Sunday, December 4, 2022
የዐማራ የህልውና ትግል መርህ Comb (1) ዐራውን መፍጀትና አገር አልባ ማድረግ፣ የቅኝ ግዛት ሕልማቸው ያልተሳካላቸው ፋሽስት ጣልያኖች ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር የወጠኑት ዕቅድ ነበር። በጽኑ የሉዓላዊነት እምነቱ የዐርበኝነቱን ተጋድሎ የመራውን ዐማራውን ነጥሎ ለመምታት አሲረው የፈጠሩት “የዐማራ የበላይነት” የሚል የጥላቻ አስተሳሰብን፣ በዘመኑ ባደራጇቸው የነገድ ግዛቶች ምስለኔ አድርገው ከሾሟቸው ባንዳዎቻቸው ወርዶ የልጆቻቸው ውርስ ሆነ። በአምስቱ ዓመት ጦርነት የዐማራ ዐርበኞችንና ተወላጆችን አንገት እየቀሉ ባቀረቡት ራስ (ቸብቸቦ) ቊጥር ጠገራ ብር ይሸለሙ የነበሩ የነዚያ ባንዳዎች ልጆች፣ ከነጻነት ማግሥት ጀምሮ በታዩ የኑሮ ቀውሶችና የአስተዳደር ቅሬታዎች ከለላ፤ በ 1966 በለኮሱት “አብዮት” በሚሉት ሽብር የዐማራ ዐርበኞችንና አዛውንት የሕዝብ አገልጋዮችን በመፍጀት የአባት ውርሳቸው የሆነውን ዐማራውን የማጥፋትና “በዐማራው አምሳል ተቀርጻለች” የሚሏትን ኢትዮጵያን የማፍረስ ተግባራቸውን ተያያዙት። እነዚያ የሽብሩ መኃንዲሶች የሆኑት ነገዳውያን የመንግሥትን ሥልጣን ጠቅልለው ከያዙ ከ 1983 ወዲህ የጥላቻ ዓላማቸውን በሕገ-መንግሥትነት ቀርጸው አለተጠያቂነት ዐማራውን እያስፈጁትና አገር አልባ እያደረጉት ይገኛሉ። አሁንም በሥልጣን ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት ፀረ ዐማራነትንናነገዳዊነትን የሚያራምድ በአገሪቱ የሰፈነውን የዐማራ የዘር ፍጅት በግልጽ የሚፈጽምና የሚያስፈጽም የወንጀል ሥርዓት ነው።
የዐማራ የህልውና ትግል መርህ የትግል ጥሪ
https://amharic-zehabesha.com/archives/178021
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment