Monday, May 15, 2023
ዛሬ ላይ ዕዉነት የሚናገር እና ለዕዉነት የሚኖር በምድረ አበሻ በጥቂት እንኳ ለመኖራቸዉ ብቻ ሳይሆን ጥቂቶችን የሚጎዳ ነዉ ፡፡
ድሮ ድሮ "ዕዉነት ካልተናገርክ ዝም በል "ያሉት ማን ነበሩ የህንዱ የነፃነት አባት ታላቁ ማህተመ ጋንዲ ናቸዉ አይደለም እንዴ ?
ዕኮ ለምንድን ይሆን ዝም ማለት ስንችል ዕዉነት መናገር ሳንፈልግ ዉሸት ለመናገር መትጋትን ምን ይሉታል ፡፡
ይህን የክህደት እና ዉሸት ሸፍጥ የሞላበት መንፈራገጥ ለማለት ከላይ በርዕሱ ተመጣጣኝ እና አርበኝነት ምን እንደሆነ የሚነገሩት የሚለወጡት ወይም የሚታደሱት መቸ እንደሆነ የማይጠይቅ እንዴት ስለ አርበኝነት እና ተመጣጣንኝ ዕርምጃ ምንነት ለመናገር የሚዳዳዉ መኖሩን ስንሰማ ያማል ፡፡
ብዙ ጊዜ ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት በኢህአዴግ የስልጣን እና ንዋይ ምኞት በመጋረድ አገር እና ህዝብ የመከራ እና ጨለማ ዘመን ለማሳጣር ህዝብ ባደረገዉ የሞት ሽረት ትግል የነፃነት እና የመብት ጥያቄ ማንሳት ጥፋት ሆኖ ለሞት ሲዳርግ ለምን ማለት ሲቻል ተመጣጣኝ እርምጃ ነዉ አይደለም እያሉ በህአዝብ ቁስል እና በአገር ደህንነት የሚሳለቁ ብዙዎች ሆነዋል ፡፡
ለመሆኑ ሠዉ በሠዉነቱ ተፈጥሯዉ ማንነቱን ለማስከበር ለምን ሲል መግደል ፣ማግለል እና መበደል በምን መለኪያ ይሆን የሰባዊ መብት ተቋማት ተመጣጣኝ እርምጃ አይመስልም እያሉ ማለት ዕኮ እንዴት ፡፡
ሠብ ማለት ሠዉ ከሆነ ሠባዊነትም ለሠዉነት ከሆነ አንድ ሠዉስ በግፍ እና በኃይል ሲሞት ደረጃ እና መረጃ እየተጣቀሰ እና እየተነቀሰ ተመጣጣኝ መረጃ ማለት ድኃ እና ብዙኃን ሲሆን ይሙት ሌላ ሲሆን ስም ፣ ስልጣን እና ሀብት ለይቶ ማልቀስ የሚቆመዉ መች ይሆን ?
ላለፉት ሶስት ዓመታት በቀን ከሶስት ሞቶ በላይ ሠዎች ዜጎች በማንነታቸዉ ምክነያት በግፍ ሲገደሉ እና ሲፈናቀሉ ስለግለሰብ እና ስለ ሌላ አገር የምናነባ እኛ ለራሳችን የማናዝን በየጊዜዉ አገር እና ህዝብ ሲሞት ስለጥፋቱ ተመጣጣኝነት ጥናት ላይ ነን ፡፡
ከዚህም ሌላ ስለ አደዋ ፣ማይጨዉ ፣ ስለ ዳግም ኢጣሊያ የነፃነት ትግል እና ተጋድሎ ሲነሳ የየዘመናት የጦር አርበኞችን መዘከር እና መመስከር ከልብ ከሆነ የሚደገፍ ቢሆንም ትዉልዱ የሚነገረዉን የሚያስተጋባ ብቻ ሳይሆን በዘመኑ ለአገር እና ለህዝብ ዋጋ የከፈሉ የዘመን ጀግኖችንም ማወደስ እና ታሪክ ማደስ አለበት ፡፡
ለዚህም በሶማሊያ ወረራ በሶስት ወር ዝግጂት ለእናት አገራቸዉ ደም ፤ የአካል እና ሞት ዋጋ ለከፈሉት እና በህይወት ላሉት ፣ በባድመ ጦርነት ከፍተኛ ሚና የነበራቸዉ ፣ ከሁለት ዓመት በፊት በትህነግ ወረራ አገራቸዉን እና ህዝባቸዉን ከጥፋት ፣ ፍረሰት እና ሞት ለመታደግ ለህልዉና ትግል ከፍተኛ የትግል እና የአርበኝነት ዋጋ ለከፈሉት ኢትዮጵያዉን የድል እና የነፃነት ተጋድሎ መታሰቢያ ክብረ በዓል ቢደረግ እንዲሁም በትገህሉ ወቅት ህይወታቸዉ ላለፈዉ እና በህይወት ለሚገኙት ያአገር ባለዉለታዎች ክብር እና መታሰቢያ ሊኖራቸዉ ይገባል፡፡
የትናንቱን እየጠዉን የዛሬዉን እያዳፈን ስለ መቶ ዓመት በፊት የነፃነት ትግል እና የአርበኝነት ተጋድሎ ማቀንቀን አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ ስለሚሆን ለሁሉም ከመናገር ወደ ተግባር ማዘንበል ለአገርም ለህዝብም የሚበጂ ይሆናል ፡፡
አንድነት ኃይል ነዉ !
"በአንድነት እና በፅናት ዘብ መቆም የነፃነት ዋጋ ነዉ!"
https://amharic-zehabesha.com/archives/182550
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment