Friday, June 30, 2023
ፀኃፊዉ ስማቸዉን ያልጠቀስኩት በፅህፋቸዉ ባሰፈሩት መጣጥፍ ላይ ስለሚገኝ እና ጊዜም ጉልበትም ላለማጥፋት ነዉ ፡፡
መነሻየ ፀኻፊዉ "የጥቅምት 2005 ዓ.ም.የአዲስ ራዕይ መፅሄት " ላይ ባካተተችዉ ሀተታ የክ/ዘመኑ ባለራዕይ እና አስደማሚ ስብዕና ባለቤት ባለችዉ ሟች የኢህአዴግ ሊ/መንበር መለስ ዜናዊ (ለገሰ ዜናዊ) ምን ዓይነት ሠዉ ነበር በሚለዉ ርዕስ በአንደኛ እና ሁለተኛ አንቀት በተጠቀሱት እና በተለይም ሁሉንም የሚወድ ፤ሉም የሚወደዉ በሚሉት አረፍተ ነገሮች ነዉ ፡፡
በዚህም አስተያየታቸዉ ሟች የሚጠሉት እንጂ የሚወዱት ስለነበር አንድም ቀን ስለሚወዱት በአንደበታቸዉ ተናግረዉ ም ተስምተዉም እንደማይተወቁ ይገልፃሉ፡፡
ርግጥ ነዉ ስለ ሟች ልዩ እና አይተኬነት በዚህም የተነሳ በሠዉ ልጂ ታሪክ ሠዉ ያዘነለት ፤ዕንባ የተራጨለት ፍጡር የለም መባሉ ለምን ይዋሻል ማለታቸዉ የሚያስማማ ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን የበደለዉን ፤የገደለዉን ቀርቶ በስሜት እና በደም ፍላት ነፍሱን ያጠፋዉን አንብቶ እና ተፀፅቶ አፈር ሳይመልስ ምግብ ዉኃ አይልም ፡፡ ይህም ከአዳም እና ሄዋን የሚነሳ ሠዉ ለዚያዉም ለዓርያ ስላሴ ወደ ዚህች ዓለም በዕንግድነት መጥቶ ወደ መጣበት ሲመለስ ማክበሩ "አስከሬን ይከበራል " በሚለዉ ተዉፊቱ ቆሞ ማሳለፍ ፤ አልቀሶ መሰናበት ሠባዊነትም ዕምነትም ይገኝበታል፡፡
ነገር ግን የሚጠሉትን እንጂ የሚወዱትን የመፅሄቱ አዘጋጆች ከየት አመጡት ለሚሉት ፀፊዉ ግር ያላቸዉ የኢህአዴግ መንፈስ አስካሁን ተፅዕኖዉ በተከታዮች እና በአባሎች ስለመኖሩ ልብ ካለማለት ነዉ ፡፡
ዛሬም በሟች ራዕይ በሚከተሉ ሠዎች ቁም ስቅል በምታይ አገር እና አሳሩን በሚከፍል ህዝብ የክ.ዘመኑ ሠዉ በሚሉ እና ከ.ዘመን ምን እንደሆነ በማያዉቁ ሰዎች በቁም ያመለኩትን ከሞት በኋላ ቢከተሉት ቢያመልኩት ከነበር ጣኦት አምላኪነት እንዴት ያንጊዜ ቀርቶ ዛሬ ላይ ሊወጡት ይችላሉ ፡፡
መወደዳቸዉን እና መዉደዳቸዉን ሁለንተናዊ አድረገዉ የወዳሉ ይወዳዳሉ ያሉ የሚወዱት ነገር ነበር ማለታቸዉ ስህተት ሊሆን የሚችለዉ በምን መለኪያ ይሆናል ፡፡
ሟች ከምርጫ ‘ 97 ዋዜማ ፣ ዕለት እና ማግስት የተናገሩትን ለሚሰማ የሚጠሉት ከሚወዱት ቢበዛም የሚወዱት ነበር ፡፡ ከህዝብ ልብ ዉስጥ እንዳልሆኑ ሌላዉ ቢቀር ከዚሁ ምርጫ ማግስት ከህዝብ ልብ መዉጣታችንን አረጋገጥን ብለዋል ፡፡ የራዕይ አዘጋጆች ግን ሁሉ የሚወዳቸዉ በሁሉ የሚወደዱ ካላሉ ከፊል አምልኮ ወይም ራዕይ የለም ለማለት ይመስላል ፡፡
በጥቅሉ የመፅሄቱ አዘጋጆች የታዘዙትን እንጂ ዕዉነቱን የማድረግ ያኔ ቀርቶ ዛሬ ስለማይችሉ ሁሉን ይወዳሉ ማለት ሲችሉ ሁሉ ይዳቸዋል ማለቱ ዕዉነት ሳይሆን ምትሃት ማስመሰል መልዕክት አስተላፊነት ሚና ብቻ ነዉ የነበረዉ ፡፡
ሆኖም የሚጠሉት ብቻ ላሉት ፀሃፊዉ ሟች ሑሉንም ይጠሉ ነበር ባንል እንኳ የሚጠሉት ነበር ካልን የሚወዱት ነገር አልነበረም ማለት እንዴት ይቻላል ፡፡
ጨለማን የሚረግም ብርኃንን ይፈልጋል፤ ብርኃንን የሚጠላ ጨለማን ይመኛል እና ብዙ ጊዜ ሟች ስለ ኢትዮጵያ ፣ ስለ ዓማራ ህዝብ ፣ ስለ ባንዲራ፣ ስለ ቤ/ክርስቲያን ፣ያለፉትን የኢትዮጵያ ስርዓተ መንግስት ፣ መሪዎችን እና በጎ ስራዎች ማንሳት ፤ማዉሳት አይደለም አንድም ቀን ከማክፋፋት እና ማጥላላት ሳይወጡ ከዚያ አስከ ዛሬ በማዉገዝ እና በመገዝገዝ የተለየ ነገር ከመናገር ዉጭ ማድረግ ሳይችሉ የነበረዉን ከመናድ ፤ከማካድ ሳይሻገሩ ለንስኃ የተሰጣቸዉን ጊዜ ሳይጠቀሙ ማለፋቸዉ የነበራቸዉ ዕይታ ከዚህ በተቃርኖ የሚመኙት /የሚሉት እንደነበር ከሚያመላክቱ ምሳሌዎች አንድ ህዝብ ወዳጂ ጠላት ፤ ጨርቅ እና ወርቅ ፣ ዓማራ ለማኝ ሆኖ የመናፈቅ ምኞት እና ፍላጎት፣ ባንዲራ ጨርቅ ነዉ፣ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጦር በትኖ የፓርቲ ጦር ማቋቋም…..ከዚህ በግልባጭ የሚወዱት ነገር የነበር ስለመሆኑ በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባር አተናል፣ሆነናል ….ዛሬም ላይ ዕዉን ሆኖ ዓለም ያወቀዉ ፀሃይ የሞቀዉ የገሀዱ ዓለም ዕዉነታ ነዉ ፡፡
አበዉ ክፉ ሞቶም ይገድላል እንዲሉ ዛሬም በሙት መንፈስ ህዝብ ሲያልቀስ አገር ሲማስ እያየን ነዉ ፡፡
እናም "ይመስላል ካሉ ይወለዳል አይገድም "እና አንድ ሠዉ የሚጠላዉ ካለ የሚወደዉን በግልባጩ ይፈልጋል ፣ይመኛል ፣ ይባዝናል ….እናም የሚወዱት አልነበርም አንልም ካልን እኛም ከሠባዊነት ዉጭ ልዩ ፍጡር እና ዘላለማዊ ማድረግ ነዉ እና የሚወዱትስ ብዙ ብዙ ነበር ፡፡
የሚወዱትም የሚወዳቸዉም ነበር ሁሉንም ይወዱ ፤ሁሉም ይወዳቸዉ ነበር ማስታወቂያ እንጂ መታወቂያ ሆኖ ሠባዊነታቸዉን ይገልፃል ማለት ሠባዊነትን መርሳት ስለሚሆን የዚያን ጊዜ የመፅሄቱ አዘጋጆች መብት ቢሆንም ዉሸት ቢደራረብ ነጠላ ዕዉነት አይሆንም እና ቢችሉስ የሚወዱትም የሚጠሉትም ነበር ብለዉ ቢያስካክሉት አሁንም ዕድሉ አለ ፡፡
በዓለማችን በጎ ሰሪዎች ስራቸዉ ቶሎ ሲረሳ በበጎ ስረቸዉ ለዘላለም ሲነሱ ስለመኖራቸዉ የሚያጠራጥርም አይደለም ፡፡ ክፉም የሰራ እንዲሁ በስራዉ ልክ ለዘላለም በታሪክ እና በትዉልድ ጅረት ሲዘከር እና ሲመረመር ይኖራል ምክነያቱም ክፉ ሠሪን ይቅር ማለት እንጂ ስራዉን መርሳት ስለማይቻል ፡፡ የሆነዉ ሆኖ ክፉን ለራሱ በጎዉንም ስራዉ ይከተለዉ ብለን ከትናንት እየተማርን ወደ ፊት መጓዝ ይገባል ፡፡
"አንድነት ኃይል ነዉ "
Allen
https://amharic-zehabesha.com/archives/184231
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment