Saturday, August 20, 2022

ሰው ለሰው እረኛ መሆን ካልቻለ ሠላምን አያገኛትም - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
(በሞራል   ቢስነት እየተገዳደልን  መኖር  ለእኛ ኢትዮጵያውያን የሚያሳፍር መሆኑንን ... ሰው መሆናችንን  ያለመገንዘብ አባዜ መሥፈኑን ። እኛ ...ራሳችንን እንዲህ እና እንዲያ ብለን ለራሳችን ሥም አውጥተን ወይም ወጥቶልን ከመጠራታችን በፊት የሁላችንም መጠሪያ ሰው አእንደነበረ አለማወቅን ።  ሥልጡኖቹ ሰው ሆነው እንደሰው እየኖሩ እኛ ሰው ነን ብለን በጋራ እንዳንኖር በፖለቲካ በተሸሸገ የዘረኝነት ሴራ ኢትዮጵያውያንን   እያገዳደሉን ለዘመናት እንደኖሩ ። ለብዝበዛቸው መንገድ ለመጥረግ ሲሉም  የእብድ ገላጋይ እየሆኑብን እንደሆነ  እና  ፣ በጊዜ እንድንነቃ  እረኛዬ ድራማ አሥገንዝቧናል   ።  በእኔ እይታ ። )

  “እረኛዬ  ድራማ “ ገመናችንን በመግለጥ ፣  የዛሬን አሥቀያሚ እውነት ቢያሳየንም የራሳችንን ፣ የፖለቲካ ማይምነት እና ድንቁርና የዘነጋን ወይም ለማሥተዋልና ከስህተት ለመማር ያልተዘጋጀኝ ብዙዎች  ግን ከዚህ ድራማ የምንማር አይመሥልም ።ብዙዎች  በድራማው ፍፃሜ በእረኛዋ እናና አሳዛኝ ሞት ብናነባም ፣ እናና የመሰዋት በግ እንደሆነች ፣በእኛ ሐጢያት ያለሐጢያቷ እንደተቀጣችም  አልተረዳንም ።

ይኽ   ድራማ የትላንትን እና የዛሬን  የፖለቲካ ማይምነታችንን ከዘመን ጋር ባለመጎዝ ቆመን መቅረታችንን፣ ከጥበብም መራቃችንን  እንደ ዜጋ ያሳየን ይመሥለኛል ። እረኛዬ  ድራማ ፣ የወቅቱን እውነት  ከማሳየቱም በላይ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ጥጋበኞች ፣ በህዝብ እልቂት አትራፊ ቢሆኑም  ፣ ጦስ ጥንቡሳሳቸው አጅግ  አደገኛ እንደሆነ የሚያሥገነዝብ ነው ። ...  ትላንት  ከ 150 ዓመት በፊት  የተጀመረው ጥጋበኛን የመፍጠር ፣ኢትዮጵያውያንን እርስ በእርሳችን የማባላት የበዝባዥ ኢፔሪያሊሥቶች ሤራ ዛሬም በሌላ መልኩ ቀጥሏል ። ይኽ ተከታታይ   ሤራ የሚያከትመው ፣  ህዝብን ወደ ጭቆና እና የባሰ ድህነት በመንዳት  ፣ አገርን በማቆርቆዝ  እና በማፈራረስ ነው  ።

አገርን ለመፈራረም ቅጥፈት በሞላው ፣ የማጋጨት ፖለቲካ  ውሥጥ በመሆን ፣ የግል ምቾትን እና ብልፅግናን ማቀላጠፍ ፤ በአንፃሩም  ኢትዮጵያን  እጅና እግሯን ጠፍሮ እና አፏን አፍኖ ፣ በምዕራባውያኑ እና በአሜሪካ ቱጃሮች የማሥገረፍ እና ለአልተቋረጠ ብዝበዛ የማመቻመች  የባዳነት ሚና  መጫወትን ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች መርጠዋል ። ...ዛሬም የነዚህ ሴረኞች የማገዳደል እኩይ ሴሬ  መቀጠሉን  በአገሪቱ አራቱም ማዕዘን ያለሐጢያታቸው ፣  በከንቱ የሚያልቁትን ንፁሐን በማሥተዋል መገንዘብ ይቻላል  ።

በእረኛዬ እረኛዬ ድራማ ፍፃሜ እናና ምንም የማታውቅና የዋህ  የእግዜር በግ ብትሆንም ፣ ለሞት የተዳረገችው በግጭት መካከል በባረቀ ጠመንጃ ጥይት ተመታ መሆኑንን ማሥተዋል ለመማር ይጠቅማል።  በነገራችን  ላይ ፣ ይኽ እውነት ትላንት ከአብዮትና ፀረ - አብዮት ፤ ከገንጣዮች እና የአርበኞች መሰዋትነት ፤ ከጨለንቆ ና ከበደኖ የጅምላ እልቂት ፣ ወደ ዛሬው ፣ የጥጋበኛ ፖለቲካ አራመጆች  ፤ ማለትም ፦

" ጉልበት አለን ፤ የሚችለንም የለም ። መግደል ብቻ እምነቱ እንዲሆን ህዝቡን ሰብከን እና በዳቦ ገዝተን አሳምነንዋል ። ..."  ወደሚሉ ፤ ሁሌም ሊሰራ በማይችል የውሸት ፕሮፖጋንዳ በሚያምኑ ፤ በተስፋ በመደለለ ሰውን በጭካኔ ተግባር ላይ በሚያሰማሩ ፤ በእጃችን ብዙ የመግደያ መሣሪያ አለ ብለውም ፣ ሳይወድ በግዱ አብሯቸው የቆመውን ህዝብ ፣ እንደ አንድ ወጥ የፋብሪካ ምርት በመቁጠር ግፋ በለው ፣ ግደል ፣ እረድ ፣ ጨፍጭፍ የሚል ትዕዛዝ በየቀኑ በሚሰጡ  ፣ በህሊና ቢስ የፖለቲካ መሪዎች በሚፈፀም ዘግናኝ ድርጊት  ዛሬ የተሸጋገረ ተከታታይ  ሴራ  ነው ።

ሴራው   እፍኝ የማይሞሉ ሂትለራዊ  አስተሳሰብ ያላቸውን ወያኔዎች በዋነኝነት አቅፎ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል ።፣ በዙሪያቸው ባሉ ጥቂት የደላቸው ጡንቻቸው የፈረጠመ ጠባቂዎቻቸው የሚተማመኑ ፤ ህዝብ ለመሰንበት ብሎ አውዳሚ ሃሳባቸውን ተቀብሎ እንዲጎዝ የሚያደርጉ ፣ ህዝብን በጠመንጃ እያሥፈራሩ ወደ ሞት የሚነዱ አደገኛ ሂትለራውያን በዚች ቅድስት አገር  ተፈጥረዋል ።

ከእነሱ  የጥፋት ፣ የመለያየት ፣ የጥላቻ ፣ የግንጠላ ሃሳብ ውጪ የሆነ የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የመቻቻል ፣በእውነተኛ ምርጫ  ራስን በእራስ የማስተዳደር ሃሳብን የሚያራምደውን ሁሉ ፣ ባላቸው የአንድ ለአምሥት ጥርነፋ ፣ አነፍንፈው በመድረስ  ለመግደል ሥልጣንን በጉልበታቸው ያገኙ  አእምሮ ቢስ  ሂትለሮች  ህዝቡን እያሰቃዩት ነው ።

እንደ እነዚህ ዓይኖቶቹ ጨካኝ ፣ ሰውን በማረድ የተካኑ የዳቢሎስ ልጆች ፣ ሤጣናት ፣ በኦነግ ሸኔ ሥም  እንኳ  ከመንቀሳቀስ ወደ ኋላ የማይሉ ነፍሰ በላዎች  ሆነው የተገኙ  ናቸው። ለብር ሟች ሥለሆኑም ፣ " ይኼን ያህል ብር በዚህ ቦታ ፣ በዚህ ሰዓት ውስጥ ካላሥቀመጥህ ያፈነውን ሰው እንቆራርጠዋለን ። " በማለት የሚያሥፈራሩ ፣ ገንዘቡን ካላገኙም ሰውን በቁሙ የሚቆራርጡ  እጅግ ጨካኝ እንደሆኑ በተግባር ያሳዩ ናቸው ።   ጥቂት ሰርጎ ገብ ኦሮምኛ የሚያውቁ  ሂትለሮችም  በኦነግ ሸኔ አመራር ውሥጥም እንዳሉ መጠርጠር አይከፋም  ።

በራሱ በኦነግ     ሸኔም ውሥጥ ናዚዎች እነሰዳሉም ተግባራቸው ይመሠክራል ።    ፣ እነዚህ ከቶ በነማን የሰለጠኑ ይመሥልሃል  ?  በባንዳዎቹ የወያኔ ነፍሰ በላዎች አይደለምን ? ወያኔዎቹሥ በቀቢፀ ተሥፋ ለምዕራቡ እና ለአሜሪካ ቱጃሮች በባርነት የሚገዙ ህሊና ቢሶች እንደሆኑ ከጥንት ታሪካቸው እንዴት ሣትረዳ ቀረህ ?? በፋይናንስ እና በሃሳብ ወያኔንን ለጥቅማቸው ብለው ባይረዱ ኖሮ በአገራችን ጦርነት ብሎ ነገር እንደማይከሰት እንዴት መገንዘብ አቃተህ ? ኢትዮጵያዊው ወንድሜ ። ..

ኢትዮጵያውያን  ሆይ ! አሜሪካም  ሆነች ብዙዎቹ ቲጃር  የአውሮፓ  መንግሥታት ፣ የአገራችንን ሠላምና ብልፅግና ከቶም አይፈልጉም ። ቢፈልጉ ኖሮ ፣ የአገራችንን ሉአላዊነት አምነው ፣ በአንዱ የአገራችን ክፍል የተከሰተውን ችግር በራሳችን መንገድ እንድንፈታ ፣ ያለአንዳች ጣልቃ ገብነት ይተውን ነበር ። ይሁን እንጂ በመሣሪያና በቴክኒክ ያላባራ ድጋፍ ለወያኔ እና ለኦነግ ሸኔ በማድረግ እርስ ፣በእርሰ ተላልቀን እንድንጠፋ ታላቅ ሤራ ከጀርባችን የሚጎነጉኑልን እነሱው ናቸቸው  ። ይኸው ዛሬም  ለእልቂት እያሰናዱን መንግሥታት እኮ  ነው ።

እረኛዬ  ድራማም ይኽንን ሃቅ እውቁ ባይ ነው ። " በከንቱ ንፁሐንን አታሥጨርሱ ። ዛሬን እንኳን ንቁ ። እንደ እናና በየሜዳው የፈሰሰው ደም እና የወደቀው የሰው ሬሳ በእናንተ ጦስ ነው ። እሥከመቼ  የጠላቶቻችን የጥፋት መሣሪያ ሆናችሁ ትቀጥላላችሁ ? " በማለት የሚያነቃ ...  ።

እረኛዋ  እናና ፀብን በፍቅር የመግደል ተመሳሌት ናት ።  በድንቁርና ሰበብ ሥለሞቱት  የመሰዋት በጎች የምታስታውሰን ም የዋህ በለ አገር ናት ። ...  በእያንዳንዳችን ቆም ብሎ ያለማሰብ የምንፀፀት ከሆነ ፣ በንፁህ ልብ  በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለን ለመወቃቀስ ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል  ። ለሚሊዮኑ እናናዎች ሥንል ።  ....

ወያኔዎችም ህዝብን ይቅርታ ለመጠየቅ ፍቃደኛ ካልሆኑ እርቅ ብሎ ነገር የለም ።  እርቅ። ከይቅርታ ይጀምራል ።  በሰላምና በፍቅር ለመኖር ይቅርታ መጠይቅ ይቀድማል ።ህሊናችሁን ዳግም ለማሰራት ዛሬም አረፈደም ። ዞሮ ፣ ዞሮ ሞት ላይቀር በታሪክ ተወቃሽ መሆንን ባትመርጡ ይበጃችኋል። ከውጪና ከውሰጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በማበር ፣ የጅል ጫዎታ በዚች በታላቅ አገር ላይ  መጫወታችሁም ይብቃ ።  "ጥጋበኝነት ይበቃል ! "  ። እርስ በእርስ የመገዳደል  ፤ ደሃን እርስ በእርሱ የማጫረስ እና አገርን የማፍረስ ሤራ ለትውልዳችን አይጠቅምምና ይበቃ ። ማንኛውም ወገን በሰው እልቂት  ትርፍ አያገኝም ። ከሰው በላ ጦርነት ትርፍ ተገኝቶ አያቅም ። እርግጥ ነው የሰው ሥጋ በመብላት እና ደሙን በመጠጣት ሤጣናት ለጊዜው ሊያተርፉ ይችላሉ ። ህዝብ ግን የሚያተርፈው ሥደት ፣ ርሃብ እርዛት እና ሞት
https://amharic-zehabesha.com/archives/176650

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...