Monday, December 12, 2022
አክሎግ ቢራራ (ዶር)
“ጣልያንም መጣ፤ ሄደ ተመለሰ፤ እንግሊዝም መጣ ሄደ ተመለሰ፤ ግብፅም ከጀለ ሄደ ተመለሰ፤
ህወሓትም ካደ፤ ሄደ ተመለሰ፤ ማን ቀረ ኢትዮጵያን እያተራመሰ?”
ቅይጥ ጥቅስ
ክፍል አንድ
ስለ ውክልና ጦርነት አደገኛነት በተከታታይ ሳቀርብ የነበረውን ሃተታና የመርህ አቅጣጫ ለጊዜው ወደ ጎን ትቸዋለሁ። የማፈቅራትና የምሳሳላት ትውልድ ሃገሬ ኢትዮጵያ ለአማራው ሕዝብ ሲዖል እና የእልቂት መናኸርያ ሆናለች። እንኳን ኢትዮጵዊ ነኝ ለሚል የሰው ፍጥረት ቀርቶ መላውን ዓለም የሚያሳዝን፤ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን አሳፋሪ እልቂት እየተካሄደ ነው።
ተስፋ ያላት ኢትዮጵያ ሁሉን አሳታፊ፤ በሕግ የበላይነት የሚመካና የሚገዛ፤ ግልጽነት፤ ሃላፊነትና ተጠያቂነት የሚያንጸባርቅ የመንግሥት አመራር የላትም ለማለት የሚያስደፍር ገጽታ ታሳያለች። ያለ ጉቦ፤ ሙስናና አድልዎ የሚሰራ አንድም ነገር የለም ለማለት እደፍራለሁ።
ለመሆኑ መንግሥት አለ ወይንስ የለም? የሚለው ጥያቄ አግባብ አለው። ከዚህ በላይ ግን እኔን የሚያሳስበኝና የሚያሳዝነኝ፤ እኛ ኢትዮጵያዊያን እንዴት እንደዚህ ጨካኝ ሆንን? ይህችን ታሪካዊና ገና ያልተዳሰሰ እምቅ ኃብት ያላትን አገር ወደ የት እየወሰድናት ነው? የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት።
ይህ ሃተታ ስለ ዘውጋዊው የፌደራል ስርዓት ትችትና አማራጭ ለማቅረብ አይደለም (The imperative of reforming ethnic-federalism). ሃተታየና ትችቴ የዚህ ዘውጋዊ ስርአት የአገዛዝና የአስተዳደር አሳፋሪነት፤ አጥፊነት፤ ሙሰኛነት፤ አድሏዊነት፤ ጸረ-ሰላምነት፤ ጸረ-አብሮነት፤ ጸረ-ብሄራዊ አንድነት፤ ጸረ-የህግ የበላይነት እና አገር አፍራሽነት ፍጹም አደገኛ ወደ ሆን ደረጃ ተሸጋግሯል የሚል ነው።
በአሁኑ ወቅት፤ ማንም ሊክደው በማይችልበት ደረጃ እጅግ የሚዘገንን ዘውግ ተኮር እልቂት በአማራው ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ነው። ከታች እንደሚታየው እናቶች፤ ልጆች፤ ዘመድ አዝማዶች እያለቀሱ ነው። በአጠቃላይ ስገመግመው የዐማራ ሆነ፤ የኦሮሞና ሌላ፤ በአገር ደረጃ ራሱን ኢህአዴግን ተክቻለሁ ብሎ የሚጠራው የብልፅግና ፓርቲ፤ የኦሮምያ ብልፅግና ፓርቲ፤ የዐማራ ብልፅግና ፓርቲና ሌሎች ባለሥልጣናት ይህንን የሚዘገንን የአማራ ሕዝብ እልቂት ሲያወግዙ፤ ገዳዮቹን በማያሻማ ደረጃ ሲያሳድዱና ለፍርድ ሲያቀርቡ አይታይም። ታሪክ ግን ባለሥልጣናቱን እንደሚፋረዳቸው አልጠራጠርም።
አንዳንድ ተቆርቋሪዎች፤ ተመልካቾችና ታዛቢዎች እንደሚሉት ኢትዮጵያ ሕግን የሚያስከብር መንግሥትና ጠንካራ፤ ለህሊናው ተገዢ የሆነ አመራር የላትም። ይህንን አደገኛ፤ ሰለባዊና አገር አፍራሺ ሁኔታ ያባባሰው ደግም የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ መሪዎች ህወሃትና ኦነግ በጋራ ተመከካረው የመሰረቱትን ዘውግ ተኮር ፌደራሊዝም እንደ መጽሃፍ ቅዱስ ስለሚቀበሉትና አዳዲስ ተጠቃሚዎች ስለተፈጠሩ፤ አንነካውም፤ ትክክል ነው በሚል ብሂል ሊያሻሽሉት ስላልደረፉ ነው።
ዘውግ ተኮሩ የፌደራል ሕገ መንግሥት ስርዓት፤ የአስተዳደር መዋቅር ሰንሰለት እና የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ልሂቃን የበላይነት ይገባኛልነት/ተተኪነት የሚያንጸባርቅ ስርዓት ነው። በአማራ ጥላቻ፤ ጥቃትና እልቂት ላይ ትኩረት ለሚያደርገው ለተተኪነት ፖለቲካ አመች ነው።
የአማራን ጥላቻንና እልቂትን ከመሬትና ሌላ የኢኮኖሚ/ፋይናንስ ባለቤትነት ለይቸ አላየውም። ስርአቱና አስተዳደሩ ለመሬትና ሌላ የኃብት ሽሚያ እና ለሙስና አመቻች ነው። ህወሃት እንዴት ኃብት እንዳካበተና ለሃያ ሰባት ዓመታ እንደ ገዛ ያዩ ኃይሎች የእኛም ተራ ደርሷል (It is our turn to eat, steal and rule) ቢሉ አይፈረድባቸውም። ይህንን ከባድ ሸክም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊሸከም አይችልም።
ህወሓት ወልቃይትን፤ ጠገዴን፤ ጠለምትንና ራያን በኃይል ይዞ፤ አማራውን ጨፍጭፎ፤ የሕዝቡን ስርጭት ቀይሮ “ምእራብ ትግራይ” የተባለ የታላቋ ትግራይ አካል የመሰረተው ሕገ መንግሥቱን መሰረት አድርጎ ነው። ይህ የመሬት ነጠቃና የህዝብ ስርጭት ግድፈት ያስከተለውንና ወደፊትም ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ በሁለቱ ዓመታት የጦርነት ወቅት አይተነዋል። ከዚህ እልቂትና ውድመት ግን ብዙም የተማርን አይመስለኝም።
በተመሳሳ፤ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የአስተዳድሩ አካል እውቅና የሰጣቸው የኢትዮጵያ መለያ ሰንደቅ አላማና የአማርኛ ቋንቋ ተወግደው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር ሰንደቅ አላማና አፋን ኦሮሞ ይተኩበት የሚለው የጽንፈኞችና ብሄርተኞች እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን ከአንድ አስጊ የእርስ በእርስ ጦርነት ወደ ሌላ የእርስ በእርስ ግጭግት እየገፋት ነው። ይህ ሁኔታ ያሳስበኛል፤ ያስጨንቀኛል። ለችግርፕቻችን ፈረንጆችን ከመውቀስ ይልቅ መጀመሪያ ቤታችን ብናጸዳ ይሻላል ወደሚል ድምዳሜ አምርቶኛል።
ብሄርተኝነትና ተተኪነት ኢትዮጵያን ያፈርሳታል።
የኦሮሞ ዘውጋዊ ጽንፈኞችና ብሄርተኞች ህወሃትን በመተካት የፖለቲካውንና የማህበረሰባዊ ኢኮኖሚ የበላይነቱን ይዘውም ቢሆን፤ አሁንም ልክ እንደ ህወሃት መሪዎች በጠላትነት የፈረጁትና ኢላማ ያደረጉት የአማራውን ሕዝብ ነው። ለራሱ ነጻነት ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ነጻነት፤ ክብርና ግዛታዊ አንድነት ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረገው የአማራ ሕዝብ ከኦሮሞው ወይንም ከትግራዩ ሕዝብ የበለጠ ጥቅም አግኝቶ አያውቅም። እንዲያውም፤ የአማራው ተራ ሕዝብ ኑሮ ሲገመገም፤ በሁሉም የማህበረሰባዊ እድገት መስፈርቶች በድህነትና ኋላ ቀርነት የተበከለ ሕዝብ ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ በኢትዮጵያ በተከታታይ የጥቃትና የጭፍጨፋ ኢላማ የሆነ ሕዝብ አማራው ነው።
ይህ በከፍተኛና በተቀነባበረ ደረጃ የሚታይ ዘረኝነትና ብሄርተኛነት ከቀጠለ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ ወደ አደገኛ የእርስ በእርስ ጦርነት እየወሰዳት ነው። ኢትዮጵያን በበላይነት የሚመራው መንግሥት የተወሳሰቡና ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች የሚንጸባርቁባትን ኢትዮጵያን በምን አይነት ራእይ እንደሚመሯት፤ ወደ የት ሊወስዷት እንደሚፈልጉ አላውቅም። ለመሆኑ አንዲት ኢትዮጵያ የምትባል አገር አለችን? በዚች አገር ማህበረሰባዊ፤ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትሥስር ላይ እንረባረብ የሚለውን እንቀበላለን? ሌላው ቀርቶ አንድ የጋራ ወይንም አገራዊ የመግባቢያ ቋንቋ እንዲኖረን የሚገባ መሆኑን ብንረዳም አሁንም ስምምነት የለም። አማርኛ ይወገድና እንግሊዝኛ የኢትዮጵያ አገራዊ/ብሄራዊ/ኦፊሲያላዊ ቋንቋ ይሁን ቢባል አይገርመኝም።
የተዛባ ፖለቲካ መርህ ውጤቱ የተዛባ ፖሊሲ ነው።
አሁን የምናየው አሳፋሪና አስጊ ሁኔታ ከስድሳዎቹ የወጣቱ ትውልድ የእምቢተኛነት አመታት ጀምሮ (1960s) እስካሁን ድረስ መልስ ያላገኘው ጥያቄ የተዛባ ዘውግ ተኮር አመለካከት የፈጠረውና የሚያሰተጋባ አመለካከት ውጤት ነው። ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች የልዩነቶቻችን መገለጫ እንዲሆኑ እነ ዋለልኝ መኮነን ከሶቢየቶች የቀዱትን ትርክት ይዘው መሆኑን አሰምርበታለሁ። ዋናው ትርክት አማራውን የጥላቻና የቂም በቀል ኢላማ አድርጎት ስር ሰዷል።
ስም የሚስብ ቢሆንም ቅሉ፤ የብልፅግና አመራር ይህንን አማራ-ጠል ትርክት ትክክል አይደለም ያለበት ጊዜ የለም። ሰው የዘራውን ይሰበስባል እንዲሉ፤ የአማራው እልቂት የተዘራው የጥላቻ ፋሬ ወይንም ዘር ውጤት ነው።
ህወሃት ተወግዷል ቢባልም ቅሉ፤ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ላይ የተከለው፤ ስር የሰደደው የዐማራ ጠል ተቋማት፤ አስተዳደር፤ ትርክትና ድርጊት ግን ሊፈታ አልቻለም። ለዚህ ነው፤ ተደጋግሞ ቢለፈፍም የሕግ የባለይነት በኢትዮጵያ ሊሰራ ያልቻለው። ሌብነት፤ ጉቦና ሙስና ሊቀረፍ የሚችልበት ሁኔታ አይታይም። አሳ የሚገማው ከአናቱ ነው እንደሚባለው ስርዓቱ በሙስና፤ በአስተዳደር ብልሹነት፤ በህግ-ወጥነት ተበክሏል። የኑሮው ውድነትን ለመቅረፍ አስቸጋሪ የሚሆነውም ለዚህ ነው። ውሳኔው ሁሉ የፖለቲካ ሥልጣን የበላይነት መርህ ሆኖ አጥፊነቱ እየከረረ መሄዱ ሊካድ አይችልም። ብልህነት ያለው አመራር መቸ ይሆን ብቅ የሚለው? ብለን እንጠይቅ።
አገር ውስጥ ሆነ ውጭ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ንፁህ ዜጎች ሲፈፈጨፉና ከቀያቸው ሲባረሩ በተከታታይ ስላየን፤ እኛ ደንዝዘናል ብል አልሳሳትም። ይህ ሁኔታ የተለመደ መሆኑ ለአማራው ሕዝብ እልቂት ድምጽና አቤቱታ ላለማሰማት ግብአት እየሆነ ነው። ይህች ከታች የምትታየው ወጣት አማራ ምን ወንጀል ሰራች ብለን ራሳችንን እንጠይቅ፤ ህሊናችንን እንቀስቅስ፤ በጋራ ሆነን የዐማራ ሕዝብ እልቂት ይቁም ለማለት እንድፈር። በኔ ግምገማና እምነት የዐማራው ሮሮና ለቅሶ የኢትዮጵያም ጭምር መሆኑን አሰምርበታለሁ።
በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የብሄር ጽንፈኞችና ተረኞች ደባና ሴራ ስመራመር፤ በዚች አምስት ሚሊየን ሕዝብ በሚኖርባት ታላቅ ከተማ ያንዣበበው የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲከሰት የሚደረግ እንቅስቃሴ ለማንም አያዋጣም።
ኢትዮጵያን ከድጡ ወደ ማጡ በመሸጋገር ላይ ናት። የኦሮሞ ልሂቃን እና የፖለቲካ መሪዎች “እኔም ኦነግ ሸኔ ነኝ” ብለው ሲናገሩ ስሰማ፤ ትዝ ያለኝ፤ የትግራይ ስደተኞችም (ዲያስፖራ) “እኛማ ህወሓት ነን” ያሉትን ነው። በኦነግ ሽኔና በህወሃት መካከል ምንም ልዩነት የለም ማለት ነው። ሁለቱም ሽብርተኞች፤ ጸረ-እትዪጵያና ጸረ ሰላም ኃይሎች ናቸው።
የብልፅግና አመራር ይህንን የአንድ ሳንቲም ግልባጭ ሴራ ግን በሚገባ አላስተዋሉትም፤ ወይንም፤ ጸረ-ዐማራ ስለሆነ ራሳቸው ችላ ብለውታል፤ አንዳንዶች እንደሚኩት ደግሞ አመቻችተውታል።
ለማንኛውም፤ በአማራ ስም ሆነ በኦሮሞ፤ በቤኒ-ሻንጉል ጉሙዝ ስም ሆነ በሶማሌ፤ በትግራይ ሆነ ሌላ ለእልቂቱና ላንዣበበው አደጋ ተጠያቂዎቹ በአሁኑ ወቅት በሥልጣን ላይ ያሉት የብልፅግና ፓርቲ ባለሥልጣናት እና የመከላከያ ኃይል ሃላፊዎች ናቸው።
ኢትዮጵያን የሚያዋጣት ሕገ መንግሥት የዘውግ ፌደራሊዝም አለመሆኑን በተደጋጋሚ አሳስቤ ነበር። በተለይ ባለፉት ሁለት የጦርነት ዓመታት። በዘላቂነት ስመለከተው የሚያዋጣት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በዜግነቱ መሰፈርት ዲሞክራሳዊና ሰብአዊ መብቱ/መብቷ የሚከበርበት ስርዓት ሲመሰረትና በሕግ ሲከበር ብቻ ነው።
የአማራ፤ የትግራይ፤ የአፋር፤ የሶማሌ፤ የአኟክ፤ የኦሮሞ ወዘተ እናቶችና ልጆች ተከታታይ ለቅሶና ምሬት ሊቀሰቅሰን ካልቻለ ምን ሊያንነሳሳን ይችላል? በክልል ሆነ በፌደራል ደረጃ የኢትዮጵያ ባልሥልጣናት ለኦነግ የነጻነት ተዋጊ ኃይል (OLA) ሰለባ ለሆኑት የዐማራ ወገኖቻች እንባና ጩኸት ካልደረሱላቸውና አስችኳይ መፍትሄ ካልተገኘ እንዴት ሆኖ ነው ዘላቂ ሰላም፤ እርጋታ፤ ፍትሃዊ ልማት፤ ብልፅግና ስኬታማ ሊሆን የሚችለው?
እኔ ሳስበው ልቀበለው ባልችልም እንኳን፤ የዐማራው ሕዝብ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ምድር እንዲጠፋ ይፈለጋል የሚሉ ታዛቢዎች ብዙ ናቸው። ይህ የፈጠራ አስተያየት አይደለም። እኔ እስከማውቀው ድረስ፤ የአማራው ህዝብ ባለፉት አምሳ ዓመታት የጥላቻ ትርክት ባስከተለው ግፍ፤ በደልና እልቂት ተካሂዶበታል፤ አሁንም በባሰ ደረጃ እየተካሄደበት ነው። አዲሱ የኢትዮጵያ ህዝብ ወጣት ትውልድ በድንቁርና እንዲበከል ተደርጓል። ከዚህ ድንቁርና መካከል እርስ በእርሱ ሊገናኝበት የሚጠቅምና አግባብ ያለው የጋራ ወይንም አገራዊ ቋንቋ እንዳይኖረው መደረጉ አንዱ ምክንያት ነው።
የተለያዩ የክልል መንግሥታት መስርቶና አዳዲስ ተጠቃሚዎች ፈጥሮ አንድ አገርና አንድ ኢትዮጵያዊ የሚባል መለያ የተቀብለ ህዝብ አለ ለማለት አንችልም። ኢትዮጵያን የጋራ አገራችን ናት የሚል እምነት ያለው የአማራ ሕዝብ “መጤ ነህ፤ ወራሪ ነህ፤ ጨቋኝ ነህ፤ ተስፋፊ ነህ” ወዘተ እየተባለ ይጨፈጨፋል፤ ይሳደዳል፤ ይዋረዳል።
ለዚህ በነጻነቱ የሚኮራና አገሩን የሚያፈቅር ሕዝብ ሊደርስለት የቻለ ወይንም የሚደፍር ባለሥልጣናት ፈልጌ ለማግኘት አልቻልኩም። አማራው ድልድይና በነጻነቱ የሚኮራ ሕዝብ መሆኑን ከተማሪው እንቅስቃሴ ጀምሬ ስደግፍ ቆይቻለሁ። ግን ብዙም ስኬት አላየሁም።
የወደፊቱን ሁኔታ ለማሰብ የምቸገረው ኢትዮጵያ ያለ ዐማራው ሕዝብ፤ የዐማራው ሕዝብ ያለ ኢትዮጵያ ፋይዳ ቢስ ስለሆኑ ነው። በመርህ ደረጃ ስመለከተው የዐማራው፤ የጉራጌው፤ የሶማሌው፤ የአፋሩና ሌላው ኢትዮጵያዊ ሕዝብና ዜጋ በማንኛውም የኢትዮጵያ አካል በሆነ ምድር ያለ ምንም ስጋትና ፍርሃት ለመኖር ካልቻለ ለምንና ለማን ዓላማ ነው ጥምር ኃይሉ ለሁለት ዓመታት ደሙን አፍስሶ፤ አጥንቱን ከስክሶ ህወሓትን፤ የውጭና የውስጥ አጋሮቹን የተዋጋቸው? የፕሪቶሪያውና የናይሮቢው ድርድርና ስምምነት ትርጉምና ፋይዳስ ምን ሊሆን ይችላል?
እነዚህን ጥያቆዎች መመለስ ያለባቸው አገሪቱን በበላይነት የሚመሩት ባለሥልጣናት መሆናቸው አያጠራጥርም። ጭና ማድረግ ያለብን ባለሥልጣናቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልስ እንዲሰጡ ነው።
ኢትዮጵያ ህወሓትን አስወግዳ በሌላ ህወሓት ልትፈራርስ መፍቀድ ለኢትዮጵያም ሆነ ለማንም ባለሥልጣን ሊያዋጣ አይችልም። ምክንያቱም፤ ይህች አገር ልትፈራርስ ትችላለች።
በኦሮምያ/ወለጋ፤ በደራ፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ ወዘተ የሚካሄደው አረመናዊ ዐማራ ተኮር ጭካኔ ከህወሕት ጭካኔ፤ ግፍና በደል አቻ ወይንም የባሰ መሆኑ በተደጋጋሚ ይታያል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በጋራ ሆኖ ህወሓትን በጥምር ኃይሉ ጀብድ ለማንበርከክ ተችሏል። ኦነግን ሸኔን በሚመለከት ግን፤ በኦሮምያ መንግሥትና በፌደራሉ መንግሥት ተቋማት ውስጥ ተሰስገው የሚገኙትን ግብረ አበሮቹን ማንም ደፍሮ ሊነሳባቸው አልቻለም።
የፌደራሉ መንግሥት ሚና ምንድን ነው?
ልክ እንደ ሌሎች መንግሥታት የፌደራሉ መንግሥት መሰረታዊ ሚና የንጹህ ዜጎችን ደህንነት መንከባከብና ማስከበር ነው። የዐማራው ህዝብ ግን የዚህ መርህ ተጠቃሚ አለመሆኑ በተደጋጋሚ ታይቷል። ጥያቄው ለምን? የሚለው ነው።
የውስጥ ተመልካቾችና ታዛቢዎች እንደሚሉት ከሆነና እኔም እንደ ታዘብኩት፤ በተራው የአማራና የኦሮሞ፤ በተራው የአማራና የትግራይ፤ በተራው የአፋሩና የትግራይ ወዘተ ህዝብ መካከከል ጥላቻና ግጭት የለም። ግጭቱን ለፖለቲካ ትርፍ የሚጠቀሙበትና በሳቱ ላይ ቤንዚን የሚረጩት የጠባብ ብሄርተኛና ጽንፈኛ የፖለቲካና የማህበረሰባዊ ኢኮኖሚ ልሂቃን (Elites) ናቸው።
በወለጋ የሚካሄደውን የሚዘገንን የዐማራ-ተኮር እልቂት በአዲስ አበባ ከተማ “የኦሮሞ ሰንደቅ አላማና የኦሮሞ ቋንቋ የሕግ እውቅና የተሰጣቸውን ይተኩ” ከሚለው የጦፈ ትግልና እምቢተኛነትና አመፅ ለይቸ ለማየት እቸገራለሁ። ህገ ወጥነት ነግሷል የምለው ለዚህ ነው።
የአሁኑ ሕግ መንግሥት አንቀጽ 5 ቁጥር 2 “የፌደራሉ መንግሥት የስራ ቋንቋ አማርኛ ነው” ይላል። የአዲስ አበባም ከተማ የስራ ቋንቋ አማርኛ መሆኑን ያንጸባርቃል። ስለሆነም፤ በቋንቋ ምክንያት ግጭቱን ከጀርባ ሆኖ የሚያስተጋባው ማነውና ለምን? ብለን መጠየቅ አግባብ አለው። በተመሳሳይ፤ ሕግ የሚከበር ከሆነ በሰንደቅ አላማውም ላይ ተመሳሳይ ግንዛቤ መያዝ አግባብ አለው። ይለወጥም ከተባለ በውይይትና በህግ እንጅ በኃይል ወይንም በጉልበት ሊሆን አይችልም። ህወሓት በወልቃይት ላይ ያደረገውን ህገወጥ ድርጊት በአዲስ አበባ እንዲደገም መፍቀድ የኢትዮጵያ ዘላቂነት ሊያናጋው ይችላል።
ኢትዮጵያ ወያኔን በሕዝባዊ አመጽና በቅርቡ ደግሞ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት አማካይነት ጦሩነቱ እንዲዲቆም፤ እርቅና ሰላም እንዲሰፍን፤ ሰብአዊ አገልግሎት በጦርነት ለተጎዱት በአፋር፤ በዐማራና በትግራይ ክልሎች ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲደርስ ሲነገር የተሰማኝ ደስታና ተስፋ ከፍ ያለ ነበር።
እርቅና ሰላም አገር አቀፍ መሆን አለበት።
የትግራይ ተራ ሕዝብ አባላት እፎይ ሲሉና ሰብአዊ አገልግሎት ፈሰስ ሲጀመር፤ ለምን በዐማራው ሕዝብ ለይ የተቀነባበረ የዘውግ ማጥፋት (Amhara genocide) ዘመቻ ተባባሰ? ማን አባባሰው? ማን በሃላፊነት ይጠየቅ? ለያንዳንዱ ለህሊናው ለሚገዛ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለማቅረብ የምፈልገው ጥያቄ በንጹህ ዐማራዎች ላይ ያለ ገደብ የሚፈጸመው አሳፋሪና ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከቀጠለ ለኢትዮጵያ ምን አደጋ ሊያስከትል ይችላል? የሚለውን ነው።
- መጀመሪያ አማራው በአንድ ድምጽ ለጋራ የህልውና መስተጋብር ለመስራት ይሞክር። የአማራው ሕዝብ በጎጥ፤ በመንደር፤ በክልልና በጥቅም ሳያከፋፈል ራሱን ከእልቂት አደጋ ለመከላከል ከብረት የጠነከረ የዓላማ አንድነት እንዲኖረውና ድርጅቲዊ አቅሙን በስልት እንዲያዋቅር እመክራለሁ።
በተመሳሳይ፤ በውጭ የሚኖረው የተበታተነውና በግሉ ብቻ የሚፍጨረጨረው የአማራ ህብረተሰብ በአንድ ድምጽ፤ ለአንድ አላማ እንዲተባበር አደራ እላለሁ።
የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት አማራው ራሱን ከእልቂት ለማዳን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በልዩ ልዩ ሰበብ--ፋኖ፤ ነፍጠኛ--በሚል ትችትና መሰናክል መፍጠር የለበትም። በወለጋና በሌሎች የጥቃት አካባቢዎች ለሚኖረው የአማራው ህዝብ የፌደራሉ መከላከያ ኃይል በአስቸኳይና አስተማማኝ በሆነ ደረጃ ድጋፍ ቢሰጠው ይመረጣል። ይህ ካልሆነ ግን፤ ሁለተኛው አማራጭ የአማራዊ ነዋሪ ህዝብ ራሱን ከጥቃት እንዲከላከል የፊደራሉ መንግሥት ባለሥልጣናትና ተቋማት የቁሳቁስ ድጋፍ የመስጠት ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስባለሁ።
ሶስተኛው አማራጭ የተባበሩት መንግሥታት ወይንም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የሰላም አገልግሎት ኃይል (UN or AU Peacekeeping contingent) ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ሰላም አስክባሪ ይሁን የሚለውን አማራጭ በበኩሌ አልቀበለውም። ይህ አማራጭ ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ፈርሳለች፤ መንግሥትም የለም ወደሚል ድምዳሜ እንደሚወስድ እሰጋለሁ። ይህ እንዳይሆን ስለምመኝ የፌደራሉ መንግሥት አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ አለበት እላለሁ።
- በወለጋ፤ በደራ፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ የተከሰቱት እልቂቶች፤ አፈናዎች ወዘተ የተለየ የመንግሥት ትኩረት ካልተሰጣቸው፤ የእርስ በእርስ ጦርነት የሚከሰትበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል የሚለውን አመለካከት እኔም አስተናግዳለሁ።
ኢትዮጵያ የብዙ ሽህ ዓመታት ታሪክ ያላት አገር መሆኗ አያጠራጥርም። የአማርኛ ቋንቋ ብቻ አንድ ሽህ አመት ታሪክ አለው። ቋንቋውን ኦፊሻላዊ ያደረጉት ደግሞ አጼ ዮሃነስ ናቸው። መሆኑም አግባብ አለው። ይህ ቋንቋ የልዩ ልዩ ሃሳቦችና ቋንቋዎች ቅይጥ እንጅ የአማራ ብሄር ቋንቋ ውጤት አለመሆኑን ምሁራን ይናገራሉ።
በተመሳሳይ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ አንዱ ከሌላው የተዋለደና የተዛመደ ሕዝብ ነው። የሚያሳፍረው ግን፤ በህያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብ ልክ እንደ ባእዳን የሚጋራው እሴት ተሽርሽሯል። ኢትዮጵያ የምትባል አገርንና ኢትዮጵያዊ የዜግነት መለያን የተቀበለው ማነው ብለን እራሳችንን እንጠይቅ?
በኔ እምነት የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮና ተቻችሎ ከመኖር ውጭ ሌላ አማራጭ የለውውም። ተተኪነትን የምተቸው ለዚህ ነው።
- ህወሃት በመወገድ ሂደት ላይ ቢሆንም እንኳን በምትኩ ኦነጋዊያን በአንድ ድምጽ በሚባል ደረጃ በአዲስ አበባ፤ በሰሜን ሸዋና በወለጋ የሚያካሂዱት አደገኛ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን እያናጋት ነው። ይህ ሁኔታ ኢላማ ያደረገው አማራውን ነው።
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ህዝብ ለአደጋ እንዲጋለጡ ያደረገው ማነው? የሚለው ጥያቄ በማያሻማ ደረጃ መልስ ነበረው። ይህም አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተጋራው መልስ ህወሃትና ግብረ አበሮቹ ናቸው የሚል ነው። በተነፃፃሪነት ሲገመገም ግን በወለጋ፤ በሰሜን ሸውና በአዲስ አበባ የሚካሄደውን አማራ ተኮር ግፍና በደል ስንመራመር የማያሻማ መልስ ለመስጠት እንቆጠባለን። ለምን ይሆን? ወደ የት እየተጓዝን ይሆን?
በኔ ግምገማና እምነት ግን፤ ወንጀሉን ማንም ኃይል ይፈጽመው ለአማራው ሕዝብ እልቂትና ለቅሶ ተጠያቆዎቹ የሚከተሉት ናቸው፤
- የፌደራሉ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፤ የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይልና ፌደራል ፖሊስ፤
- የኦሮምያ መንግሥት ባለሥልጣናትና የኦሮሞ ልዩ ኃይልና ፖሊስ፤
- የአማራውን ህዝብ እወክላለሁ ብሎ የሚናገረው የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር።
ባጭሩ፤ ባልታጠቀውና በማንም ህዝብ ላይ ጥፋትና ጥቃት ባላካሄደው የአማራ ሕዝብ ላይ በተካሄደውና አሁንም በሚካሄደው እልቂት ላይ የማሻማና ቆራጥ እርምጃ መውሰድ የነበረባቸው ከላይ በአንድና በሁለት ያስቀመጥኳቸው ባለሥልጣናት ናቸው።
በተዛማጅ ደግሞ በማያሻማ አንደበትና ደፋርነት ይህ የአማራ እልቂት ያስጥይቃል፤ መፍትሄ ካላገኘ ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት ያመራል ብለው ድምጽና አቤቱታ ሳይሰለቹ ማሰማት ያለባቸው ደግሞ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ናቸው።
ስለሆነም፤ ሶስቱም በስልጣን ላይ የሚገኙ አካላት ከተጠያቂነትና ከሃላፊነት ሊሸሹ አይችሉም።
በመጨረሻ፤ በውጭ የሚኖረው ግዙፍ የአማራ ሕዝብ ለአማራው ብሶትና እልቂት በአንድነት ሆኖ ሊሰራ አለመቻሉ የአደባባይ ምስጢር ነው።
- ድርጂትከመፈልፈል ውጭ የአማራው ምሁር፤ ልሂቃን፤ ጋዜጠኛ፤ አስተማሪ፤ የግል ባለ ኃብትና ሌላ ባለሞያ በአንድ ላይ ሆኖ፤ በዝግ ችሎት ሆነ ሌላ እኛ የምናየው ክፍተት ምንድን ነው? ከህወሓት ሆነ ከኦነግ ምን ለመማር እንችላለን? ብሎ መፍትሄ የሚፈልግበት ወቅት ዛሬ ነው።
- በግል ደረጃ ሲታይ፤ አማራው ስኬታማ ነው ለማለት ይቻላል። በጋራ ሆኖ ለጋራ ዓላማ ግን ለመቆም አልቻለም። ይህ ሁኔታ በአስቸኳይ መለወጥ አለበት።
- የአስተሳሰብ ለውጥ ካላደረግንና በጋራ ለመስራት ካልቻልን ለአማራው ጠበቃ ለመሆን አንችልም።
December 12, 2022
ብልጽፍና ከህወሓት መራሹ ኢህአዴግ በምን ይለያል?
የዚህ ሃተታ ይዘትና ትኩረት በአማራው ሕዝብ ላይ የሚካሄደው ግፍ፤ ጭካኔና ጭፍጨፋ ለኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ይሆናል የሚል ነው። አማራው የሚጨፈጨፈው ወንጀል ሰርቶ ወይንም በሌላው ወገኑ ለይ ጥቃት ሰንዝሮ አይደለም። አማራው ኢላማ የሆነበት ዋና ምክንያት በማንነቱ ብቻ ነው፤ አማራ ስለሆነ። የእስልምና ተከታይ ሊሆን ይችላል። የኦርቶዶክስ ወይንም ሌላ የክርስትና እምነት ተከታትይ ሊሆን ይችላል።
የብልጽግናው ፓርቲ ከመመስረቱ በፊትና ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በባሰ ደረጃ በአማራው ላይ ያላቋረጠ ግፍና በደል፤ ጭፍጨፋና ፍልሰት ደርሶበታል። ጥቃት የፈጸሙት መሪዎች፤ ቡድኖችና ግለሰቦች በህግ ፊት ቀርበው የተፈረደባቸው ጊዜ ቀርቶ በሃላፊነት የተጠየቁበት ጊዜ ፈልጌ ለማግኘት አልቻልኩም። የአማራው ህይወት ከዶሮ ህይዎት በታች ሆኗል ለማለት የሚያስደፍር ሁኔታ ይታያል። በሽህ የሚቆጠሩ የአማራ እናቶች፤ ሴቶች፤ ህጻናት፤ አዛውንቶች ተገድለዋል። በዚህ ሃተታ እንባዋን የምታፈሰው የአማራ ወጣት ሴት ምን ወንጀል ሰራች? በዚህ ሃተታ የማሳያት ህጻን ልጅ የኔ፤ የእናንተ ልጅ ብትሆን ምን ይሰማናል/ይሰማችኋል?
ዘውግ ተኮር ጭፍጨፋ በሚካሄድበት ወቅት፤ የተጎዳው የሞተው ብቻ አይደለም። ለተሰደዱት፤ ከቀያቸው ለተባረሩት፤ አሁንም ተደብቀው ለህይወታቸው የሚጸልዩት ሁሉ ከፍተኛ የምግብና የመጠለያ እጥረት፤ የስነ ልቦና ጫናና ተግዳሮት ይገጥማቸዋል፤ ማን ይደርስላቸው ይሆን? ታፍነው ወደማያውቁት ቦታ የተወሰዱትስ?
በጥቅሉ ሲታይ ይህ ሁኔታ ኢ-ሰብ አዊ ብቻ ሳይሆን አረመናዊ ድርጊት ነው። ሰው መሆንን ጥያቄ ውስጥ ያስገባል።
ለመመራመርና ሃቁን ለመናገር እንድፈር።
እኔን ያሳዘነኝ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዶር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲወጡ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ያሸጋግሯታል የሚል ተስፋ ነበረኝ፤ ልክ እንደ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ። ግን በተደጋጋሚ የታየው ሃቅ በመተከል፤ በወለጋ፤ በሰሜን፤ በምስራቅና ምእራብ ሸዋ፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ በአማራው ድሃ፤ ታታሪና አገር ወዳድ ህዝብ ላይ በዓለም ፍርድ ቤት የሚያስጠይቅ (International Criminal Court/ICC) ጭፍጨፋ (genocide) እና የብሄር ማጽዳት ዘመቻ (Ethnic cleansing) ተካሂዶበታል። ሁኔታውን ያባባሰው፤ ሕዝቡ ድረሱልኝ ሲል የደረሰለት አለመኖሩ ነው። ይህ ነው መንግሥት የለም የሚያስብለው።
ተገቢውን ምላሽ መስጠት አልቻለም፣ አልፈለገምም። ለተማጽኗቸው ተገቢውንና ከማንኛውም መንግሥት እንደሚጠበቀው ሁሉ እንኳን
ሕይዎታቸውን ሊታደግና ጭፍጨፋውን ሊያስቆም ቀርቶ፣ ዜናው በሌላው ዓለም እንዳይሰማ በማፈን፣ ጭፍጨፋው በተፈፀማባቸው
ጊዚያት ሁሉ ትኩረት ማስቀየሪያ ትእይንቶችን በማዘጋጀት በተደጋጋሚ ለጨፍጫፊወች ሽፋን ሰጥቶአል።
አሁን ግን መደባበቅ ሳያስፋልገው በጭፍጨፋው ተዋናይ መሆኑ ገሃድ ስለሆነ የዚህ የዘር ፍጅት ወንጀል ተባባሪ ካልሆነ
በስተቀር አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አውቆታልና ኅሊና ያለው ወገን ሁሉ በአንድነት በመቆም ይህንን አረመኔአዊ ወንጀል ሊያስቆመው
ይገባል። በቃህ ማለትም ይጠበቅበታል። ኢትዮጵያ በአብይ አህመድና በሺመልስ አብዲሳ በሚዘወረው መረን የለቀቀ ተረኝነት
በተጠናወተው የኦሮሚያ ብልፅግና መገዛቱ እስከቀጠለ ድረስ የዐማራው ጭፍጨፋ በኦሮሚያ፣ በመተከልም ሆነ በሌሎች ቦታዎች
ሊያቆም አይችልም።
ይህንን ዐማራውን ከኦሮሚያ አካባቢወች የማፅዳቱን ስራ አንደ ኦፌኮ ያሉ የኦሮሞ የፓለቲካ ድርጅቶችም የቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ
እገዛ እየሰጡት ይገኛሉ። ሀሰተኛ ዜናወችን በማሰራጨት እየተባበሩ መሆናቸውን በየጊዜው ድርጅቶቻቸው ከሚያወጧቸው መግለጫወች፣
መሪዎቹ (መራራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባና ጀዋር መሀመድ) ከሚሰጧቸው ቃለ መጠይቆች፣ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ከሚለጥፏቸው
ፅሁፎቻቸው መረዳት ችለናል። የጊዜ ጉዳይ እንጅ ኦፌኮም ሆነ መሪዎቹ በዐማራው ዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ከተጠያቂነት አያመልጡም።
ስለዚህ ዐማራው ብሎም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን መሰል ንፁሃንን በማንነታቸው በመለየት የሚያስጨፈጭፍን መንግሥት
በቃህ ሊሉት ይገባል። ዜጎችን በእኩልነት አይቶ በሚያስተዳድር መንግሥት ለመለወጥም ወሳኝ ትግል ማድረግ ይኖርበታል። በዐማራው
ላይ እየተካሄደ ያለውን ይህን የዘር ማጽዳት እና ማጥፋት ዘመቻ ዐማራው ብቻ ሣይሆን ሰብአዊነትና ፍትህ ግድ የሚለው ኢትዮጵያዊ
ሁሉ ተባብሮ በጋራ ሊቆምና ሊታገለው ይገባል። ለሰላማዊ ሰልፍ ከመውጣት አልፎ፣ ህዝቡ መስአዋትነትን ለሚጠይቅ መራር ትግል
መዘጋጀት አለበት። ዛሬ በዐማራ ላይ የሚካሄደውን ጭፍጨፋ እንዳሰቡት ሲያጠናቅቁ፣ ከዘግናኝ ጭፍጨፋው እና የመስፋፋት ወረራው
ሌሎች ነገዶችም እንደማያመልጡና ሁሉም ላይ እንደሚደግሙት ኅሊና ያለው ሁሉ ከልብ ሊረዳ ይገባል። ይኸ ሁሉ ጥረታቸው
‘ነፃይቱንና ታላቂቱን ኦሮሚያ’ የማዋለድ የቆየ ህልማቸውን እውን ለማድረግ የሚያደርጉት እኩይ ተግባር አካል መሆኑን መገንዘብ
ያስፈልጋል።
አዲስ አበባም ከዚህ ወረራ እንዳላመለጠች በተግባር እየታየ ነው። ያለ አንዳች ሃፍረትና በለየለት እብሪት ብዙ የአዲስ አበባ
ቦታወችን ወደ ኦሮሚያ “በስምምነት” ሰጠን በማለት፣ በአቀማመጣቸው የማይጎራበቱ አምስት የአዲስ አበባ ትናንሽ ከተሞችን በአንድ
ላይ በማድረግ በአንድ ከንቲባ የሚመራ ‘ሸገር’ የሚል ከተማ መስርተናል ሲሉ፣ አዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ
ባንዲራ ስቀሉ፣ የኦሮሚያን ህዝብ መዝሙር ዘምሩ እያሉ ተማሪው አንፈልግም ሲል ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ተማሪወችን ስርአቱን
እንዲጠብቁ ባዘጋጅአቸው ቅልብ ፓሊሶች በመሳሪያ የተጋዘ ሺብር እያደረሱ መሆኑ፣ ወዘተ...የዚያው በኢትዮጵያ መቃብር ላይ አዲስ
አገር የመመስረት ዓላማን በጉልበት ለማሳካት፣ካልሆነም የኦሮሞን የበላይነት በቀርው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለመጫን የሚደረግ ግብግብ
መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ዐማራው በከፈለው መራር መስዋዕትነት በደሙ የመለሳቸውን ወልቃይትና ራያን ለህወሃት ለመስጠት
ስምምነት ላይ የደረሱበት ሚስጢርም ዐማራውን ከማዳከምና ከመጨረስ ጋር በቀጥታ የተያያዘ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። ዘር-
ተኮር ጭፍጨፋው በአገር አንድነትና በሕዝብ የጋራ ህልውና ላይ የተሸረበ አደገኛ ሴራ ስለሆነ፣ በጋራ ትግል ሊቆምና ተጠያቂነት
ሊኖር ይገባል።
ስለሆነም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለጋራ ህልውናው መከበር፣ ተጠያቂነት እንዲኖር፣እና ለፍትህና እኩልነት መስፈን ነገ ዛሬ ሳይል
እንዲነሳና ታግሎ ተፈላጊውን ለውጥ እንዲያመጣ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን::
ባለፉት የህወሃት/ኢህዴግ/ብልፅግና አገዛዝ ዓመታት የውጭ መንግሥታት እና በኢትዮጵያ የሚደግፏቸውን የዘወግ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስተች ቆይቻለሁ። ህወሓትና ኦነግ በጋራ የመሰረቱት ሕገ መንሥት፤ ስርዓትና መዋቅር አደገኛ መሆኑን በተደጋጋሚ አሳስቤ ነበር። መሪሩ ሃቅ አንድ ነው። ይህ በዘውግና በቋንቋ የማይታረቁ ልዩነቶች ላይ የተዋቀረ ስርዓት ለኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮነት እና ለሃግሪቱ ዘላቂነት እስጊ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።
ጥቂት ምሳሌዎችን ላቅርብ። ባለፉት ሳምንታት በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤቶች የኢትዮጵያ መለያ የሆነው ሰንደቅ ዓላማና የጋራ የሆነ ው ቋንቋ ተነስቶ “በኦሮሞ/ኦነግ ባንዲራና በኦሮሞፊፋ ቋንቋ ይተካ የሚሉ ጩኸቶችና ሰላማዊ ሠልፎች እየተደረጉ ነው የሚለውን ስሰማ “እትዮጵያ ከድጡ ወደ ማጡ” እያመራች ነው ወደሚለው አቅጣጫ ተሸጋግሬአለሁ።
አዲስ አበባ ከአምስት ሚሊየን በላይ የሚገገመት ስብጥር የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚኖሩባት ራሷን የምታስተዳድር ከተማ ናት። ስለሆነም ሰንደቅ አላማውና ቋንቋው በሕግ የተወሰነ እንጅ ማንም የዘውግ አካል፤ ፓርቲና ሌላ ቡድን እንደ ፈለገ የሚቀይረው አይደለም፤ መሆንም የለበትም። የሕግ የበላይነት ይከበር እላላእሁ። ሕገ ወጥነት ያስከተለውን ግፍ፤ በደል፤ እልቂትና ውድመት ህወሓት ባካሄደው የሚዘገንን ጦርነት አይተነዋል።
ኢትዮጵያ፤ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሜሪካና የአውሮፓ የጋራ ማህበር አባላት መንግሥታት ያመሰገኑትና ስኬታማ እንዲሆን የሚያበረታቱት የሰላምና የህወሓትን/ትግራይ መከላከያ ኃይልን ትጥቅ ማስፈትት ስምምነት ስኬታማ ለማድረግ ጠት
የኢ-ፍትሃዊ ሕገ መንግሥት መዘዝ
ወልቃኢት
አዲስ አበባ
ከዚህ በፊት ባጋጠሙኝ አንዳንድ የውይይት መድረኮች ላይ የነበረን ንትርክ ኢትዮጵያ ውስጥ ፉል ስኬል የሆነ አሲምሌሸን ነበር ወይም አልነበረም የሚል ነበር። አክራሪ የሆኑ የእነግ አባላት ኦሮሞዎች ላይ የባህል መጫን ነበር። ብዙ ኦሮሞ የአማራ ስም አውጥቷል፣ የአማራን ባህል በግድ ተግቷል እያሉ ይሞግቱን ነበር።
ለውጥ መጣ ሲባል ለውጡ ወዲያው በተረኞች መጠለፉን ብንገልጽም ሰሚ አላገኘንም ነበር። የሆነ ሆኖ ዛሬ ችግሩ አፍጦ መጣና አዲስ አበቤን በግድ አሲምሌት አድርግ እያሉት ነው። ይህ ድርጊት ሳይንሳዊ ስም ያለው ሲሆን ስያሜው forced assmlation ይባላል። የኔን ዘፈን በግድ ዝፈን፣ የእኔን ባህል በግድ ከውን የሚሉ ሀይሎች ድርጊት ሰያሜ ማለት ነው። ከባድ ወንጀል ነው። ከወንጀልነቱ ባሻገር የዚህ የኦሮሚያ ዘፈንና ባንዲራ ጉዳይ በአዲሰ አበባ ውስጥ በፍጥነት መታገድ አለበት። ለዚህ ምክንያቴ የሚከተሉት ናቸው።
- አዲስአበባየኦሮምያ ዋና ከተማ ለመሆኗ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ የለም። አዱስ አበባ የኦሮምያም የፌደራልም ዋና ከተማ ለማድረግ ከተፈለገ ህገ መንግስት መሻሻል አለበት። ክልሎች እየተነሱ አዲስ አበባ ዋና ከተማዬ ናት ማለት አይችሉም። ሰለዚህ ትምህረት ሚንስተር እና ፖሊስ ኦሮምያ አዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ላይ ባንዲራ ልሰቅል ነው ሲል ህገ መንግስታዊ መብት የለህም ማለት አለባቸው።
- በዚህዘመንፎርስድ አሲምሌሽን ከባድ ወንጀል ነው። ስለዚህ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ህግ አስከባሪዎች ይህንን ድርጊት ሊያሰቆሙ ይገባል።
ከሁሉ በላይ የኦሮምያ መንግሰት ይህንን ኢ ህገ መንግሰታዊ ድርጊቶችን ከማድረግ ይቆጠብ። አዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ላይ የሰቀላቸውን ባንዲራዎች ያውርድ። አዲስ አበባ ከፌደራል ጋር የኦሮምያ ዋና ከተማ እንድትሆን የኦሮሞ መንግስት ከፈለገ የህገ መንግስት ማሻሻያ እንዲደረግ የኢትዮጵያን ህዝብ ይማጸን። ከዚህ ውጭ ህገ ወጥ ሰራውን ያቁም።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
በኦሮሞ ክልል ውስጥ እንደ ወለጋ ባሉ አካባቢዎች ላይ እየደረሰ ያለው አሰቃቂና ዘግናኝ እልቂት እንደ ሰው ልጅነቴ አጥንቴን ሰርስሮና ሰብሮ ይሰማኛል፣ እንደ ኢትዮጵያዊ ስብዕናም ንዴትና እልህ ይተናነቀኛል:: ሰው ነኝና እያሰብኩ ለምን እስከዚህ ድረስ ተደረሰ፣ እንዴትስ መልስ ይሰጠው የሚል ሃሳብ ሳሰላስል አዕምሮዬን ጨምቄ የማገኘው መልስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፊት ለፊት ገጥመው ማሸነፍ ያልቻሉ የሀገራችን ጠላቶችና በፖለቲካ ዝላያቸው ነጥብ ማስቆጠር የተሳናቸውና ተስፋ የቆረጡ የውስጥ ቅንቅኖች በመንግሥታዊው ሥርዓት ውስጥ ካሉ ተባባሪዎቻቸው ጋር እየተናበቡና እየተባበሩ የሚፈፅሙት እልቂትና ውድመት መሆኑ ይታሰበኛል::
ዓላማው ማእከላዊውን መንግሥት እያናጉ በድክመቱና በውድቀቱ እንደየፍላጎታቸው ምኞታቸውን ለማሳካት የሚታሰብ ነው:: እንዳንዶች ለእነሱ ተንበርካኪና አሸርጋጅ የሆነ አዲስ መንግሥት ያስፈልጋቸው ይሆናል፣ ሌሎችም ከቻሉ መንግሥት ለመሆን ካልሆነም ለእኛ ያልሆነች ኢትዮጵያ ባፍ ጢሟ ትደፋ የሚል የሥልጣን ፍቅር አውሯቸው ሊሆን ይችላል፣ የቀሩት ደግሞ ሀገር ስትረጋጋና ወደ ሰላማዊ ጎዳና ስታቀና የለመዱት ዝርፊያና ቡጥቦጣ ሊጋለጥ እንደሚችል ስለሚረዱ ይህ እንዳይሆን የሀገሪቱን ለውጥ ለማገት የሰላም አየር እንዲደፈርስ በመፈለጋቸው ሊሆን ይችላል::
ለዚህ ሁሉ በየድርሻቸው ለሚለኩት ግብ መድረሻ መሳሪያቸው የእርስ በእርስ ጦርነት ሰደድ እሳት ማያያዝ ነው:: ለዚህም አንዱና ዋናው ግኝታቸው እነከሌ ሳይባሉ ተደብቀው በኦሮሞና በአማራ ኅብረተሰቦች ውስጥ እርስ በእርስ የሚያጣርስ እጅግ አፀያፊና ትዕግስት አስጨራሽ ድርጊቶችን መፈፀም ነው:: እንነዚህ ሁለት ታላላቅ ኅብረተሰቦች ትዕግስታቸውን አሟጠው ጨርሰው ካልክኝ ልበልሃ ከተባባሉ ክፉ አሳቢዎች በእርግጠኝነት ስለታቸው እንደሚሰምርና ያሰቡትንም እናገኛለን ብለው ያምናሉ:: የሚያሰላስል አእምሮ ላለው ሁሉ ሕዝብን እርስ በእርስ በማፋጀትና ሀገርን በማፍረስ የሚገኝ ጥቅምና ሥልጣን የለምና ጥፋት ላይ የተሰማሩት የእኛዎቹ ጅሎች ይህን አውቀው እንዲታረሙ ይመከራሉ:: ያሰቡት ቢሳካላቸው (አማራንና ኦሮሞን አንገት ላንገት ማተራረድ) እጣው የሚወጣው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ለሚያስቡ የውጭ ጠላቶች እንጅ ኢትዮጵያን ለሚያጠፉ ኢትዮጵያዊያ አይሆንም::
ወገኜ ሆይ፣ እየደረሰ ያለውን አንገፍጋፊና አሰቃቂ በደል በሀገር ህልውና ላይ የተቃጣ አረመኔ እርምጃ አድርገህ ውሰደው:: ይህን ግፍ ለመቃወምና ለመመከትም ሕዝባዊ አንድነት ያለው መልስ ያስፈልገዋል::
በአማራና በኦሮሞ ደም የኢትዮጵያ አንድነትና ሕልውና ተከብሮና ተጠብቆ ይኖራል እንጅ የሚይፈሱት ደማቸው በእነሱ ላይ ዶፍ ሁኖ ሀገራቸውን ከምድረ ገፅ አያጠፋም::
ከአማራና ኦሮሞ ኅብረተሰብ ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከወንድሞቹ ጋር በመተባበር ከፋፍሎ ሊያጫርሳቸው የወሰነውን ኃይል ይፋረዳል እንጅ መቸውንም ቢሆን የዳር ተመልካች አይሆንም::
ከመንግሥት በኩልም የራሱን አንድነት ጠብቆ በሕዝብ ጠላቶች ላይ ወሳኝ የሆነ መከላከልና ማጥቃት እንዳለበት ዳር እስከ ዳር ሕዝብ እየጮኸ ነው:: ሕዝብ በጠራራ ፀሃይ እንደ በግ እየታረደና እንደ እሸት እየተጠበሰ የሕዝብ ደህንነትንና የሀገርን ሉዓላዊነት የመጠበቅ ዋና ተግባሩን ረስቶ ለሁሳሳ መሆን ከተባባሪነት ይቆጠራል:: በሚያየውና በሚሰማው የተሸበረውን ሕዝብም ማነጋገርና ማረጋጋት ያስፈልጋል:: ሕዝብ ጠላትና ወዳጁን ጥርት ልቅም አድርጎ እንዲያውቅና እንዲታገል ያልዘገየና ያልተድበሰበሰ መረጃ ያስፈልገዋል::
It's appalling and disgusting that people are trying to rationalize the beheading and public display of disfigured human bodies because of their alleged affiliation to cetail group or their alleged crimes. Mob justice is not going to solve any problem, but worsen a very volatile situation in the country. Over the years, we have become accustomed and tolerant to such violence. We are not outraged by human savagery, that disgusts me
A few years ago, I visited the Auschwitz-Birkenau Memorial Museum, on the sites of Auschwitz Concentration Camp, the largest Nazi concentration and extermination camp.
https://amharic-zehabesha.com/archives/178207
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment