አህያ ጂብ ሲያይ ከመራቅ ይልቅ ይጠጋል ፡፡ እንዲዉም አንድ የጂብ እና የአህያ ንግግር እና ስምነት በቀልድ መልክ ይነገራል ፡፡ ቀልድ ደግሞ ነባራዊ ህይወትን በስማ በለዉ የሚገለፅበት አዝናኝ፣አስተማሪ እና ታሪካዊ ይዘት አለዉ ፡፡
በአንድ ወቅት ጂብ እና አህያ በአንድ ወንዝ ከላይ እና ታች ሆነዉ በቅርብ ርቀት ዉሀ ሲጠጡ ጂብ ሆይ ስበብ ሲፈልግ አህዮን የወንዙ ዉኃ ደፈረሰ ይላታል ፡፡
አህዮም እንኳን ታዝዛ እንዲሁ ጂብ ስታይ ራሷን ከማራቅ እና ከመጠበቅ ይልቅ እየተንቀጠቀጠቀጠች መቅረብ ተፈጥዊ ግዴታ እንደሆነ ተለማድዋለች ፡፡
እናም መብላት ስልጣኑ እና መብቱ የሖነዉ ጂቦ ትዕዛዝ አህዮ ሆይ ነይ ከፍ በይ ሲላት መጠጋት እነ መበላት ዕጣ ፋንታዋ አድረጋ የጠለማመች አህዮ መሄዷ አይቀሬ መሆኑን ሆዷ እያወቀ መምጣቱንስ ልምጣ ግን …….. ብላ ጠየቀች ይባላል ፡፡
ወደ እኛ አገር ነባር ሁኔታ ሲመለስ ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ለራሳቸዉ እና ለአገራቸዉ ሉዓላዊ የማይገሰስ ተፈጥሯዊ መብታቸዉ ሆኖ ሳለ ካለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት ጀምሮ ዕጣ ፋንታቸዉ ን ሁሉ ለኢህአዴግ ሰጥዉ ዕረፍት አልባ ዕንቅልፍ ተኝተዉ በሁንም በህልምም ህይወትም ሞትም እንዳል ክ ብለዉ ሁሉን ክፉ ነገር አስተናግደዋል ፡፡
ኢህአዴግም የመብት ፣ የይገባኛል ፣የነፃነት ……ጥያቄ ለሚየነሳ ሁሉ አንዴ የተልባ ወጥ አንዴ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብትነሱ አትራመዱ ፤ በትናገሩ አትኖሩ በማለት እንደ አባጂቦ ገርፎ ጯሂ፤ አደፍርሶ አደፍራሽ ፤ በድሎ ተበዳይ …እያለ ህዝብ የሁሉ ነገር ተሸካሚ አህያ አድርጎት የሁሉ ነገር ባለቤት ሲሆን ፤የሁሉ ነገር ተጠያቂ ደግሞ ህዝብ ከሆነ ብዙ ዓመታት (1983 ዓ.ም ጀምሮ) ተቆጥረዋል ፡፡
ሆኖም ኢህአዴግ ለዘመናት በኢትዮጵያ እና አማራ ህዝብ ጀርባ ሆኖ እየማለ በተቃራኒዉ በጥላቻ እና በዕብሪት ለዓማታት አገር እና ኅዝብ ዕየገደለ የሰላሳ ዓመታት የተጫነበት የመከራ ቋጥኝ እና ባላሳለሰ ሁኔታ ዕየደረሰበት ያለዉ ዕንግልት፣ ስደት ፣ ዉርደት እና ሞት መነሻ እና መድረሻ የዓማራ ህዝብ ሆኖ ተከሳሽ እና ተወቃሽ በማድረግ ብዙ የመከራ እና ስቃይ እንዲሳልፍ ተደርጓል፡፡
ኢትዮጵያ የእስር እና የአሳር ምድር ሆና ለሁሉም ዕንድትበቃ ሆና የተረከብናት ታላቅ እና ሰፊ አገር ሆና ሳለ በእኛ አንሶ በማነስ አሳንሰታናል፤ ኢትዮጵያ የዕስር እና አሳር ምድር ሆና በደም እና ዕንባ ጎርፍ ተሸርሽራ እንድትጠብ ሆናለች ፡፡
ዛሬም ለምንገኝበት የጦርነት አዙሪት ለመግባታችን በድንገት የሆነ ሳይሆን ጦር አምጣ እያሉ ምድር ለሚደበድቡት አዲስ አይደለም ፡፡ አሁን አሁን የሚባለዉ በዕዉነት ቀድሞ ከታሰበዉ ዉጭ ግጭት፣ ህግ ማስከበር ….ሲባል የሚያሳስበን ለሁሉም ኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያ አንድነት የማይበጂ ተጨፈኑ ለማኛችሁ የሚለዉ አስተሳሰብ እና ማሳበብ የሚረባን አይደለም ፡፡
መንስኤ ሳይታወቅ የበሽታ መድኃኒት መገመት እንደማይቻል ሁሉ በኢትዮጵያችን ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንስዔዉ የዓማራ ኅዝብ የትህነግን ወረራ ለመቀልበስ ስንቅ ያለዉ ሰንቅ ፣ትጥቅ ያለዉ ትጥቅ ይዞ እንዲዘምት ሲሆን ተጠይቆ እንጂ ታጥቆ አልነበረም ፡፡
በዚህም ህዝቡ በላቡ ያልነበረዉ በደም ዋጋ ከጠላት የታጠቀዉ ጠብ መንጃ "ጥቁር ጠበንጃ "ለማስወረድ የተለያየ ጥረት ተደርጎ ያልተቀበልነዉን አንሰጥም መባሉ ኢህዴግ በኃይል በማንበርከክ ለማስመለስ የተጀመረዉ የጥቁር ታሪክ ሙጃ ዘር ነበር ፡፡
የዓማራ ህዝብም ንብረታችሁን አምጡ ፤ ትጥቅ ፍቱ ማለቱ ይሁን ግን ምን ታስቦ ነዉ የሚለዉን ህዝብ ለምን ቢልም ሰሚ ያጣ ህዝብ ከመሞት መሰንበት ብሎ መከላከል ማድረጉ በምን ዋጋ እና ስሌት በደል ላይ በደል እንዲጫንበት ስለምን ይፈለጋል ?
"አንድነት ኃይል ነዉ !"
Allen
https://amharic-zehabesha.com/archives/185242
Thursday, August 17, 2023
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment