Tuesday, November 1, 2022

ዕዉነት እና ሞት  በምኞት አይቀርም
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም.  ጦርነት የተጀመረበት ሳይሆን የስልጣን ክፍፍል እና ድልድል ስግብግብነት የተነሳ የጦርነቱ ማግስት ነዉ ፡፡

ይህም ጦርነት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. መጀመሩን ያስታዉሷል፡፡ የአሮጌዉ ኢህአዴግ የስም ለዉጥ እና መንፈራገጥ  ሲጀመር  ከዓመታት በኋላ ተከታዩ ኢህአዴግ  “ብልፅግና ”ሲደላደል  የነባሩ አህአዴግ  ቁንጮ ትህነግ በተከታዩ ኢህአዴግ  እና በህገ- ኢህአዴግ /ህገ- መንግስት ተስፋ መቁረጥ የጫካዉን የ1960ዎች  ድብቅ አመል  በብሶት ሰይፉን ጥቅምት ሀያ አራት ሁለት ሽ አስራ ሶስት ዓ.ም. መዟል፡፡

ሆኖም ትህነግ ሳይነሳ እንዲወድቅ  የሆነዉ በራሱ የማይደርቅ  የጥላቻ እና የበላይነት ዕብሪት ዕኩይ ፍላጎት  ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና የዓማራን ህዝብ ዳግም ወረራ እና ምዝበራ ለማካሄድ ጦርነት ተከፈተ ፤ በዓማራ እና በኢትዮጵያ ህልዉና እና ደህንነት ፡፡

ጦርነቱ ሲያገርሽ   የትህነግ በትግራይ ምርጫ ማካሄድ እና ይህም ነባር እና ተከታይ ኢህዴግ ህገ- መንግስት መሰረት አድርጎ የነበር ትንቅንቅ ነበር ፡፡

ለዚህም የተከታይ ኢህአዴግ የህግ-የበላይነት ለማስከበር ሲል አባት ትህነግ-ኢህአዴግ በህገ መንግስት -ህገ ኢህአዴግ መሰረት በህዝብ ምርጫ የተገኘ የክልል አስተዳደር ኃላፊነት ነዉ የሚል ነበር ፡፡

በዚህ መኃል ወረራ እና ዳግም ምዝበራ የታወጀበት የዓማራ ህዝብ ህልዉናዉን በክንዱ ለማስከበር የህልዉና እና የብሄራዊ ደህንነት የመራጋገጥ ትግል ማድረግ እንዳለበት አዉቆ የመከላከል መስዋዕትነት ከፍሏል፡፡

በዚህም ሁለቱንም የጉየጦርነቱ መነሻ እና መዳረሻ ተዋናያንን  በመታደግ አሁን ባሉበት ደረጃ እንዲደርሱ እና አሁን ላይ ለመነጋገር እና ለመደራደር በማብቃት ምክነያት ሆኗል፡፡

ዛሬ ላይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የዳር ድንበር ጉዳይ ለድርድር ማቅረብ ሌላዉ ከጦርነቱ እና ከሚጠበቀዉ የአባት እና ልጂ ስምምነት ጋር የሚጣረስ ነዉ ፡፡

የጦርነቱ ጅምር እና የስምምነቱ እንደምታ  የብሄራዊ እና የሉዓላዊነት ጉዳይ ከሆነ የሱዳን የኢትዮጵያን ግዛት መያዝ፣ከኢትዮጵያ ግዛት የኤርትራ ጦር አለ ፤ይዉጣ የሚሉት ትህነግ እና ግብረ አበሮች ዕዉነት ከሆነ በድርድሩ ሱዳን፣ኤርትራ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እና የዓመታት የዕልቂት እና ሞት ቀንበር ተሸካሚ -ዓማራ ህዝብ መኖር እና መተባበር ብቻ ነዉ በድርድሩ የኢትዮጵያ እና ህዝቧ ኅልዉና እና ብሄራዊ  አደጋ ከስጋት ሊድን የሚችለዉ ፡፡

የህዝብ እና የብሄራዊ ዳርድንበር ሉዓላዊነት ስጋት መባል ያለበት የፖለቲካ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ከዚህ በላይ የኢትዮጵያ አንድነት ፣የህዝቦች ሉዓላዊነት እና የዓማራ ህዝብ ሠባዊ፣ ተፈጥሯዊ ፣ ብሄራዊ እና ዓለማቀፋዊ መብት እና ነፃነት ዕዉን የሚሆንበት አዉድ ሲኖር እና ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ ፡፡

የዘገየ ዕዉነት  ዉሸት እንደማይሆን ሁሉ የዘገየ ሞትም እንደማይቀር  በማወቅ ለማይቀረዉ ግን ለሚድበቀበቀዉ የብሄራዊ  አንድነት እና ሉዓላዊነት ሥጋት በሆኑት የዉስጥ ነቀርሳዎች ላይ ሳይቃጠል በቅጠል ብሎ መፍትሄ መሻት ያስፈልጋል፡፡

ከየትኛዉም ቡድን ጥቅም እና ፍላጎት በላይ ህዝብ እና የአገር ሉዓላዊነት ጥቅም ፤ስም እና ችግር ቅድሚያ ሊሰጥበት ይገባል ፡፡

በኢትዮጵያ የቆ ታሪክ እና መልካምድራዊ አቀማመጥ የኢትዮጵያ ግዛት አካላት የነበሩትን የጎንደር ፣ የወሎ እና የጎጃም ክ/ሀገር ግዛቶች አካላትን ወልቃይት፣ ራያ እና መተከል  ብሄራዊ የግዛት አንድነት ስጋት የሆኑት ትህነግ እና ግንባር ድርጂቶች በህገ- ኢህአዴግ ጠርንፈዉ የተከሉት“ ዕሳት እና ሥጋት ነዉ” ፡፡

ለዚህ ነዉ ጦርነቱ ቅድመ ሆነ ድህረ  1983 ዓ.ም  መነሻዉ የባተዉ ያን ጊዜ ነዉ ፡፡ ዛሬ የጥቅም ግጭት እንጂ  የብሄራዊ ስጋት  አሜኬላ ብቅለት ያኔ ከግማሽ ምዕተ ዓመት አስቀድሞ ነበር ፤ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ የምትድነዉም ፤የምትታመመዉም  በራሷ ልጂ ነዉ ፡፡ ከራሷልጆች ዉስጥ ይህ ክማሽ ክ/ዘመን ዓመታት በፊት ጀምሮ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና የህዝብ ህልዉና ስጋት ዳፋ ቀማሽ የሆነዉን የኢትዮጵያን ህዝብ እና ዓማራ ህዝብ ነፃነት እና ህብረት ጆሮ ሊሰጠዉ ይገባል፡፡

ህገ -ኢህአዴግ ለዘመናት አግላይ እና ገዳይ ሆኖ በኖረበት ከህዝብ እና አገር ጥቅም በላይ የሚታይ የፖለቲካ ጥቀም እና ወገንተኝነትም ሆነ ህግ በኢትዮጵያ ሠማይ ስር  ከኢትዮጵያ እና ከብዙኃን ህዝብ በተለይም ከዓማራ ህዝብ ህልዉና እና ነፃነት መፃኢ ሁኔታ አኳያ መቃኘት እና መታየት አለበት ፡፡ሁላችንም ግማሽ ዕዉነት  አለመኖሩን አዉቀን ከታሪክ እና ከነባር ብሄራዊ ችግር በመማር ወደ ሙሉ ነጻነት እና ዕዉነት መትጋት ይጠበቅብናል፡፡

ወደድንም ጠላንም ዕዉነት እና ሞት በምኞት አይቀርም ፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ !”

Allen Amber
https://amharic-zehabesha.com/archives/177582

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...