Friday, December 23, 2022
December 23, 2022
Vision Ethiopia
መግለጫና የትግል ጥሪ
የአማራው ሕዝብ ተወላጆች በኦሮሚያ ክልል፣ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝና በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በተደጋጋሚ በዘር ላይ ያተኮረ ጭፍጨፋ ሲደርስባቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከአንድ የሃገር መሪ ቀርቶ፣ ከአንድ ሰብአዊ ህሊና ካለው ሰው የሚጠበቅ መቆርቆር ሳያስዩ ቆይተው፣ በዛሬው እለት (December 23, 2022) የአማራውን ሕዝብ እንባ ጠባቂዎች፣ ከጽንፈኛው ኦነግ ሸኔ በማመሳሰል፣ “የአማራ ሸኔ” ሲሉ የተናገሩት የእብሪት ዛቻ፣ ብዙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኗል፣ አበሳጭቷል፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም እስካሁን የተደበቀ አላማ በግልጽ አሳይቷል።
ምንም እንኳን፣ በአማራው ሕዝብ ላይ ሲካሂድ የቆየው የዘር ማጥፋት ዘመቻና በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ የሚታየው የኦሮሙማ መስፋፋት ዘመቻ በመንግሥት መዋቅር የተደገፈና፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ እውቅና የተሰጠው መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ቢሆንም፣ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን ስለአገር አንድነት በማሰብ፣ ከዕለት ወደ ዕለት ሁኔታዎች ይሻሻሉ ይሆናል በሚል ምኞት፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስዉር ደባ የሚገባዉን ትኩረት ሳይሰጡትእስካሁን መቆየታቸው ይታወቃል።
በዛሬው እለት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አንደበት የተሰነዘረው የማን አለብኝነት አነጋገር፣ የኦሮሙማ የበላይነት በገሃድ እንዲረጋገጥ የተፈለገበት ደረጃ ላይ መድረሱን ከማረጋገጡም በላይ፣ የአማራውንና ሌሎች ጭቁን ወገኖች ትግልም ከተሸፋፈነት ጋቢ ወጥቶ፣ አግጥጦ ከመጣው አደጋ ጋር በግልጽ መታገል ያለበት እርከን ላይ የሚገኝ መሆኑን በማያሻማ መንገድ ግልጽ አድርጎ አሳይቷል።
የአማራውን ሕዝብ እንባ ጠባቂዎች፣ ከጽንፈኛው ኦነግ ሸኔ አመሳስሎ “የአማራ ሸኔ” በሚል የእብሪት ስያሜ መስጠቱ፣ በድንገት የመጣ የአንደበት ዉልመት ሳይሆን፣ በተራቀቀ መንገድ የታሰበበትና፣ መጪዉን የኦሮሙማ የበላይነት ማረጋገጫ እቅድ በሥራ መተግበሪያ አካል ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ እንደ ኢላማ ያደረጉት፣ የአማራውን ሕዝብ በግፍ መጨፍጨፍ ለመከላከልና የኦሮሙማን ያልተለጎመ መስፋፋት ለመግታት የሚጥሩትን የፋኖ ኃይሎች በጽንፈኝነት በመሰየም፣ ከባድ ዘመቻ አካሂዶ በማያዳግም ሁኔታ ማጥፋት ነው።
ሌላው እቅድ ደግሞ፣ በህቡእና በገሃድ የሚታየው፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የጸጥታና የባህል መዋቅሮችን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አዉሎ፣ ከመልከአ ምድር እስከ መዋእለ ንዋይ ተቀናቃይ የሌለው የኦሮሙማን የበላይነትን ማረጋገጥ፡ነው።
ስለዚህ በዉጭና በአገር ዉስጥ የሚገኙ፣ ለሰላም፣ ለነጻነት፣ ለአንድነትና ለእኩልነት የቆሙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ በዐብይ አሕመድ የሚመራዉን ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ዘመቻ፣ የሚቻለውን መንግድ ሁሉ በመጠቀም፣ በተቀነባበረ የተቃዉሞ እርምጃ እንዲታገሉ አስቸኳይ ጥሪ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
ትግሉ የረጅምና የአጭር ጊዜ ትልም ቢያስፈልገዉም፣ ከዚህ በታች የተሰነዘሩትን እርምጃዎች በአስቸኳይ መውሰድ አማራጭ የሌለው የህልዉና ማረጋገጫ ስልት ይሆናሉ።
- የመዋእለ ንዋይ ዘመቻ። የአገር ዉስጥ ነዋሪዎች በተከታታይ የሥራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ፣ የዉጭ ነዋሪዎች የብልጽግና መንግሥት የዉጭ ምንዛሪ የሚያገኝባቸውን ምንጮች እንዲያደርቁ፤
- ሰላማዊ የሕዝብ አመጽ። ተማሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ሊሎችም የሀብረተሰብ ክፍሎች ሰላማዊ የሕዝብ አመጽ እንዲያካሂዱ፤
- የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ። የዲያስፖራ አባሎች በበይነ መረብ የዓለም አቀፍ ተቃዉሞ በተከታታይ እንዲያራምዱ፤
- የድርጅቶች ጥምረት።በተናጠል ተሰማርተው የሚገኙት የዉጭና የውስጥ ድርጅቶች፣ ኃይላቸውን በአንድነት የሚያስተባብሩበት መንገድ እንዲፈጥሩ በተናበበ መንገድ ተግሉን እንዲያፋጥኑ፤
- የገንዘብና ቁሳቁስ እርዳታ። በውጭ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት አገር ዉስጥ ለሚደረገው የሞት ሽረት ትግል የሚዉል የፋይናንስና የቁሳቁስ አቅርቦት በማዘጋጀትና በማስተባበር ኢትዮጵያዊ ግዴታቸዉን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ የአንድነት ትግል የፍትህና እኩልነት አገር ሆና ለዘላለም ትኖራልች!!
“መጀመሪያ በሶሻሊስቶች ላይ መጡ፣ እኔም ድምጼን አላሰማሁ-
ሶሻሊስት አልነበርኩምና።
ቀጥለው በሠራተኛ ማሕበረተኞች ላይ መጡ፣ እኔም ድምጼን አላሰማሁ-
የሠራተኛ ማሕበረተኛ አልነበርኩምና።
ከዚያ በአይሁዶች ላይ መጡ፣ አሁንም ድምጼን አላሰማሁ-
አይሁድ አልነበርኩምና።
በመጨረሻ በራሴ ላይ መጡ -
ድምጹን ስለእኔ ለማሰማት የተረፈ ሰው ግን አልነበረም።”
-- Martin Niemoller
Vision Ethiopia is a 501 (c) (3) nonprofit organization incorporated in Washington, D.C. EIN 81-0729204. http://visionethiopia.org. Email:
VisionEthiopia@VisionEthiopia.org
https://amharic-zehabesha.com/archives/178404
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment