Sunday, December 18, 2022
በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
በእየ አራት ዓመቱ በሚደረገው የዓለም የእግር ኳስ ውድድር ከሁሉም የሚደንቀው ሕዝብ ለአገሩ ሰንደቅ አላማ ያለው ከልብ የመነጨና የሚያስለቅስ ፍቅር ነው፡፡ የአሸነፈ ሕዝብ ከልጅ እስከ አዋቂ በደስታ የተሸነፈውም በሐዘን ሰንደቅ አላማውን በእንባ ሲያጥብ ማየት የተለመደ ነው፡፡ በእውነቱ ይህ የሰንደቅ አላማ ፍቅር ተአካላዊና መንፈሳዊ ሰውነት ጋር ያለው ቁርኝት ልዩ ሳይንሳዊ ጥናት የሚያስፈልገው ነው፡፡
በልጅነታችን ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የኢትዮጵያ መዝሙር ሲዘመርና ሰንደቅ አላማዋ ኩል ወደ መሰለው የኢትዮጵያ ሰማይ ቀስተ ደመና መስላ ስትወጣ ብዙዎቻችን እንባችን በጉንጫችን ያለማቋረጥ ይወርድ ነበር፡፡ ሰንደቅ አላማዋን ለመስቀል አስተማሪዎቻችን ሲመርጡን እግዜር የመረጠን ያህል በደስታ መንፈስ እንሞላ ነበር፡፡ አባቶቻችን ሰንደቅ አላማዋን ሲያዩ በክብር ቀጥ ብለው ቆመው እንደ ታቦት ተሳልመዋት ያልፉ ነበር፡፡ የኔ አባት እንዲያውም የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንደ ዳዊት ተኪሱ አትጠፋም ነበር፡፡ ድንገት ረስቷት ተወጣ ወደ ቤት ተመልሶ መጥቶ ይወስዳት ነበር፡፡ እንኳን ሰንደቅ አላማዋን ቀስተ ደመና ሲያዩ ከብቶቻቸው ሳይቀር ቆመው እንዲያከብሯት የሚያደርጉ ዜጎችም እመለከት ነበር፡፡
እንደ አለመታድል በ1991 ዓ.ም. ባንዶች ሰንደቅ አላማዋን ክፉኛ የሚጠሉ ኃይሎችን ትክሻ ተፈናጠው ወደ ወንበር ሲወጡ ይህችን ስንት ትውልድ ደምና እምባ ሲገብራት የኖረችውን ሰንደቅ አላማ እያወረዱ መቀዳድ ጀመሩ፡፡ ሰንደቅ አላማዋን አናስነካም ወይም አታወርዱም በሚል ብዙዎች እንደ ቅድመ አያቶቻቸው ለብሰዋት ተሰው፡፡ በሰንደቅ አላማዋ ምክንያት ሕዝቡ ሲቆጣ የባንዳዎች አምበል ስለሰንደቅ አላማ ሕዝብን ሲያስተምር “ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ ጨርቅ መሆኑን ያውቃል?” ሲል ተሳለቀ፡፡ መቼም በዚህ ዘመን ኢትዮጵጵያ ወንበር እውቀትን እንጅ እውቀት ወንበርን ስለማይወልድ ብዙው ባንዳና ወለወልዳም የዚህን ከንቱ “ጨርቅ ድስኩር” እንደ እውቀት ቆጥሮ እያደነቀ ገለፈጠ፡፡ የሕዝብ ልብ ግን እስካሁን እንደ አዘነና እንዳረረ አለ፡፡
የብራዚል ሰዎች የእግር ኳስ ታላሸነፉና ሰንደቅ አላማቸው ከፍ ከፍ ታላለች ራሳቸውን እስከማጥፋት እንደሚደርሱ የታወቀ ነው፡፡ በዚህ ዓመት የዓለም የእግር ኳስ ውድድርም የሚፍለቀለቅ የሰንደንቅ አላማን ፍቅር እንደ ጉድ እየታየ ነው፡፡ የአርጀንቲናና የፓሪስ ሕዝብ ፊቱን፣ ክንዱን፣ እግሩን፣ ምግቡንና ምድሩን ሁሉ ሰንደቅ አላማ እየነቀሰው ነው፡፡ የዓለም ሕዝብ ሰንደቅ አላማውን ለብሶ የሚያብደው እንደ ኢትዮጵያውያን ሰንደቅ አላማ ጨርቅ መሆኑን የሚያስተምር “መሪ” ነኝ ባይ ገና “ስላልታደለ” ወይስ የሰንደቅ አላማ ትምህርት የማይገባቸው ደነዝ ስለሆነ ነው?
ሰንደቅ አላማ ጨርቅ መሆኑን የሚያስተምር ሌላ “መሪ” ነኝ ባይ ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ አልነበረም፤ መተንበይ ታስፈለገም ወደፊትም ሌላ አገር አይኖርም፡፡ ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ ምናልባትም እስክታልፍ ድረስ ሰንደቅ አላማ ጨርቅ መሆኑን በሚያምን ከንቱና ከንቱው ይኸንን እያስተማረ ባሳደጋቸው እርጉም የእንጀራ ልጆቹ የተገዛች አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናትና ይህ እርግማን እንደ ጉም በኖ እንዲጠፋ አስራ ሁለት ጊዜ “እግዚኦ መሐርነ” በሉ! ያላችሁን እግዚያብሔር ይባርካችሁ ያላላችሁትንም ምህረት ያውርድላችሁ፡፡
ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ. ም.
https://amharic-zehabesha.com/archives/178347
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment