Saturday, January 14, 2023

ጥር 6 ቀን - የመይሳው ካሳ የልዴት ቀንና የአሁኗ ኢትዮጵያ በአንክሮ ( እውነቱ ቢሆን)

ጥር 6 ቀን - የመይሳው ካሳ የልዴት ቀንና የአሁኗ ኢትዮጵያ በአንክሮ  ( እውነቱ ቢሆን)
ዛሬ ጥር 6 ቀን መንጋ የብልጽግና ሆድ አደሮች፣ ተረኞችና  የወያኔ ውርጋጦች  የሚያላግጡባትን ታላቋን ኢትዮጵያ ከገነገነ የመሳፍንት አገዛዝ አውጥተው አንዲነቷ የተጠበቀ ዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን ያደረጉት ታላቁ ንጉስ አጼ ቴዎድሮስ የተወለዱበት ቀን ነው፡፡ በጀግንነት ስማቸው "መይሳው ካሳ" ተብለው የሚታወቁት አጼ ቴወድሮስ የተወለዱት ጥር 6 ቀን 1811 ዓም ነበር፡፡ የመሳፍንት አገዛዝን አፍርሰው አገሪቱን አንድ ካደረጉ በኋላ በዚያ ዘመን በጠላቶቿ እጅ ወድቃ የነበረችውን እስራኤልን ከጠላቶቿ ለማስለቀቅ መርከብ ለማሰራት አቅደው የነበሩት ታላቁ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንጉስ አጼ ቴወድሮስ ለዚህ ውጥናቸው ህዝቡ እንዲህ ሲል ግጥም ገጥሞላቸዋል፡፡

ታጠቅ ብሎ ፈረስ ካሳ ብሎ ስም


ዓርብ ዓርብ ይሸበራል እየሩሳሌም

የአሁኑ ዘመን ወጣቶች የንጉሱን ታሪክ ለመመርመር ይረዳቸው ዘንድ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ቴወድሮስ አደባባይ ያለውን መታስቢያቸውንና ሊያሰሩትም አስበው የነበረውን "መድፍ " አይቶና መርምሮ ለአገራቸውየነበራቸውን ህልምና የስልጣኔ አሻራቸውን ምን ያህል ከፍተኛ እንደነበረ መረዳት ይችላል፡፡

ስለ ንጉሱ ታሪክ፣ ስለእንግሊዞች ወረራ፣ እንግሊዞችን እስከመቅደላ ድረስ ማን መርቶ እንዳመጣቸው፣ ለባንዳወቹ በዉለታ  እንግሊዞቹ የሰጧቸው ምን እንደነበረ፣ ንጉሱ ለአገራቸው ክብር ሲሉ እጃቸውን ለእንግሊዞች ሳይሰጡ ሽጉጣቸውን ጠጥተው እንደሞቱ፣ ስለምርኮኛው የንጉሱ ልጅ ስለ ልዑል አለማየሁ ቴወድሮስ፣ ምርኮኛው ልዑል በያኔዋ የእንግሊዟ ንግስት እንዴት እንዲያዙ እንደተደረገ፣ መቅደላ ላይ ከንጉሱ ጸጉር ተቆርጦ ወደ እንግሊዝ ተወስዶ ስለነበረው ቆንዳላቸው ......ወዘተ ብዙ ታሪካዊ እውነቶችን ማወቅ ይችላሉ፡፡

አጼ ቴወድሮስ መቅደላ ላይ በነበረው ዉጊያ  የቀኝ እጃቸው የነበረው ገብርዬ እንደወደቀ ሲያዩ አልሸሽም ብለውና እጃቸውንም ለእንግሊዝ ጦር ሰጥቼ አልማረክም ብለው በጀግንነት ሽጉጣቸውን ጠጥተው በኩራትና በክብር ለአገራቸው ሞተዋል፡፡ ንጉሱን ለመያዝ በባንዳወች እየተመራ መቅደላ ድረስ የመጣው የእንግሊዝ ጦር መሪ ንጉሱን በህይወት ሳይማርካቸው በመቅረቱና ይልቁንም ራሳቸው ሽጉጣቸውን ጠጥተው እንደወደቁ በተመለከተ ጊዜ በህይወት ሳይማርካቸው በመቅረቱ ቢያዝንም በንጉስ ደረጃ ሆነው ሽጉጣቸውን ጠጥተው ክብራቸውን ለአገራቸው በመስጠታቸው በድርጊታቸው እጅጉን ተድንቋል፡፡ ይህም በስፋት በውጭ አገራት ተዘግቧል፡፡ ለዚሁ በንጉስ ደረጃ ተሁኖ ለተወሰደ ወደርየለሽ  ጀግንነት አዝማሪ እንዲህ ሲል ግጥም ገጥሞላቸዋል፡፡

መቅደላ አፋፉ ላይ ጩሀት በረከተ


የሴቱን አላውቅም ወንድ አድንድ ሰው ሞተ

የንግስና የዘር ግንድ የሌላቸውና የኮሶ ሳጭ ልጅ ስለነበሩት ስለቋራው ካሳ ማለትም አጼ ቴወድሮስ ታሪክ የውስጥም ሆነ የውጭ አገራት የታሪክ ድርሳናት ይህንኑ እውነታ በሰፊው መዝግበው ይዘውታል፡፡ ይህንን የመሠሉ አያሌ መስዋእትነት ተከፍሎባት የጸናችን አገር በማፈራረስ ላይ ያሉት የአሁኖቹ ወፍዘራሾችና ተረኞች ያኔ የት እንደነበሩ ማስረጃችውን ማቅረብ ግድ ይላቸዋል፡፡

የአሁኑ ትውልድ መላው ጠፍቶታል፡፡ ሌላ አገር እንዳለው ሁሉ በመናኛ የገዥወች ጥቅሞች እየተታለለ አገሩን እያጠፋ ያለ ትውልድ ሆኗል፡፡ አገር ከጠፋች አትመለስም፡፡ አገሮች ፈርሰው ህዝቦች ማንነታቸውን አጥተው አይተናል፡፡ አገርየለሽ መሆናቸውንም ሰምተናል፡፡ በእኛም አገር የዚሁ ጅማሮ የሆነውን የአገርየለሽነቱን ሂደት ከአሁኑ ምን ያህል የመረረ እንደሆነ እያየነው ነው፡፡

በሰላምና በእኩልነት ተስማምቶ መኖር የሚቻልባትን አገራችንን ኢትዮጵያን እየበታተንናት ነው፡፤ ሁኔታወች አሁን በሚታየው ሂደት ከቀጠሉ 100% እርግጥ ሆኖ መናገር የሚቻለው በኢትዮጵያዊነትን መቃብር ላይ ኦሮማዊነትን መትከል እንደማይቻል ነው፡፡

እቅጩን እናፍርጠው፡፡ ይህ የተረኞቹ ህልምና ቅዠት ሆኖ ይቀራል እንጅ ኦሮሙማ የበላይ ቀሪውወይንም የተወሰነው  ኢትዮጵያዊ የበታች ተሁኖ የሚኖርባት ኢትዮጵያ አትፈጠርም፡፡ የፈለጉትን ውሸት ቢዋሹ፣ የፈለጉትን ማስመሰያ ቢጠቀሙ ያሻቸውን ‘’CONVINCE and/or CONFUSE’’  ዘዴያቸውን  ቢጠቀሙ (ፖለቲከኞችን ላኩም) ህዝቡን ማታለልና ማጭበርበር  አይሳካላቸውም፡፡ ህዝቡ ስለሁኔታወቹ በሙሉና በነቂስ  ከሚገምቱት በላይ ያውቃል፡፤ ከሚገምቱት በላይ ግፍ አንገሽግሾታል፡፤ ከሚገምቱት በላይ ድሉን በእጁ ለማስገባት ቆርጧል፡፡

በአብይ አህመድ በሚዘወር ያልበሰለና የጨነቀረ የተረኝነት ስሌትና የተበላ ቁማር ሁሉም ግልብጥብጥ ብሎ ብትንትኑ ይወጣል እንጅ አገር አትጸናም፤፡ በአጭሩ ካልታረሙ አገሪቱ ፈራርሳ ለማንም ሳትሆን ትቀራለች፡፤ እንዲያውም ይህ ከሆነ ችግሩ ይብሱኑ የሚበረታው እኔ የበላይ ልሁን በሚለው የጅሎቹ “ኬኛወች” መንደር ይሆናል፡፡

ያኔ ዳግማዊ አጼ ቴወድሮስ ይፈጠሩ ይሆናል፡፡  በአሁኑ”እኛ ኬኛወች ብቻ” ወይንም “እኛ የታላቂቱ ትግራይ ህልመኞች” ብቻ  አሸናፊ ሆነን እንወጣለን የሚለው ሀሳብ አንዲት ኢንች አያራምድም፡፡ ሀሳብ ብቻ ሳይሆን ቅዠት ሆኖ መክኖ ይቀራል፡፡

 

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/178784

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...