ጭራቅ አሕመድ ስልጣኔን ለመንካት ብታስቡ መቶ ሺወቻችሁ ባንድ ጀንበር ትታረዳላችሁ በማለት ባዲሳቤወች ላይ በግልጽ ዝቷል፡፡ ልብ በሉ፣ ጭራቅ አሕመድ ያለው ተቃውሞ ይነሳል ወይም ሁከት ይፈጠራል ሳይሆን፣ መቶ ሺወች ይታረዳሉ ነው፡፡ ቁጥሩን ደግሞ አስቡት፡፡ መቶ ሺወች ነው ያለው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ቢያንስ፣ ቢያንስ ሁለት መቶ ሺወች ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ጭራቅ አሕመድ በግልጽ የዛተው በስልጣኔ ብትመጡብኝ ቢያንስ፣ ቢያንስ ሁለት መቶ ሺወቻችሁ ባንድ ጀንበር ትታረዳላችሁ በማለት ነው፡፡ በርግጥም ጭራቅ አሕመድ፣ ጭራቅ ብቻ ሳይሆን፣ ጭራቀ ጭራቅ (የጭራቆች ጭራቅ) ነው፡፡
አሁንም እንደገና ልብ በሉ፣ ጭራቅ አሕመድ ያለው ስልጣኔን ብትነኩ ሳይሆን ስልጣኔ ለመንካት ብታስቡ (ማለትም እኔን ተቃውማችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ብትወጡ ወይም ድንጋይ ብትወረውሩ) ነው፡፡ ግራዚያኒ ቦንብ ተወረወረብኝ ብሎ ባንድ ጀንበር ሠላሳ ሺ ጨፈጨፈ ብለን ለዘመናት ጉድ ስንል፣ የኦነጉ ጭራቅ ደግሞ ድንጋይ ብትወረውሩብኝ መቶ ሺወቻችሁን ባንድ ጀንበር አርዳችኋለሁ ብሎ በግልጽ ዛተ፡፡ ዛቻውን የዛተው ደግሞ ትታረዳላችሁ የሚለውን ዘግናኝ ቃል ካንደበቱ ሲያወጣ ምንም ሳይሰቀጥጠውና፣ ዛቻውን እንደሚፈጸመው ፍጹም ርግጠኝነቱን በግልጽ በሚያመላክት ሁኔታ ፍጹም በተረጋጋ መንፈስ ነበር፡፡
ጭራቅ አሕመድ በርግጠኝነት መንፈስ ይህን ዓይነት ሰቅጣጭ ዛቻ ሊዝት የሚችለው ደግሞ፣ በቀጥታ የሚያዘውና ትዛዙን ለመቀበል በተጠንቀቅ የሚጠባበቅ፣ እረድ ያለውን ሁሉ ለማረድ ቅንጣት የማያቅማማ ተወርዋሪ አራጅ ሠራዊት አዘጋጅቶ ካስቀመጠ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ጭራቁ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በየዕለቱ የሚከሰቱት ሁሉም ክስተቶች በማያሻማ ሁኔታ የሚያረጋግጡት ደግሞ፣ ይህ የጭራቅ አሕመድ ተወርዋሪ አራጅ ሠራዊት ሌላ ማንም ሳይሆን፣ ራሱ ጭራቅ አሕመድ ኦነግ ሸኔ የሚለው፣ የራሱ የጭራቅ አሕመድ ክብርዘብ (republican guard) የታጠቀውን ዘመናዊ መሣርያ እንዲታጠቅ ያደረገው አራጅ ሠራዊት ነው፡፡
የጭራቅ አሕመድ ኦነግ ሸኔ ሚና ከኤዶልፍ ሂትለር (Adolf Hitler) ኤስ ኤስ (Shutzstaffel, SS) ሚና ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ጭራቅ አሕመድ ኦነግ ሸኔን ፈጥሮ የሚጠቀመበት፣ ኤዶልፍ ሂትለር ኤስ ኤስን ፈጥሮ ይጠቀምበት በነበረው መንገድ ነው፣ ምንም እንኳን የጭራቅ አሕመድ ሸኔ ባውሬነቱ፣ የሂትለርን ኤስ ኤስ ቀርቶ የሃብያሪማናን (Habyarimana) ኢንትራሃምዌ (interahamwe) ሺ እጥፍ የሚያስከነዳ ወደር የለሽ ጭራቅ ቢሆንም፡፡
ኤዶልፍ ሂትለር ታላላቅ የጀርመን ጦር መሪወችን በተለያዩ ምክኒያቶች ገድሎ፣ አባሮና በጡረታ አሰናብቶ፣ በምትካቸው ዊሊያም ካይትልን (Wilhelm Keitel) የመሳሰሉ፣ በናዚ አስተሳሰብ የሰከሩ፣ ሲጠራቸው አቤት፣ ሲልካቸው ወዴት የሚሉ አሸርጋጆችን (yes men) በመሾም፣ የጀርመንን መከላከያ ሠራዊት (Wehrmacht) የናዚን የመስፋፋት አጀንዳ የሚያስፈጽም የናዚ ሠራዊት አደረገው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የጀርመን ሕዝብ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛለት ሽበር ለመልቀቅ፣ ጀርመናዊ ተቃዋሚወቹን ለመረሸንና፣ ይሁዳወችን በይሁዳነታቸው ብቻ ለመጨፍጨፍ ኤስ ኤስ የተሰኘውን ኢመደበኛ ሠራዊት (paramilitary force) መሠረተ፡፡
ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ ደግሞ እሱ ራሱ ጠቅላይ አዛዥ በሆነበት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ቀንደኛወቹን አነጋውያን ብርሃኑ ጁላን ኢታማዦር ሹም፣ ቀንዓ ያደታን መከላከያ ሚኒስትር፣ ይልማ መርዳሳን አየር ኃይል አዛዥ በማድረግ በኦነጋውያን ቁጥጥር ሥር አውሎ፣ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት የኦሮሙማን የመስፋፋት አጀንዳ የሚያስፈጽም የኦሮሙማ መደበኛ ሠራዊት አደረገው፡፡
ይህ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትነት ወደ ኦሮሙማ መደበኛ ሠራዊትነት የተለወጠ የኦሮሙማ ግዙፍ ጦር የኦሮሙማን የመስፋፋት አጀንዳ የሚያስፈጽመው ደግሞ ኦነግ ሸኔ ከሚባለው በጭራቅ አሕመድ በቀጥታ ከሚታዘዘው የኦሮሙማ ኢመደበኛ ሠራዊት ጋር በመናበብ እየተቀናበረ የተለያዩ ዘዴወችን በመጠቀም ነው፡፡ ከነዚህ ዘዴወች ውስጥ ደግሞ ዋና ዋናወቹ የሚከተሉት ሦስቱ ናቸው፡፡
ያንደኛው ዘዴ ዓላማ የኦሮሙማን አጀንዳ የሚቃወሙትን፣ የኦሮሙማ ጅብ በመጨረሻ የሚበላው ራሱን የኦሮሞን ሕዝብ መሆኑን የተረዱትን፣ ባንኮችን አላስዘርፍ፣ ጌድኦወችን አላፈናቅል፣ አማሮችን አላሳርድ፣ ጋሞወችን አላዋርድ የሚሉትን አገር ወዳድ ኦሮሞወችን ማስወገድ ነው፡፡ በዚህ ዘዴ መሠረት አገር ወዳድ ኦሮሞወች ባውራ ጎዳና ላይ በጠራራ ፀሐይ እየተረሸኑ፣ ለሌሎች አገር ወዳድ ኦሮሞወች መቀጣጫ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ አያሌ ኦሮሞወች በተለያዩ የወለጋ ከተሞች ውስጥ ባደባባይ የተረሸኑት በዚህ ዘዴ መሠረት ነው፡፡
የሁለተኛው ዘዴ ዓላማ ኦሮምያ የሚባለውን፣ ወያኔ አማራን ለመጉዳት ሲል ብቻ አንቦራቆ የፈጠረውን ጊዜው ሲደርስ ሙሉ በሙሉ መፈራረስ ያለበትን ኢፍትሐዊ ክልል ሙሉ በሙሉ ካማሮች ማጽዳት ነው፡፡ በዚህ ዘዴ መሠረት የኦሮሙማ መደበኛ ሠራዊት አማሮች በብዛት በሚገኙባቸው ቀበሌወች ገብቶ በመስፈር አማሮች መከላከያ አለልን ብለው እንዲዘናጉ ካደረጋቸው በኋላ፣ በድንገት ለቆ ይወጣል፡፡ እሱ በድንገት ለቆ ሲወጣ ደግሞ የኦሮሙማ ኢመደበኛ ሠራዊት (ማለትም ኦነግ ሸኔ) እግር በግር ተከትሎ ይገባና የተዘናጉትን አማሮች ሴት፣ ወንድ፣ ሕፃን፣ አረጋዊ ሳይል በገጀራ ይቆራርጣቸዋል፡፡ ከጭፍጨፋው አምልጠው ጫካ የገቡት ደግሞ በረሐብ እንዲያልቁ ይደረጋሉ፡፡ ባቅራቢያ የሚገኙ አማሮች ደግሞ በጭፍጨፋው ዘግናኝነት በመሸበር ማቄን፣ ጨርቄን ሳይሉ ጣጥለው ይጠፋሉ፡፡ ቀበሌውና አቅራቢያወቹም ሙሉ በሙሉ ካማራ ይጸዳሉ፡፡
የሦስተኛው ዘዴ ዓላማ በሌሎቹ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ መሬቶችን ወደ ኦሮምያ ማጠቃለል ነው፡፡ በዚህ ዘዴ መሠረት አነግ ሸኔ (መከላከያ ከጀርባው ሁኖ በከባድ መሣርያ ከፍተኛ እገዛ እያደረገለት) ወደተወሰነ ቀጠና በተደጋጋሚ እየገባ ጅምላ ጭፍጨፋ እያካሄደ ከፍተኛ መፈናቀልን ያስከትላል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ደግሞ ጭፍጨፋውና መፈናቀሉን ሰበብ አድርጎ በኦነጋዊ ጀነራል የሚመራ ኦነጋዊ ኮማንድ ፖስት ያቋቁምና፣ የቀጠናውን አስተዳደር ሙሉ በሙሉ በኦነጋውያን ቁጥጥር ሥር ያደርገዋል፡፡ በቀጠናው ውስጥ የተቋቋመው ኦነጋዊ ኮማንድ ፖስትና ኦነጋዊ አስተዳደር ደግሞ ከጭፍጨፋውና ከመፈናቀሉ የተረፉትን አማሮች በሽብርተኝነትና በሌሎች ምክኒያቶች እየነቀለ በምትካቸው ኦሮሞወችን በመትከል የሕዝብ አሰፋፈርን ቀይሮ ቀጠናውን የኦሮምያ አካል ያደርገዋል፡፡ በመተከል፣ በሰሜን ሸዋና በደቡብ ምሥራቅ ላኮመልዛ የተደረገውና እየተደረገ ያለውም ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡
ሂትለር ኤሰ ኤስን የመሠረተው፣ ውድቀታቸውን ሁሉ በይሁዳወች እያሳበቡ በይሁዳ ጥላቻ የተመረዙ እርነስት ሮምን (Ernst Rohm) የመሳሰሉ ውድቀታም (loser) ወታደሮችን በማሰባሰብ ነበር፡፡ ጭራቅ አሕመድ ደግሞ የኦነግ ሸኔን አስኳል የፈጠረው በኤርትራ በርሓ የሚሰቃዩትን ስቃይ በፀራማራ ትርክት እንዲያስታግሱ ይደረጉ ከነበሩት፣ ትጥቃቸውን ሳይፈቱ እንዲገቡ ካደረጋቸው የኦነግ መንጋወች ውስጥ ይበልጥ ጽንፈኛ የሆኑትን በመምረጥ ነው፡፡
ያይሁዶች ዋና ጠላት ናዚው ሂትለር እንደነበር ሁሉ፣ ያማራ ሕዝብ ዋና ጠላት ደግሞ ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ ነው፡፡ ሂትለር ሲወገድ አይሁዶች ከናዚ እንደተገላገሉ ሁሉ፣ ጭራቅ አሕመድም ሲወገድ የአማራ ሕዝብም ከኦሮሙማ ይገላገላል፡፡ የአማራ ሕዝብ ዋና ትኩረቱን በዋና የሕልውና ጠላቱ በጭራቅ አሕመድ ላይ አድርጎ ጭራቁን ጨርቅ ካደረገ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com
https://amharic-zehabesha.com/archives/177828
Sunday, November 20, 2022
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment