Monday, December 12, 2022
ጠላትህ ሲጀምር ራሱን ማጋለጥ፣ እስኪጨርስ ድረስ ታዘበው ብለህ ጸጥ
(Never interfer with your enemy while he is destroying himself, Napoleon Bonapart)
ውድ እህቴ መስከረም አበራ፣ ፀራማሮች ከተለያዩ አቅጣጫወች የተለያዩ ጦሮችን ለምን እንደሚወረውሩብሽ አንቺው ራስሽ በደንብ ስለምታውቂ በዚህ ረገድ መካሪ እንደማያሻሽ አውቃለሁ፡፡ ይችን ምክር ቢጤ ለመክተብ የተነሳሁትም አንቺን ለመምከር ሳይሆን፣ ላንቺ ያለኝን አክብሮትና ድጋፍ ለመግለጽ ያህል ነው፡፡ ለጦቢያ አምላክ የምጸልየውም፣ የአማራ ሕዝብ ወያኔንና ኦነግን በማያዳግም ሁኔታ ድል አድርጎ ሕልውናውን ለዘለቄታው እስከሚያረጋግጥ ድረስ በያዝሽው መንገድ እንድትቀጥይ እንዲረዳሽ ነው፡፡ አንቺም ብትሆኝ ለምታመልኪው አምላክ አጥብቀሽ መጸለይ ያለብሽ፣ ከመንገድሽ መዳረሻ ሳትደርሽ በፊት፣ ባንድ ወቅት ጉምቱ ይባሉ እንደነበሩት የተለያዩ ግለሰቦች በተለያዩ ምክኒያቶች ተሰናክለሽ እንዳትቀሪና፣ እየደከምሽና እየተጎሳቆልሽ፣ እየተወረፍሽና እየተዘለፍሽ፣ እየታሰርሽና እየተፈታሽ የጣርሽውን ጥረት ሁሉ ውሃ እንዳይበላው ነው፡፡ የነብርን ጅራት አይዙም፣ ከያዙም አይለቁም፡፡
ደረጀ ዘለቀ የሚባለው ላፉ ለከት የሌለው፣ መረን የለቀቀ ስድ ግለሰብ፣ አንቺን የሚሳደብ እየመሰለው ራሱን በራሱ እየተሳደበ ከፍ ዝቅ አድርጎ ሊያዋርድሽ ሲሞክር ሰምቸዋለሁ፡፡ በዚህ ድርጊቱ በግልጽ ያስመሰከረው ደግሞ ግለሰቡ ጥራዝ ነጠቅ የእንግሊዘኛ ቃሎችንና ሐረጎችን እዚህም እዚያም እያስገባ ጉራማይሌ በመናገር ምሁር ለመምሰል የሚሞክር፣ ምሁርነት ሲያልፍም ያልነካው ተራ ካድሬ መሆኑን ብቻ ነው፡፡
ቀድሞውንም ቢሆን፣ ታላላቅ የአማራ ምሁሮችን ስልጣን በያዘ ማግስት ካዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በብጣሽ ወረቀት ያባረረው የወያኔ መንግስት፣ የወያኔን ፀራማራ አጀንዳ የማያራምድ ካልሆነ በስተቀር በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዲያስተምር ቀርቶ ወደ ዩኒቨርሲቲው ግቢ ዝር እንዲል እንደማይፈቅድለት የታወቀ ነው፡፡ የወያኔ አለቃ መለስ ዜናዊ በግልጽ እንደተናገረው፣ የወያኔ የሥራ መስፈርት የወያኔን አጀንዳ ማራመድ መቻል እንጅ ትምህርት አይደለም፡፡ የወያኔን አጀንዳ አራማጅ እስከሆነ ድረስ፣ ማንም ሰው በማናቸውም ቦታ ይቀመጣል፡፡ ቦታው ላይ ለመቀመጥ ዶክተር ወይም ፕሮፌሰር መባል የሚበጅ ከሆነ ደግሞ ዶክተርነቱና ፕሮፌሰርነቱ ከሚመጣበት እንዲመጣ ይደረጋል፡፡
አፍ ሲከፈት ይታያል ማንነት እንዲሉ፣ የደረጀ ዘለቀ አፍ የሚያመለክተው ደግሞ ተራ ካድሬ ብቻ ሳይሆን ተራ ዱርየ መሆኑንና ዶክተር ወይም ፕሮፌሰር ቀርቶ አቶ መባልም እንደሚበዛበት ነው፡፡ ለዚህ ነው አቶ ልለውም ያልፈለኩት፡፡ ለዚህ ደግሞ አንባቢን ይቀርታ እጠይቃለሁ፡፡
ደረጀ ዘለቀ በራሱ አንደበት እንደተናገረው፣ ምንም ያላደረጉትን፣ ከነመፈጠሩም የማያውቁትን አላፊ አግዳሚ መንገደኞ ከፍ ዝቅ አድርጎ እየተሳደበ አበሳጭቶ ማወራጨት ከልጅነቱ ጀምሮ የተካነበት፣ በሰፈሩ ልጆች የሚደነቅበት፣ አለቅጥ የሚኮራበት ልዩ ችሎታው ነው፡፡ ይህ ደግሞ የአሳማ ባሕሪ ነው፡፡ አሳማ ሲባል አረንቋ ውስጥ መጨማለቅ ስለሚወድና ከፍተኛ እርካታ ስለሚሰጠው፣ ዋና ምኞቱ ተጨማልቆ ማጨማለቅ ነው፡፡
ስለዚህም ውድ እህቴ መስከረም አበራ፣ ምንም ረብ የሌለው እንቶ ፈንቶ ጉራማይሌ ከዚህም ከዚያም እየለቃቀመ በፍየል ምላሱ ከመፈንተት በቀር ምንም ካልተከረ፣ በማናቸውም ረገድ ያንቺ ቢጤ ካልሆነ፣ የጨምላቃ አሳማ ባሕሪ ከተጠናወተው ከዚህ ከወረደ ግለሰብ ጋር ወደታች ወርደሽ፣ እሰጥ አገባ ገጥመሽ ተጨማልቆ እንዳያጨማልቅሽ በትህትና እመክርሻለሁ፡፡ ደረጀ ዘለቀ ስድ አፉን በመክፈት እውነተኛ ማንነቱን እሱ ራሱ እያሳየ፣ አንቺን የሰደበ ቢመስለውም እሱን ራሱን እየሰደበ ስለሆነ፣ ንቀሽ ተይው፡፡ መልስ እንዳትሰጭው፡፡
ካልተውት በስተቀር ንቀው ብለው ቀላል
ትንሽ ሰው ትንሽ ነው አንሶ ያሳንሳል፡፡
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com
https://amharic-zehabesha.com/archives/178204
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment