Wednesday, April 5, 2023

ለአቶ አዲሱ አረጋ አድርሱልኝ - ገለታው ዘለቀ

ለአቶ አዲሱ አረጋ አድርሱልኝ - ገለታው ዘለቀ
#image_title

አቶ አዲሱ ሆይ! ይህቺን ቁጥብ መልእክት የምልክልዎ በውነት ከልቤ እያዘንኩ ነው። እርስዎ ስለ ሩዋንዳ ያነሳሉ። ሩዋንዳ ውስጥ ወደ ስምንት መቶ ሽህ ሰው ካለቀ በኋላ ሩዋንዳ ወደ ነፍሷ ተመልሳ ዛሬ ወደ ልማት አተኩራለች።

እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎት አቶ አዲሱ::  እርስዎ የሚያማክሩት  አብይ አህመድ ስልጣን ላይ ከመጣ በሰሜኑ ጦርነት ብቻ አንድ ሚሊዮን ወገናችን አለቀ አይደለም ወይ? በወለጋ በየወሩ የምንሰማው እልቂት ሲደመር በብዙ ሽህ አማሮች አለቁ እኮ አቶ አዲሱ! ፣ በሶማሌና ኦሮምያ ግጭት መቶ ሽህ ሰው አለቀ እኮ አቶ አዲሱ! ቤንሻንጉል ውስጥ በነበረው ፍጅት ሽህ ሰው አለቀብን እኮ! በጉጂና ቡርጂ ውጊያ ብዙ ወገን አጣን እኮ፣ በጌዲኦና በጉጂ ጦርነት ሽህ ሰው አልቆ ሚሊዮን ተፈናቅሎብናል እኮ! ደብብ ውስጥ ባሉ የብሄር ግጭቶች እልፍ መፈናቀል እልፍ ስደት አየን እኮ፣ አብይ አህመድ ስልጣን ከያዘ በብሄር ግጭት የሞተውንና የተፈናቀለውን በእርሳቸው ቋንቋ ብንደምረው የሩዋንዳውን የእልቂት መጠን አልፈን ከሄድን ውለን አድረናል እኮ! እኛ ከሩዋንዳ የተለየነው እውነት ነው በየግጭቱ ለሞቱ ወገኖቻችን አጽም ማስታወሻ አልተውንም። እንደ ባህላችን እንደደ ወጋችን አልቅሰን አልቀበርንም። ምንድን ነው የሚሉት አቶ አዲሱ?   ሩዋንዳ ላይ ያልታዬ የአገዳደል ጭካኔ የታየው በዚህ ዘመን እኮ ነው፣ እንዴት ነው የዚህ ሁሉ የወገንዎ እልቂት ልብዎን ሳይሰብር ሩዋንዳ የሄዱት። ለመሆኑ አጽሙ እንኳን ያልተሰበሰበው ወገንዎ ኢትዮጵያዊ እንዴት አላሳዘነዎትም?

አብይ ይውረድ ፖለቲካዊ ለውጥ ይምጣ የምንለው እኮ ለዚህ ነው አቶ አዲሱ። ከሩዋንዳ በላይ ወገን ስላለቀብን ነው እኮ። ሚሊዮን ወገናችን ስለተፈናቀለ በደል ስለበዛ እልቂት ስለበዛ እኮ ነው! እናንተ ሰዎች ለመሆኑ ይሄ ሁሉ የሀገራችን ህዝብ እልቂትና መፈናቀል  እንዴት አላስደነገጣችሁምና ነው ስለ ሩዋንዳ የምታወሩት? አይበቃም ወይ?

አቶ አዲሱ ሆይ ስለዚህ አሁን የሚሻለው  አብይን ገለል አድርጉና የፖለቲካ ለውጥ አድርጋችሁ ለሁሉን አቀፍ የሽግግር ስርአት ሥሩ። ይህን ብታደርጉ ይሻላል። ይበቃል። በእርስ በርስ እልቂት ከሩዋንዳ የቀለጠ ኪሳራ አስመዝግበናል። በቃ።  ደግሞ በቃ ስንል እያስፈራራችሁ ሀገር አታፍርሱ። ውጥረት ላይ አትቆዩ ውጥረት አይቀጥልም። እባካችሁን እባካችሁን እባካችሁን...
https://amharic-zehabesha.com/archives/181586

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...