Thursday, September 29, 2022
ቤተሰብና አብሮ አደጎቼን ለመጠየቅ ሰሜን ሸዋ መሃል ሜዳ ከተማ ውዬ አደርኩና አዲስ አበባ መመለሻዬ ደረሰ። ስለሆነም ትናንትና የአውቶቡስ ትኬቴን ቆርጬ ዛሬ ማለዳ ወደ አውቶቡስ ተራ አቀናሁ። የአውቶቡሱ ረዳት ትኬት የቆረጥነውን ሁሉ ቦታ ቦታችንን እንድንይዝ አድርጎ ገና ጎህ ሳይቀድ አውቶቡሱ ወደ አዲስ አበባ መጓዜ ነው ለማለት ዳፉ.... ዳፉ ....ዳፉ......ማለትን ያዘ።
አውቶቡሱ መንቀሳቀስ ሲጀምር ረዳቱ እንዱህ አለ።
ጉዟችን በኤፌሶን፣ በሸዋሮቢት በደብረ ሲና አድርጎ ነው።
ረዳቱ እንዳለውም ያንን ጠመዝማዛ ዳገታማ መንገድ ተያያዝነው። ታዲያ በመጓዝ ላይ ሳለን ከእኔ ፊት ከተቀመጠች አንዲት ወጣት ዘንድ ስልክ አቃጨለ። ይህቺ ወጣት ስልክ አንስታ ስታወራ ድንጋጤ ስለታየባት የአካባቢውን ሰው ትኩረት ሳበች።
ምን ተፈጠረ ? አለ አንዱ አይ ወደ አዲስ አበባ መግባት አይቻልም አሉ አለች እያዘነች።
ሁላችንም ተደናገርን። ወሬው እየዘለለ ሄዶ ሹፌሩ ዘንድ ቢደርስም ከፍጥነቱ ቅንጣት አልገታውም። ይህቺ ይህንን ክፉ ዜና ያመጣች ወጣት ደጋግማ እየደወለች ታረጋግጣለች። ይሁን እንጂ አውቶቡሱ አሁንም ጉዞውን ቀጥሏል።
አይደረስ የለም ሽኖ ከተማ ልንገባ ስንል ለፍተሻ ቁሙ ተባልን። አውቶቡስ ሲቆም አንድ ሁለት ወታደሮች ወደ ውስጥ ገቡና ወሎ አለ....ወሎ አለ.... ሲሉ ጠየቁ። ሁላችንም የመጣነው ከመንዝ መሃል ሜዳ ስለሆነ ተሳፋሪው በአንድ ድምፅ
የለም፣ የለም፣ የለም፣ ከመንዝ ነን አሉ። ይህ አባባሉ ያበሳጨን ብዙዎች እያጉረመረምን ሳለ ውረድ..... የሚል ቀጭን ትእዛዝ ተሰጠን። ሁላችን ከአውቶቡሱ ወርደን ተፈተሽንና ጉዞ እንድንቀጥል ስለተፈቀደ ጉዞ ስንጀምር ብዙ ሰው አዲስ አበባ የመግባት ተስፋው ለመለመ መሰለኝ ጨዋታ ደራ። ይሁን እንጂ ረዳቱ ግን ጭንቀት ይታይበት ነበር።
ሾፌሩ ያንን አውቶቡስ እያበረረ ሲሄድ አለልቱ ስንደርስ ለፍተሻ ቆምን። አንዳንድ ህፃናት የያዙ ሴቶች እባክህ አምላካችን በሰላም አግባን እያሉ ሲያማትቡ ይታያል። በመሃል አንድ ወታደር ገባና.....ወሎ አለ፣ ወሎ አለ፣ ወሎ አለ እያለ ያማትራል። ሁሉም በአንድ ድምፅ መሃላ እየጨመሩ ወሎ የለም፣ ከመሃል ሜዳ ነው....ከመሃል ሜዳ ነው ይላሉ።
እነዚህ የኬላ ጠባቂዎች ይህንን የወሎን ስም እንደገና ሲጠሩ ስንሰማ ተንጫጫን። ትንሽ ሳንቆይ ውረዱ ተባልንና በጨዋነት ወረድን። በዚህ ጊዜ ከተሳፋሪዎች መሃል የአዲስ አበባ መታወቂያ የያዙት በኬላው ጠባቂ አዛዥ ጫማ ስር ወድቀው ፅኑ ልመና ገቡ። የተቀሩት ህጋዊ መታወቂያ ያለን ነን.... ንፁህ ጨዋ ዜጎች ነን.... ወንጀለኛ ካየን አጋልጠን የምሰጥ ነን.....እያሉ ይማፀናሉ።
እኔም በበኩሌ ፓስፓርት መያዜንና ፓስፓርት ደግሞ ለዚህ ለሃገር ቤት የውስጥ ዝውውር ቀርቶ በመላው አለም ለመጓዝ የሚያስችል ከፍተኛ መታወቂያ ነው እያልኩ ለማስረዳት ብሞክር ከቶውንም ጠቀሜታ እንደሌለውና ርባና የሌለው ነገር እንደሆነ አንዱ ወታደር ገለፀልኝ።
ተሳፋሪዎች ልመና ባበዙ ጊዜ የኬላው ሃላፊ ተቆጣ። ሹፌሩን አሽቆጠቆጠው። ሌላው ወታደር አንዲት ጥቁር ላስቲክ የለበሰች የሽቦ ዱላ አምጥቶ መደብደብ ሲጀምር አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ መኪናችን ውስጥ ገባን።
ሾፌሩ እሳት ጎርሶ መሪውን ወደ መጣንበት አዞረ። እንዳዞረ ትንሽ በማቆሙ አንዳንዶቻችን ዘለን ወረድን።
እኔ በበኩሌ ጥያቄ አቀረብኩ።
አንድ የትራፊክ ልብስ የለበሰ ሰው አገኘሁና።
ለመሆኑ ጥፋታችን ምንድን ነው አልኩት።
መልስ አልሰጠኝም።
እሺ ይሁን ለመሆኑ መቼ ነው ወደ አዲስ አበባ መግባት የምንችለው? ብዬ በትህትና ጠየኩ። አጭር መልስ ሰጠኝ። ከመስከረም 23 በኋላ......።
አንዱ ወታደር ወዲያው ወደ አውቶቡሱ ገብተን እንድንቀጥል ዱላውን እያወዛወዘ ትእዛዝ ስለሰጠን ወደ መጣንበት ጉዞ ጀመርን። ብዙዎች ተጓዦች ወዴት እንደሚሄዱና ምን እንደማያደርጉ ጨንቋቸው ይታያል።
በጉዟችን መሃል የዞኑን አስተዳደር ማደሪያ ፈልግ፣ እንዲህ ስንጠቃ ዝምታውስ ምንድን ነው? እንበል የሚል ድምፅ አየለና ከነአውቶቡሳችን ወደዚያው ስናቀና እንደኛው አዲስ አበባ አትገቡም የተባሉ አያሌ መኪኖችንና ተጨማሪ ህዝብ አገኘን። የዞኑ አስተዳደር ከጠዋት ጀምሮ ይህ ችግር እንዳለ እንደሚያውቅ ገልፆ እዚህም እዚያም ግንኙነት ፈጥረን ችግሩን ለመቅረፍ እየጣርን ነው አለ። ለነገ ጠዋትም ቀጠረን።
እኔ ለራሴ በአማራነቴ እንደዚህ ውርደት ተሰምቶኝ አያውቅም። አዲስ አበባን ለማቅናት እኮ መንዜዎቹ ቅድም አያቶቼ የአንበሳውን ድርሻ ይዘዋል። ግን ሁል ጊዜም አዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም የለም፣ አዲስ አበባ የሁላችን ናት የሚለውን መርህ ከፍ አድርጌ እኖራለሁ። ዛሬም ነገም ይሄው ነው እምነቴ።
አዳነች አበቤ ሆይ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ እንዳልገባ አድርገሽ የተወሰኑ እቅዶቼን አበላሽተሻል። አሁንም አዲስ አበባ የሁላችን ናትና ልትከለክይን አትችይም። መስቀል በአል ሲከበር፣ ጥምቀት ሲከበር አዲስ አበባ አትግባ የሚባል ነገር እንደሌለ ሁሉ ኢሬቻም ሲከበር ልዬ ነገር ሊኖር አይችልም። እናንተ የኦሮሞ አክራሪ ሃይሎች እሚያኗኑረንን አስቡ። መንዜን አዲስ አበባ እንዳይገባ አድርጋችሁ አትቀጥሉም። ታቀቡ። መታቀብ ጥሩ ነው። ጥጋብ ጥሩ አይደለም። አንድን ህዝብ በማንነቱ ዝውውር መከልከል ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። አንድን ህዝብ እንደ ህዝብ እንቅስቃሴውን መገደብ ከባድ ማንነት ላይ ያነጣጠረ ወንጀል ነው።
የሆነው ሁሉ ሆኖ አማሮች አዲስ አበባ አትገቡም እየተባሉ ሲጉላሉ፣ ሲያለቅሱ፣ ሲያማርሩ ባየሁ ጊዜ በልቤ የአማራ መንግስት በቁም ሞቷል አልኩ። ትክክል ነኝ በእውነት።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ ይባርክም
https://amharic-zehabesha.com/archives/177253
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...
-
Yonas Biru, PhD In the last fifty some years, four governments have ruled Ethiopia. Emperor Haile Selassie lasted in office for 44 years. ...
-
Contact information: Girma Berhanu Department of Education and Special Education (Professor) University of Gothenburg Box 300, SE 405 ...
-
#image_title አበዉ ኢትዮጵያዉያን "የወንድ ልጂ ሞቱ የተናገረዉን ወይም የሰራዉን የረሳ ዕለት ነዉ ይላሉ "፡፡ ዕዉነት ብቻ ሳይሆን ህያዉ እና በተግባር የተገለፀ ነባር ሀቅ ነዉ ፡፡ ዛሬ በአገራችን ...
No comments:
Post a Comment