1. የትግራይ ክልል መዝሙር /የአማርኛ ትርጉም
የማንወጣው ተራራ
የማንሻገረው ወንዝ የለም ፤
ፍፁም ወደኋላ የለም
መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም!
በፀሀይ ሀሩር እና በቁር
ነፍሳችን ውሀ ይጥማት
አለት ይሁን ትራሳችን
ዋሻ ይሁን ቤታችን
ሌትም ቀንም ጉዞ ይድከመንም ይራበንም
ሆኖም መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም፤
በጅቦች እንከበብ መሬት ይክበበን
የጠላቶቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር!
ስጋችን ላሞራ ደማችን እንደ ጎርፍ ይፍሰስ፤
አጥንታችን ይድቀቅ ዱቄት ሆኖ ይበተን
መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በፍፁም አንሸነፍም፤
የጦር መሳሪያ መርዝ ፋሽስታዊ ንዳድ
ሚሊየን ጠላቶቻችን ፊታችን ላይ ይጉረፉ
መስዋዕትነት መቁሰል እና ኪሳራም እንከፍላለን፤
የከፋ መከራም ቢመጣ ወደን እንከፍላለን
መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን፤
በዚህ ሁሉ ጉዞ ግን አሸናፊዎች እኛ ነን።
☞ በማለት የትግራይ ክልል መንግስት በትግራይ ባሉ ትምህርት ቤቶች ላለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እስካሁን ድረስ ይዘምራል ።
2. የኦሮሚያ ክልል መዝሙር / የአማርኛ ትርጉም /
ኦሮሚያ //2// የትልቅ ህዝብ ታሪክ እናት
የኦሮሞዎች እምብርት ፥ የገዳ ስርአት አዳራሽ
የህግና ስርአት መሬት ፥ የጨፌ ኦዳ እናት
የብልጽግና ልምላሜ ፥ ሁሉን አብቃይ እናት
የመቶ አመት እድፍ ፥ በደማችን አጠብንልሽ
በብዙ እልፍ እልቂት ፥ ባንዲራሽን ከፍ አደረግን
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ፥ ስልጣንን መልሰን አገኘን
ሰላምና ዴሞክራሲ ፥ የሰብአዊነት መብት
አስተማማኝ ልማት ፥ ዘላቂ ልማት
ከህዝቦች ጋር ሰላምና ፍቅር
ለመኖር ዋስትና ትልቅ አላማ አድርገን
ኃይላችንን አሰባስበን ፥ ተነስተናል ተማመኚብን
ኦሮሚያ አብቢ ፥ ለምልሚና ኑሪ!
☞ በማለት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እንካሁን ድረስ በኦሮሚያ ክልል ይዘመራል ። አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ካልተዘመረ እየተባለ በተደጋጋሚ እየተነሳ ነው ።
3. የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መዝሙር
የታታሪ ህዝቦች የታሪክ ማህደር
የአኩሪ ባህል አምባ የድንግል ሀብት አፈር
የህዝቦችሽ ተስፋ ለሟ ክልላችን
በሰላም በፍቅር በልማት ጉዟችችን
ተባብረን በስራ እንገነባሻለን
የአማራነት ክብር ደማቅ አርማ ይዘን ፥
ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተከባብረን
በፍቅር በአንድነት አብረን እንዘልቃለን ።
☞ በማለት የአማራ ክልል ህዝብ መዝሙር ይቋጫል ፡፡ ይህ መዝሙርም ላለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እስከአሁን ድረስ በክልሉ ይዘመራል ።
ለትውልዱ የጥላቻና የክፋት መርዝ እየጋተ ፥ ሀገርን የሚያፈርሰው ማን እንደሆነ ፥ የህዝብ ህሊና ፍርዱን ይስጥ!
https://amharic-zehabesha.com/archives/178148
Thursday, December 8, 2022
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
The west is rigidly stuck in its heydays of colonialism and slavery. And it has a very good reason for being so stuck, albeit sentimental. ...
-
By Dr. Suleiman Walhad July 16 th , 202 This is a continuation of an article I published in Zehabesha on April 19th, 2022and entitled :...
-
By Dr. Suleiman Walhad July 10th, 2022 It is fully defined now, the Horn of Africa States! It is marked by droughts , secessionism, inte...
No comments:
Post a Comment