Thursday, August 10, 2023

አባባሉ “ጀዉሳ” እንጅ “ጃዉሳ” አይደለም (እዉነቱ ቢሆን)
ዲያቆን?? ዳንኤል ክብረት አቶ (ዶ/ር?) ለገሰ ቱሉን አሳስቶታል፡፡ ቃሉ በአንዳንድ የአማራ ቦታወች ይነገራል፡፡ በተለይ እኔ ባደግሁበት ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብ ሳይሰጠው ራሱ ምግቡን አንስቶ ለሚበላ ወንድ ልጅ ከቤተሰቡ የሚሰጠው ቅጽል ነው፡፡ ይህ አባባል በማደግ ላይ ያለንና ከጉርምስና በፊት እድሜ ላይ ያለን ታዳጊ ወንድ ልጅን ብቻ ይመለከታል እንጅ ትልልቅ ወንዶችንና አጠቃላይ ሴቶችንም ፈጽሞ አይመለከትም፡፡

አንድ ልጅ ከብት ጥበቃ ላይ አርፍዶ ወይንም ከብት ሲጠብቅ ውሎ ወይንም ሌላ ስራ ላይ ቆይቶ ቤቱ ሲመለስ እቤቱ እንደደረሰ እናቱ ወይንም እህቱ ቆሎም ሆነ ንፍሮ ወዲያዉኑ ሳይሰጡት ሲቀር ራሱ ቆሎው ወይንም ንፍሮው የተቀመጠበትን እቃ (ቦታ) ፈልጎ በማግኘት በራሱ ፍላጎትና ዉሳኔ ዘግኖ ይበላል፡፡ ምግቡ እስከሚሰጠው አይጠብቅም፡፡ ይህንን አይነቱን ድርጊት የፈጸመውን ልጅ ቤተሰቡ “ልጁ ጀውሳ ነው” ይለዋል፡፡ ልጁ በቤተሰቡ ጀውሳ የተባለበትም ዋና ምክንያት ሳይሰጠው በራሱ አንስቶ ስለበላ ነው፡፤ በጉልበቱ ተጠቀመ ማለት ነው፡፡

ዳንኤል ክብረት በህዝብና በአገር ላይ ጥቃት ሲደርስ ለዘመናት የህዝብ አለኝታ፣ የህዝብን እንባ አባሽና የህዝብን ደም መላሽ የሆነውን ፋኖን እንዴት ጀውሳ ብሎ ሊፈርጀው እንደፈለገ ራሱ ይጠየቅበት፡፡  ፋኖ ሌላ ወያኔ ሌላ፡፤ ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረድ!!!!

አንድ ልጅ በቤተሰቡ ጀውሳ መባሉ ትርጉሙ ይህ ሲሆን ስድብ እንዳልሆነ አሰያየሙ ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፡፡ ማንም ይሁን ማን ፋኖን በዚህ አጠራር ያለቦታውና ያለአግባቡ ለመፈርጅ መሞከሩ ግን በፍጹም ትክክልም አግባብም አይደለም፡፡

ፋኖ በአጭር ቀናት ውስጥ ከማንም ግምት ውጭ የሆነ ታላላቅ ጀብዶችን ስለሰራ የአማራ ጠላቶች ፋኖን ጀውሳ ማለታቸው በፋኖ የህዝብ አለኝታነት ምን ያህል እርር ኩምትር ለማለታቸው ማሳያ ነው፡፡ እኔ እዚህ ላይ ነገሩን ያነሳሁት አባባሉ ጃውሳ ሳይሆን ጀውሳ እንደሆነና ትርጉሙም ምን ማለት እንደሆነ ለህዝብ ለማስረዳት ብቻ  ነው፡፡

ፋኖ ለአማራ ህዝብ ጥቃት ቀድሞ ደርሶ አማራውን ከኦሮሙማና ከወያኔ የተጣመረ የእልቂት ድግስና ወረራ ለመታደግ በጣም አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ የተደራጀ አማራዊ ብሎም ኢትዮጵያዊ ሀይል ነው፡፡ ፋኖ 27 አመት የተደራጀን የዘረኝነት ፖለቲካ በ 27 ቀናት ቆራጥ ተጋድሎ ያነቃነቀና ያስጨነቀ ሀይል ነው፡፤ ማነቃነቅና ማስጨነቅ ብቻም ሳይሆን ፋኖ ኦሮሙማን ከማእከላዊ መንግስት ስልጣን መንግሎ ለመጣል አቅዶ እየስራ ነው፡፡

ፋኖ አስቀድሞ ክልሉን ነጻ በማድረግ የመላው ኢትዮጵያዊያን አገር የሆነችውን ኢትዮጵያን የሁሉም እኩል የጋራ አገር ለማድረግ  ቆርጦ የተነሳ ማድረግም የሚችል ሰፊ የአማራ ህዝብ ድጋፍ ያለው ሀይል ነው፡፤ ሰፊው የአማራ ህዝብ ስንል ወያኔና ኦሮሙማ ለጥቅማቸው ሲሉ ብዛቱን ሆን ብለው ከኦርሞ ህዝብ ቁጥር በታች አድርገው ያሳነሱትን የአማራ ህዝብ ቁጥር ሳይሆን እውነተኛውንና ቢያንስ ቢያንስ ከ56 ሚሊዮን በላይ የሆነውን አማራማለታችን ነው፡፡

ይህ ቁጥር እውነት ወይንም ስህተት መሆኑን ለማረጋገጥ ተአማኒ፣ ሀቀኛና የውጭ ታዛቢወች ያሉበት ነጻ የህዝብ ቆጠራ ማድረግን ይጠይቃል፡፤ ይህንን መሰሉን ሀቀኛ የህዝብ ቆጠራ ወያኔም ሆነ ኦሮሙማ እስካሁን አላደረጉትም፡፤ ኦሮሙማወች  ስልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ወደፊትም አያደርጉትም፡፡ ምክንያቱም ሀቁና እውነቱ በነጻ የህዝብ ቆጠራ ዉጤት  ሲረጋገጥ ጥቅማቸው ሲለሚቀርና 32 አመት ሙሉ የአማራን ህዝባ ቁጥሩን አዛብተው ከበጀት ምደባና ድምጽ አቆጣጠር/ ድምጽ አሰጣጥ /ዉክልና ....ወዘተ  አሰራሮች አኳያ ለፈጸሟቸው ማጭበርበሮችና ላካበቱት የተዘረፈ የበጀት አመዳደብ ተጠያቂነትን ስለሚፈሩ ነው፡፡ መቼም ቢሆን ተጠያቂነታቸው አይቀርም!!!!!

ፋኖ  አስቀድሞ ክልሉን ከዚያም መላዋን ኢትዮጵያን ከኦሮሙማ መንጋጋ ነጻ የማድረግ ዘመቻው ግብ መምታት ረዥሙን ጉዞውን ገና አንድ ብሎ ጀመረ፡፤ በኦሮሙማ መብታቸውና ህልውናቸው እየተናደ ካሉ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር እየተናበበ በጋራ በመታገል አገሩን ከኦሮሙማ ነጻ ያደርጋል፡፡ አሁን እንጭጩ አቶ አብይ አህመድ እንደሚያላግጥባት ሳይሆን  ያኔ ኢትዮጵያ ሁሉም ዜጎች በእኩልነትና በአንድነት የሚኖሩባት ሉአላዊት፣ ሀቀኛ ፌደራላዊትና ሰላም የሰፈነባት አገር ትሆናለች፡፤

በዚህ ሂደት ውስጥ አብይ አህመድ የአማራ ከተሞችን በመድፍ በታንክና በድሮን በመምታት ለማውደም (በሻሻ ለማድረግ) የጀመረውን የምቀኝነትና የአውሬነት ስራ ፋኖ ለጊዜው በሳል ስሌት አድርጎና ወስኖ  ከተቆጣጠራቸው ከተሞች ወጣ ማለቱ ትክክልና ወቅታዊ ም ብቻ ሳይሆን እጅግ የተዋጣለት የዉጊያ ስትራቴጅም ነው፡፤

ይህ የአማራ ህዝባዊ ግንባር ዉሳኔና በሳል እርምጃ በዙሪያው ያሉ የአብይ ቱሪናፋወች እንድሚያናፍሱት ፋኖ የአብይ አህመድ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒፎርምን አልብሶ ያሰማራውን መዴደውን የኦሮሞ ወርሪ መንጋ መግጠም አቅቶት አይደለም፡እርሱንማ በ27 ቀናቱ አውዴ ዉጊያወች ገጥሞት ትቢያና የአፈር ማዳበሪያ ድርጎታል፡፡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ወጣቶችን ራሳቸው በጫሩት ጦርነት አስበልተውና ሌሎች መቶ ሽህወችንም አካለ ጎደሎ አስድርገው አሁን ላይ አብይ ጉያ ውስጥ የተወሸቁት ወያኔወች እንደሚያስቡትም ፈርቶ አይደለም፡፤ የፋኖ ከከተማወች ለጊዜው ገሸሽ የማለት እርምጃው የኦሮሙማ የጅቦች መንጋና ከአማራ ክልል ፈርጥጦ አዲስ አበባ ሆቴሎች የሚያቅራራው የአማራ ትርፍ አንጀቶች ስብስብ እንደሚሉት ፋኖ ተሸንፎም አይደለም፡፡ በጭራሽ!!! ከከተሞች ለጊዜው ገሸሽ የማለት የፋኖ የተጠና እርምጃ ከተሞች በከባድ መሳሪያ  እንዳይወድሙ ሁኔታው ያስገደደውና መወሰድ የነበረበት ምርጥ ስትራቴጅ ነው፡፡ ህዝባዊነት ነው፡፤ ለህዝብና ለትግሉ ማሰብ ነው፡፡

በዚህ የህልዉና ተጋድሎ ውስጥ የአማራ ህዝብ ህልውናውን በትግሉ ካላረጋገጠ በስተቀር ለእርሱ ይህም ሞት ያም ሞት የሆነበት ሁኔታ ውስጥ ነው የሚገኘው፡፡አብይ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው የአማራን ዘር ማጥፋት(GENOCIDE) ነው፡፤  ለዚህ እውነትነት በተለይ በኦሮምያ ክልል የሚሊዮን አማራወች በአማራነታቸው እየተለዩ መታረዳቸው ከ200 ሽህ በላይ አማራወች በአዲስ አበባ ዙሪያ ቤት አልባ {ህጋዊ ድሀ} መደረጋቸው፡፣{እስከ 40ሽ አማራወች በአማራነታቸው እየተለዩ  እስር ቤት መወርወራቸው ...ወዘተና  ሌሎች አያሌ አማራ ላይ የተሰሩ ስፍር ቁጥር የሌላቸው በማስረጃነት ተሰንደው የተያዙ ግፎችና በደሎች  በቂ ማሳያወች ናቸው፡፡ ይህ በሆነበት አጣብቂኝ ውስጥ የተነሳን የህዝብ የአልገዛም ባይነት ተጋድሎን ማን ድል እንድሚያደርግና እንዴትስ ድል እንደሚያደርግ ሂደቶች ፍንትው አድርገው በቅርቡ ያሳዩናል፡፡

ታሪክ እንደሚያስረዳን ህዝባዊ ወኔ፣ መገፋት፣ አማራጭ ማጣት እንጅ የተረኞች የከባድ መሳሪያ ጋጋታ ድልን አያቀዳጅም፡፡ ይህ እውነታ  በገሀዱ አለም ውስጥ በተለያዩ ህዝቦች ትግሎች ላይ የተረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡  እንኳን ጀግናውን የአማራን ህዝብ በሩ በተዘጋ ቤት ውስጥ አንድ እንሰሳን ብትደበድበው መውጫ ሲያጣ ወደአንተው ይመጣብሀል፡፡

የአማራ ወደዚህ የህልዉና ተጋድሎ ውስጥ የገባው ተገዶ ነው፡፡ ፋኖ መላው የአማራ ህዝብ ከጎኑ ስለሆነ ያለጥርጥር ያሸንፋል፡፡ ለትግሉና ለድሉ የሚያስፈልጉትንም የሎጅስቲክ ጉዳዮች በፍጥነት በሁሉም መስኮች ከህሉም አጣጫ እያሟላ ይሄዳል፡፡አንዱ ምንጭ ምርኮ ነው፡፡

ፋኖነት ለአማራው ህዝብ  ልክ እንደ አማራነቱ፣ ልክ እንደ ነፍጠኛነቱ መለያው፣ መመኪያውና የማንነቱ መገለጫው ነው፡፡

ሁሉም አማራ ፋኖ ነው፡፡ እኔም ፋኖ ነኝ!!!!
https://amharic-zehabesha.com/archives/184894

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...