Friday, February 24, 2023
ለቦረና ወገናችን መከታ እንሁን
ቀደም ባለው ጊዜ በስራ ምክንያት ቡርጂ አካባቢ አንድ አመት ቆይቻለሁ። ጉጂዎችንንና ቦረናዎችን በቅርብ አውቄ ጓደኝነት መሰርቼ ኖሪያለሁ። እኔም እንደነሱ ወተት ወዳድ ነበርኩና ቅዳሜ ቅዳሜ ይዘዋት የሚመጧትን የቅል ወተት ለእኔ ለማቀበል አይኖቻቸው ሲንከራተቱ የማያቸው ጉጂዎችና ቦረናዎች ነገር ዘወትር ከህሊናዬ አይጠፋም። እኔ ኦሮምኛ አልችልም። እነሱ አማርኛ አይችሉም። ነገር ግን የሰው ልጅ ፍቅር ካለው የሚግባባበት ሌላ የሆነ ረቂቅ ነገር ያለው ፍጡር ነወ።
ቦረናና ጉጂ ህይወታቸው ከብቶች ናቸው። እነዚህ ህዝቦች ለዚህ ምድር ኑሯቸው የሚሿት ትንሽ በቆሎና ወተት ነው። ወተት ምግባቸው ብቻ ሳይሆን ጌጣቸውም ነው። ስለዚህ ይህንን ህዝብ ረሀብ ላይ እንዳይወድቅ የድርቅ ምልክት ሲታይ የከብት መኖ እርዳታ ነው የሚያሰፈልገው። ቦረና ላሙ ከሞተች የሱም ህይወት አይቀጥልም። ለዚህ ነበር ቀደም ባሉት ወራት አደጋ መከላከል ላይ የምትሰሩ ወገኖች ለዚህ ወገን መኖ አግዙት እያልን ስንጮህ የነበረው። መኖ ከምድረ ኢትዮጵያ አልጠፋም ነበር። ሌላው ቀርቶ ብዙ ስንዴ አምርተናል የሚሉ ወገኖች ለዚህ ህዝብ ገለባውን ቢያቀብሉት ከየቤቱ ሁለት ላም ቢተርፍ ያ ህዝብ ይተርፋል። አሁን ነገሮች ከፍተው ወገናችን ተርቧል። አሁን አርብቶ አደሩ ረሀብ ላይ ነው። መወቃቀሱ ለታሪክ ይቀመጥና አሰቸኳይ እርዳታ እናድርግ።
እርዳታውን እንዴት እንላክ?
በግለሰብና በቡድን መሞከሩ ውጤታማ አይሆንም። የሚሻለው ከዚህ በፊት በእርዳታ ስራ ልምድና ኔት ወርክ ያለውን ግሎባል አሊያንስን እንደግፍ። ዛሬ ይህንን ደብዳቤ ስጽፍ ወደ ግሎባል አሊያንስ መሪ ደውዬ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ እንደመከሩበትና ጎፈንድ ሊከፍቱ እንደ ሆነ ገልጸውልኛል። ሰለዚህ ሁላችንም በዚያ በኩል እናግዝ። ሌሎች አካባቢዎችም በተለይ ደብረ ብርሀን ከፍተኛ ተፈናቃይ አለና በዚያም በኩል ለወገን እንድረስ። እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ ይጠብቅ። አሜን።
ገለታው ዘለቀ
https://amharic-zehabesha.com/archives/180172
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment