Saturday, January 7, 2023

በአዲስ አበባ ላይ ስለሚካሄደው የተረኞቹ እራት ማብላትና .ማእድ መጋራት…ወዘተ የስልቀጣና ዘረፋ ስልቶች
እውነቱ ቢሆን

ከሁሉ በፊት ስለ አዲስ አበባ ከተማ ማወቅ ያሉብን ጥቂት ሀቆችን እንገንዘብ፡፡ ጥንት አዲስ አበባ የዳዊት ከተማ ነበረች፡፡ ስሟም በረራ ይባል የነበረ ሲሆን በእርስትነትም የአማራው ነበረች፡  በታሪክ ሂደቶች መተካካት የአሁኗ አዲስ አበባ ከተማ የአገሪቱ መዲና ከመሁኗ በተጨማሪ የአገሪቱ የፖለቲካ ሙቀት መፍለቂያና የየወቅቶቹ የፖለቲካ ትኩሳት መለኪያ ሆና ሰርታለች፡፡እየሰራችም ነው፡፡  በጊዜ ብዛትም እያደገችና እየተመነደገች ሄዳ ከየትኛውም የአገሪቱ ክልሎች በላቀና በበለጠ ደረጃ የአገሪቱ ከፍተኛ የገቢ ማፍለቂያና መሰብሰቢያ ለመሆን በቅታለች፡፡ አሁን በአዲስ አበባ መስተዳድር ውስጥ ከ6 ሚሊዮን ህዝብ በላይ አዲስ አበቤ የሚኖርባት ከተማ ሆናለች፡፡

ስለ አዲስ አበባ ከተማ ይህንን ካልን በአሁኑ ጊዜ በተረኞቹ ኦሮሙማወች በከተማዋ ላይ ስለሚከናውነው ዘረፋና የከተማዋ ጭፍለቃ/ስልቀጣ ጉዳይን በአጭሩ ወደሚዳሰስው ርእሳችን እንመለስ፡፡

ለገና በአል ፣ ለፋሲካ ፣ለአዲስ አመት ለመውሊድ ለምናምን.... ወዘተ ወዘተ ቀናቶች ከንቲባ አዳእች አበቤ "" ምሳ ማብላት፣ ማእድ መጋራት፣ ተማሪወችን መመገብ፣ አብሮ መብላት... ወዘተ ወዘተ እየተባለ 292 ሚልዮን ብር፣ 600 ሚሊዮን ብር ፣ 2 ቢልዮን ብር  .....ወዘተ ወዘተ ወጪ ተደርጎ ከንቲባዋ አንድ ሽህ ሰወችን ፣ 5 ሽህ ችግረኞችን ፣አረጋዊያንን፣ ሁለት መቶ ሽህ ....የከተማዋ ድሀ ነዋሪወችን፣  የእኔ ቢጤወችን . ተማሪወችን  ….ወዘተ ወዘተ አበሉ፣ አብረው  ምግብ ተቋደሱ .....ወዘተ ወዘተ ተብሎ ይነገራል፡፡ ይዘመራል፡፡

በዚህ መሰሉ  ሰበባ ሰበብ ለከተማዋ ነዋሪወች, ተማሪወች, ችግረኞች፣ የእኔ ቢጠወች.....ወዘተ ወዘተ   እየተባለ በተለያዬ መልኩ ከከተማዋ ነዋሪወች  የሚሰብሰበው የህዝብ ገንዘብ  ይዘረፋል፡፡  ደጋግሞም ይዘረፋል፡፡  አሁንም ዘረፋው አላቆመም፡፡ የሚዘረፈው ገንዘብ በብዙ መቶ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ሲሆን ዘረፋው ከራሳቸው ከተረኞቹ ዘራፊ ሽመኞች አልፎ ከህዝቡ ካዝና ወጥቶ ድግሱን ለሚያዘጋጁት የተመረጡ ተረኞችና ሌሎች ጥቅመኞች እንዲጠቀሙበት ጭምር  እየተሰራበት ነው፡፡

የተራበን ማብላት፣ የታረዘን ማልበስ የተጠማን ዉሀ ማጠታት አግባብም፣ ሞራላዊም ባህልም ነው፡፡ ነገር ግን በሰበብ እየዘረፉ፣ ሰበብ እየፈጠሩ የህዝብ ገንዘብ እየመዘበሩ መሆን የለበትም፡፡ አንዲትም ሳንቲም የህዝብ ገንዘብ ታስጠይቃለችና፡፤ በመሰረቱ የህዝብ ገንዘብ ቂጥኝ ነው፡፡ በሽታ ነው፡፡ ያስጠይቃልም፡፡

ፍሬ ነገሩ ተማሪወች አይመገቡ አይደለም፡፡ ምን ይቅደም ነው፡፡ ጡረተኞች አይረዱ አይደለም፡፡ ስአት ይያዝ ነው፡፡ ለከተማዋ ለብዙሀኑ ምን ችግር ቅድሚያ ይሰጠው ነው፡፤ የትናው ችግር ሚዝን ይደፋል የትናው ጉዳይ የብዙወችን ችግር ለማቃለል ቀዳሚ ይሁን ነው ጉዳይ፡፡ በህግ ይመራ ነው ጥያቄ ያስነሳው ጉዳይ፡፤ ኢንስቲቲዩሽኖችን በህግ አቋቁሞ በሀቅ መስራት ሳይቀድም በሰበባ ሰበቡ በቢሊዮኖች የህዝብ ገንዘብን ያውም በዘረኝነትንና ተረኝነትበተጨመላለቀ መንገድ ተቧድኖ የህዝቡን ገንዝብ ሀብትና መረሬት መዝረፍ አንድም ወንጀል ነው ሌላም ነውር ነው፡፡ ስለሆነም ያስጠይቃል፡፡ ይህ ነው የጉዳዩ ማጠንጠኛ፡፡

አዳነች እቃ ናት፡፤ እቃነቷንም ተረኛው ኦሮሙማ አሳምሮ እየተጠቀመበት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሴትዮዋ በአንጻራዊ ትንንሽ መጠን ያለው  ጉቦ ከምትበላበት አገር ውስጥ ገቢ መስሪያ ቤት ሀላፊነቷ ተነስታ ብዙ ወደምታስበላበት በከንቲባነት ቦታ  አዲስ አበባ ላይ ባእውሬው አብይ አህመድ ከንቲባ ተደርጋ እዚያ የተሾመችው፡፡

አዳነች አበቤ  ለከተማዋ እድገትየሚበጁ፣ ቁልፍ የሆኑና በህዝቡ ህይወትና በከተማዋ እድገቶች ላይ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን የሚፈታ አንድም ፕሮጀክት የላትም፡፡ አንድም ችግር አልፈታችም፡፡  በመሰረቱ የከንቲባነት ችሎታም እውቀትም ዝግጁነትም የሌላት ሴት ነች፡፤ እርሷ የአሩሲዋ እመቤት ከዳሚነቷ ላይ ተወዳዳሪ የሌላት ከዳሚ ነበረች፡፡ አሁን ላይ በአሩሲዋ እመቤት ከዳሚነት ምትክ የኦርሙማ ሹመኞች ከዳሚ ሆናለች፡፡  አሁን ባለችበት ቦት ላይ ሆና  በደንብ አድርጋ የኦሮሙማን መንጋ እየመገበች ነው፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ የአንድ ከተማ ከንቲባ የህዝቡን ተመራጮች ፈቃድ ሲያገኝና  ህግ በሚፈቅደው የከተማዋ አሰራር /ቻርተር/ መሰረት ስራወቹን ይፈጽማል እንጅ በራሱ ፍላጎት፣ ከህግ ውጭ ከከተማዋ መመሪያና ደንብ ውጭ ከመስተዳድሩ ተመራጮች እውቅናና ፈቃድ ውጭ በራሱ ቅንጣት ነገር መፈጸም አይችልም፡፡ ይህ የሚሆነው ግን ህግ፣ ስርአትና  ነጻና ህዝባዊ ተጠያቂነት በተረጋገጠበት መዋቅር/ አስራር ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር አሁን ላይ የተረኞቹ ኬኛወች  መጨዋቻ ሜዳ ህኗል፡፤ ዝረፍ እንዝረፍ ነው፡፡

አዳነች አበቤ ለከተማዋ እድገት ሳይሆን ለከተማዋ ውድቀት በተረኝነት ተግታ የምትሰራ አንድት ዘረኛ ሴትዮ በአብይ አህመድ አዲስ አበባን ለምታክል ከተም  ""ከንቲባ"" ተብላ መሾም አልነበረባትም፡፡ ሴትዮዋ ከላይ እስከታች ተደበላልቃለች፡፡ በከተማው ግብር ከፋይ ገንዘብ ሆነ እንጅ መደበላለቋ የራሷ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን  የግብር ከፋዩ ህዝብ ገንዘብ  በአውሬው አብይ አህመድ ተሹማ በራሷ ፍላጎት  የምታባክነውና እንደፈለገችው የምታዝበት ሊሆን ፈጽሞ አይፈቀድም፡፤ ያስጠይቃል፡፡ ሁለቱንም!!!አብይም ሆነ አዳነች በአዲስ አበባ ላይ እየሰሩት ያለው ወንጀል በሙሉ በሰነድ ተሰንዶ ተይዟል፡፤ መጠየቅ አይቀርምና ያስጠይቃል፡፡

ሰው ተኮር ፕሮጀክት ተብሎ የተወሰኑ ሰወችን ማብላት የተወሰኑ ሰወችን ቤቶች ማደስ የተወሰኑ የታይታ ፕሮጀክቶችን ላይሰሩ አቅዶ ሚደያ ላይ ማውጣት  ስራ መስራት ማለት  አይደለም፡፤

ከከተማዋ 6 ሚሊዮኑ ነዋሪ  ህዝብ ውስጥ ከ5 ሚሊዮን በላይ የሆነው ነዋሪ  በቀን ስንት ጊዜ ይበላል?? ከዚህ ውስጥ 200 ሽህ ሰወችን መርጦ እራት አብሮ መብላት ምን ማለት ነው??? ነዋሪን ምገባ ማለት ይህ ነውን?? ስንቱ ነዋሪ ዉሀ/መብራት ሳይቆራረጥ በየቀኑ ይደርሰዋል? ስንቱ ነዋሪ መጸዳጃ ቤት አለው?? የከተማዋ ትራንስፖርት ችግር የት ላይ ነው? የከተማዋ ገበያና ግብይት ሁኔታ የት ደረጃ ላይ ይገኛል??  መንገዱስ፣  ጸጥታውስ የጤናስ ጉዳይ  ወዘተ ወዝተ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆን ነበረብባቸው፡፡

ዘራፊዋ አዳነች የቱን ሰራች? ለየቱ የማጭበርበሪያ ርእሶች ስንት ቢሊዮን ብር አውጥታ ስንቱንስ ወደኪሷ ወሰደች?? ስንቱን በዘረፊወች አማካይነት እንዲባክንና እንዲዘረፍ አመቻቸው? ስንቱንስ አዘረፈችው?  ስንቱንስ ለተረኞች ሰጠችው? ምንስ አደረገችው?? ይህ ገንዘብ የእርሷ ነውን?? ይህ ወንጀል አይደለምን??

ሁሉንም ያደረገችው አውቃና ፈቅዳ ወይንም በአብይ አህመድ አድርጊ ተብላ ታዝዛ ስለመሆኑ ውስጡን ለቄስ ነው፡፡  እነዚህም ድርጊቶች ጸረ ህዝብ ድርጊቶች ናቸው፤ ሌብነቶችና ዘረፋወች ናቸው፡፡ድርጊቱ ከላይ እስከታች ያሉትን በኦሮሙማ ኔት ወርክና በድርጅት የተሳሰሩትን በሙሉ ሁሉንም ያስጠይቃል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞከንቲባ ተብየዋ አዳነች አበቤ  በክተማው ህይወት ላይ፣ ህዝቡ ቆጥቦ ባጠራቀመው የኮንዶሚኒየሞች እጣ አወጣጥ ስነ ስርአት ላይ አቋሟ ጸረ ህዝብና ጸረ አዲስ አበቤ መሆኑን በተግባር አረጋግጣለች፡፡  በተለይም  በቅርቡ ከኦሮምያ ክልል ጋር ባደገችው ህገ  ወጥና ያልተገባ የአከላለል አፈጻጸም ላይ የከተማው የተለያዩ  ክፍሎችን ሴትዮዋ ወደመጣችበት ክልል ማለትም ወደኦሮሚያ ክልል እንድካለል ማድረጓና ምማስደረጓ  የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ተብየዋ  አዳነች አበቤ   አዲስ አበባ ከተማን ጎድታለች፡፡ ኦሮሙማን ወግና መቆሙዋን በተግባር አረጋግጣለች፡፡

ይህ ሁለቱም የድንበር ተካላይ ወገኖች  የአንድ ፓርቲ አባላት የሆኑበት የሁለት ወገኖች የሚመስል አከላለል  ከህግ ውጭ፣ ከህገ መንግስት ውጭ ፣ ከቻርተር ውጭ፣ በግላቸው ወስነው የሰሩት ህገወጥነት ስለሆነ አይጸድቅም፡፡ ቆይቶ እነርሱ ግፉ በቃኝ ብሎ በቆመው በህዝቡ አልገዛም ባይነት ሲገረሰሱ በማግስቱ ፈራሽ ነው፡፡

ሁለቱም ድንበር ተካላዮች ከኦርምያ ክልል የመጡና የኦሮሙማ ብልጽግና ፓርቲ ባለስልጣናት ናቸው፡  የሁለቱም ወገን የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ስራ አመራር አባላት ሆነው ከህግ ውጭ ከአግባብነት ውጭ ከአዲስ አበባ ለዚህ ጉዳይ በህግ የተወከለ አንድም ሰው በሌለበት አግባብ ድንበርን ያህል ነገር  የተካለሉበት ሁኔታ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ምን ያህል ሸፍጥ፣ ወንጀልና ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ እንንደቀበሩ ለዛሬ  ላይገባቸው ይችል ይሆናል፡፡ ነገሩ ፉርሽ ብቻ አይሆን ዉሎ ሳያድር ይፈነዳል፡፡ይሻራል፡፡በህዝብ ትግልና ህገወጥ በመሆኑ ፋራሽ ይደረጋል፡፡

ይህ የከንቲባዋ ስራ በኦሮሙማወች ዘንድ ከአብይ አህመድ ጀምሮ ከላይ እሰክታች የተወደሰ ሲሆን በድፍን 6 ሚሊዮኑ የአድስ አበባ ነዋሪወችና ይልቁንም ከአክራሪወች ውጭ ባለው በመቶ ሚሊዮኑ ኢትዮጵያዊ ዘንድ የተወገዘና የተኮነነ ስራ ነው፡፤ እንድገመው፡፡ ለጊዜው ነው እንጅ ፉርሽ ነው፡፡ ፈራሽም ነው፡፡ ምክንያቱም አዲስ አበባ የአገሪቱ መናገሻ ዋና ከተማ ነች፡፤ በኢህአደግ ጊዜም ቢሆን ከተማዋ ለብዙ አመታት ስሟ ክልል 14 ተብላ ራሷን የቻለች ክልል የነበረች መሆኗ ታሪክ ምስክክር ነው፡፡ ወያኔና ኦሮሙማ የራሳችን ነው ብለው ባጸደቁት በራሳቸው ህገ መንግስትም ቢሆን ራሷን የቻለ ቻርተር ያላት ከተማ መሆኗ ተደንግጓል፡፡

ኦሮሙማ ሊውጣት ያቆበቆበው የእኛ የሁላችን የሆነችው አዲስ አበባ ከተማ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የሆነች ራሷን በራሱ የምታስተዳድር የማንም ክልል አካል ያልሆነች ነጻ የከተ  አስተዳደር ነች፡፡

የአሩሲዋ እመቤት አሸርጋጅና ከዳሚ የነበረች ሴትዮ ያለእውቀትና ችሎታ በዘረኝነት ከንቲባ ተደርጋ ተሹማ በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ትምህርት ቤቶች ላይ የኦሮሙማ "የመቶ አመት እድፍሽን አጠብንልሽ" መዝሙር እንዲዘመር ማስገደዷና የኦሮምያ ባንድራ የራሷ ቻርተር ባላትና ከኦሮሙማ ነጻ በሆነች ከተማ ውስጥ እንዲሰቀል ማስገደዷ  ሌላው ወንጀሏ ነው፡፤

ይህ የአከላለል፣ የባንድራና የኦሮሙማ መዝሙር ችግር በአዲስ አበባ ላይ ኦሮሟወች የፈጠሩት ችግር  ነው፡ ችግሩ ለጊዜው ኦሮሙማ በሚሰራው ድራማ ትኩረት የተነፈገው ቢመስልም ችግሩ ትንሽም ሳይቆይ መልሶ ያመረቅዛል፡፡ መርዝ ነው፡፤በከተማዋ ላይ የተነሰነሰ/የተተከለ ነቀርሳ ነው፡፤በባህርይ /በተፈጥሮ ነቀርሳ ተቆሮጦ ካልተጣለ ይገድላል፡፡ እንደሚታወቀው በማንኛውም ደረጃ ያለ ነቀርሳና ነቀርሳነት ተነቅሎ ካልተጣለ አገርንም ህዝብንም ያጠፋል፡፡

አብይ አህመድ፣ አዳነችና ሌሎችም የኦሮሙማ ሹመኞች የኢትዮጵያ ነቀርሳወች ናቸው፡፤ ካልተነቀሉ እያመረቀዙ  መልሰው ነቀርሳቸውን ያስተላልፋሉና መነቀል አለባቸው፡፡

አዲስ አበቤ ሆይ፡_ አቅምህን ሙሉ ተጠቅምህ ነቀርሳወቹን ከላይህ ላይና ከውስጥህ  አስወግዳቸው፡፤ ነቅለህም ጣላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ራስህ አስበህ፣ መርጠህና ወስነህ በመሪነት ቦታ ላይ ከምታስቀምጠው ግለሰብም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲ ውጭ በራስህ ከተማ ውስጥ ማንም ከየትም ተለቃቅሞ  እየመጣ እንዲፈነጭብህ አትፍቀድ፡፤  እንደዚያ ባለማድረግህ እስካሁን የደረሰብህ  ጉዳት በቂ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፦ ምንም ይሁን ምንም ከአሁን የባሰ አይጨልምብህም፡  የአሁኑ የገዥወችህ ጥጋብ ነገህንም እያጨለመ ያለ የተረኞች ጋጠወጥነት ዛሬዉኑ መቆም አለበት፡፡

የፈለገውን ያህል ይጓሽ ፣የፈለገውን ያህል ይበጥበጥ ፡፡ የፈለገውን ያህልም ጉም ይምሰል፡፤ ውሎ ሲያድር ግን ይጠራል ፤ አንዴ ከጠራ በኋላ  ራስህ እወቅበት እንጅ ዘለአለም ባሪያ ሆነህ እንድትኖር የሚያደርግህን አማራጭ አትከተል፡፡ በውርደት ለውርዴት  አትኑር፡፡

ከወያኔ በባሰ ሁኔታ በአገር ደረጃ  የህዝቡን ብሶት ያባባሰው የኦሮሙማ ግፍና ሞልቶ ስለፈሰሰ በህዝብ ትግል ወደመቃብሩ ሊወረወር ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡ በቅርቡ ከፍተኛ የህዝብ እምቢተኝነት ይወለዳል፡፡ ተረኞቹ ከነተባባሪወቻቸው ይወገዱ ዘንድ ትግሉ በመላዋ አገሪቱ የትም መቀጣጠል አለበት፡፡ በመላዋ አገሪቱ የህዝቡ ትግል ዉጤት ያመጣ ዘንድም  አዲስ አበቤ አንተም የራስህን የህዝባዊ እምቢተኝነት እርምጃወችን በከተማህ ውስጥ በተጠናና በተናበበ “የአዲስ አበቤነት የህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴ” አስፈላጊነት ላይ ወስነህና ቆርጠህ ዛሬዉኑ ጀምር፡፡

የህዝብ አመጽና የህዝብ አልገዛም ባይነት ምንጊዜም አሸናፊ ነው፡፤ ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
https://amharic-zehabesha.com/archives/178675

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...