Wednesday, May 24, 2023

ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ - ድምፅ አልባው ገዳይ በሽታ
#image_title

የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ምንነት

ሄፒታይተስ ከጉበት ኢንፍላሜሽን ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሲሆን፤ ከኤድስና ከቲቢ በሽታዎች የበለጠ ገዳይ እንደሆነ በስፋት ይነገርለታል።

የሄፓታይተስ በሽታ አይነቶች ብዙ ሲሆኑ፤ እንደ:- ሄፒታይተስ ቢ ሁሉ ሌሎችም አይነቶች አሉት። ሄፓታይተስ ኤ፣ ቢ፣ ሲ፣ ዲ እና ኢ ይገኙበታል።

በአጠቃላይ የሄፓታይተስ በሽታ በኬሚካሎች፣ አደንዛዥ እጾች በመጠቀም እና ከመጠን በላይ የአልኮል መጠጥ በመጠጣት ወይም በቫይረስ ሊመጣ ይችላል። ሄፓታይተስ ቢ የሚመጣው በሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ነው።

የበሽታው ምልክቶች

ብዙ ሰዎች በሄፓታይተስ ቢ ሲያዙ መጀመሪያ ምንም ዓይነት ምልክት አያሳዩም፤ ከእነዚህም መሃል አንዳንዶቹ ከብዙ ዓመታት በኋላ ጉበታቸው ይጎዳል ወይም የጉበት ካንሰር ይይዛቸዋል። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች የቫይረሱ “ተሸካሚ" የሚባሉ ሲሆን፤ ቫይረሱን ወደ ሌላ ጤነኛ ሰው ማስተላለፍ ይችላሉ።

የበሽታው ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታል:-

የቆዳ እና ዓይን ቢጫ መሆን (ጃውንዲስ በመባል ይታወቃል)

የሽንት መጥቆር

የፊት መገርጣት

የድካም ስሜት

የሆድ ህመም

የምግብ ፍላጎት መቀነስ

ማቅለሽለሽና ማስመለስ

የመጋጠሚያ (የአንጓ) ህመም ናቸው።

አንድ ሰው በሄፓታይተስ ቢ እንዴት ሊያዝ ይችላል?

የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ በበሽታው በተያዘ ሰው ደም፣ ጉበት እና የሰውነት ፈሳሽ ውስጥ ይገኛል። ሄፓታይተስ ቢ ተሸካሚ የሆነች አንድ ሴት ወይም እናት በእርግዝናዋ ወቅት ወይም በወሊድ ጊዜ ቫይረሱን ወደ ሕፃኑ ልጅ ልታስተላልፍ ትችላለች። በአውስትራሊያ ውስጥ ሕፃናት በሙሉ ከተወለዱ በኋላ የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ይሰጣቸዋል።

የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ እንዴት ይሰራጫል?

ንጹሕ ባልሆኑ የመርፌ መውጊያ መሳሪያዎች፣ በቀዶ ጥገና ሕክምና ወቅት፣ ጥርስ በሚነቀልበት ሂደት ውስጥ ወይም በንቅሳት (Tattoo) ጊዜ።

የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ያለው የሰው ደም ሲሰጥዎት። በብዙ አገራት ለሰዎች የሚሰጥ ማንኛውም ደም (Blood transfusion) ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ነፃ ለመሆኑ ምርመራ ይደረግለታል።

ሄፓታይተስ ቢ ያለው ሰውን እቃዎች ለምሳሌ ምላጩንና የጥርስ ብሩሹን (ደም ያለበት ሊሆን ይችላል) በመጠቀም።

ሄፓታይተስ ቢ ካለው ሰው ጋር ያለኮንዶም የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ለበሽታው ስርጭት አስተዋጽዎ ያደርጋሉ።

የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ምርመራ

ከዚህ ቀደም የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ይዞዎት እንደሆነ በደም ምርመራ ለማወቅ ይቻላል።

የደም ምርመራው ቫይረሱ ከሰውነትዎ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ እንደሆነ ያሳያል። ቫይረሱ ከሰውነትዎ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የተወገደ ቢሆንም የሄፓታይተስ ቢ አንታይ-ቦዲስ (በሽታ እንዳይዘን የሚዋጉ ፕሮቲኖች) በሰውነትዎ ውስጥ ይገኛሉ።

ምርመራው እስካሁን የሄፓታይተስ ቢ ተሸካሚ መሆንዎትን ካረጋገጠ ዶክተርዎ በድጋሚ እንዲመረመሩ ያዛል ወደ ስፔሻሊስት ዶክተሮች ክሊኒክ እንዲሄዱም ይጽፍልዎታል።

የሄፓታይተስ ቢ በሽተኛ ከሆኑ የሚከተሉትን በማድረግ ህመምዎን ማስታገስ ይችላል:-

አልኮል መጠጦችን መጠጣት ያቁሙ

የተመጣጠኑ እና ፋት ያልበዛባቸውን ምግቦች ይመገቡ

ሳያቋርጡ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

በሚደክምዎት ጊዜ እረፍት ማድረግ።

የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ መከላከያ መንገዶች

አንድ ሰው ሄፓታይተስ ቢ እንዳይዘው ምን ማድረግ ይኖርበታል?

ከአዲስ የተቃራኒ ጾታ ጓደኛ ወይም የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ካለወሰደ ሰው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲፈጽሙ ሁል ጊዜ ኮንዶም ይጠቀሙ።

መርፌዎች፣ ስሪንጆች ወይም አደንዛዥ እፅ መወጊያ ወይም መውሰጃ መሳሪያዎችን ከሌሎች ሰዎች ጋር በመጋራት አይጠቀሙ።

የጥርስ ብሩሽ ወይም ምላጭ ከሌሎች ጋር በመጋራት አይጠቀሙ።

መከላከያ ከሌለዎት የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ክትባት ይውስዱ፤ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ካለበት ሰው ጋር አብረው የሚኖሩ ሰዎች የሄፓታይተስ ቢ ክትባትን ማግኘት ይኖርባቸዋል።

የቫይረሱ ተሸካሚ ከሆኑ እናቶች የሚወለዱ ሕፃናት፤ ከተወለዱ በኋላ ሄፓታይተስ ቢ ኢሚኖግሎፕሊን መርፌ በመወጋት ተጨማሪ መከላከያ እንዲያገኙ ይሰጣቸዋል።

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ:
https://amharic-zehabesha.com/archives/182857

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...