውስጃ ጊዜ ላይ ነው ፋኖ ያለው፡፡
ይህ ነው መራራው ሀቅና የማይቀረው ሁነት፡፡ ድል ለፋኖ!!!!
https://amharic-zehabesha.com/archives/187462
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment