Monday, August 7, 2023

ዉኃን ምን አጮኸዉ ቢሉ ድንጋይ አሉ !
 

ሁላችንም ሠዉ ሆነን የጠፈጠርን ኢትዮጵያዉያን በራሳችን አገር እና ወገን ለዕድሜ ልክ  አሳር እና እስር የዳረገን ምን እና ማን እንደሆነ እንኳን ማገናዘብ አጥቶን ኢትዮጵያ አገራችን ከረጂም ዓመታት ጀምሮ ለብዙኃን ኢትዮጵያ ጣራ አልቦ አሰር ቤትሆና ቆይታለች ፡፡

ይህም በጥቂቶች እና በጥላቻ በሰከሩ ስግብግቦች ማን አለብኝነት እና ንቀት የቀንድ አዉጣ ፖለቲካ ከዕዉነት መለየታቸዉን መስማት በማይፈልጉት የተወለደ የአገር እና ህዝብ መከራ ነዉ ፡፡

ኢህአዴግ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የፖለቲካ ስርዓትን በመጠበቅ የጭቆና እና አድሎ ስርዓትን በማዘርጋት እና በማጥብቅ በዜጎች ላይ ወዳጂ እና ጠላት አድርጎ የመፈረጂ አባዜ ከራሱ ዉጭ አገሪቷ ችግር እና የዜጎች የመከራ ዘመን መራዘም እንደ ጊዜ መግዣ በማድረግ የሕዝቡን ዕሮሮ የቁራ ጩኸት እያለ ራሱን በራሱ ቁራ አድርጎ ይኸዉ አስከዛሬ ቀጥሏል፡፡

ዛሬ ላይ ስለ ሠላም አስፈላጊነት እና ጦርነት ክፋት ኢህአዴግ ሲናገር መስማት የተለመደ ቢሆንም ሌሎች ስለ ሠላም እና ጦርነት እንናገር የሚሉ ከየትኛዉም ቡድን፣ተቋም ሆነ ክፍል ሲናገሩ መስማት ግን እጂግ ያሳዝናል ፡፡

ለዚህም ኢህአዴግ የቀድሞዉን መንግስት ህዝባዊ መዋቅር በኢትዮጵያ ጠል አካላት ትብብር አፍርሶ ሽግግር መንግስት በሚል ሽግግረ -ኢህአዴግ ሲመሰርት የኢትዮጵያን ምሁራን ወክለዉ ከተገኙት ፕ/ር አስራት ወ/የስ እና መኮንን ቢሻዉ በቀር ያኔም ሆነ አሁን ያሉ እና የነበሩት እንደሚያወቁት  ትምክህተኛ ምሁር ተብለዋል፡፡

ይህም የሽግግር መንግስቱን ሲመሩ የነበሩት ሟች ያሉትን ይዞ ከላይ የተጠቀሱትና ሥራቸዉ ህያዉ ሆኖ የሚኖሩት ኢትዮጵያዉያን አገር ለማፍረስ ለመስማማት እና ሽግግር መንግስት ለመመስረት በለመስማማታቸዉ መድረክ ረግጠዉ እንደ ወጡ ስልጣንም ፣ጥቅምም ሆነ መኖር ሳያጓጓቸዉ ወደ ኋላ አለማለታቸዉን ታሪክ እና ትዉልድ አይዘነጋዉም ፡፡

እዚህ ላይ ሁላችንም መረዳት ያለብን ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ፣አብሮነት ፣ ሠላም እና የጦርነት አስከፊነት ለመናገር የህሊናም ሆነ የህግ ልዕልና ያልነበራቸዉ ከዚያ አስካሁን ለአገር እና ለህዝብ ሳይሆን ለቡድን እና ለግል ጥቅም የፖለቲካ ስርዓት አምላኪ እና ተላላኪ ድርጂቶች፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ዝም ብለዉ አገሪቷ እና ህዝቦች ከዚያ የሽግግር ጊዜ የኢትዮጵያ የጥልመት ዘመናት መባቻ ጀምሮ አስካሁን ያጨበጨቡ በአቋማቸዉ ቢቆሙ ይሻላል፡፡ በምንም መንገድ የሠላም እና የአንድነት ሀዋርያ ሊሆኑ አይችሉም ፡፡

ለዘመናት ዜጎች በተለይም ብዙኃኑ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል የሆነዉ የዓማራ ህዝብ በትዉልድ አገሩ ለሶስት አሰርተ ዓመታት በስደት ፣በሞት እና በዘመናዊ ባርነት የበይ ተመልካች ሲሆን አንድም ዓለማዊ ሆነ ኃይማኖታዊ ድርጂት ድርጊቲቱን በስሙ ጠርቶ መሞገት ቀርቶ ጉዳዩን ፍትኃዊ እና ተፈጥሯዊ አድርጎታል፡፡

ሠዉ በሰዉነቱ እና በማንነቱ ሲሞት ሠዉ ሞተ ተብሎ ሳይሆን …….ብሄረሰብ ሞተ ከማለት ዉጭ አንድም በህዝብ እና በአገር ሀብት የሚንቀሳቀስ የመገኛኛ ብዙኃን አስከዚህ ሠኣት ለህዝብ ጆሮ አድርሶ አያዉቅም ፡፡

ሌላዉ ቀርቶ ለሠዉ ልጆች ሠባዊ መብት መከበር እንሰራለን የሚሉ እና ገለልተኛ ተቋማት እንኳ ከዚኅ በኋላ ተመጣጣኝ ግድያ፣መፈናቀል….ይሁን ሲሉ እንጂ ይህ ጉዳይ የዚህ ተጠያቂነት ነዉ ብለዉ ከዳር ሲደርሱ አይታወቅም ፡፡ ለአስረጂነት በጥቂቱ የትናንቱን የ17 ልጆች ፣ የመንገድ ላይ ተፍኖ የቀሩት ዜጎች ምንነት እና ደህንነት የት ደረሰ የሚል ካለ ህዝብ ፊት ይቁም ፡፡

ዜጎች ስለ ሠባዊ ክብራቸዉ ፣ ስለ አገራቸዉ ፣ ስለ ህዝባቸዉ ፣ ስለ ማንነታቸዉ፣ ስለ ዕምነታቸዉ …..ለዓመታት ሲሳደዱ ፣ ሲዋረዱ ፣ሲታረዱ ፣ሲሞቱ……ከህዝብ እና ከአገር መከራ ፊት የቆመ አይደለም ለምን ያለ የማህበረሰብ ፣የኃይማኖት እና የፖለቲካ ድርጂት መሰረታቸዉ አገር እና ህዝብ ሆኖ በምን ቸገረኝነት እና በአድር ባይነት ማየታቸዉ ዛሬ ለምንገኝበት ዝቅጠት ምክነያት ከመሆን በላይ እንኳን የመከራ ቀንበር ተሸካሚ ህዝብ ሰይጣን ዕምነቱን እንደሚነሳቸዉ አይጠረጠርም ፡፡ ለምን ለሚል ለራሱ አገር እና ሠዉ የማይሆን ሠባዊ ፍጡር ለአጋንት ሊሆን አይችልም ፡፡

በድምሩ ዛሬ ስለ ሠላም ፣ ዕርቅ ፣ጦርነት የሚያወሩ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያዉቃቸዉ እና የሰለቻቸዉ መሆኑን ዕልፍ አዕላፍ ማስረጃዎች መኖራቸዉ መጥቀስ ሳያስፈልግ በዚህች አገር ላይ ደካሞችም ብዙኃን እና አገሬ ብለዉ የሚኖሩ እና የሚጮሁ ስለሆነ ጩኸታቸዉን መስማት እና ራሳቸዉን ለይቅርታ እና ለተጠያቂነት ማዘጋጀት አለባቸዉ ፡፡ እነማን ነበሩ በሰላማዊ መንገድ ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ ሲሉ ሲታገሉ ሲያታግሉ ዕድሜ ዘመናቸዉን ሲሳደዱ ፣ሲዋረዱ ፣ሲታሰሩ ሲፈቱ ኖረዉ የሞቱ ፤የተንገላቱ …..? ይህን ለትዉልድ እና ለታሪክ መተዉ ነዉ ፡፡

ሁላችንም ባለችን አንዲት አገር ተከባብረን እና ተብረን ለመኖር ብቸኛዉ እና ወቅታዊ መድኃኒት ዕዉነት እና ዕዉነትን ለመናገር እና ለመተግበር ድፈረት እንጂ ስብከት እና ብልጣብልጥነት የቀንድ አዉጣ ፖለቲካ ነዉ እና በቃን ስሙን ፤ተቀበሉን ብሎ ፈሊጥ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን አይጠቅምም፡፡

ሁላችንም  ፍርኃትን፣አድር ባይነት ፣ክፋትን ፣ምቀኝነትን እና ስግብግብነትን  በድፍረት በቃን አለማለታችን  የመከራ ጊዜን ከማራዘም ዉጭ የአገሪቷንም ሆነ የህዝቧን የመከራ ቀንበር ያጠነክረዋል እንጂ አይሰብረዉም ፡፡

የኃይማኖት ተቋማት ታላቆችም ሠወችንም ሆነ ጥቅም ማጣትን በመፍራት ሆነ በማዳላት ዝምታን አስካሁን መምረጣቸዉ መቆም እና ለህዝብ እና ለአገር በሚበጂ ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚሉበት ጊዜ አሁን ነዉ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

 

Allen!

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/184818

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...