July 16, 2023
T.G
በአሜሪካ (ካሊፎርኒያ ግዛት) ለሚሠራው ገዳም በእሸቱ ማህበራዊ ሚዲያ (ዶንኪ ቲዩብ) በመካሄድ ላይ ስላለው ዘመቻ ባለፈው ሳምንት (July 10) "ዛሬም ከአስቀያሚው ወለፈንዲነት (ugly paradox) ሰብሮ ለመውጣት አልሆነልንም!" በሚል ርዕስ አጨር ሂሳዊ አስተያየት ሰንዝሪያለሁ። ይህ የዛሬው ሂሳዊ አስተያየቴም ያንኑ የሚያጠናክርና ይበልጥ ግልፅ የሚያደርግ ነው።
በዚያኛው አስተያየቴ እንደገለፅኩት ጥያቄዬ በሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች እና የሃይማኖት መሪዎችንና አስተማሪዎችን ጨምሮ በአንዳድ በአድርባይነት ልክፍት በተለከፉ ወገኖች ምክንያት የገዛ አገሩ ምድረ ሲኦል ሆናበት ከወገን አልፎ ባእዳንን የእለት ምፅዋዐት በመማፀን ላይ ለሚገኘው መከረኛ ህዝብ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ መረባረብ ሲገባ በተሰኑ ሰዓታትና ቀናት ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ካልሰጣችሁን “በረከቱ ቀረባችሁ” በሚል ዘመቻ ላይ መጠመድ እንኳንስ ለተቀደሰ ሃይማኖታዊ እምነት ለሞራልም (ለሚዛናዊ ህሊናም) በእውን ይመጥናል ወይ? የሚል እንጅ ገዳምና ሌላም አገልግሎት ሰጭ ድርጅት አያስፈልግም የሚል በፍፁም አይደለም ።
ይህንን ካልኩ ወደ ዋናው የአስተያየቴ ክፍል ልለፍ፦ የዚህ ዘመቻ አባላት ሆይ ፦ በገዛ አገሯ የምድር ፍዳ የምትቀበለውን እናት፣ መልካም አባውራነት ወደ ሰቆቃ ህይወት የተቀየረበትን አባት፣ በመከራ ውስጥ ተወልደው በማያቋርጥ መከራ ውስጥ የሚገኙ ህፃናትንና ታዳጊዎችን፣ አኗኗራቸው ብቻ ሳይሆን አሟሟታቸው የከፋ እህትና ወንድሞችን፣ እና በአጠቃላይ የምድር ላይ ሲኦል ሰለባ የሆኑ ንፁሃን ወገኖችን በአንድ በኩል እና በሌላ በኩል ደግሞ የተጠመዳችሁበትን ፈፅሞ የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረትን የማይጠይቅ እጅግ አስቀያሚ የዶላር ውለዱ ዘመቻ ከምር በሆነ አይነ ህሊናቸሁ አጤኑትና ንስሃ ገብታችሁ እውነተኛው አምላክ ወደ የሚወደውና የሚባርከው ባህሪና ተግባር ተመለሱ!
በዚህ አይነት በእጅጉ የቅድሚያ ትኩረትን የሳተ አስተሳሰብና አካሄድ የሚገነባን ገዳም ማደሪያው የሚያደርግ እውነተኛ አምላክ ፈፅሞ የለምና እውነተኛ አማኞች ከሆናችሁ ልብ ግዙና ለመከረኛው ወገናችሁ የምትችሉትን ፈጥናችሁ አድርጉ!
እውነተኛው አምላክ የሚገኘው በእንዲህ አይነቱ የቅድሚያ ቅድሚያን ግድ በሚል የወገን ለወገን ርብርብ ውስጥ እንጅ የመከረኛውን ህዝብ የሰቆቃ ጩኸት እንደ ቁራ ጩኸት እየቆጠሩ እና የዳያስፖራን ማህበራዊና ሃይማኖታዊ ህፀፆች በእጅጉ እያጋነኑ ባህር ማዶ በሚያስገነቡት ዘመናዊ ገዳም ውስጥ ፈፅሞ አይደለም! አይሆንምም!!!
በማቴዎስ ወንጌል እንደተፃፈው ክርስቶስ ብራብ አበላችሁኝን? ብጠማ አጠጠችሁኝን? ብታረዝ አለበሳችሁኝን? ብታሠር ጠየቃችሁኝን? እንግዳ ሆኘስ አስተናገዳችሁኝን በሚሉ መሠረታዊና የቅድሚያ ቅድሚያን አስፈላጊነት በሚያሳዩ ጥያቄዎች አይደለም እንዴ ተከታዮቹን ያስተማረው?
መቼና የት ተርበህ፣ ተጠምተህ፣ ታርዘህ፣ ታመህ እና ታሥረህ አየንህና ነው? ብለው ሲጠይቁትስ እውነት እውነት እላችኋለሁ በሚል ሃይለ ቃል ለሌሎች ማለትም ለተራቡት፣ ለተጠሙት፣ ለታረዙት፣ ለታመሙት እና ለታሠሩት ምስኪን ወገኖች የምናደርገው ሁሉ ለእርሱ የሚደረግ እንደሆነ ነገረን (አስተማረን) እንጅ የመከረኛ ወገናችን ሸክም በስሙና ለስሙ በሚሠራ (በሚገደም ገዳም) መታደግ እንደሚቻለን አልነገረንም፤ አላስተማረንምም።
እናም አገርና ወገን ለማመን ቀርቶ ለማሰብም በእጅጉ በሚከብድ (በሚዘገንን) ሁኔታ ውስጥ በሚገኙበት መሪር ሁኔታ ውስጥ የቅድሚያ ቅድሚያ ሃላፊነትንና የውዴታ ግታን በአፍ ጢሙ ደፍቶ እጅግ በተሻለ የዓለም ክፍል የሚኖረውን ዳያስፖራ ማህበራዊና ሌሎች ችግሮችን እያጦዙ በማጋነን “ለባህር ማዶ ዘመናዊ ገዳም ማሰሪያ ያላችሁን ሳንቲም ሁሉ ካላረገፋችሁ በረከቱ ቀረባችሁ ፤ እኛም በወረፋ እየተኛን እንቀጥላለን እንጅ አንላቀቅም” የሚል ዘመቻ ከእውነተኛው አምላክ ፍላጎትና ፈቃድ ጋር ጨርሶ ግንኙነት የለውምና ልብ ያለው ልብ ይበል!!!
https://amharic-zehabesha.com/archives/184246
Tuesday, July 18, 2023
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment