Tuesday, February 28, 2023
የዓድዋ ድል ክብረ በዓል የነፃነት እና የአንድነት ዓርማ ነዉ
በኢጣሊያ የወራሪዎች ቅዠት በዕብሪት እና በከንቱ ምኞት በምስራቅ አፍሪካ የታሪክ ፣ የስነ ፅሁፍ፣ የባህል ፣ የማንነት ባህል ፣ዕምነት እና ወግ ያላት የሰዉ ልጆች ምንጭ የሆነች ታላቅ እና የአምስት ሽ ዘመናት ስር መንግስት ያላት አገር መኖር ዕንቅልፍ የነሳዉ ለወረራ በሰሜን ሲገባ አደዋ (አምባላጌ) ላይ የሚጠብቀዉ የዉስጥ እና የዉጭ ቅጥረኛ እና ምንደኛ ባንዳ እንደነበር ማሳቡ ለሽንፈት ዳርጎታል፡፡
ይህም ጠላት ከነበረዉ ዝቅተኛ ግምት በላይ ዕምየ ሚኒሊክ እና የጊዜዉ ቅድመ አያቶቻችን በአገር እና በርስት የማይደራደሩ መሆናቸዉን ካለመረዳት ምሱን ሰጥተዉ ወራሪዉ ጠላት የሰበሰበዉን በትኖ በበቃኝ የተረፈዉ በዕግሬ አዉጭኝ በመጣበት ተመልሷል፡፡
ዕምየ ሚኒሊሊክ የጥበብ ፀጋ የተላበሱ ፣ ለሠዉ ልጆች ነፃነት በጨለማ ዘመን የደረሱ ፣ አርቆ አስተዋይ ለህዝባቸዉ ቀርቶ ለመላዉ የሰዉ ልጂ የነፃነት እና የመንፈስ አባት መሆናቸዉን ከዚያ አስከዛሬ አሳይተዉናል፡፡
ደግነት ፈጥኖ ይረሳል እንዲሉ የጀግንነት እና የደግነት ማማ ዕምየ ሚኒሊክ ታላቅ አገር አስረክበዉን ዛሬ ስራቸዉን አይደለም ስማቸዉን መስማት ይጓጉጠናል ፡፡
ዕዉነት ነዉ ክፉ ቀን ያወጣ ክፉ ቀን ይመስላል ነዉ ፡፡ ስለ ዕምየም ሆነ ስላለፉት የኢትዮጵያ ታላላቆች ለማለት ችሎታዉም ዕዉቀቱም የለኝም ግን አንድ ማለት ዕወዳለሁ ፡፡
ይኸዉም መቸ ነዉ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዉያን ብሎም ለአፍሪካ እና ለመላዉ ጥቁር ሠዉ ልጆች የነፃነት ቀንዲሎች በዕዉነት የሚዘከሩት ፡፡
የፖለቲካ ስርዓት የቡድን ዓመለካከት እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ እና ታሪክ አይለዉጥም ፤ አይተካም ነግር ግን በዓደዋ በዓል ማስታወቂያዎች ላይ የዕምየ ሚኒሊክ ምስል በኢህአዴግ ዓርማ መወከሉ ጥያቄ ሆኖብኛል ፡፡
ዕዉን ኢህአዴግ በ1888 ነበር ወይስ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ያለዉን አቋም ኢትዮጵያዉያን አያዉቁም ፡፡
ዕዉነት ኢህአዴግ ስለ አገር እና ህዝብ ቢገደዉ የኢትዮጵያን የቆየ ታላቅነት እና የረጂም ዘመናት ታሪክ በአንድ ሠዉ ዕድሜ ይቀነብብ ነበር ፡፡
ኢትዮጵያ ባንዲራዋ አረንጓዴ ፣ ቢጫ ፤ቀይ ሆኖ ሳለ በዕምነት ተቋማት ሳይቀር የድርጂት ዓርማ ካላየ የሚጨንቀዉ በአዳዋ የድል ክብረ በዓል የድርጂቱን አርማ እዩልኝ ማለት ዕዉነትም በ18ኛዉ ክ/ዘመን መጨረሻ ከዉጭ አፍራሽ ጠላቶች ጋር መፈጠሩን ለማሳየት ይሆን ፡፡
መፈጠሩን ካመነ በጊዜዉ በዓደዋ ጦርነት ጀግኖች ይዘዉት የነበረዉን የኢትዮጵያ ባንዲራ ዛሬ ላይ በማስታወቂያ ላይ ለማሳየት መስጋት አሁንም ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነዉ እና የኢትዮጵያ ባንዲራ ትዉልድ የሞተለት፤ ትዉልድ የሚኖርበት አረንጓዴ ፣ቢጫ ፣ቀይ ነዉ እና ዕምየም ኢትዮጵያዊ ፤አፍሪካዊ የነፃነት አባት ፤ የጀግንነት እና የአንድነት ምሳሌ ናቸዉ እና ቢቻልስ በአፍሪካ ህብረት እና በሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት አደባባይ ስማቸዉ ፣መስላቸዉ እና የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ ሊል ይገባል ፡፡
የትናነቷ አገር አሜሪካ የነፃነት አባት የምትለዉን ጆርጂ ዋሽንግተን የብሄራዊ ገንዘቧ መመሰል ፤ መዲናዋ መሰየም ለአፍሪካ እና ለኢትዮጵያ ሚኒሊክ ቢመለክ ምኑ ነዉ ስህተቱ የት ላይ ነዉ ፡፡
በመጨረሻም ዕምየ ሚኒሊክ የጥቁር ሠዉ ልጆች የነፃነት እና የሉዓላዊነት መንፈስ እንጂ እርሳቸዉም ሆኑ ኢትዮጵያ ከየትኛዉም ተቋም ወይም የፖለቲካ ድርጂት በፊት እና በላይ የነበሩ መሆናቸዉ ታዉቆ ኢትዮጵያ እና ንጉስ ሚኒሊክ ምልክታቸዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ባንዲራ ሆኖ ዕድሜአቸዉ ፭ ሽ ዘመናት የተሸገረ መሆኑን መርሳት ክህደት እንዳይሆንብን ሊታሰብ ይገባል ፡፡
አንድነት ኃይል ነዉ
Allen Amber
https://amharic-zehabesha.com/archives/180278
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment