
የኢትዮጵያ መንግስትና የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ባለስልጣናት ሁለት ጊዜ ፊትለፊት ተገናኝተዉ መነጋገራቸዉን የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አስታወቁ።ሊቀመንበር ደብረ ፂዮን አዲሱ ዉጊያ ከመጀመሩ በፊት ባለፈዉ ማክሰኞ ለዓለም መሪዎች ባሰራጩት ደብዳቤ እንዳሉት የመንግስትና የቡድናቸዉ ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቢል ባለስልጣናት በሚስጥር ግን ፊት ለፊት ተገናኝተዉ ተወያይተዋል።የመንግስትና የሕወሓት መሪዎች በሚስጥር ተወያይተዋል የሚባለዉን ዘገባ ሁለቱም ወገኖች በተደጋጋሚ ሲያስተባብሉ ነበር።የብሪታንያዉ ማሰራጪያ ቢቢሲ የሕወሓቱን መሪ ደብዳቤ ጠቅሶ እንደዘገበዉ ግን የተፋላሚ ኃይላት መሪዎች በሚስጥር ባደረጉት ዉይይት ዉጊያ ለማቆምና በትግራይ ላይ የተጣለዉን እገዳ ለማንሳት ተግባብተዋል።ድርድሩ የተደረገበት ጊዜና ሥፍራ አልተጠቀሰም።ይሁንና ደክተር ደብረፂዮን «በትግራይ ላይ ያንዣበበ» ያሉትን ጦርነት ለማስቀረት ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብም ሆነ የአፍሪቃ ሕብረት የወሰዱት ርምጃ የለም በማለት ወቅሰዋል።ቡድናቸዉ «እራሳችንን ለመከላከል አስፈላጊዉን ርምጃ ሁሉ ይወስዳል» ብለዋልም።
DW
https://amharic-zehabesha.com/archives/176712
No comments:
Post a Comment