Friday, June 9, 2023
ክፉዎችን የሚያስፈራዉ ዕዉነት ነዉ!
#image_title
አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡
ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡
ዛሬ በአገራችን ስለ ዕዉነት ብለዉ ለራሳቸዉ ፣ስለ ህዝቦች እና አገር ነፃነት ፣ ፍትህ እና ህልዉና የሚተጉ አስተዋይ እና ልባሞች በጠላትነት የሚያቸዉ መኖሩ በአገራችን የፖለቲካ ልማድ ነባር እና ተጠባቂ ነዉ ፡፡
ይህም በሀሰት እና ክህደት መኖሪያቸዉ ላደረጉት ምንግዴዎች አግሪቷ የግል ንብረት በማድረግ ሌላዉን ስለ ዕዉነት እና ፍትኃዊነት የሚቆሙትን በጠላትነት መፈረጁ የቆየ የፖለቲካ ታሪክ አካል ነዉ ፡፡
በኢትዮጵያችን የዕዉነት እና የነፃነት ጎህ አስኪቀድ ስለ አገር እና ህዝብ ያሉ ሁሉ ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ ካላቸዉ ነዲድ ፍቅር እና ክብር ሲሉ ከፍተኛ እና ትዉልድ የማይረሳዉ ዋጋ ከፍለዋል ፤ አልፈዋል ፡፡
ሆኖም አንዳንዶች ያለፉትም ሆነ በህይወት ያሉት ፍትህ ፣ መብት እና ነፃነት ከቀማቸዉ በምህረት እና በችሮታ እንዲመለስላቸዉ የሚጠብቁ ስለ እነርሱ ሁላችንም እናስባለን ፡፡
ለምን ሲሉ የእነርሱ የዋህነት እና ገርነት ከጠላት ጥርስ የሚገፋቸዉ እንጂ የሚታደጋቸዉ አለመሆኑን ባለመረዳት ለህዝብ እና አገር የጀመሩትን ጉዞ በጂምር እንዲቋረጥ በማድረግ በሚከተላቸዉ እና በሚያማናቸዉ መሪዎች መዘናጋት ተስፋ የሚያስቆርጥ ዉሃ ስለሚቸልሳ ነዉ ፡፡
ከዚህ ጋር መታየት ያለበት ፍትህን እና ነፃነትን በተግባር ለባለቤቱ አስከሚሆኑ ጊዜ ድረስ በፅናት እና በአንድነት ከመታገል ዉጭ ከነጣቂ እና ከአሳባቂ መጠበቅ ልክ ጉድጓድ ዙሪያ ሆኖ ገዳዩን እንደሚጠብቅ ቀበሮ ነዉ ፡፡
ብዙዎች ለአገር እና ለወገን አለኝታ የሆኑ ወንድ ልጆች (ጅግኖች) ይዘዉ የተነሱለትን ዓላማ ሃሳብ እና ተግባር ከዚህ በተቃራኒ ከቆሙት እና ባላጋራ ከሆኑት በዕርቅ እና በይሁንታ የሚዘልቁ መሆናቸዉን በመቀበል በአጭሩ የተበሉትን በተለይ ባለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት ታሪክ እና ትዉልድ ይቁጠረዉ ፡፡
እናም ዕዉነተኛ የህዝብ እና የአገር ወዳድ ዜጎች ለነፃነት እና ለፍትህ በምታደርጉት ፍልሚያ አገር እና ህዝብ ወድቀዉ ከሚገኙበት አረንቋ አዉጥቶ ለማሻገር የሚጥሩ የሚናገርትን እና የሚያደርጉትን በጎ ተግባር ከፍሬ ለማድረስ የታረቁትን ጠላት ማመን ይቅር ፡፡
እንደሚባለዉ "የታረቅከዉን ጠላት እና ዳግም የተቀቀለ ስጋ አትመን " የሚለዉን ኢትዮጵያዉያን ጀግኖች የመኖር ጉዳይ የሁሉም የኢትዮጵያ አንድነት እና ህልዉና በተጨባጭ አስኪረጋገጥ የሑሉም ኢትዮጵያዉያን ፍላጎት እና ምኞት ነዉ ፡፡ ስለዚህ በህይወት እና በዓላመ ፅናት ለምትገኙ ነገረት ግን ስማችሁን ለመጥቀስ አንዱን ካንዱ ማቀዳድም ስለሚሆን ስራችሁ እና ታሪክ የሚያዉቀችሁ እና የሚመሰክራላችሁ መሆኑን ስታዉቁ በምንም በማንም ጊዜያዊ ነገር ላለመዘናጋት በፅናት መኖርን ማስቀጠል ነዉ፡፡
"ጠላት አይተኛም ፤ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ሞቶም ከመግደል አይቆምም !"
"ለነፃነት፣ፍትህ እና ህልዉና የሚደረገዉ ጥያቄ እና ትግል በተጨባጭ አስኪረጋገጥ ድረስ መቀጠል አለበት ፡፡ "
"ሻሽ የጠመጠመዉ ሁሉ ቄስ አይደለም ፤ በቃ አንታለልም ፡፡ "
አንድነት ኃይል ነዉ !
Allen !
https://amharic-zehabesha.com/archives/183261
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment