Thursday, May 25, 2023

በኢትዮጵያ "ኢህአዴግ አስካለ " የመከራ ቀንበር ይኖራል !
ኢህአዴግ ስል "የሞተዉን አያ ይለዋል " እንደሚለዉ የአገራችን ብሂል ከየት የመጣ ወይም የት ነበርክ  ብሎ አንዳንድ አንባቢ እንደሚደመም እገምታለሁ ፡፡

እኔ ግን ድሮዉንም ቢሆን ከዕባብ ቅርጫት ሙሉ ዕንቁላል ርግቦች እንዴት አሉ ብየ ተገረምኩ እንጂ ኢህአዴግ እንዳልተቀየረ ግን የዘመናት ብሄራዊ ችግር እና ብሄር መር ዘረኛ አገር እና ህዝብ ጠል ድርጂቱ  ኢህአዴግ እንደነበረ ከአንዱ ጉልቻ በቀር ድመት መንኩሳ….እንዲሉ ቆዳዉን ለዉጦ ፤አመሉን ዉጦ ከህዝብ ስሜት ጋር ማዋኃዱን ነዉ የምናዉቀዉ ፡፡

ኢህአዴግ በዉስጡ የፀነሰዉ በጥላቻ እና በስጋት የተረገዘ አግላይ እና በዳይ የፖለቲካ ትርክት በመሆኑ  ቆዳዉን ቀርቶ ቢጣድ የማይበስል የአህያ ጭንቅላት መሆኑ ካለመረዳት ሳይሆን ለራሱ ሲል በአገር እና በህዝብ ላይ ለሶስት አሰርተ ዓመታት ያደረሰዉን ፈርጀ ብዙ ጥፋት እና ክህደት አምኖ ህዝብን ይቅርታ ይጠይቃል ለዚህም ተገቢዉን የሞራል እና የቁሳአካል ካሳ የሚያደርግ ሆኖ ላደረሰዉ ወንጀል ህዝብ ምህረት አድርጎለት  አገሪቷን እና ህዝቧን ከጥፋት ለማዳን በሚደረግ ብሄራዊ ጥረት ከአናቱ  አስከ ቀርጭምጭሚቱ በንስኃ ታጥቦ መንገድ ይለቃል የሚል ግምት ነበር ፡፡

ዳሩ "ድመት መልኩሳ ዓመሏን አትርሳ" ሆኖ ለአመታት በብሄራዊ አንድነት ፣ በህዝቦች ሉዓላዊነት ፣ በዜጎች በአገራቸዉ ሰርቶ የመኖር ፣ በማንት ተኮር ጥቃት ፣ ስደት ፣ ማፈናቀል …በማፋፋም ቀጥሎበት ዛሬ ላይ ተደርሷል፡፡

ርግጥ ኢህአዴግ አስካለ  ግንቦት ፳ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓ.ም. ጀምሮ በአዋጂ የተተከለዉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን የማናጋት እና የማጥፋት ሴራ መቀጠሉ  ዕንግዳ ባለመሆኑ የሚገርም ባይሆንም ይህን የጥፋት እና የሞት አዋጂ እንደ ድል ቀን ተቀብሎ በዚህ ምክነያት በኢትዮጵያ ዳር ድንበር መደፈር ፣ በኢትዮጵያዉያን በጦርነት ፣ በርሀብ ፣ በግጭት ፣ በዘርፍጂት …በመሳሰሉት ወንጀሎች ራሱ ስርዓቱ ተጠያቂ መሆን ሲገባዉ እና በስርዓቱ ቸልተኝነት እና ይሁን ባይነት በማንነታቸዉ እንዲሞቱ ፣ እንዲሰደዱ ፣ እንዲፈናቀሉ ፣እንዲገለሉ….ወዘተ ለሆኑት የሠላሳ ዓመት ሰማዕታት መታሰቢ እንዲደረግ ባለመጠየቁ  ዛሬም ይህ ሠባዊ እና ብሄራዊ ጥፋት በዓይነት እና ፍጥነት  ዕጥፍ  እንዲቀጥል ፈቃድ ተሰጥቶታል ፡፡

በመጨረሻም በማንኛዉም መመዘኛ በተድበሰበሰ እና በጥገናዊ ለዉጥ የስልጣን ልዉዉጥ እና መገለባበጥ ካልሆነ በቀር የዚች አገር እና ህዝብ መከራ  እንደ ተራራ ሲገዝፍ እንጂ ሲቀረፍ ማየት የጨለማ ሩጫ ስለሚሆን ኢህአዴግ ከግንባሩ አስከ ስሩ ካልተመነገለ የአገር እና ህዝብ መከራ አለ ፡፡

ዕዉነተኛ  የኢትዮጵያ ትንሳኤ  ዕዉን ሚሆነዉ  በመገለባበጥ ለዉጥ ሳይሆን   በዕዉነተኛ  የዜጎች የነፃነት እና አንድነት ላይ የሚቃኝ ዕዉነተኛ  የለዉጥ እና ዕድገት ሀዲድ ብቻ ነዉ ፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ !

Allen .T. Selassie!

 

"In order to have real change that is progress, reform has to begin from the top and ends to the bottom.”

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/182909

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...