Thursday, December 29, 2022

ሰው በተፈጥሮው ልዩ ና ግለሰባዊ ነው መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
" ሰው ትርጉም ያለው በግለሰብነቱ ነው ። በቡድን ውስጥ የግለሰብ ታላቅ ሰብዕና ሊዋጥ ይችላል ። እናም ቡድናዊነት እጅግ አደገኛ ነው ። " ይላሉ ሃሳብያን ።

ሰው  ፤ ( Human being ) እንግሊዘኛው በቅጡ ይገልፀዋል ። መሆንን ፣ መቻልን ያመለክታል ። ሰው በራሱ የቆመ ፣ በራሱ አንድ ተቋም የሆነ ነው ። ሰውን በመሠረታዊ ፍላጎቱ አሥገዳጅነት በአንድ ልታሰበስበው ትችላለህ እንጂ ፣ አእምሮውን አጥረህ በአንድ ጭንቅላት እንዲያሥብ አታደርገውም ።

እያንዳንዱ ሰው ፣ ብቻውን ወደዚህ ዓለም ራቁቱን  እንደመጣ ሁሉ ፣ ብቻውን ራቁቱን ሥጋው ወደ አፈሩ ይመለሳል ።

ከመወለድ እስከ ሞት ባለው ጊዜ ውስጥ እያንዳንዱ ግለሰብ ፣ የራሱን የህይወት ሩጫ ይሮጣል ። በዓለማዊ እና በመንፈሳዊው የመሮጫ ሜዳ ግለሰባዊ ሚናውን ይጫወታል ። በሂደቱም ተራ ሞች የማይሆንበትን የታላቅነት አክሊል ተቀዳጅቶ በሰው ልጅ ታሪክ ለዘላለም ይነግሳል  ።

ፅሑፉን ለማሳጠር ፣ በዓለም ላይ  በዓለማዊና በመንፈሳዊ ሥራቸው አማካኝነት የታላቅነት አክሊል  የተቀዳጁ አያሌ ግለሰቦች አሉ ።

እነዚህ ግለሰቦች ሰው መሆናቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ  ፤ አሁን እና ዛሬ መሞታቸውን የተገነዘቡ ፤  ከግብዝነት የፀዱ ፤ ዘር ፣ ቋንቋ፣ጎሣ ፣ ብሔር ብሔረሰብ ሳይሉ ፣ በዓለም ለሚኖረው አምሳያቸው ሁሉ   የተሻለ  መንፈሳዊ ህይወትን እና ሥጋዊ ጥቅምን ያሥገኙ ናቸው ።

እነዚህን የዓለማችንን ድንቅ ሰዎች ለማስታወስ  የፍራንሲስ አልበርት ሲናትራን  ( ከታህሳስ 12 ፣ 1915 - እሰከ  ግንቦት 14፣ 1998 የኖረ ) አሜሪካዊ ዘፋኝ እና ተዋናይ ነበር ። “ የቦርዱ ሊቀመንበር ” የሚል ቅጽል ስም ነበረው ። በኋላም “ኦል ባለሰማያዊ አይኑ” እየተባለ የሚጠራው ሲናትራ በ1940ዎቹ፣ 1950ዎቹ እና 1960ዎቹ በጣም ተወዳጅ ከሆኑ የኪነጥበብ ሰዎች  አንዱ ነበር ።  ከ150 ሚሊዮን በላይ የሙዚቃ ሽያጭ ሪከርድ ያለው ዘመን አይሽሬ የኪነ ጥበብ ሰው ነው ።

( ከዚህ ቀጥሎ ያለው ግጥም ከፍራንክ ሲናትራ " የኔ መንገድ " ከተሰኘ ዘፈኑ ሃሳቡ ተወስዶ በራሴ ህሳቤ የተፃፈ ነው ። ክቡራን አንባብያንለንፅፅር የእንጊሊዘኛውንም ትርጉም  በመጨረሻ ላይ  አቅርቤዋለሁ ። )

በመኮንን  ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

 

ሩጫዬን ጨርሻለሁ

ወደ ማብቄያው ፣ ወደፍፃሜው ተቃርቤያለሁ

የመጨረሻው የህይወት መድረክ ላይም ተገኝቻለሁ

ጓደኞቼ ፣ የምላችሁ ይገባችኋል ?

አያችሁ ፣ የመቀበሪያ ሣጥኔ ተዘጋጅቷል ።

መሞቴ እርግጥ ነው

የተፈጥሮ ሃቅ ነው ።

ሞቴ ቢቃረብም

አልፀፀትም ።

ህይወትን በሚገባ

ያለአንዳች ሸፍጥ

ኖሬያለሁ ።

የህይወትን የመጨረሻውን ጥግ

አንድ በአንድ አካልያለሁ ።

ከዚህ የህይወት ትግል ባሻገርም

ህልሜን በሚገባ ኖሬያለሁ ።

በእርግጥ  ፀፀቶች ቢኖሩኝም

መናኛ በመሆናቸው ለተረክ አይበቁም ።

በተሰጠኝ ዘመን ሁሉ

ያለአንዳች ስስት በመክሊቴ  ተጠቅሜያለሁ

መከወን ያለብኝን ሥራ  ፈፅሚያለሁ ።

የህይወት መሥመሬንም በሚገባ  ተግብሬአለሁ ።

እያንዳንዷን እርምጃዬንም በጥንቃቄ ተጉዣለሁ ።

ከዚህ ዙረት ባሻገርም

ኖሬለሁ ፣ የራሴን ህልም ...

ሁላችሁም እንደምታውቁት

ማላመጥ የምትችሉትን

አይደለም እንዴ ...

ከአጥንቱ ላይ የምትቦጭቁት  ?

ያለመጠን  በመስገብገብ

ከጉንጬ አቅም በላይ በጎርስ ኖሮ

እታፈው ነበር ከሚገድለኝ እጉሮሮዬ ተሰንቅሮ ።

ይሁን እንጂ ይህንን አላደረኩም

ባለማድረጌም በህይወት ገዝፌያለሁ

የራሴን ህልምም በሚገባ  ኖሬያለሁ ።

በህይወት ጎዳና ብዙ አይቻለሁ

አያሌ ቀናት በደሥታ ሥቄያለሁ

በመጥፎ ገጠመኝም ደጋግሜ አልቅሻለሁ ።

አውቃለሁ ...

ሙሉና ጎዶለነት  እንደ ሰው ነበሩኝ

ዘወትር ፣ ሌት ና ቀን የሚፈትኑኝ ።

አሁን እነዛ ቀናቶች ተደምድመዋል

አዲስ ብርሃን ፣ አዲስ ቀን ይታየኛል

እንባዬ መፍሰሱን አቁሞ ፣ ልቤ ደስታን ያዜማል

የህይወት ትርጉሙን ተረድቶ መንፈሴ በሐሴት ይናጣል ።

ሆኖም ግን አልዋሻችሁም ...

አይናፋር ፈፅሞ አልነበርኩም

ድንቅ ሥራዎቼንም

ያለ ፈጣሪ እገዛ ...

ለዓለም አላበረከትኩም ።

አትሳቱ ...

አይደለም ! አይደለም !

ያለ ፈጣሪ እኔ ነኝ ፣ ምንም ።

እናም ...ሩጫዬን ጨርሻለሁ

የጉዞዬን መዳረሻ አውቄለሁ ።

.........................................

ምንድን ነው ሰው ፤ ሁሉንም ቢያገኝ ?

ያለ ፈጣሪ ፍቃድ ሥራው ይሆናል ብናኝ ።

በብልጣብልጥነት ከሚያገኘው ይልቅ

ተንበርክኮ የሚቀበለው  ይሆንለታል  ዕፁብ ድንቅ ።

እኔ ዛሬ ና አሁን ፤

በጠንካራ እሜነቴ  እርሱ ፈቅዶ ሁሉን አግኝቻለሁ

የማይጨበጠውን ነፋስ እንኳን በእጄ ጨብጫለሁ

የህይወት መንገዴንም ፤ በወጉ ተጉዤ ጨርሻለሁ ።

( መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ታህሣሥ 19/2015 ዓ/ም )

.........................

 

( Frank sintra " my way )

Francis Albert Sinatra (sɪˈnɑːtrə/; December 12, 1915 – May 14, 1998) was an American singer and actor. Nicknamed the "Chairman of the Board" and later called "Ol' Blue Eyes", Sinatra was one of the most popular entertainers of the 1940s, 1950s, and 1960s. He is among the world's best-selling music artists with an estimated 150 million record sales And know ,the end is near,

and so  i face

the final curtain  .

My friend, i 'll  say it clear ,

i'll state my case ,

Of which i'm certain .

I've lived a life that's full

I've traveled each

and ev'ry highway

But more ,much more than this,

I did it my way .

Regrets , i 've had a few ;

But then again , too

few to mentin .

I did what i had ti do

And saw it through

Without exemption .

I planned each charted course ;

Eche careful step

along the by way

And more ,much more than this

I did it my way .

Yes thre were times ,

I am sure you knew

When i bit off more

Then i culd chew ,

But through it alm ,

When there was doubt ,

I ate it up spit it out .

I faced it alk and i stood tall ;

and did it my way .

I've loved ,i've laughed and cried .

I've my fill ; my share of losing .

And  now , as tears subside ,

I find it alk so amusing .

To think i did all that ;

And may i say not- in a shy way ,

"Oh no, Oh no

Not me ,

I did it my way . "

For what is a man .

What has he got ?

If not himself , then he has naught  .

To say the things he truly feels ;

And not the words of one who kneels ,

The record shows

I took the blows _

And did it my way  !

 

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/178497

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...