Sunday, October 23, 2022
ጥቅምት 12 ቀን 2015 (ኢዜአ) “አፍሪካን ለማፍረስ የተያዘው ውጥን አልፎበታል አፍሪካ ነቅታለች በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ጫና በአፍሪካ ቀንድና በዓለም ሰላም ላይ የሚደረግ ጥቃት ነው” ሲሉ አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ገለጹ።
“ለኢትዮጵያ እቆማለሁ፤ ድምጼን አሰማለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በተካሄደው ህዝባዊ ሰልፍ ላይ አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለሙያዎችን በመወከል በእንግሊዘኛ ቋንቋ መልዐክት አስተላልፈዋል።
“እኛ የነጻነት ዜጎች ነን እኛ ከአለም ቀደምት ከሚባሉት መንግስታት በሕግ፣ በቋንቋ ባህልና ሃይማኖት አደረጃጀት ስረወ መንግስታችን የጸና ነው” ብለዋል በመልዕክታቸው።
ሀገራችን በቀኝ ካልተገዙ ሀገራት ግንባር ቀደሟ ናት ያሉት አንጋፋው አርቲስት ደበበ፤ ኢትዮጵያን ለመውረርና በቅኝ ለመያዝ ቢያንስ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ጫና ሲያደርጉ እንደነበር አስታውሰዋል።
በዘመኑ በተካሄደው የአድዋ ጦርነትም ኢትዮጵያ ላይ የተሞከረውን የቅኝ ገዢነት ወረራ ቁርጠኛ ልጆቿ ጠላቷን ድል አድርገው አስቀርተወውታል ሲሉ ገልጸው፤ ይህም ለአፍሪካውን የአዲስ ምዕራፍ መከፈቻ መንገድ ሆኖ ለብዙሃን የነጻነት ቀንዲል እንዳበራ አስገንዝበዋል።
በአሁኑ ወቅትም በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠውን መንግስት ባለመቀበል የአፍራሽ ተልዕኳቸው አስፈጻሚ የሆነውን አሸባሪው ህወሓትን ከሞት አፋፍ ለመታደግና ወደ ስልጣን ለመመለስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እየተዳፈሩ ነው ብለዋል።
በቅርቡም በቅኝ ገዥ አስተሳሰብ የታጠሩ ምዕራባውያን ያለንበትን የአለም ክፍል ”ጫካ” ሲሉ መናገራቸውን በማስታወስ እኛም በጫካ ውስጥ ያለን አንበሶች እንደሆንን በክንዳችንም ቅኝ ገዥነትን እንዳንበረከክነው ልናስታውሳቸው እንወዳለን ሲሉ አስታውቀዋል።
“አፍሪካን ለማፍረስ የተያዘው ውጥን አልፎበታል አፍሪካ ነቅታለች” ያሉት አርቲስ ደበበ፤ ከአፍሪካውያን ምድር እየተወሰዱ ለሌሎች መጠቀሚያ የሆኑ የተፈጥሮ ሃብቶቻችን በአፍሪካውያን ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል ብለዋል።
እኛ ግድቦችን እየገነባን ግዙፍ ኢንዱስትሪዎችን እያቋቋምን እንገኛለን ለእድገታችን የሚሆኑ ፈጠራዎችንም እየተገበርን እንገኛለን ነው ያሉት።
እኛ አፍሪካውያን ኢትዮጵያውያን አለም እንዲውቀው የምንፈልገው ነገር “በቃ በቃ በቃ” ነው ያሉት አርቲስት ደበበ፤ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ጫና በአፍሪካ ቀንድና በዓለም ሰላም ላይ የሚደረግ ጥቃት ነው ሲሉም አመልክተዋል።
አሸባሪው ሕወሓት በኢትዮጵያ ለተከሰቱ አጥፊ ተግባራት ሁሉ ጠንሳሹና አስፈጻሚው እንደሆነ ገልጸው፤ ምእራባውን አሸባሪውን መደገፍ የለባቸውም በቃ በቃ ልንልን ይገባል ብለዋል።
https://amharic-zehabesha.com/archives/177466
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment