Sunday, November 26, 2023

      በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሁለ-ገብ የኢኮኖሚ ዕድገት ለብሄራዊ ነፃነት መከበርና ለተሟላ ሰላም መስፈን ወሳኝ ነው!
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

ህዳር 26፣ 2023

 

በአገራችንም ሆነ በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ያለው ትልቁ ችግር ወደ ውስጥ ያተኮረ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ እንዲሁም የሚያማምሩ ከተማዎችና መንደሮች መገንባትና፣ እነዚህም በተለያዩ የመመላለሻ ዘዴዎች መያያዝ እንዳለባቸው ያለመረዳት ነው። አንድ ህዝብ በአስተማማኝ የኑሮ ሁኔታ ሲኖርና፣ የሰለጠነና በሁሉም አቅጣጫ በምሁራዊ ዕውቀት መንፈሱ የዳበረ ሰፋ ያለ የህብረተሰብ ክፍል ካለ አንድ አገርና ህዝብ በቀላሉ በውጭ ኃይሎች ሊታለሉና ህዝቦቻቸውም ከውጭ በሚመጣ የተበላሸ ባህል ሰለባ በመሆንና በገንዘብ በመታለል የአገራቸውን ህልውና በፍጹም አይሸጡም።  እንደሚታወቀው አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች በባሪያ ንግድ የተነሳና፣ በኋላ ላይም በቅኝ-ግዛት አስተዳደር ውስጥ በመውደቃቸው ወደ ውስጥ ያተኮረ በስራ-ክፍፍል ላይ የተመሰረተ ማህበረሰብ እንዳይመሰርቱ ተደርገዋል። የቅኝ ግዛት አስተዳዳሪዎች አፍሪካን እናሰለጥናለን ብለው ቢሄዱም ያደረጉት ነገር እስከዚያ ጊዜ ድረሰ የነበሩትን ዕድገቶችና የታሪክ ቅርሶች እንዳሉ ነው ያወደሙባቸው። አንዳንድ በማደግ ላይ የነበሩ ከተማዎችንና ቤተመንግስቶችን እንዳለ ነው ያፈራረሱባቸው። በተጨማሪም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የዕድገትና የስልጣኔ ምልክቶች የነበሩ የታሪክ ቅርፆችን እየነቃቀሉ ነው ወደ አዎሮፓ ዋና ዋና ከተማዎች ማጋዝ የጀመሩት። እነዚህ  ከብረታ-ብረት፣ ከዕብነ-በረድ፣ ከተለያዩ የዲንጋይ ዐይነቶችና ከእንጨት የተሰሩ የሚያማምሩ ቅርፃ ቅርፆች በአሁኑ ወቅት በየሙዚዬሞች ውስጥ በመቀመጥ በህዝብ የሚጎበኙ ናቸው። በዚህ የተነሳና የኋላ-ኋላም ከቅኝ-ግዛት ከተላቀቁና ነፃነታቸውን ተቀዳጁ ከተባሉ በኋላ በተዘዋዋሪ የቅኝ-ግዛት እንዲሆኑ ነው የተደረገው። የተለያዩ በነፃ ገበያ ስም ሳይንሳዊ ያልሆኑና ወደ ውስጥ ህዝባዊ ሀብት ሊፈጥሩ የማይችሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ብለው የሚጠሯቸውን ራሳቸው ባቋቋሟቸው የዓለም አቀፍ ተቋማት ብለው በሚጠሯቸው እያስገደዱ ነው ወደ ተግባርነት እንዲመነዘሩ ለማድረግ የበቁት። የነጩ የኢሊጋርኪ መደብ በማንአለኝበት መንፈስ በመወጠር አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች  በራሳቸው ጥረትና በምሁሮቻቸው ጥናትና ክርክር ጠንካራ ኢኮኖሚና ማህበረሰብ እንዳይገነቡ  የዕድገቱን መንገድ ለመዝጋት በቅቷል። አንዳንዶች ከዚህ ዐይነቱ የስውር ቅኝ አገዛዝ ለመላቀቅ ጥረት ሲያደርጉና አንዳንድ ዕርምጃዎች ሲወስዱ የመንግስት ግልበጣ ሊደረግባቸው ችሏል። አንዳንዶች በራሳቸው ጓዶች እንዲገደሉ ለመደረግ በቅተዋል። ይህም የሚያመለክተው በምንም ዐይነት የነጩ ኦሊጋርኪ መደብ ጥቁር አፍሪካውያን ጠንካራና የበለፀገ ማህበረሰብ እንዳይገነቡ ቀን ከሌት እንደሚሰራና፣ ካስፈለገም በተዘዋዋሪ የርስ በርስ ጦርነት በማስነሳት የኋላ-ቀርነት ዘመኑ እንዲራዘም እንደሚያደርግ ነው። ዛሬ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የሚካሄዱት የርስ በስር ጦርነቶች በመሰረቱ የውክልና ጦርነቶች ሲሆኑ፣ የሚካሄዱትም የእስላም አክራሪን ኃይል ለመዋጋትና የራስን የጂኦ ፖለቲካ ጥቅም ለማስጠበቅ በሚል ስም ነው።

 

ወደ አገራችን ስንመጣ ግን አገራችን ለጥቂት ጊዜያት ካልሆነ በስተቀር የቅኝ ግዛት ሰለባ ባትሆንም ህዝባችን ብሄራዊ ነፃነቱን ለማስከበር የሚያስችለው በሳይንስና በቴክሎጂ ላይ የተመሰረተ፣ የሚያማሩ ከተማዎችና መንደሮች፣ እንዲሁም እነዚህን የሚያያዙ ልዩ ልዩ የመገናኛ ዘዴዎች ባለመዘርጋታቸው ህዝባችንና አገራችን የመከበር ዕድል በፍጹም አላገጠማቸውም። ይህንን ዐይነቱን ጉድለት የተረዳ የተገለጸለት ምሁራዊ ኃይል ብቅ ማለት ባለመቻሉና፣ ጥቂት ተማርኩ ነኝ የሚለው የአሜሪካ ርዕዮተ-ዓለም ሰለባ በመሆንና የእሱም የጥፋት ድርጊት ተላላኪ በመሆን የአገራችን ብሄራዊ ነፃነት እንዳይከበርና፣ አልፎም በመሄድ አገራችን እንድትፈራርስ የማይሰራው ሴራ የለም። ይህ ዐይነቱ የመንፈስ ድክመትና ለውጭ ኃይል መገዛትና ብሄራዊ ነፃነትን በመሸጥ አገራችን በጠንካራ መሰረት ላይ እንዳትገነባ ማድረግ ከሁሉም ብሄረሰብ በተውጣጡ ኤሊቶች የሚሳበብ ሳይሆን ከተወሰኑ ብሄረሰቦች የተውጣጡ ኤሊቶች ዋና ተግባር ሊሆን በቅቷል። በተለይም ከአደሬ ብሄረሰብ፣ ከአማራው፣ ከትግሬና ከኦሮሞ ብሄረሰብ የተውጣጡና የመማር ዕድል ያገጠማቸው ኢሊት ነን ባዮች ንቃተ-ህሊናቸው በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ ባለፉት አርባና ሃምሳ ዓመታት በአሜሪካን የስለላ መረብ ውስጥ በመካተት የዕድገትና የብሄራዊ ነፃነት ጠንቅ በመሆን ህዝባችንና አገራችን ፍዳቸውን እያዩ እንዲኖሩና እንዲዋረዱም ለማድረግ በቅተዋል።  ያም ሆነ ይህ ይህንን ጉዳይ ዘርዘር በማድረግና በማነፃፀር  ከህብረ-ብሄር ምስረታ አኳያ የብሄራዊ ነፃነትንና  የየዜጎችን መብት መከበር ጉዳይ ጠጋ ብለን እንመልከተው።

 

እንደሚታወቀው በ18ኛውና በ19ኛው ክፍለ-ዘመንም ሆነ ከዚያ ቀደም ብሎ ህብረ-ብሄሮች እንደዛሬው ዘመን በአንድ ግዛት ውስጥ ተጠቃለውና መለያ የሚሆናቸው የየራሳቸው ባንዲራ ሳይኖራቸው በነበረበት ዘመን ኃያል ነን የሚሉ መንግስታት ደካማ አገሮችን ጦራቸውን በማዝመት ነው በቀጥታ የሚወሯቸው የነበረው። በቀድሞው ዘመን አንዳንድ አገዛዞች በውጭ ኃይሎች ግዛቴ ተደፈረ፣ ተወረርኩም በማለት ህዝባቸውን በማስተባበር የወረራቸውን ኃይል መክተው ለመመለስ የሚጠቀሙበት ዘዴ በቀጥታ ከወረራቸው ኃይል ጋር በመፋለም ነው ብሄራዊ ነፃነታቸውን የሚያስከብሩት። በዚህ መልክ በቀጥታ የተወረሩ አገሮች አገዛዞች የተገለፀላቸው ከሆነ እንደገና ላለመወረር ሲሉ ቶሎ ብለው የሚወስዱት እርምጃ የተበታተነውን ህዝብና  በአንድ ማዕከላዊ አገዛዝ አልገዛም በማለት የሚያስቸግረውን የክልል አገዛዝ በመሰብሰብና በማታለል፤ እንዲያም ሲል በማሸነፍ ወደ ውስጥ ያተኮረ ሁለ-ገብ የሆነ የአገር ግንባታና ለሰፊው ህዝብ የስራ መስክ የሚከፍት ትናንሽና የማዕከለኛ ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋም ነው አገራቸውን ዘመናዊ ለማድረግ የበቁት። ከዚህም አልፈው በመሄድ ህዝባቸውና ቀስ በቀስ እያደገ የሚመጣው የንዑስ ከበርቴው የህብረተሰብ ክፍል ብሄራዊ ስሜት እንዲያድርባቸውና አገራቸውንም በጋራ እንዲጠብቁ የሚወስዱት እርምጃ መንፈስን የሚሰበስቡና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚያስተናግዱ ከተማዎችንና መንደሮችን መገንባት ነው።  ከዚያም አልፈው በመሄድ ከተማዎችንና መንደሮችን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በማስተሳሰር የንግድ ልውውጥና እንቅስቃሴ እንዲዳብር ማድረግ ነው። በተጨማሪም እዚህና እዚያ ለመኖሪያ የሚሆኑ ቤቶችን መገንባት፣ የተለያዩ የትምህርት ዘርፎችንና የሙያ ማስልጠኛ ማዕከሎችን በማስፋፋትና፣  ክሊኒኮችንና የገበያ አዳራሾችን፣ እንዲሁም  ለሰፊው ህዝብ የመዝናኛ ማዕከሎችን በመገንባት አንድ ህዝብና ተከታታዩ ትውልድ ተከብረው የሚኖሩበት አገር ጥለው ያልፋሉ። ለሰፊው ህዝብ የሚጠቅሙና ግልጋሎትም የሚሰጡ የሰለጠኑ ተቋማት በመገንባት ማንኛውም ዜጋ ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረግ ለህዝባቸው አለኝታ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። ተከታታይ አገዛዞችም በዚህ ዐይነቱ አገርን መገንባትና የህዝብ አገልጋይ መሆን መንፈስ ተኮትኩተው ስለሚያድጉ እነሱም በበኩላቸው አገራቸውን በተሻለ መልክ በመገንባት ለተከታታዩ አገዛዝ የሚሆን በቀላሉ ሊደፈርና በተለያዩ የውስጥ ኃይሎች በቀላሉ ሊረበሽ ወይም ሊናጋ የማይችል አገርና ማህበረሰብ ጥለው ያልፋሉ።

 

በዚህ መልክ በ19ኛው ክፍለ-ዘመን በቀጥታ በውጭ ኃይሎች ይደፈሩ የነበሩ እንደጀርመን፣ ጃፓን፣ የኋላ ኋላ ደግሞ ደቡብ ኮርያና፣ ከ1949 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ቻይና  እንደገና በውጭ ኃይሎች ላለመወረር ሲሉ እንደምንም ብለው በድል አድራጊነት ከወጡ በኋላ ተግባራዊ ማድረግ የጀመሩት በሁለ-ገብ የአገር ግንባታ ላይ በመሰመራት ነው አገሮቻቸውን በጠንካራ መሰረት´ ላይ ለመግንባት የቻሉት። ለዚህ ነው ጀርመን እስከ 1871 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ የውጭ ኃይሎች በመወረሯና ወደ ውስጥ ያተኮረ የአገር ግንባታ ማካሄድ ባለመቻሏ ይህንን  ድክመት የተረዱት የፕረሽያ ሞናርኪዎችና ሁለ-ገብ ዕውቀት ያላቸው ምሁራን ዋናውን ምክንያት በመፈለግና የሚያስቸግሯቸውን ኃይሎች ድል በማድረግና ሌሎችንም በማታለል በፈረንሳይ ላይ ድልን ከተቀዳጁ በኋላ በሙሉ ኃይል ወደ ውስጥ ያተኮረ ሁለ-ገብ የአገር ግንባታ ማካሄድ የጀመሩት። በተለይም ለዕውቀት ማዕከላዊ ቦታ በመስጠትና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠቅም ሁለ-ገብ የሆነ የትምህርት የጥገና ለውጥ በማካሄድና፣ በተለይም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ ትምህርት በማስፋፋት፣ ከዚህም በላይ ለኢንጂነሪንግና ለዕደ-ጥበብ ሙያዎች ከፍተኛ አትኩሮ በመስጠት ነው ጀርመን በአንድ ትውልድ ጊዜ ውስጥ እንግሊዝንና ፈረንሳይን ቀድማ ለመሄድ የቻለችው። ተግባራዊም በሆነው ሰፋና ጠለቅ ያለ የትምህርት የጥገና ለውጥ አማካይነት ነው ጀርመን በ20ኛው ክፍለ-ዘመን ሁለት-ሶስተኛውን የሚሆን የኖቭል ዋጋ ተሸላሚ ሳይንቲስቶችን ማፍራት የቻለችው።

 

ወደ አገራችን ስንመጣ ጣሊያን ሁለት ጊዜ ከመውረሩ በፊት ኢትዮጵያችን በተለያዩ የጎረቤት አገሮች ትደፈር ነበር። በጊዜው ህዝቡን የሚያስተባብር ማዕከላዊ ግዛት ባለመኖሩና በየክልሉም ፊዩዳላዊ አገዛዝች በመኖራቸው ይህ ዐይነቱ የውስጥ ሽኩቻ ለውጭ ኃይሎች ወረራ አመቺ ነበር። ይህንን ድክመት የተረዱት አፄ ቴዎድሮስ አሻፈረኝ የሚለውን ኃይል በሙሉ በማሸነፍ ነበር የድርጅትን አስፈላጊነት በመረዳት አገራቸውን የኢንዱስትሪ አብዮት ባለቤት ለማድረግ ከእንግሊዙ ሞናርኪ ጋር ይጻጻፉ የነበረው። በአንድ በኩል የጥገና ለውጥን አሻፈረኝ የሚለው ፊዩዳላዊ ኃይልና ሌሎች፣ በሌላው ወገን ደግሞ በእንግሊዝ መንግስት ተንኮለኛነት የተነሳ አፄ ቴዎድሮስ የተመኙትን አገርን በአስተማማኝ መሰረት የመግንባት ዕድል አላገጠማቸውም። በጊዜው አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዙ ንግስት ከነበሩት ከንግስት ቪክቶሪያ ጋር ይጻጻፉ የነበረው ኢንጂነሮችን፣  የዕደ-ጥበብ ሙያተኞችን፣ የከተማ ግንባታ አዋቂዎችንና ሌሎችንም ለአገር ግንባታ ይጠቅማሉ የሚሏቸውን ሙያተኞችን እንዲልኩላቸው ነበር። ንግስት ቪክቶሪያና አገዛዛቸውም አፄ ቴዎድሮስ የጠየቁትን ሙያተኞች ከመላክ ይልቅ ሃይማኖትን የሚያስፋፉና የሚሰብኩ ቄሶችን  ነበር። በዚህ ድርጊት የተናደዱት አፄ ቴዎድሮስ የተላኩትን ቄሶችንና ሌሎችን ቀሳውስቶች በማሰር ነው ብረታ-ብረት እንዲቀጥቅጡና ልዩ ልዩ መሳሪያዎችንም እንዲሰሩ ያስገድዷቸው የነበረው።  በአፄ ቴዎድሮስ ድርጊት የተናደደችው እንግሊዝ ጦሯን በመላክ ነው አፄ ቴዎድሮስ በሰው ልጅ ከምገድል ይልቅ በማለት ራሳቸውን የገደሉት። አፄ ቴዎድሮስ ራሳቸውን ካጠፉ በኋላ አገርን በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባቱ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ  የኋላ ኋላ በአፄ ምኒልክ ትከሻ ላይ ነው ሊወድቅ የቻለው።

 

አፄ ምኒልክ እ.አ. አ በ1896 በአደዋ  በጣሊያን ላይ ድልን ከተቀዳጁ በኋላ ተግባራዊ ማድረግ የጀመሩት እርምጃ ቢያንስ ህዝባቸውን የሚያስተሳስርላቸውንና ብሄራዊ ስሜቱ እንዲያድር የሚያደረገውን አገርን የመገንባት የመጀመሪያውን እርምጃ ነው መውሰድ የጀመሩት። ትምህርት ቤቶችን መክፈት፣ ድልድዮችን ማሰራት፣ የብሄራዊ ባንክ መክፈትና ለመገበያያ የሚሆን በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው ገንዘብ አትሞ ማሰራጨት፣ የባቡር ሃዲድ ማሰራትና የፖስታ ቤት መክፈት ለህብረ-ብሄር ምስረታ የሚያመቹb  የመጀመሪያዎች  እርምጃዎች ነበሩ። ህብረ-ብሄር ለመመስረት የሚያስችሉ በየቦታው የተሰሩና የተገነቡ ከተማዎች ስላልነበሩና፣ በተለይም ወደ ደቡቡ የኢትዮጵያ ግዛት አብዛዎችም መሬቶች ጠፍ ስለነበሩና፣ በየቦታውም የተገለጸለት ወይም የተማረ ኃይል ባለመኖሩ አፄ ምኒልክም  ሀ ብለው መጀመር ነበረባቸው። ወደ ማዕከላዊ መንግስት አካባቢም ስንመጣ በሁለ-ገብ ዕውቀት የሰለጠነ ምሁራዊ ኃይል ባለመኖሩ የአፄ ምኒልክን ፍላጎትና ምኞት በመረዳት የማህበራዊ መሰረት በመሆን ምኞታቸውን ዕውን የሚያደርግ ኃይል ሊኖር ባለመቻሉ ኢትዮጵያን ዘመናዊ የማድረጉ ጉዳይ ሙሉ በሙሉ ሊሳካ አልቻለም።  ከተማዎችንና መንደሮችን በአስተማማኝ መሰረት  ላይ መገንባት አልተቻለም። የተዘረጋው የባቡር ሃዲድ ለውጭ ገበያ እንዲያመች በመሆኑ ለውስጥ ገበያ ዕድገት የሚያመቹ ልዩ ልዩ የመገናኛ ዘዴዎች ለመገንባት ባለመቻላቸውና፣ ይህንንም ተግባራዊ የሚያደርግ በኢንጂነሪንግ ሙያ የሰለጠነ የህብረተሰብ ኃይል ባለመኖሩ ለአንድ አገር ብሄራዊ ነፃነት መከበር አስፈላጊ የሆነው የአገር ውስጥ ገበያ ዕድገት አስፈላጊው አትኩሮ ሊሰጠው በፍጹም አልተቻለም። ከዚህም ጋር ተያይዞ ለብሄራዊ ገበያና ለብሄራዊ ሀብት መፈጠር በጣም አስፈላጊ የሆነው የማሺን ኢንዱስትሪ ስለማይታወቅና በዚህም የተነሳ ተግባራዊ ለመሆን ባለመቻሉ የአገራችን ህዝብ ከእጅ ወደ አፍ አልፎ ሊሄድ በማይችል የግብርናና የዕደ-ጥበብ ሙያ ነው ይተዳደር የነበረው። ይሁንና አፄ ምኒልክ ጥለው የሄዱት መሰረት ህዝባችን ብሄራዊና አገራዊ ስሜት እንዲያድርበት ለማድረግ  በቅቷል ማለት ይቻላል።

 

አፄ ምኒልክ ከሞቱ በኋላ አገርን በፀና መሰረት ላይ ለመገንባት የጃፓናዊ ዐይነት እንቅስቃሴ ቢኖርምና ቀስ በቀስም ምሁራዊ ኃይሎች ብቅ ቢሉም በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ምክንያት የተነሳ በ1920ዎች የነበረው የዘመናዊነት እንቅስቃሴ ሊዳፈን ቻለ። በጊዜው የነበረው ትንሽ ምሁራዊ ኃይል በጣሊያኑ ወራሪ ኃይል ደበዛው እንዲጠፋ ለመደረግ በቃ።  ጣሊያን ድል ከሆነና አፄ ኃይለስላሴ እንደገና ስልጣናቸውን ሲረከቡ ሁሉም ነገር በሳቸው ትከሻ ላይ የወደቀ ነበር ማለት ይቻላል። ጣሊያን ህዝባችንን እንደዚያ እየጨፈጨፈ፣ በሌላ ወገን ደግሞ ሊሰራ የሚችለውን የአገራችንን ህዝብ ከጣሊያኑ ጋር በማሰማራት በአምስት ዐመት ያህል ጊዜ ውስጥ ትላልቅ ከተማዎችን ለመገንባት ችሏል። አንዳንዶች ከተማዎችም በብዙ ሺሆች የሚቆጠርን ህዝብ ለማስተናገድ የሚችሉ የተሟላ የከተማ አገነባብና ተቋማት እንደነበራቸው የማይታበል ሃቅ ነው። ጣሊያንም አገራችንን ሲወር እዚህና እዚያ ኢንዱስትሪዎችን ተክሏል፤ መንገዶችንም ገንብቷል፤ የሬዲዮ ጣቢያም አቋቁሟል። ይሁንና እንግሊዞች አፄ ኃይለስላሴን ይዘው ከመጡ በኋላ የአገዛዙን ድክመት በመመልከት ጣሊያን የተከላቸውን ኢንዱስትሪዎችና የሬዲዮ ጣቢያዎች፣ እንዲሁም የአየር ላይ ባቡር ማስኬጃ የብረት ገመዶችን እየነቀለችና እያፈራረስች ነው ወደ ሌላ የቅኝ ግዛቶቿ ማጋዝ የጀመረችው። ይህም ማለት አፄ ኃይለስላሴ ኢትዮጵያን እንደገና ዘመናዊ ለማድረግ ሲፈልጉ ሀ ብለው መነሳት ነበራባቸው። በጊዜው የአገራችንም ዋናው ድክመት የውጭ ኃይሎችን አሻጥር የሚረዳ ሰፋ ያለ ምሁራዊና ብሄራዊ ባህርይ ያለው የከበርቴ መደብ አለመኖሩ ነው።  ከ1950ዎቹ ዐመታት መጀመሪያ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ቢስፋፉም፤ ኢንዱስትሪዎችም ቢተከሉምና፣ ሀኪም ቢቶችም ቢስፋፉና መንገዶችም ቢሰሩ፣ በተለይም የትምህርት ቤቶች መስፋፋትና የትምህርት ስርዓቱ ለመሰረታዊና ስር-ነቀል ለሆነ ሁለ-ገብ ዕድገት የሚያመቹ አልነበረም። መንፈስን የሚገልጽና ንቃተ-ህሊናን የሚያዳብር ለመሆን ባለመቻሉ በዚህ ዐይነቱ የተኮላሸ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ሊፈጠር የቻለው ትዕቢተኛ የሆነና ለብሄራዊ ነፃነቱ የማይቆረቆር ኤሊት ነኝ ባይ ነው። በተለይም የፍጆታ ምርትን ለማምረት ብቻ የተቋቋሙት ኢንዱስትሪዎች የተለያዩ ቀላል ምርቶችን ከማምረት አልፈው ለተሟላና ለሁለ-ገብ ዕድገት የሚያመቹ አልነበሩም። እንደሚታወቀው የኋላ ኋላ ወደ ውስጥ ያተኮረና ተከታታይነት ያለው ዕድገት የተጎናፀፉ አገሮች ስርዓት ያለው(Systematic Industrialization)  የኢንዱስትሪ ፖለቲካን የተከተሉት በማሽን ኢንዱስትሪ ላይ በማትኮርና፣ ይህንንም ከምርምርና ከዕድገት (Research and Development)  ጋር በማማያዝ ነው። በማሽን ኢንዱስትሪ መኖርና በማኑፋክቸሪንግ አማካይነት ነው የተለያዩ ምርቶችን፣ ማለትም የአጭርና የረጅም ዕድሜ ያላቸውን የምርት መሳሪያዎች ሊያመርቱና ለአምራች ኃይሉም ሊያቀርቡ የሚችሉት። በዚህም አማካይነት ብቻ ነው ግልጽነት ያለው የውስጥ ገበያ(Home Market) ሊያድግና ሊስፋፋ የሚችለው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ አንድ አገር በባህል፣ ማለትም በስነ-ጽሁፍ፣ በሙዚቃ፣ በስዕል፤ በሳይንሳይዊ ምርምርና በሌሎችም መጥቃ ልትሄድ የምትችለውና በማንኛውም የውጭ ኃይል ለመከበር የምትችለው ይህንን ዐይነቱን የተሟላ የዕድገት ፖሊሲ ስትከተል ብቻ ነው። ይህንን መሰረታዊ የሆነ ለተሟላና ለተስተካከለ የሁለ-ገብ ዕድገት መሰረት ሊሆን የሚችለውን የኢኮኖሚ ዕድገት ፖሊሲና ለባህላዊ ለውጥ የሚያመቸውን ሂደት የተረዳ ኃይል ሊኖር ባለመቻሉ ዛሬ የወደቅንበት የብሄራዊ ውርደትና ወደ አገር መፈራረስ አደጋ ላይ ልንደርስ በቅተናል። ዛሬም እንደትላንትናው ሁሉም በትናንሽ አስተሳሰብ በመወጠርና ልዩ ልዩ ተንኮሎችን በመፍጠር ለዕድገት የሚያመች የተሟላ ሳይንሳዊ ዕውቀት እንዳይስፋፋ የማይሸርበው ተንኮል ይህ ነው አይባልም። ለአገሩ ብሄራዊ ነፃነት ከመታገልና ለህዝቡ የሚሆን አስተማማኝ ሁኔታ ከመፍጠር ይልቅ ለነጭ የኦሊጋርኪ መደብ የበላይነት ካለደርኩ እያለ እዚህና እዚያ የሚቅበዘበዘው ኃይል ቁጥሩ ትንሽ ነው አይባልም። አብዛኛው ደግሞ በጥራዝ ነጠቅ የአካዴሚክስ ዕውቀት የተካነ በመሆኑ ከዚህ በመላቀቅ ሰፋ ያለ ምርምርና ጥናት ለማድረግ አይፈልግም። በአካዴምክስ ዕውቀት ብቻ እየኮራ አገሩ ወደ አዘቅት ውስጥ ስትወድቅ ዝም ብሎ እየተመለከተ ነው። ይህ ዐይነቱ የህብረተሰብ ኃይል በዚህች ዓለም ለምን እንደሚኖርና ተልዕኮውም ምን እንደሆነ የተረዳ ባለመሆኑ ከራሱ ጊዜያዊ ጥቅም ባሻገር ለማሰብ የሚችል አይደለም። ስለሆነ ይህ ዐይነቱ የህብረተሰብ ኃይል ለተሟላ ዕድገት እንቅፋት የሆነነ የህዝባችንን ድህነትና ኋላ-ቀርነት የሚያራዝም ነው ማለት ይቻላል።

 

ያም ሆነ ይህ በአፄው ዘመን አንዳንድ ለውጦች ቢታዩም በተለይም የሰፊውን ህዝብ ፍላጎት ለሟሟላት የሚችሉ ባለመሆናቸውና፣ ከዚህም በላይ በየቦታው የመስፋፋት ኃይላቸው ደካማ በመሆኑ የተነሳ ወደ ውስጥ ያተኮረ  ኢኮኖሚያዊ ግንባታ ማካሄድ አልተቻለም። በአፄ ኃይለስላሴ ዘመንም ህዝቡን የሚያስተሳስረው ትንናንሽና ትላልቅ መንደሮችና ከተማዎች ስርዓት ባለው መልክ ባለመገንባታቸውና፣ ከተማዎችን በአማረ መልክ የመገንባት አስፈላጊነት የተረዳ ኃይል ባለመኖሩና፣ በተለይም ሰፊው ህዝብ ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ለመጓዝ እንዲችል የባቡር ሃዲዶች ባለመዘርጋታቸው የተነሳ በበቁሎና በእግሩ የሚጓዘው የህብረተሰብ ክፍል ቁጥሩ ትንሽ አልነበረም። የእርሻ መስኩም በተለያየ ደረጃ ዘመናዊና ምርታማ እንዲሆን በጊዜው አስፈላጊው የጥገና ለውጥ ስራዎች ባለመሰራታቸው ህዝባችን በተደጋጋሚ ለሚከሰት ረሃብ ይጋለጥ ነበር። አፄውና አገዛዛቸው በጊዜው የነበረውንና የሰፈነውን ሰላምና፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነበረውን በጊዜው ለሁለ-ገብ ዕድገት የሚያመቸውን ሁኔታ ባለመረዳትና አስፈላጊውን እርምጃ ተግባራዊ ለማድረግ በላመቻላቸው ህዝባችንና አገራችን በቀላሉ ሊደፈሩበት የሚችሉበትን ሁኔታ ሳያውቁት አመቻችተው ሂደዋል ማለት ይቻላል። በአፄው ዘመን እዚያው በዚያው ኋላ-ቀርነትና የተኮላሸ የዘመናዊነት ዕርምጃዎች አንድ ላይ ይጓዙ ስለነበር፣ በተለይም የተማረው ኃይል በግልጽ የሚመራበት መመሪያ አልነበረውም። ቤተ-መጻህፍትና ሌሎች የዕውቀት ማዕከሎች በየቦታው ባለመስፋፋታቸው የተነሳ በወጣትነት ጊዜው ለጭንቅላት ዕድገትና ለፈጠራ ስራ የሚጠቅሙ ዕውቀቶችን ለመቅሰም የሚችለው ወጣት ጊዜውን ባልባሌ ቦታዎች ነበር የሚያባክነው ማለት ይቻላል።

 

ይህንን ዐይነት ያልተሟላ ዕድገትና፣ ህዝባችንን በድህነትና በተደጋጋሚ ረሃብ የሚያሰቃየውን ሁኔታ ለማሰወገድ በአብዮት ወቅት አንዳንድ የጥገና ለውጦች ቢካሄዱም በጊዜው በነበረው የርስ በርስ መሻኮት የተነሳና፣ በተለይም ስልጣንን የጨበጠው ደርግ የሚባለው ከወታደሩ የተውጣጣ ያልተገለጸለትና በምሁራዊ ዕውቀት ጭንቅላቱ ያልታነፀ የወታደር ስብስብ በጊዜው የሚታዩ ችግሮችን በፖለቲካ ዘዴ ከመፍታት ይልቅ ወደ አመፅ ነው ያመራው። ሌሎች ታጋይ ነን ይሉ የነበሩ ኃይሎችም በጊዜው የነበረውን ድክመት በመረዳት ሁኔታውን ለማርገብ ዘዴ ከመፈለግ ይልቅ በተቀጣጠለው እሳት ላይ የባሰውን ቤንዚን ማርከፍከፍ ነው የጀመሩት። ይህ ዐይነቱ በብስለትና በምሁራዊ ዕውቀት የማይመራ ፖለቲካ የሚሉት ፈሊጥ ቀስ በቀስ የደርግን አገዛዝ ´ከሰረሰረ በኋላ አገርን ለመከፋፈልና ለማዳከም ለሚችሉ በጣም አደገኛ ኃይሎች ነው ሁኔታውን አመቻችቶ ጥሎ የሄደው።  የደርግንና የተቀረውን የሚሊተሪና የስለላ ኃይል የዕውቀት ደረጃ ስንመለከት ደግሞ አብዛኛዎቹ በአሜሪካን ጭንቅላትን በሚያደነዝዝ “የሚሊተሪ ሳይንስ” ብለው በሚጠሩት የሰለጠኑ ናቸው። የቢሮክራሲውና የቴክኖክራሲውም አሰለጣጠን አገርን በተሟላ መንገድ ላይ እንዲገነባ በሚያደርግ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ባለመሆኑ በቀላሉ ለአሜሪካኖች የሚያጎበድድና አገርንም የሚሸጥ ነበር። በሌላ ወገን ግን ብሄራዊ ነፃነታቸውን ያስከበሩና ጠንካራ ኢኮኖሚን በመገንባት ህዝባቸውን ከድህነት በማላቀቅ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ የሁኑ አገሮችን የመንግስታት አወቃቀር ስንመለከት አንዳቸውም መንግስታት ውጭ ሰልጠነውና የአሜሪካንን ርዕዮተ-ዓለምን በሚያራምዱና አገራቸውን በሚያደኸዩ አጎብዳጅ ኃይሎች አልተሰገሰጉም። እንደነዚህ ዐይነት ኃይሎች ካሉም በፍጥነት ነው እርምጃ የሚወሰድባቸው። ወደ አገራችን ስንመጣ ግን ለአሜሪካን የስለላ ድርጅት መስራትና አገርን ማፈራረስ እንደትልቅ ነገር ነው የሚታየው። እንደዚህ ዐይነቱም ሰው  ነው በጣም  የሚከበረው። ይህም የሚያረጋግጠው የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ኤሊት ጭንቅላትና የአንዳንድ የታወቁ ሰዎች ተከታዮቻቸው ጭንቅላት የቱን ያህል ጨቅላ እንደሆነ ነው።

 

ህወሃት ወይም ወያኔ የሚባለው አገዛዝ በአሜሪካንና በእንግሊዝ ኢምፔሪያሊስት ኃይሎችና በሰለላ ድርጅቶቻቸው ተደግፎና ተረድቶ ስልጣንን ሲጨብጥ ሆን ብሎ የጀመረው ስራ አገርን በፍጥነት ማዳከምና ብሄራዊ ነፃነቷ እንዲደፈር ማድረግ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ የጎሳ ፌዴራሊዝም ብሎ የሚጠራውንና የሚያቆላብሰውን አገርን የሚሰነጣጥቅውንና  የህዝቡን ብሄራዊ ስሜት የሚያዳክመውን ነው ተግባራዊ ያደረገው። ከዚህም በላይ ይህ ዐይነቱ ሂደት ጠንካራ ህብረ-ብሄር እንዳይመሰረት የሚያደርግ አደገኛ አካሄድ ነው። ተፈጥሮአዊ ከሆነው የህብረ-ብሄር ምስረታ አንፃርም ስንመረምረው የኋሊት ጉዞ የሆነና የህብረ-ብሄርንና የተፈጥሮ ህግን የሚጥስ ኢ-ሳይንሳዊ አካሄድ ነው።  በመሰረቱ የጎሳ ፌዴራሊዝም  ለብሄረሰቦች ዕውነተኛ ነፃነትን ያጎናፀፈና የፈጠራ ኃይላቸው እንዲዳብር ያደረገ ሳይሆን ለራሱ ለወያኔ የከፋፍለህ ግዛው ፖሊስና በየአካባቢው የሚገኙ የጥሬ-ሀብቶችን እንዲበዘብዝ የሚያመቹ ናቸው። ህወሃት ወይም ወያኔ በዓለም ኮሙኒቲውና ተላላኪዎቻቸው በሆኑት፣ በዓለም የገንዘብ ድርጅትና(IMF) በዓለም ባንክ(World
https://amharic-zehabesha.com/archives/187409

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...