Wednesday, August 9, 2023
ደሞዝ ሳትቆርጥለት፣ መሣሪያ ሳታዘጋጅለት፣ ሽልማት ሳታበረክትለት፣ ለወገኑና ለሀገሩ ክቡር ሕይወቱን በሰጠ ኢትዮጵያዊ መሥዋዕትነት የቆመ ሀገር ነው ያለን። ይህ በነጻ ለሀገር የሚከፈል፣ ለወገን የሚሰጥ የሕይወት መሥዕትነት ፍልስፍና አለው። በቅርቡ ታሪካችን እንኳን በአምስቱ የጠላት ወረራ ዘመን ያየነው እውነታ ነው፡፡ ይህ ገድል፣ ይህ አርበኝነት ሥያሜ አለው። "ፋኖነት" ይባላል። በፈቃዱ፣ በፍላጎቱ ራሱን ለዚህ መሥዋዕትነት ያዘጋጀው አርበኛም "ፋኖ" ይባላል።
ፋኖነት እና ሽፍትነት በምንም በምን አይገናኙም። ፋኖነት በራስ ፈቃድ፣ በራስ ወጪ፣ በግል መሳሪያ ለአንድ ታላቅ ዓላማ የሚፈጸም የጦር ሜዳ ውሎን የሚያመለክት ሲሆን ሽፍትነት ግን ሕገ ወጥነትን፣ ወንጀለኝነትን የሚያሳይ ሐሳብ ነው። የታሪክ ዕውቀት፣ ራስንና ማንነትን የማወቅ ጥበብ ጉድለት ባለበት በዚህ ዘመን ሁለቱን የሚያምታቱ ሰዎች ማግኘታችን የሚደንቅ አይደለም። ነገርን ነገር ካነሣው አይቀር ግን ሁለቱንም በሚገባቸው ቦታ ማስቀመጡ ተገቢ ይሆናል፡፡
ፋኖነት ክቡር መሥዕትነት ነው። በታሪክ መዝገብም የተቀመጠው በክቡር ቀለም ተጽፎ ነው። ዛሬም ያ ክቡር ስም ጥላሸት እንዳይቀባ ሊጠበቅ ይገባል። ቅርስ ነው፣ የአንድ ሕዝብ የሕይወትና ራስን ከጠላት የመከላከል ፍልስፍና ነው፡፡ ፋኖነት በመላው ሀገራችን ባይኖር ኖሮ የነገሥታቱን የወታደር ብዛት ብቻ አይተው በንቀት የወረሩን ባዕዳን ባሪያዎች አድርገው ባስቀሩን ነበር። ግማሽ ቀን አርሶ፣ በሬዎችን ፈትቶ ቅዳሴ ገብቶ ቀድሶ፣ ቃለ እግዚአብሔር አስተምሮ ሃይማኖቱን ባቆየውና ጠላት ሲመጣበት የዕለት ኑሮውን ትቶ ፣ ፋኖነት ገብቶ ሀገሩን ከወራሪ በታደገው ወገናችን መሥዋዕትነት የቆመ ማንነት ነው ያለን።
አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ::
ፋኖነት ቅርሳችን ነው።
ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ
https://amharic-zehabesha.com/archives/184869
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment