Monday, May 1, 2023

ግራኝ አህመድ
#image_title

በተለምዶው ግራኝ አህመድ ተብሎ የሚታወቀው የጦር መሪ ሙሉ ስሙ ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ ሲሆን የኖረውም ከ1507 እስክ ታህሳስ 21፣ 1543 እ.ኤ.አ ነበር። በዘመኑ በእስልምና ሃይማኖት የኢማምነት ደረጃ የደረሰ ሲሆን የአዳል ግዛት ተብሎ ይታወቅ የነበረውን የጥንቱን የኢትዮጵያ ክፍል በመምራት እንዲሁም በዘመኑ የነበሩትን ነገስታት ከመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል እንዲያፈገፍጉ በማድረግ በታሪክ ይታወቃል።

በዚህ የተነሳ 3/4ኛ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ክፍል ለተወሰነ ጊዜ መቆጣጠር ችሏል። አንድ አንድ የታሪክ ተመራማሪዎችም የግራኝ አህመድ ሰራዊት ከሞላ ጎደል በሱማሌ ጎሳ ሰዎች ላይ ድሎችን በመቀዳጀቱ ምክኒያት በዚህ ስያሜ እንደጠሩት ይነገራል። ይህ መሪ ከ1529 እስከ 1543 ከነበሩት የመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል ነገስታት ጋር ጦርነት እንዳረገ ታሪክ ይዘግባል።

ጻህፍት ዘንድ እንደሚታመነው ግራኝ አረብ እንደነበር ሲሆን በሌሎች ታሪክ ተመራማሪወች ዘንድ ግን ሱማሌ እንደሆነ ነው። እንደ እስራኤላዊው የታሪክ ተመራማሪ ሃጋይ ኽልሪች ግን ግራኝ አህመድ ሱማሊኛ ቋንቋን እንደማይናገር አትቷል። በሌላ ሁኔታ ብዙ የታሪክ ጸሃፍት እና መረጃዎች ግራኝ አህመድ የሐረር ተወላጅ መሆኑን ጠቅሰዋል። ለግራኝ አህመድ እንቅስቃሴ አስተዋጾ ያደረጉ ነገዶች እንደ ኢሳቅ፣ ዳሩድ እና ማረሃን የተሰኙት የሱማሌ ጎሳወች ሲሆኑ ጎሳወቹ ግን በዘር ምክንያት ሳይሆን ያብሩ የነበሩት በሃይማኖት ተመሳሳይነት ነበር።

የኢማሙ ጉዞዎች

የኢማሙን በ18 ዓመት እድሜ የተገኘ ድል ሰምቶና ደንግጦ መናገሻ ከተማውን ሀረርን ጥሎ ወደ ሶማሊያ የሸሸው ሱልጣን አቡበክር ኪዳር (ኪዳድ) በምትባል ቦታ ተደበቀ። ኢማሙም በነካ እጁ በሙስሊሙ መካከል ጥላቻ እንዲስፋፋና ሙስሊሙ የአንድነት ሀይልና ወኔው እንዲነጥፍ ምክንያት የሆነውን ሱልጣን አቡበክር ለማጥቃት ወደተደበቀበት ከተማ ተጓዘ።

ኢማሙ ቦታው ላይ ሲደርሱም ሱልጣኑ ጦሩን አሰልፎ ጠበቃቸው። ሁለቱ ጦሮችም ዝሁር ወቅት ላይ ተገናኙ ኢማሙና ጓዶቻቸውም በኢስላማዊ ህብረትና ወኔ ማጥቃት ጀመሩ። በርካታው የሱልጣኑ ሰራዊት ተገደለ። ከፊሉም ሱልጣኑን ጨምሮ ሸሸ። ኢማሙ 20 አመት ሳይሞላቸው ሁለተኛውን ጦርነታቸውን በፍፁም ድል አድራጊነት ተወጡ። የሱልጣኑን መሸሸጊያ አወደሙ።

በዚህ ጦርነትም ኢማሙ 30 ፈረስና ሌሎች ቁሳቁሶችን ማረኩ። ነገር ግን ኢማሙ ሐረር ገብተው ብዙ ሳይቆዩ ሱልጣኑ ለቁጥር የሚያዳግት ሰራዊት እዛው ሶማሌያ ላይ ሰበሰበና ኢማሙን ለማጥቃት ወደ ሐረር ተመመ።

የሱልጣኑ ጦር በርካታ ፈረሰኞችን ያካተተ ስለነበር ኢማሙ የሱልጣኑን መቃረብ ሲሰሙ ስልታዊ ማፈግፈግን መረጡ። ከነጦራቸውም ወደ ሁበት ተጉዘው ጋረሙለታ ተራራ ላይ መሸጉ። ሱልጣኑም ሐረር ገባ። ኢማም አሕመድ በጋሪሙለታ ተራራ ላይ መስፈራቸውን የሰማው ሱልጣን ጦሩን ይዞ ሁበት ገባ። ተራራውንም ለቁጥር ባዳገተው ሰራዊት አስከበበው። ከፍተኛ ጥበቃም አደረገ።

የኢማሙ ጦር ከተራራው መውረድና ለህይወት መሠረታዊ የሆኑትን ምግብና የመጠጥ ውሀ ማግኘት አልቻሉም። ሱልጣኑ በዚህ ሁኔታ ለሁለት ሳምንታት ያህል ከበባውን አጠናክሮ ቀጠለ። በስተመጨረሻ ግን የኢማሙ ጦር ተዳከመና ተስፋ መቁረጥ ታየ። ስለሆነም በለሊት የኢማሙ ጦር ወርዶ ከሱልጣኑ ጋር ጦርነት ገጠሙ። ዳሩ ግን የኢማሙ ጦር ለ2 ሳምንት ታግቶ የቆየ በመሆኑ ውጊያው ላይ ቀልጣፋ መሆን አልቻለም። በመሆኑም የኢማሙ ጦር በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃ። ከአንጋፋ የኢማሙ የጦር አዝማቾች መካከል አንዱ ዑመረዲንም ተገደለ።

ኢማሙና ጥቂት ጓዶቻቸው ግን አመለጡ። የኋላ ኋላ ግን በዘመኑ ዑለማኦች ከፍተኛ ጥረት በሁለቱ አሚሮች መካከል ስምምነት እንዲኖር ተደረገ። ስምምነቱም ሱልጣኑ ሸሪዓን ሊጠብቅና በፍትህ ሊያስተዳድር ኢማሙና ጦራቸው ደግሞ መሸፈቱን አቁሞ ለሱልጣኑ ታዛዥ ሆኖ በሰላም እንዲኖር የሚያግባባ ነበር። ስምምነቱም መተግበር ተጀመረ። ኢማሙም ጥማታቸው የስልጣን ሳይሆን የሸሪዓ መጠበቅ መሆኑን ሰጥ ለጥ ብለው ለሱልጣኑ በመታዘዝ አሳዩ። በኋላ ግን ሱልጣኑ ስምምነቱን አፈረሰ።

ኢማም ግራኝ አህመድ የተወለደው ዘይላ ተብላ ትታወቅ በነበረው የባህር በር አካባቢ በሰሜናዊ ምዕራብ አዳል ( በአሁኑ ዘመን ሶማሊያ) ነበር። የአዳል ሱልጣኔት ይህ ታሪካዊ አዳል (ሶማሊያ) የእስልምና ሃይማኖትን የሚከተል መንግስት ይሁን እንጂ በጊዜ ለነበረ የክርስትና ተከታይ ኢትዮጵያው መካከለኛ መንግስት ግብር ይከፍል ነበር። ግራኝም በጎለመሰ ጊዜ ማህፉዝ የተባለን የዘይላ አስተዳዳሪን ልጅ ባቲ ድል ወምበሬ አገባ።ነገር ግን ማህፉዝ ከመካከለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ተጣልቶ በአጼ ልብነ ድንግል ላይ ጥቃት አድርሶ ሲመለስ በ1517 ተገደለ። በአዳል እርስ በርስ ጦርነት ተነሳ። ግራኝ አህመድም ከተወሰኑ የትግል ዓመታት በኋላ በስልጣን የሚሻኮቱትን በማሸነፍ ሐረርን ተቆጣጠረ። በዚህ ጊዜ የአዳል መሪ ሆነ።

የግራኝ ድል

በ1527፣ የአዳል መሪ ከሆነ በኋላ፣ ከአዳል ከትሞች የሚጠበቀውን ግብር ለመካከለኛው የኢትዮጵያ መንገስት እንዳይከፈል አገደ። አጼ ልብነ ድንግልም የባሌ ጦር አዛዡን ደግላን ግብሩን እንዲያስከፍል ላከ። ደግላን ግን በአዲር ጦርነት ተሸነፈ። ከዚህ ቀጥሎ ግራኝ ወደ ምስራቅ በመዝመት ሱማሌውችን በጦርነት ግዛቱ አደረገ።

ቀስ ብሎም ወደ ምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ብዙ ዘመቻወችን በማካሄድ ስፍር ቁጥር የሌላችቸው ባሪያወችን በመፈንገል በደቡብ አረቢያ፣ ለዘቢድ አስተዳዳሪ በስጦታ መልክ በመላክ በተራው የብዙ ጠመንጃወች ባለቤት ሆነ። በ1528 የልብነ ድንግል ሰራዊት በአዳል ላይ ጥቃት ስላደረሰ፣ ይህን ለመበቀል በ1529 በክርስትያኑ ንጉስ ላይ ኢማም አህመድ ዘመቻውን የኢትዮጵያና አዳል ጦርነት ጀመረ።

መሰረታዊው የኢማም አህመድ አላማ ግን "ጅሃድ" ወይም "በሃይማኖት መታገል" ነበር ። በዚህ ጊዜ የአጼ ልብነ ድንግልን ሰራዊት መምጣት የሰሙት የግራኝ ወታደሮች በፍርሃት ተውጠው ለመሸሽ ሲሞክሩ፣ ግራኝ ግን በጽናትና ቆራጥነት አብዛኞቹ ባሉበት እንዲቆሙ በማድረግ የልብነ ድንግልን ሰራዊት ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ደቡብ ምስራቅ በምትገኘው በሽምብራ ቁሬ ጦርነት መጋቢት 1529 አሸነፈ

የማሪያም መንገድ.com
https://amharic-zehabesha.com/archives/182144

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...