Sunday, August 14, 2022

ማን ቼ ፖለቲካ - ሲና ዘ ሙሴ 
ክልል ቅብርጥስዮ እያላችሁ ጫጫታ አታብዙ ። ጉራጌ ክልል ሆነ ዞን ለጉራጌ ደሃ ጠብ የሚልለት ነገር የለም ። ሌላውም ክልል ልሁን ባይ ፣  የጉራጌን ህዝብ ዓይነት ዕጣ ፈንታ ነው ያለው ። ሺ ቢታለብ ከገሌ አያልፍም እንዳለችው ድመት ነው ነገሩ ። የጉራጌ ደሃ የሚኖረው በአዲስ አበባ ፣ በአዳማ ፣በሃዋሳ፣በሻሸመኔ፣ በድሬደዋ፣ በጅጅጋ፣ ወዘተ ። የኢትዮጵያ ከተሞች  እንደሆነ  ይታወቃል ። ሁለት ሚስት አግብተው አንዷን መሬት ጠባቂ አንዷን የከተማ ዘመናይ አድርገው የሚኖሩም አሉ ። ያም ሆነ ይኽ የጉራጌ አገሩ ከተማ ነው ። ክልል አሜረኝ የሚለው እንደ እርጉዞ ሴት መሆኑ ነው ። አይቅርብኝ ። እኔም ከ60 ዎቹ የደቡብ ጎሳዎች አንዱ ነኝ ባይ ነው  ። ነው ። በቃ ። ግን ፣ ግን  በአዳማ ካሉት ሀብታሞች  የበለጠ ወልቂጤ የጉራጌ ሀብታም እንደሌላት እያወቀ  የኢንጊሊዝ ፕሪመር ሊጋ ይመሥል " ወያላው ዝምን እየዘፈነ ክልል አማረኝን ምን አመጣው  ? የተኮታኮተው ማንቼ እና የጨሰው አርሴ ጫወታ መሰለ ' ኮ ! ፖለቲካው ። በበኩሌ በእንጊሊዝ አፍ “ ማን “ እና በእኛው ቋንቋ “ ቼ “ ለዛሬው የክልል ፖለቲካ የሚመጥን ርዕሥ ነው ። ( ሰው ቼ እየተባለ ለማይረባ ጉዳይ ሁሉ ፣ አደባባይ  መውጣት ብርቁ አይደለም ። በደርግ የተጀመረው የቼ ሰልፍ  በኢህአዴግ እንደቀጠለ አንዘነጋም ።)  ( እግርኳስም የሚያምረው በጥበብ በተሞሉ ተጫዋቾችና በጥበብ በበለፀገ አሠልጣኝ ሲከወን ነው ። አሠልጣኙ ሁሌም ተጨዋቾቹን በጥበብ እየሞላ ሜዳ ካላስገባ በስተቀር ፣ በጫወታ ሂደት   መንጋነት መንፀባረቁና ቡድኑንን   ለሽንፈት መዳረጉ አይቀርም ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከጥበብ መራቅ የጀመረው ፣  ከቀዳማዊ ኃይለሥላሤ (ቀኃሥ) ውድቀት በኋላ ነው ። በነማን እየተጠመዘዘ ከሁለት ሦሥቴ በላይ አገረ መንግሥቱ  ውድቆ እንደተነሳ ያላሥተዋለ (ጅሌ ) " ክልል !  ክልል ! "  እያለ በሞኝነት ይጮኻል ።" መላው ኢትዮጵያ የራሱ መሆኗ እንዴት እንዳልገባው ግርም ይለኛል ።

በህዝብ ሥም የተደራጁ  አንዳንድ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጥቂቱን ህዝብ ፤ በተለይም በስሜት ፍላሎት የሚነዳውን  ጀብደኛ ወጣት አእምሮ በመኮርኮር ፣ ክልል በመሆኑ ብቻ እንደ ጨው ዘር በመላው ኢትዮጵያ ተመልሶ ወልቂጣ የሚገባ ይመሥል በጣጣ የተሞላውን ክልል ናፋቂአድርገውታል ። እነሱ እንደሚሉት   ከሰልል መሆን ታላቅነት እየመሰለው ፣ ከአገር በፊት ጎሣ ማሥቀደሙ የሚያሥገርም ነው ። ይኽ ድርጊቲ አፐርነሰ አኮስሶ እንደ ማየት ይቆጠራል ።

አገር ከቋንቋ  የምታንሥ ተራ ነገር አየደለችም ። አገር እኮ እንደሰማይ የገዘፈች   ናት ። አገር ከህዝብ ቁመት በላይ ናት ። ልክ እነደ ሰንደቅ ዓላማ ። ለዚህ ነው የአገር ሰንደቅ ዓለማ በከፍታ ላይ የሚውለበለበው ። ትልቅነቷን ለማመልከት ። ደግሞም አገር ታላቅ እንድትሆን የቀደመው ትውልድ የሚከፈለውን መሰዋትነት  መዘንጋት የለብንም ።  አገር ያለመሰዋትነት እንዳልተገነባችም መዘንጋት አልነበረበትም ።

ይኽ ሥህተትህ ነው ፤ " በዚች አጭር ዕድሜዬ በአገሬ ላይ በነፃነት  እንደ ልቤ ተዘዋውሬ ሳልሳቀቅ  ፤ ሠላሜ ና ደህንነቴ ተጠብቆ ደሥታዬ በዝቶ የምኖርበት የፖለቲካ አውድ ይፈጠር ። " እንዳትል ያደረገህ ። ለጥቂት የፖለቲካ ቁማርተኞች ብልፅግና አገር ያለ አቅሟ 60 ክልል ይኑራት ማለትህ ልክ አይደለም ።    በትልቋ ጠቃሚዋ ኢትዮጵያሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት ላይ በማተኮር ቢያንሥ " አገሬ የበለፀጉትን አገራት ፖለቲካ በመከተል ፣ ህዝብ ሰብዓዊ መብቱ ተጠብቆ  ዴሞክራሲያዊ መብቱ በወጉ ተረጋግጦ ፤ መሠረታዊ ፍላጎቶቹ ተሟልተው ፤ አጭር ዕድሜውን በወጉ እንዲኖር ይደረግ  ። " እንደማለት ፣ ክልል ሲኮን ለምሥኪኑ ገበሬ ና ከተሜ መና ከሰማይ ይወርድለት  ይመሥል ፣ የመከፋፈልን መንገድ መምረጥ በበኩሌ የጥበብን መንገድ አፈርድሜ ማሥበላት ነው ። ይኽንን ወደ አዘቅት ወሳጅ መንገድ ከአንተ ካልባነንከው እየኮረጁ ፣   በየሶሻል ሚዲያው  የሚያራግቡትም  ፣ ፖለቲካ ዛሬም ድረስ ዘልቆ ያልገባቸው  የፖለታካ ማይሞች ናቸው ።  በማጋጨት እና በማባላት ትርፍ ለማግኘት የሚሯሯጡ ሞራለ ቢሶች ። ያም ሆነ ይኽ ዩቲዩብም እንጀራ ያሥገኛል ።

የጥቂት  ዩቲውበሮች ፣ ጭፍን የመከፋፈል ድጋፍ በድንቁርና የተሞላ ነው ። ለእንጀራ ተብሎ አገርን ለማፈራረስ ቢንዚን ማርከፍከፈ ተገቢ አይደለም ። ... ለመሆኑ  ደቡብ ውሥጥ 60 ጎሣዎች ሥላሉ አገሪቱ በሌላት ሀብት 60 ቦታ የቢሮክራሲ መንደላቀቂያ መድረክ ታዘጋጅ ማለት ከድንቁርና የዘለለ ሥም ይሰጠዋል እንዴ ? ወያኔ የሰራውን ሥህተት ለማረም ባልተቻለበት መንገድ ላይ ዛሬም እንጓዝ ማለትሥ በራሱ እብደት አይደለም ወይ ?   በበኩሌ የትላንቱም ሆነ የዛሬው በመንጋነት ላይ የተመሠረተ ጫወታ በቀድሞዎቹ ቅኝ ገዢዎቻችን የሚታገዝ ነው ። ብዬ አምናለሁ ። የፖለቲካ ሥልጣንን በመከላከያቸው ና በደህንነታቸው ኃይለኝነት እንዳይናጋ አድርገው ሲያበቁ ፣ ላወጡት ህግ ተገዢ ሆነው በየአገራቸው በክብር ይኖራሉ ። በእኛ አገር የእነሱን ዓይነት ጠንካራ  የመንግሥት ቅብብሎሸሸ እንዲኖር ሥለማይፈቅዱ አሜሪካኔ አውሮፓ ፣ ትላንት  ኤርትራን አሥገንጥለዋል ። ዛሬም ትግራይን ለማስገንጠል እየሰሩ ነው ።

ኤርትራን ሲያሥገነጥሉ ሥለዴሞክራሲና ሥለ ሰብዓዊ መብት አሰያወሩ ነው ። ኤርትራ ከተገነጠለች በኋላ ግን ለብዝበዛቸው ነው የተጣደፉት ። ይሁን እንጂ ኢሳያስ አልፈቀደላቸውም ። እናም ኢሳያስን ለማሶገድ በብርቱ ጣሩ ። አልተሳካላቸውም ።  ዛሬ ደገሞ ትግራይን ለማሥገንጠል ፣ ትግራይ የሁመራን ኮሪደር እንድታገኝ እየጣሩ ነው ። ለብዝበዛቸው ሲሉም ትግራይን ለማሥገንጠል የማይፈነቅሉት ዲንጋይ የለም ። ቆም ብለን ወያኔ ያቋቋመልንን ከፋፋይ ሥርዓት አደገኝነት አሥተውለን አሽቀንጥረን ካልጣልነው በስተቀር ፣ በመሰዋትነት የሰራነው የአባይ ግድባችን እንኳን ዋሥትና አይኖረውም ። እያደጉ የመጡት ከተሞቻችንም መፈራረሳቸው አይቀርም ። ይኽ እንዳይሆን ጨከን ያለ  የሥርዓት ለውጥ ያሥፈልገናል ።

በበኩሌ ለሥልጣን የቋመጥኩ ፖለቲከኛ ባልሆንም ፣ " ሥልጣን ለአንድ ቀን ቢሰጥህ ምን ታደርጋለህ ? " ተብዬ ብጠየቅ " ሥልጣን ለአንድ ቀን ቢሰጠኝ ክልል የሚባለውን ሥያሜ አፈራርሼ የቀድሞውን ክፍለ አገር አነብር ነበር ። ለሉዩነት ምክንያት የሚሆኑትን እና ለጥቂቶች ብዝበዛ የተሰነዱትን ማዋቅሮች ሁሉ አፈራርሳቸው ነበር ። በቃ ሁሉንም እንደ አገሬ መከላከያ ኢትዮጵያዊ አደረጋቸው ነበር ።   ጎሣ  እንደማትመርጠው ሴቷ ኢትዮጵያ በህዝብ ሥም የሚነግደውን ፖለቲከኛ ተራ ህዝብ ና ሰው እንደሆነ አሳውቀው  ነበር ። " ከዛሥ  ? " አትሉኝም ? " ከዛማ !  በህግ የበላይነት የሚያምን ፤ ፈጣሪን የሚፈራ ፤ በህዝብ ምርጫ ሥልጣንን በየጊዜው ከህዝብ እየተረከበ አገር የሚመራ ፤ የፖለተካ ፓርቲ እንዲኖር አሥፈላጊውን ፖለቲካዊ ምህዳር  እንዲኖር መንገዱን አደላድል ነበር ።   ፈጣሪ በፈጠራት ምድር  በኢትዮጵያ ተወልዶ አየኖረ ፤ ከሥግብግብነቱ የተነሳ ኢትዮጵያን የሚጠላውን ደግሞ  ፣ አይቀጡ ቅጣት እቀጣው ነበር ። ይኽንን  በህግ የበላይነት ሥለማደርገው 90 %  ኢትዮጵያዊ ከጎኔ ሆኖ  ዓላማዬን እንደሚያሳካ አመሰግናለሁ ።

እናም ዛሬ በትረ ሥልጣኑንን የያዘው ምን ይጠብቃል ? በከንፈር ሽንገላ ብቻ ከሌባ ካድሬ  ጋር  እየተለማመጠ አገሪቱን ወደ አደጋ የበለጠ እያሥጠጋ መጓዝን ይመርጣል ወይስ የሌቦች እጅ እንዲሰበሰብ ፣ የህዝብን ሀብት በመመዝበር ሺዎችን በርሃብ የቀጡና በመቶ የሚቆጠሩ እንዲሞቱ ያደረጉትን በሥቅላት በመቅጣት አዲስቷን ኢትዮጵያ በጠንካራ አለት ላይ ለመገንባት በብርቱ ይንቀሳቀሳል ? ወይስ “ በሬ ካራጁ  ....” እንዲሉ ዛሬም በያዘው በከፊል ጨለማ መንገድ ይጓዛል  ?  እስከጊዜው .....

 
https://amharic-zehabesha.com/archives/176595

No comments:

Post a Comment

https://youtu.be/VUfa5eupQTc?si=Zm73w18dFB27xlqD       https://youtu.be/LcFmz2Xq5MY?si=7uP6VZsd2ksEulUf   https://youtu.be/7dUVmj8go7s?si=Px...