Tuesday, August 8, 2023
ክፍል ሶስት፡
ከኦሮሙማው የፋሽስት መንግሥት ጋር ድርድር አይሞከር፤ ለፋሽስቶች ድርድር ጠላቶቻቸውን አዘናግቶ ማጥፊያ መሳሪያ ነውና!!!!!!
በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ - በሆላንድ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ
E-mail -àDebesso@gmail.com - አምስተርዳም (ሆላንድ) ነሃሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም.
ፋሽስቶች ሁልጊዜም በአሸናፊነት እንጂ በድርድር አምነው አያውቁም፤ አያምኑምም።
ህወሃት ከደደቢት ተነስቶ በትግራይ ውስጥ ተሃትን፤ ጠርናፊትን (ኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት)፤ ኢህአፓን፤ ሥልጣን ላይ ከወጣ በሁላ የሥልጣን ተቀናቃኜ ናቸው ያሉትን የፓለቲካ ተቃዋሚዎች (መአህድን፤ ኦነግን፤ ቅንጅትን፤ ወዘተ) በድርድር ሳይሆን በኃይል፤ ሲያቅተው ደግሞ በብልጠት፤ በሽምግልና ሥም ቄስና ሼክ እየላከና እያታለለ ሁልጊዜም ቢሆን ፍላጉቱንና ፍቃዱን በሌሎች ላይ ጭኗል። ህወሃት በ49 ዓመት ታሪኩ አንዳችም ጊዜ በድርድርና በሰጥቶ መቀበል አምኖ ያደረገው ነገር በ49 ዓመት ታሪኩ ውስጥ አንድም ቦታ አላነበብንም፤ አላየንም፤ ወደፊትም አናይም።
ፋሽስቶች ከላይ በጠቀስኩት የሶሻል ዳርዊኒስት እምነታቸው ምክንያት በባህርያቸው ባሸናፊነት ፍላጎታቸውን ጠላቶቻችን ናቸው የሚሏቸውን ሁሉ በኃይልም ሆነ በብልጠት አታሎ ከማጥፋት ውጭ በሰላም ሰጥቶ መቀበል በሚባለው የድርድር ሂደት ጨርሶ አያምኑም። ፋሽስቶች በጭራሽ ከያዙት ግትር አቋም ሽግሽግ (shift) እና ድርድር (negotiation) በማድረግ እነሱንም ሆነ ተቃዋሚዎቻቸውን በሚያረካና በሚያስማማ የሰጥቶ መቀበል ዘዴ አንድን ግጭት ከእኔ ይቅር ካንተ ይቅር በሚል የሰጥቶ መቀበል ዘዴ (compromise) ግጭትን ለመፍታት አይፈቅዱም። ስለዚህ ፋሽስቶችን አምኖ በምንም ዓይነት ከህወሃትም ሆነ ኦሮሙማን ክሚያራምደው የዓቢይ አህመድ መንግስትም ሆነ ከሌሎች የኦሮሙማ ፓለቲካ አራማጆች የሆኑ የኦሮሞ አክራሪ ብሄረተኞች ጋር አማራውም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ማስቀጠል የሚፈልገው ህዝብ ድርድር ማድረግ የለበትም፤ መታለል፤ መበለጥ የለበትም።
ህወሃትም ሆነ እሱን የተካው ዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው የኦሮሙማ መንግሥት በሰላም አያምኑም። ፋሽስቶችን ሰላምና መረጋጋት ስለሚረብሻቸው ሁልጊዜም የእነሱ ሰላምና እርካታ የሚረጋገጠው የማያቋርጥ ጦርነት፤ የህዝብ መፈናቀል ልቅሶ ሲኖርና ሲቀጥል ብቻ ነው። ስለዚህም ፋሽስቶች ሰላምን ያመጣሉ ብሎ በእነሱ ላይ ለአፍታም እንኳን እምነት መጣል አያስፈልግም።
ፋሽዝም አክራሪ የሆነ ምድራዊ ኃይማኖት ነው
“ብሔርተኝነት በነገሠበት ዘመን፣ ማኅበረሰቦች ጭምብላቸውን አውልቀው በመጣል ራሳቸውን በግልፅ ያመልኩታል።”
“In a nationalist age, societies worship themselves brazenly and openly, spurning the camouflage”. Ernst Gellner
ትግራዋይነት የሚባለውና የትግራይን የበላይነት የሚሰብከው ፋሽስታዊ ፍልስፍናም ሆነ ዛሬ ወያኔን ተክቶ ሥልጣን የተቆናጠጠው ኦሮሙማ የሚባለውን የኦሮሞን ነገድ ተወላጆች የበላይነት የሚሰብክ ፋሽስታዊ ሥርዓት እንደ ኃይማኖት ራሳቸውን የቻሉ አዲስ እምነቶች ሆነው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይና የኦሮሞ ተወላጆች የሚያመልኳቸው ናቸው። ፋሽዝም ምድራዊ ኃይማኖት ተብሎ የሚታወቅ የፓለቲካ ፍልስፍና ሲሆን በአንድ የፋሽስት ፍልስፍና የሚመራ ድርጅትም ሆነ ተከታዩቹ የራሳቸውን ነገድ የወል ማንነት እንደ ጣዖት ማምለክ ይጀምራሉ። ፋሽዝም የአንድ ነገድ ተወላጆች ከራሳቸው የነገድ ማንነት ጋር በተጋነነ መልክ ፍቅር ይዟቸው ካለአንዳች ይሉኝታ የእኛ ነገድ ከሌሎች ሁሉ ልዩ ነው፤ ጀግና ነው፤ የጠራ ደም ያለው ምርጥ ህዝብ ነው፤ እኛ ብቸኛ የሥልጣኔ ምንጭ ነን፤ የማንኛውም ነገር ፈጣሪ ነን፤ እኛን የሚስተካከል አንዳችም ሌላ ፍጡር የለም ወዘተ የሚል የእብሪትና የትምክህተኝነትን አስተሳሰብ በጭፍንነትና በጀሌነት በሚከተሉት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮቹ ዘንድ እንደ ተላላፊ በሽታ የሚያስፋፋ መርዘኛ ርዕዮተዓለም ነው።
ፋሽዝም ለነገድ ማንነት ልዩ ቦታና ቅድስና በመስጠት አንድ የፋሽዝም መሰረት በሆነ አክራሪ ብሄረተኛነት ያበደ ህዝብ የራሱን ማንነት እጅግ በተጋነነ መልክ ቅድስና ሰጥቶ እንደ ጣዖት ማምለክ የሚጀምርበት ምድራዊ ኃይማኖት ነው። የትግራይ ተወላጆች ትግራዋይነት በሚባለው የአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት መገለጫ የሆነ አዲሱ ኃይማኖታቸው ሰክረው ምን ይሉኝን በማያውቅ እብሪትና ማንአህሎኝነት ከዚህ በታች በጥቅስ ውስጥ ያሰፈርኩትን ዘፈን ስለራሳቸው ልዩ ፍጡር መሆን፤ በሰብዕናቸው፤ በታሪካቸው፤ በማንነታቸው፤ የንጹህ ዘር ተወላጆች በመሆናቸው ወዘተ ከሌሎች የኢትዮጵያ ነገዶች ሁሉ እንደሚበልጡ በአደባባይ ይዘፍኑ ነበር። ኤደን ገብረሥላሴ የተባለቸው ድምጸ መረዋ የሆነችው ታዋቂ የትግራይ ዘፋኝ ከዚህ በታች ያለውን ዘረኛና በእብሪት የታጨቀ ዘፈን ስትዘፍን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ከመላው አውሮፓ የተሰበሰቡ የትግራይ ተወላጆች በነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ. ም. እንደ አውሮፓ አቆጣጠር እኔ በምኖርበት በአምስተርዳም (ሆላንድ ሀገር ውስጥ) ከተማ ባደረጉት የትግራይ ተወላጆች በዓል (ፌስቲቫል) ላይ በኩራትና በድል አድራጊነት እንደዚሁም በታላቅ የአሸናፊነት መንፈስና ስሜት ይጨፍሩ ነበር። በዚያን ወቅት ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአማራና በኦሮሞ ክልሎች ውስጥ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በርካታ ንጹሃን የሚገደሉበት ወቅት ነበር። ይህንን ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተጨፈጨፈ አምስተርዳም ላይ የትግራይ ተወላጆች የሚያደርጉትን ጭፈራና ድግስ በመቃወም በሆላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በድግሱ ቦታ ተገኝተው የተቃውሞ ሰልፍ ቢያደርጉም በድግሱ ቦታ ላይ የነበሩት የትግራይ ተወላጆች ድግሱ የሚካሄድበት አዳራሽ በራፍ ላይ ሆነው ሰልፈኞቹን ሲያንጓጥጡና ሲያላግጡባቸው ነበር። ኤዴን ገ/ሥላሴ የሚከተለውን እያለች ነበር ድግሱ ላይ በኩራት ትዘፍን የነበረው። “ትግሬዎች ፈጣሪ ሲፈጥራቸው ጥቂቶች ቢሆኑም ልዩ ፍጡር አድርጎ ነው የፈጠራቸው፤ እኛ ሁሉም ነን ማለትም የታሪክ፤ የቅርስ፤ የጀግንነት መፍለቂያዎች ነን። እኛ ትግራውያን ጀግኖች ባለ ሱሪዎች ነን። እኛ ወያኔዎች የእነዚያ ከጠራ ዘር የወጣን እንክርዳድ ወይም ቆሻሻ የማይደባለቅባቸው ትግራውያን ልጆች ነን! !!! አምሳ ቢወለድ አምሳ ነው ጉዱ። ትግራዋይ ግን አንድ ይበቃል ሃምሳዎቹን ይመክታል በአንድ ክንዱ
አብዛኞቹ የጀርመን ተወላጆች በናዚ ዘመን የጀርመን የአርያን ዘር ልዩና ምርጥ የሆነ ዓለምን መግዛት ያለበት ዝርያ ነው ብለው በጭፍን ይህንን እምነት በአምልኮ ደረጃ እንደ አንድ ኃይማኖት ይከተሉት ነበር። የትግራይ ተወላጆች በተለይ የወያኔ መንግሥት ሥልጣን ከተቆናጠጠበትና ትግሬዎችን ጉልህ የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ካደረጋቸው ጊዜ ጀምሮ ትግራዋይነት የሚባለውን እጅግ ዘረኛ የሆነ የትግራይን ተወላጆች የበላይነት የሚሰብክ አዲስ አምልኮ በኃይማኖትነት ሲያመልኩት ቆይተዋል። በእኔ እምነት በዛሬው ጊዜ አብዛኛው የትግራይ ተወላጅ (ክርስቲያንነትንም ሆነ እስልምናን እከተላለሁ የሚለው ትግሬ) የዚህ ፋሽስታዊ አምልኮ ተከታይ ነው ብዬ እሞግታለሁኝ። ለወትሮው በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮቹ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ዋልድባ ገዳም ገብተው ያንን ታላቅ ገዳም የዘረፉበት፤ ሴት መነኮሳትን የደፈሩበት፤ ገዳሙን ያረከሱበት ድርጊት፤ እንደዚሁም በወረራ በዘመቱባቸው የጎንደርና የወሎ ግዛቶች ገዳማትን፤ ቤተክርስቲያናትን የዘረፉበት (ዘራፊዎቹ እንዲያውም የትግራይ ቀሳውስቶች ጭምር ናቸው) ድርጊት አዲሱ የትግሬዎች ኃይማኖት የኦርቶዶክስ የክርስትና ኃይማኖት ወይም የእስልምና ሃይማኖት ሳይሆን ትግራዋይነት የሚለውና ከማናቸውም ነገር በላይ ቅድስና የተሰጠው በአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ላይ መሰረቱን የጣለው አዲስ ኃይማኖት መሆኑን አንባቢያን ግልጽ እንዲሆንላቸው አሳስባለሁኝ። የትግራይ ተወላጆች በወረራ በገቡባቸው የአፋር ተወላጆች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች መስጊድ ውስጥ ገብተው አልኮል እየጠጡ፤ ቁራን እየቀደዱ የተከበሩ የእስልምና እምነት ሥፍራዎችን ያረከሱበት ድርጊት የዚህን አዲሱን ፋሽዝም የተባለውን የበርካታው የትግራይ ተወላጅ እምነት የሆነውን የፓለቲካ ኃይማኖት በትግራይ ውስጥ መስፋፋት የሚያሳይ ነው። የትግራይ ተወላጆች በእውነት በክርስትናም ሆነ በእስልምና ኃይማኖት የሚያምኑ ይህንን መሰል ጸያፍና ታሪክ የማይረሳው ድርጊት በክርስቲያኖችና በእስላሞች የእምነት ቦታዎች ላይ ባልፈጸሙ ነበር። ነገር ግን አዲሱ ፋሽስታዊ እምነታቸው እነዚህን ጸያፍ ድርጊቶች እንዲፈጽሙ አድርጓቸዋል።
ፋሽዝም ነባር ኃይማኖቶችን ተክቶ በራሱ እንደ አዲስ ኃይማኖት የሚመለክ፤ የሰዎችን አስተሳሰብ፤ ድርጊትና ባህርይ የሚቀይር እንደሆነ በአንድ ሁሉት ምሳሌዎች ላስረዳ። ከጥቂት ዓመታት በፊት በመረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ፓርቲ ገብረ ጉራቻ በሚባለው አካባቢ በጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ኃይለሚካኤል ታደሰ የሚባል አንድ ግለሰብ እዚያ ለተሰበሰቡት በብዙ አስር ሺዎች ለሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች መርዘኛ ንግግር ያደርግ ነበር። በንግግሩም ውስጥ ኃይለሚካኤል ታደሰ ለአዳማጮቹ የደብረሊባኖስን ገዳም እያመለከተ እዚያ ያሉትን “መጤዎች” እንዲያባርሯቸው ህዝቡን ሲቀሰቅስ ታዝበናል። ታዲያ ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ዲያቆን ነው የሚባል ሰው ይህንን መሰል መጤዎችን መንጥሯቸው የሚል አደገኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ ከጀርባው የቆሙት የኦርቶዶክሱ እምነት ተከታይ መረራ ጉዲናና የእስልምና ተከታዩ ሀጂ ጀዋር መሀመድ በደስታ ሲንሸኳሾኩ ይታያል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተከታይ የሆኑትን ካድሬውን ኃይለሚካኤል ታደሰንና መረራ ጉዲናን ከእስላሙ ሀጂ ጀዋር ጋር ያስተሳሰራቸውና በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ያፈራው አዲሱ የኦሮሞ አክራሪ ብሄረተኞች ኃይማኖት ኦሮሙማ ይባላል። ይህ ኦሮሙማ የሚባለው አዲሱ ፋሽስታዊ ኃይማኖት ነው ዛሬ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆነውን በቀለ ገርባን፤ የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች የሆኑትን መረራ ጉዲናንና ኃይለሚካኤል ታደሰን፤ የእስልምና ተከታይ የሆነውን ሀጂ ጀዋር መሃመድን (ሃጂ እያልኩ የምጠራው መካ መዲናን ተሳልሞ ስለመጣ ነው) በአንድነት በማስተባበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን ተቋሞችን እናፍርስ፤ “መጤ” የሚባሉትን የኦርቶዶክስ ኃይማኖት መሪዎች ከኦሮሚያ እናጽዳ የሚያሰኛቸው። ኦሮሙማ ከእስልምናም፤ ከክርስትናም ሆነ ከማንኛቸውም ሌሎች እምነቶች በላይ መሆኑን ደግሞ ሽመልስ አብዲሳ የተባለው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ግልጽ ባለ ቋንቋ ገልጾታል። አሁን በቅርቡ እንኳን ሸገር በሚባለውና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ እንዲሆን ተደርጎ ወደ ኦሮሚያ የተካለለው ከተማ ውስጥ የሚገኙ በርካታ መስጊዶች ሲፈርሱ፤ እዚያ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑና የእስልምና እምነት ተከታዮች የሆኑ የሌሎች ነገዶች ተወላጆች የሆኑ ኢትዮጵያውያኖች ቤቶች ሲፈርሱ፤ ኦሮሞ ያልሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች በጥይት ሲገደሉ፤ በካራ ሲታረዱ ትላንት “ድምጻችን ይሰማ” እያሉ በታሰሩበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን ከእሥር ይፈቱ እያሉ ድጋፋቸውን ይሰጧቸው የነበሩት፤ ሰልፍ ሲደረግላቸው የነበሩት እነ አህመዲን ጀበል፤ ሌሎችም የኦሮሞ ኡስታዞች ድምጻቸውን አጥፍተዋል። እውነቱ ይህ ነው። ዛሬ በአዲሱ የኦሮሙማ ኃይማኖት የሰከሩት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የተለያዩ የኦሮሞ ብሄረተኞች የሚመሯቸው የፓለቲካ ድርጅቶች ደጋፊዎች፤ እንደዚሁም የትላንትናዎቹ የእስልምና መሪዎች ነን እያሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያታልሉ የነበሩት የእነ አህመዲን ጀበልም ሆነ የሌሎች የኦሮሞ ኡስታዞች ብቸኛውና ዋነኛው የህይወት መመሪያቸው ኦሮሙማ የሚባለው የኦሮሞን ነገድ ተወላጆች የበላይነት የሚሰብክና የሚተገብር አዲስ ፋሽስታዊ ኃይማኖት መሆኑ ግልጽ ይሁን። በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩት የኦሮሙማም ሆነ የትግራዋይነት አዲስ ኃይማኖት ወይም እምነት ተከታዮች ይህንን አዲሱን አክራሪ ኃይማኖታቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ጥለው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ማስቀጠል ከሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት ይሰለፋሉ ብሎ መጠበቅ ትልቅ የዋህነት ነው። ይልቁንም ሌላው ኢትዮጵያዊ እነዚህን በፋሽስታዊ ፍልስፍና የሚመሩና ትግራዋይነትንና ኦሮሙማማን በኢትዮጵያ ላይ የጫኑ ድርጅቶች በጋራ በመናበብ ድርጅታዊ ህልውናቸውን ለማጥፋት ሰፊ ጸረ-ፋሽስት ግንባር ፈጥሮ ማክሰም ይገባዋል። እነዚህ ሁለት ኃይሎች የሚያራምዱትም ዘረኝነትን፤ የእርስ በርስ ጥላቻን፤ ጦረኛነትን፤ ትምክህትን፤ ማንአህሎኝነትን፤ ጠበኛነትን፤ የዘር ጽዳትን፤ ኢ-አመክንዮታዊነትን (irrationality or unreason)፤ ኢ-ግብረገባዊነትን (immorality)፤ ኢ-ህጋዊነትን (lawlesness)፤ ኢ-ዲሞክራሲያዊነትን (anti-democratic stance)፤ ጭፍን አምባገነንነትን (totalitarian political system) በኢትዮጵያ ላይ የጫኑ ኃይሎች የፈጠሩትን በነገድ ማንነት ላይ የተመሰረተ ሥርዓት ህገወጥ ማድረግ የግድ ይላል። ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም እንዲኖሩ ከተፈለገ ይህንን የታሪክ ፍርድ መቀበል ግድ ይላል።
ፋሽዝም የሰዎችን ነጻነት የሚጻረር ኢ-አመክንዮታዊና ስሜተኛነት የተጠናወተው አክራሪ እምነት ነው።
የፋሽስት ርዕዮተዓለም የሰውን ልጅ አስተሳሰብና ምኞት በነገድ ማንነት ክልል ውስጥ ያጥራል። ፋሽዝም ሰዎች የወጡበትን የነገድ ድንበራቸውን በመዝለል ከእነሱ ነገድ ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር ሁሉን-አቃፊ ወይም ሌሎችን የሚያካትት (inclusive values) እሴቶችን እንዳይጋሩ እንቅፋት ይሆናል። ፋሽዝም የጎሳን፤ የሃይማኖትን ድንበሮች በመሻገር ሰዎች የሚፈጥሯቸውን ጥልቀት ያላቸውን ሰብዓዊ መስተጋብሮችና ሰብዓዊ እሴቶች (fascism opposes humanist values) ይቃወማል። ፋሺዝም የሰው ልጆች እራሳቸው የፈጠሩዋቸውን የጎሳ፤ የሃይማኖት ወዘተ ድንበሮችና አጥሮች ተሻግረው ከእነዚህ ሰው-ሰራሽ ልዩነቶች ባሻገር የሰው ልጆች በዓለም ላይ በህብረትና በፍቅር ህይወታቸውን የሚመሩበትን፤ ደስታና ሃዘንን በጋራ የሚጋሩበትን፤ የሚደጋገፉበትን፤ አንተ ትብስ፤ አንቺ ትብስ የሚባባሉበትን ሰላማዊ የአብሮነት ሂደት ይቃወማል። ፋሽዝም እኩልነንትን (equality)፤ ፍትህና ርትዕን (justice)፤ አቃፊነትን (inclusiveness)፤ ዲሞክራሲን ወዘተ ይጻረራል። ፋሽዝም ማናቸውንም ኢትዮጵያውያን የመሰሉ ያንድ ሀገር ዜጎች የሚጋሯቸውን ጎሳ-ዘለል (supra-ethnic)፤ ኃይማኖት-ዘለል (supra relgious) የወል እሴቶችን (collective values) ያፈርሳል። ጎሳ-ዘለል የሆነቸውን የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ለመበታተንና በነገድና በጎጥ ለመከፋፈል የትግራይና የኦሮሞ ልሂቃን ያልተቀደሰ ጋብቻ ፈጥረው ይህቺን አስተሳሳሪ የሆነች ቤ/ክርስቲያን ለማፈራረስ የተነሱት ከዚህ ሁለቱም በጋራ ከሚጋሩት ፋሽስታዊ እምነት ተነስተው ነው። መንፈሳዊ አባቶችም በእነ ዓቢይ አህመድና ካድሬዎቹ መለሳሰስና መቅለስለስ ተታለው በድርድር ሥም ይህቺን ቤ/ክርስቲያን ለጥፋት እንዳይዳርጓት እሰጋለሁኝ።
በትግራይ ክልል ጦርነት በሚካሄድበት ወቅት አንድ አሉላ ሰለሞን የሚባል በአሜሪካን ሀገር የትግራይ ተወላጆች ማህበር ሊቀመንበር የሆነ አክራሪ ብሄረተኛ “እኛ በጋራ የምንጋራው ነገር የለንም” እያለ የደነፋበት ሃሳብ ዛሬ እሱ ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩና ትግራዋይነት የሚለውን ፋሽስታዊ አስተሳሰብ የሚያንጸባርቁ የትግራይ ተወላጆች የሚጋሩት እምነት ይመስለኛል። እንደዚሁም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦሮሙማ የሚባለውን ፋሽስታዊ አስተሳሰብ የሚያመልኩ የኦሮሞ ተወላጆች ዛሬ ኢትዮጵያዊነት የሚባለው ማንነት እጅግ የሚያንገሸግሻቸው ሃሳብ እንደሆነና እነሱ እንደ ኃይማኖት ከሚያመልኩበትና ከሚከተሉት ኦሮሙማ ከሚባለው የኦሮሞ ነገድ ተወላጆችን የበላይነት ከሚሰብክና ከሚተገብር አክራሪ የፓለቲካ እምነት ጋር እንደሚቃረን እረዳለሁኝ። ይህንን ፋሽዝም የተባለ አክራሪ የሆነ ምድራዊ የፓለቲካ ኃይማኖት እምነት የሙጥኝ ካሉት የኦሮሙማም ሆነ የትግራዋይነት ፓለቲካ አራማጆች ጋር በፍጹም ለድርድር መቀመጥ የለብንም። እነዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 32 ዓመታት ጦርነትን፤ ጥላቻን፤ ግጭቶችን፤ ዘረኝነትን፤ ተስፋፊነትን፤ ጠበኛነትን፤ ክፋትን፤ ስግብግበኛነትን፤ ይሉኝታቢስነትን፤ መተሳሰብን፤ ግብረገባዊነትን ወዘተ ያፈረሱ የፋሽስት ፍልስፍና መገለጫ የሆኑት የትግራዋይነትም ሆነ የኦሮሙማ እምነቶች በጭራሽ ህጋዊ ሆነው እንደ ፓለቲካ ኃይል ህልውናቸው ሊቀጥል አይገባም። ትግራዋይነትም ሆነ ኦሮሙማን የሚያስፋፉት አክራሪና ጽንፈኛ የፓለቲካ ድርጅቶች በአውሮፓ ውስጥ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ በህግ እንደታገዱት የፋሽስትና የናዚ የፓለቲካ ድርጅቶች በኢትዮጵያም ውስጥ ሊታገዱ ይገባል። ይሄ ሃሳቤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራዋይነትና የኦሮሙማ ፋሽስታዊ እምነት ተከታዮችን ሊያስቅ ይችላል። ነገር ግን የትግራይም ሆነ የኦሮሞ ተወላጆች ከሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ጋር በሰላም መኖር ከፈለጉ ትግራዋይነትንም ሆነ ኦሮሙማ የሚባሉትን ተናዳፊና ተንኳሽ የሆኑ፤ ተናካሽነትን፤ ጠበኝነትን፤ ጦረኛነትን የሚያስፋፉ፤ የኢትዮጵያን ማህበራዊ ሰላም የሚያደፈርሱ የፋሽስት ፍልስፍና አስፋፊ እምነቶችን የሙጥኝ ማለትን መተው አለባቸው።
ይህ ደግሞ የእነዚህን የፋሽስት አመለካከት ደጋፊዎች ይሁንታ በማግኘት የሚመጣ አይደለም። ይህ ሊመጣ የሚችለው ኢትዮጵያ እንደ በሃውርታዊ (multi-ethnic) ሀገር ትቀጥል የሚለው በርካታው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰፊና አካታች ጸረ-ፋሽስት ግንባር መስርቶ የኦሮሙማን ሆነ የትግራዋይነትን አስተሳሰብ የሚያስተናግደውን መንግስት በመጣል ዘረኝነትን መሰረት ያደረገውን በነገድ ማንነት ላይ የተመሰረተ (ethnic federalism) ህገመንግሥት ሽሮ በግለሰብ ነጻነት ላይ የተመሰረተ ህጋዊ፤ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግስታዊ ሥርዓት በመመስረት ብቻ ነው። የወያኔ ፋሽስታዊ ድርጅትም ሆነ እሱን የተካው የኦሮሙማ መንግስት እንደማንኛውም የፋሽስት ኃይል ሙሉ በሙሉ ተደምስሰው የሚከተሉትን የፋሽስት ፍልስፍናም ሆነ የሚወክሏቸው ድርጅቶች አንዳችም ዓይነት ህጋዊ ሰውነት እንዳይኖራቸው ማድረግ ይገባል። ይሄ ለበርካታ ይህን ጽሁፍ ለሚያነቡ ሰዎች ሊያስቅ ይችላል። በአክራሪ ብሄረተኛነት የማዕዘን ራስ ላይ የቆመ የፋሽስት ፍልስፍና ተከታዮች ለአመክንዮታዊ ክርክርና የሃሳብ ልውውጥ ዝግጁ አይደሉም።
ፋሽዝም ኢ-አመክንዮታዊነትን፤ ስሜታዊነትን መሰረት ያደረገ ፍልስፍና ስለሆነ ችግሮችን በውይይት፤ በመግባባት፤ በስምምነትና በሰጥቶ መቀበል ዘዴዎች የሚያስተናግድ አይደለም። የሰው ልጆች ኢ-አመክንዮታዊ የሆነና ስሜት ላይ የተመሰረተ ማዕቀፍ ውስጥ ሆነው በመካከላቸው የሚከሰቱ ችግሮችን በሰላም ሊፈቱ አይችሉም። ለዚህም ነው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በፋሽዝም ምክንያት 60 ሚሊዮን ያህል ህዝብ ያጡት የአውሮፓ ህዝቦች ማናቸውንም በፋሽስታዊ ፍልስፍና የሚመራ የፓለቲካ ድርጅት ህልውና በህግ ያገዱት። አንዳንድ የኢትዮጵያ ምሁራን ባለፉት 32 ዓመታት ይህን ያህል ጥፋት ከደረሰ በኋላ እንኳን አሁን ያለውን በነገድ ማንነት ላይ የተመሰረተ መንግሥታዊ ሥርዓት ለብዙ ዓመታት ስለቆየና ብዙ ተከታዮች ስላሉት እሱን ለማፍረስና ህገወጥ ለማድረግ መነሳት አደገኛ ነው ይላሉ። ለመሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት የቀጠፈ (የቅርቡ የሰሜን ጦርነት እንኳን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን አጥተዋል)፤ ኢትዮጵያን በዓለም በተፈናቃይ ቁጥር የአንደኛ ደረጃ ያሰጣትን፤ በብዙ መቶ ሺዎች ዜጎቿን ሀገር-አልባ አድርጎ ለስደት የዳረገውን ይህን ባለፉት 32 ዓመታት እንደ ነቀርሳ ይህቺን ሀገር ሲያጠፋት የቆየ የፋሽስት ሥርዓት ከማፍረስ ውጭ ምን ዓይነት አማራጭ ይኖራል? በእኔ እምነት ጽንፍ የረገጠ ጥላቻን፤ ልዩነትን፤ ጦርነትን፤ ጠበኛነትን፤ ተስፋፊነትን ወዘተ የህልውናው መሰረት ያደረገው ፋሽስታዊ የፓለቲካ ሥርዓት አንድም ቀን ሊቆይ የሚገባው ሥርዓት አይደለም። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ፋሽስታዊ የሆነ መንግሥታዊ ሥርዓት ከማፍረስ ውጭ አንዳችም ዓይነት ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም።
https://amharic-zehabesha.com/archives/184844
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment