Sunday, December 11, 2022
ከሚድ ዌስት አሜሪካ ዲሰምበር
11/2022
በትውልድ ሃገራችን ኢትዮጲያ በነአብይ ለማና ገዱ የተጀመረውን የኢትዮጲያ ተሃድሶ በማማን የሚታመንባቸውን ታላቆች ከቪዥን ኢትዮጲያ እስከ ስመጥሩ መንፈሳዊ መሪዎች ድረስ ሰምተን ሚኖሶታ ድረስ አብይን ለመቀበል የሄድንባቸው ቀናቶች ከቶ አይረሱም::
ሚኒሶታን የደራሲያን ማህበር መስራች አማረ ማሞ በላንጣቸው ከስራ ያሰወገዷቸው ቄስ ጉዲና የጀመሩት የኦሮሙማ ማህበር አድጎ ጎልምሶ በነአብይ አቀባበል ላይ የኦሮሞ ባንዲራ ብቻ መድረኩን ይቆጣጠር ዘንድ ዘፈኑም ኦሮምኛ ብቻ ይሆን ዘንድ የነበረው ትእይንት ለዛሬው ምስቅልቅል አሰቃቂ የወገኖቻችን መታረድ መፈናቀል ሂደት መንገድ ጠራጊ መሆኑን በሂደት ተረዳን:: ከዚያ ስንሰባ መልስ” ኢትዮጲያ ሱሴ” ተቀይሮ” ኦሮሞ ሱሴ” መሆኑን ያረጋገጥን ሲሆን ከአጣዬ ጀምሮ በነለማ ቅንብር ሿሿ ተደርጎ ከኤርትራ በረሃ የገባው ኦነግ በዳቦ ስሙ ሸኔ በአማሮች በጉራጌዎችና በገሙዎች ላይ ይፋ ጭፍጨፋውን ቀጥሎ ለዛሬዋ ሰቆቃዊት ኢትዮጲያ ደርሰናል::
ከሰሞኑ በሚኒሶታ በዲሲ የሚገኙ ከወንጌላዊት ተገንጥለው ወጥተው የኦሮሞ ወንጌላዊት ሉተራን ወዘተ ያሉትን የተለያዩ ዩቱቦች በመቀባበል በቀለ ገርባና ጃዋር መሃመድን በዋቢነት በመጥቀስ “
ፋኖ በወለጋ ህዝባችንን ጨረሰ” የሚል የአዞ እንባ ያቀርባሉ::
ለመሆኑ ሽመልስ አብዲሳ በመቶሺዎች በልዩ ስልጠናና ትጥቅ ያሰለጠናቸውን ብዙሃኑ በትክክል ወደ OLA የገቡትን በቁጥር ፋኖዎቹ በልጠው ነው ወይንስ ልክ እንደእስራኤሎቹና አረቦቹ በቁጥር አነስተኛው ብዙሃኑን አቸንፎ ነው? ይህን የምጠይቀው መልሱ ጠፍቶኝ ሳይሆን ሰሞኑን የሚነዛውን “ፋኖ ወለጋ ህዝባችንን ጨፈጨፈ” የሚለውን ሃሰተኛ ትርክት ለመመከት ነው:: በትክክል ጄነራል አሳምነው በብቃት ለማሰልጠን ሲጀምር “ብሩን በወታደራዊ ወጭ ፈጃችሁት” ብሎ አብይ አህመድ ሲያግድ ከዚያም የእርስበርስ መቃቃራቸውን ተጠቅሞ ያመነመነው የአማራው ልዩ ሃይል ወያኔን መመከት ያቃተው በወኔ ተንቀስቅቅሶ ከአፋር ነብሮች ጋር አብይን የደገፈው ፋኖ ዛሬ ውለታው “ኢመደበኛ ያልሆነ” በሚል ጅማሮ መሪዎቹንማሰር ማሳደድ ለመሆኑ በይፋ የሚያትን ነውና ለኦነግ የገበራችሁት የኦሮሞ ልዩ ሃይል ሰላማዊ ህዝባችንን ኦሮሞውን ጭምር የሚፈጄውን በፋኖ ማሳበብ ማላከክ ቀሽም ፕሮፓጋንዳ መሆኑን በመግለጽ ከቤንሻንጉል ነጻ አውጭ ጋር በተደረገው አይነት ከሁሉም ታጣቂ ጋር ስምምነት ተፈጥሮ ሃገሪቱን ሁሉም ብሄረሰቦች ያካተተ ብሄራዊ መከላከያ ይመሰረት ዘንድ ምክሬን እሰጣለሁ::
https://amharic-zehabesha.com/archives/178192
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment