Friday, December 2, 2022
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ አስከሆነች ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ህዝብ በመሆኑ አንድብሄራዊ ሠንቀደቅ ዓላማ ፣አንድ አገር እና አንድ መዲና መኖር ዉድ ሳይሆን ግድ ነበር ግን ገላጋይ ጠፋ ፡፡
አንዲሁም ኢትዮጵያ የራሷ ሆሄ ፣ ቋንቋ ታሪክ ያላት አገር መሆኗ ከዉስጥ ቢካድም በዉጭ እንደሚታወቅ አይካድም ፡፡
እንኳንስ ኢትዮጵያ የሶስት ሽ ዓመታት ታሪክ ፣ ባህል፣ቋንቋ እና ሠንደቅ ዓላማ ያላ አገር እና ህዝብ ቀርቶ ቅኝ ተገዥዎች የነበሩት እና በኢትዮጵያዉያን የነፃነት ትግል ተምሳሌት ነፃ የወጡት ከምዕራብ እነ አሜሪካ፣ካናዳ…፤ከአፍሪካ ብዙዎች ፣ ከምስራቅ እነ ህንድ ፣ቻይና…የራሳቸዉን ባህል ፣ቋንቋ ፣ ሠንደቅ ዓላማ ይዘዉ ቀጥለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ስንል የኢትዮጵያን የቆየ በጎ ነገር በመካድ እና ኢትዮጵያዊነትን በማሳደድ የሚሆን የሚመስለን ካለ ሞኝነት ነዉ ፡፡
በአገር ጉዳይ ከእኔ በላይ ላሳር በማለት የቀደመዉን ኢትዮጵያዊነት እና ማንነት ገሸሽ አድርጎ ለሚያልፍ ጊዜ መጥቶ ጊዜ ሲያልፍ እንዳንተዛዘብ ሊተኮርበት ይገባል፡፡
ያለፈዉ እና የሆነዉ የመከራ ቀንበር ሳይበቃ በአዲስ አበባ ት/ቤቶች አጥር ግቢ የአንድ ክልል ባንዲራ እንዲዉለበለብ ለማድረግ ማሰብ ምክነያቱ ባይታወቅም ለዓመታት በአገሪቷ ላይ ሲካሄድ ከነበረዉ የመከራ ሙከራ ድርጊቶች ከማስቀጠል እና ከማግለል እና መገለል ዉጭ ለኢትዮጵያም ሆነ ለህዝቧ የሚበጂ አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ አገራችን የሁላችን ጎጆ አስከሆነች አዲስአበባ የሁላችን መንበር እና መንደር ናት፡፡ ይህ ከሆነ ኢትዮጵያ አንድ አገር ፤ ህዝቧም በብዙ ቀለማት ዉህደት አንድ ህዝብ እንደመሆኑ በአንድ ሉዓላዊት አገር እና ሉዓላዊ ህዝብ አንድ ነገር የግድ ነዉ ለአንድ አንድ ነዉ ፡፡ ይህም በአንድነት እና አብሮነት ልዩነት የለም ማለት አይደለም ፡፡
ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በአንድነት ዉስጥ ፩ነት ፩ ነፃ አገር ፣ ነፃ ህዝብ፣ ሠንደቅ አላማ፣ ቋንቋ፣ ባኅል…..ያላቸዉ መሆኑን ዓለም የሚመሰክረዉ ሆኖ በዚህ በጋራ ታሪክ እና ማንነት እኛ ካልተስማማን “የፍክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል እንዲሉ ” በተከፈተዉ አጉል ፍክክር በተከፈተ በር ለጂብ እንዳንሆን የ12 ክልሎች ባንዲራ በአዲስ አበባ ት/ቤቶች ይቁም እና እንደምንለዉ ዉጤየቱን እንየዉ ፡፡ ኢትዮጵያ የእኛ ፤አዲስ አበባም እኛ ከሆን በአንድነት እና በመስማማት የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ከፍ ማድረግ ካልቻልን በተናጠል መቆም እና ማቆም ምን እንደሆነ ስናይ ከወረቱ ስንቁ ሲሆን ወደ ዕዉነተኛዉ ማንነት እና አንድነት ለመመለስ ትምህርት ይሆነናል ፡፡
እኛም ሆነ አገራችን የመከራ ቤተ ሙከራ ከመሆን ወጥተን ከህልም ዓለም እንወጣ ዘንድ መትጋት እና በህብረት ዘብ መቆም አለብን፡፡
አንድነት ኃይል ነዉ ፡፡
Allen Amber!
https://amharic-zehabesha.com/archives/177985
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment