Saturday, September 16, 2023

አማራ ክልል:- ከትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ አሳሳቢነታቸው የቀጠለ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች
በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን፣ ከሕግ/ፍርድ ውጭ የሆኑ ግድያዎችን እና የዘፈቀደ እስሮችን በአፋጣኝ ማስቆም ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል የሚታየው የጸጥታ ችግር በተለይ ከነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም. ወዲህ ተስፋፍቶ ወደ ትጥቅ ግጭት ማምራቱን ተከትሎ፣ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችን በቅርበት መከታተሉን ቀጥሏል፡፡

 

People waiting in line to be treated; A health professional heard speaking to youngsters who complain to him of pain & illness; The hall is being vaccated for cleaning as there is an apparent infectious disease, but people are crowded, making the situation worse. #Ethiopia 💔 pic.twitter.com/ga0g2iY5PP

— Mulu Worku Yimer (@MuluWorku6) September 15, 2023

ግጭቱና የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች እርምጃዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ በተለይም በሲቪል ሰዎች ላይ እያደረሰ ያለውንና ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት አስመልክቶ በነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፤ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሔ ማፈላለግን ጨምሮ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰቡ የሚታወስ ነው። በተጨማሪም ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን ተጽእኖ በመከታተል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ እና የአዋጁ መርማሪ ቦርድን ጨምሮ የሚመለከታቸውን የመንግሥትና የጸጥታ አካላትን በማነጋገርና ምክረ ሐሳቦች በመስጠት በቅርበት ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል።

ኮሚሽኑ ይህን መግለጫ ይፋ እስከአደረገበት ጊዜ ድረስ ባደረገው ክትትል መሠረት፤ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች፣ ከሕግ/ፍርድ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎች እና የዘፈቀደ እስር እጅግ አሳሳቢ ሆነው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ናቸው፡፡

በተለይም በአማራ ክልል ኮሚሽኑ ከነዋሪዎች፣ ከተጎጂዎች፣ ከተጎጂ ቤተሰቦችና ከዐይን ምስክሮች ባሰባሰባቸው መረጃዎች መሠረት የትጥቅ ግጭቱ ወደ ክልሉ ልዩ ልዩ ወረዳዎች መስፋፋቱን ተረድቷል፤ በነዋሪዎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳትም ተባብሶ ቀጥሏል። ለምሳሌ ከነሐሴ 19 እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በተለይም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ፣ በሰሜን ጎጃም ዞን አዴትና መራዊ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር፣ በማእከላዊ ጎንደር ዞን ደልጊ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ፣ ሸዋ ሮቢት እና አንጾኪያ ከተሞች እና በአካባቢዎቻቸው በሚገኙ አንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች በግጭቱ ዐውድ በርካታ ሲቪል ሰዎች መሞታቸውን፣ ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን እና የንብረት ውድመት እንደደረሰባቸው ለመረዳት ተችሏል። በተኩስ ልውውጦች ወይም በከባድ መሣሪያ ተኩስ ከሚሞቱ ሰዎች መካከል በመንገድና በእርሻ ሥራ ላይ እንዲሁም በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ጭምር የሚገኙ መሆኑን ቤተሰቦች እና የዐይን ምስክሮች ያስረዳሉ።

 

pic.twitter.com/dCOAH5lFZI— MENELIK III⚔️💚💛❤️🦅 (@Ebrahim53277131) September 15, 2023

 

በዚሁ የግጭቱ ዐውድ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከሕግ/ፍርድ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎች (extrajudicial killings) እጅግ አሳሳቢ ነው። ለምሳሌ ከሐምሌ 24 እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በተለይም በአዴት፣ ደብረማረቆስ፣ በደብረ ታቦር፣ ጅጋ፣ ለሚ፣ ማጀቴ፣ መራዊ፣ መርጦ ለማርያምና ሸዋ ሮቢት ከተሞች ተስፋፍተው በተፈጸሙ ከሕግ/ፍርድ ውጪ የሆኑ ግድያዎች ሰለባ ከሆኑ ሰዎች መካከል ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ የተያዙ ሰዎች፣ በግጭቱ ወቅት መንገድ ላይ የተገኙ እና ያልታጠቁ ሰዎች፣ “የጦር መሣሪያ ደብቃችኋል አምጡ” በሚል የተያዙ ሰዎች፣ የሰዓት እላፊ ገደቦችን ተላልፈው የተገኙ ሲቪል ሰዎችና በቁጥጥር ስር የዋሉ የታጣቂው ቡድን (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚታወቀው) አባላት የሚገኙበት ሲሆን፤ በኮሚሽኑ እና በአስቸኳይ ጊዜ መርማሪ ቦርዱ አማካኝነት የተሟላ ምርመራ ሊደረግበት የሚያስፈልግ ነው፡፡

pic.twitter.com/o8hVObZoF8

— Fano (Amhara) (@FanoAmhara2) September 15, 2023

ከዚህ በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ኮማንድ ፖስት በይፋ ካሳወቃቸው እስሮችና ቦታዎች ውጪ በተለይ በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በአስቸኳይ ጊዜ ዐውዱ የተስፋፋና የዘፈቀደ እስር የተፈጸመ ሲሆን፣ ለምሳሌ በአማራ ክልል በባሕር ዳር፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ጎንደር፣ ላሊበላ፣ መካነሰላም፣ ቆቦ እና ሸዋ ሮቢት ከተሞች፤ በኦሮሚያ ክልል በተለይ በሸገር ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጸሙ የዘፈቀደ እስሮች ይገኙበታል፡፡ ከእነዚህ ታሳሪዎች ውስጥ በደቡብ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ግቢ (በተለምዶ አቦስቶ በመባል የሚታወቀው ቦታ) የነበሩ ታሳሪዎችን ጨምሮ ከተለያየ ጊዜ መጠን በኋላ የተለቀቁ መኖራቸውን ማወቅ የተቻለ ቢሆንም፤ በአንጻሩ ገና ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቀ ሰዎች ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ። በመንግሥት የጸጥታ አካላት የሚታሰሩ ሰዎች በአብዛኛው “ለታጣቂ ቡድኑ ድጋፍ ታደርጋላችሁ” እና/ወይም “የጦር መሣሪያ ደብቃችኋል” በሚል ምክንያት ነው፡፡

Leaked photos expose the horrific conditions faced by Amhara detainees. We call on the international community to demand accountability and an end to these atrocities. #AnharaGenocide#AmharaConcentrationCamps @npratc @hrw @GiorgiaMeloni @GenocideStudies @EUinEthiopia @cnni pic.twitter.com/hPXBmwyRGO

— ASHEWEGOGO (@AmharaHQ) September 15, 2023

በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ውስጥ ሲዳ አዋሽ ወረዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ጊዜያዊ ማቆያ ማእከልን በተመለከተ በዚህ ማእከል ውስጥ ተይዘው የነበሩ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፊትና በኋላም ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ሕፃናትና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ውሏቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ነዋሪዎች ከጎዳና ላይ ተነስተው እንዲቆዩ የሚደረግበት ቦታ መሆኑን፣ በቅርቡ ወደ ማእከሉ ከተወሰዱት ውስጥ 29 ሰዎች በመታወቂያ ካርዳቸው ተለይተው እንዲለቀቁ መደረጉን፣ የተወሰኑት ደግሞ በመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም ወደየመጡበት አካባቢዎች እንዲመለሱ የተደረገ መሆኑን፣ በጣቢያው ውስጥ ተከስቶ የነበረው ተላላፊ በሽታ በቁጥጥር ስር የዋለ መሆኑን ኮሚሽኑ በክትትሉ ተመልክቷል። እንዲሁም የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችን በተለይም ሕፃናትን በተመለከተ በችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ላይ ከዚህ በፊትም ኮሚሽኑ ያቀረባቸውን ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ክትትሉን ይቀጥላል፡፡

በኮማንድ ፖስቱ ትእዛዝ በእስር ላይ መሆናቸው ከሚታወቁት ሰዎችና ቦታዎች ውስጥ ኮሚሽኑ በአዋሽ አርባ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. መጎብኘቱና ማሳወቁ የሚታወስ ሲሆን፤ በሌሎቹም ቦታዎች ተመሳሳይ ክትትል ያደርጋል።

ስለሆነም ኢሰመኮ ከዚህ በፊትም ባቀረበው ጥሪ እንደገለጸው ግጭቱን በዘላቂነት ለመፍታት ላሉት ሰላማዊ አማራጮች በሙሉ ቅድሚያ መስጠትን ጨምሮ፤

If you’re so concerned about the suppression of human rights why did you call and thank @AbiyAhmedAli for waging a genocidal war on Amharas in #Ethiopia? Thousands of Amharas are languishing in concentration camps at this moment while you remain silent. #AmharaGenocide https://t.co/r9eSOGTWhl pic.twitter.com/4Yef2kbWK4

— ነብዩ (@neby_G) September 15, 2023

- በየትኛውም ወገን የሚወሰዱ እርምጃዎች ሲቪል ሰዎችን ወይም የመሠረተ ልማቶችን ዒላማ ከማድረግ ሙሉ በሙሉ እንዲቆጠቡ፣ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳይቋረጥ መከላከል ጨምሮ ለሲቪል ሰዎች ተገቢው ጥበቃ እንዲደረግ፤ በማናቸውም ሁኔታ ሊገደቡ የማይችሉ መብቶችን በተለይም በሕይወት የመኖር መብት እና ከኢ-ሰብአዊ አያያዝ የመጠበቅ መብት እንዲከበሩ፣

As this disparaging ethnic slur is broadcasted via a govt-owned TV; it is not unreasonable to conclude that the gov’t endorses all of it. If they publicly say this about Amharas, I wonder what the Oromo-led PP could do secretly against their Amhara victims in concentration camps. https://t.co/lt1XCwyzKm

— Ermi (@ermidejene) September 15, 2023

- በሲቨል ሰዎች ላይ ግድያ በፈጸሙና በዘፈቀደ እስራት ላይ በተሳተፉ አካላት ላይ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፣

- ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ትእዛዝ ውጪ የታሰሩ ሰዎችን በሚመለከት ጉዳዩ በመደበኛው የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር መከናወኑ እንዲረጋገጥ፤ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት የታሰሩ ሰዎችም የተጠረጠሩበት ወንጀል ምርመራ በአስቸኳይ በማጠናቀቅ ፍትሕ የማግኘት መብታቸው እንዲረጋገጥ፣

- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለመተግበር የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ በተለይም እስራትና የሰዓት እላፊ ገደብ ማስፈጸም በአስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት፣ ከአድልዎ ነጻ የመሆን እና ሕጋዊነት መሠረታዊ መርሖች እንዲመሩ እንዲደረግ ያሳስባል፡፡
https://amharic-zehabesha.com/archives/185769

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...